Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

አስገደን የማዳን ዘመቻ (ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው)

$
0
0

ፖለቲካን ትተን ወደ ሰብአዊነት ከፍ ስንል መረዳዳትን እናገኛለን፡፡ ጀግኖችን መርዳት አንድም ሰብአዊነት ሁለትም ውለታ ነው፡፡ የዛሬውን ባለውለታ ችላ ብንል ለነገ የሚሆን ባለውለታ አናገኝም፡፡

አስገደ ደግሞ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሂወቱን ለህዝብ የሰጠ ጀግና ስለመሆኑ ከኢህአዴግ ኤሊቶች እስከነ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉት የሚመሰክሩት እውነታ ነው፡፡ ስለዚህ፣ አስገደ የሚልየኖች ቢሆንም ሺዎች እንበቋለን፡፡ አስገደ መንግሥት ከጎኑ ሊሆንለት ቢገባም ህዝብ አለለት፡፡ የልብ ህመም ደግሞ የሚታወቅ ነው፤ ፋታ አይሰጥም፡፡ እኛም አስገደን ለማትረፍ ፋታ አይኖረንም!!

አስገደን ለመረዳት አድራሻ የጠየቃችሁ፣ ለመረዳት የምህትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ትችላላችሁ:
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1000088897963-አስገደ ገ/ስላሴ ወልደሚካኤል
ስ.ቁ፡ 09-14-75-72-42 (09-75-45-73-47)
ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው፡፡አሜሪካ እና አውሮፓ ያላቹ በጎፈንድ በኩል መርዳት ትችላላቹ።

(((እርዳታ የሚያደርጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ-የህዝብ አለኝታ ናቸውና)))

Help spread the word!

https://www.gofundme.com/lets-help-asgede-gebreasilasie

 


አቶ አሰገደ ገብረስላሴ የማውቀው ከአረና ምስረታ ጀምሮ ነው፡፡ ለተበደሉ ሁሉ የሚቆረቆር ታጋይ ነው፣ ለእኔ በብዙ ነገር ምሳሌ የሆነኝ ትልቅ ሰው ነው፡፡ አሁን ታመዋል፣ ማሳከሚያ አጥቶ ለህዝብ እርዳታ እየጥየቀ ነው ይሚገኘው፣ እንግዲህ ሀገራችን ታላላቆቹዋን ማከም የማትችል ሀገር ከሆነች ቆይታለችና የአስገደን ህይወት ለማዳን መረባረብ ያስፈልጋል፡፡

ለህክምናው የሚያስፈልገው ወጪ 300_ሺ_ዶላር ነው ተብለዋል፤ ሁሉም የአቅሙን ቢያዋጣ፣ ሊታከም ይችላል፡፡
አስገደን ለመረዳት የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚከተለውን መጠቀም ትችላላችሁ:
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1000088897963-አስገደ ገ/ስላሴ ወልደሚካኤል
ስ.ቁ፡ 09-14-75-72-42 (09-75-45-73-47)
በነገራችን ላይ በቤተሰብ ጉዳይ ወደ ትግራይ ሄጄ ነበር፣ ዛሬ ነው ከተምቤን ወደ መቀሌ የተመለስኩት፣ አዲስ አበባ ስመለስ ደግሞ ስለታጋይ አሰገደ የማውቀውን ያህል መፃፌ አይቀርም፣ እዚህ መቀሌ ዛሬ ቤቱ ሄጄ አይቸዋለሁ፤ እየታገለው ነው እንጂ ህመሙ እየጠናበት ነው ያለው፡፡
አቶ አስገደ ለመርዳት ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው!

በኣስራት ኣብረሃም

—-

The post አስገደን የማዳን ዘመቻ (ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News 24/7: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles