Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በባህርዳር በሚካሄድ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆኑ

$
0
0

ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ያለምንም ተለዋጭ ቤትና ቦታ ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉት፣ በቀበሌ 14 አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ትናንት ባሉዋን ሲደበድቡባት ጩኸት ያሰማች ነፍሰጡር ሴት ፣ በፖሊሶች በደረሰባት ድብደባ ከፉኛ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች። አንድ ህጻንም በነበረው ግርግር ተረጋግጣ ህይወታ ማለፉ ታውቋል።
አብዛኞቹ ወጣቶች ጫካ በመግባት ከድብደባ አምልጠዋል። ሁኔታው አስከፊ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በአገራችን የት እንሂድ ሲሉ ይጠይቃሉ። በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች፣ የሚመለከታቸው ሁሉ ፈጥነው እንዲደርሱላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በአካባቢው በተለያዩ አመታት ተስረተው የነበሩ ወደ 2 ሺ የሚጠጉ ቤቶች እንሚፈርሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ አካባቢ ይኖር የነበረ የዙሪያ ወረዳ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆነው የወታደር ባህሩ ቤት ሌሊት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሃይሎች በቦንብ መምታቱ ታውቋል። ጥቃቱ በቤተሰቦቹ ላይ ያደረሰው የህይወት ጉዳት ባይኖርም፣ በቤቱ ላይ ግን ጉዳት አድርሷል።

The post በባህርዳር በሚካሄድ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆኑ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News 24/7: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles