Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የአውሮፓ የስፖርት ሚዲያዎች የዘገቧቸው አበይት የዝውውርና ሌሎች ስፖርታዊ ወሬዎች

$
0
0

በ  ወንድወሰን ጥበቡ

በዕለተ ሃሙስ የአውሮፓ የስፖርት ሚዲያዎች የዘገቧቸው አበይት የዝውውርና ሌሎች ስፖርታዊ ወሬዎች ስለ ሃሪ ኬን፣ ሉኬ ሻው፣ ዲያባላ፣ አንቶኒዮ ኮንቴ፣  ጆን ቴሪ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ አሌክሲ ሳንቼዝ ጉዳዮች እና ሌሎች ትኩስ የዝውውር ወሬዎች ተካተውበታል።

ሀሙስ የካቲት 23፣ 2009 ዓ.ም 

ኪን የማንችስተር ዩናይትድ የ80 ሚ.ፓ አማራጭ ሆኗል

ማንችስተር ዩናይትዶች አንቶኒ ግሪዝማንን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በ80 ሚ.ፓ የዋጋ ስምምነት ለማስፈረም ፊታቸውን ወደቶተንሃሙ አትጥቂ ሃሪ ኬን ያዞራሉ።

ምንጭ: ደይሊ ስታር

ማን ዩናይትድ ለዲባላ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል

የጁቬንቱሱ የፊት ተጫዋች ፓውሎ ዲባላ ከማንችስተር ዩናይትድ በርካታ የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለታል።

ምንጭ: ካልቾመርካቶ ድረገፅ

ኮንቴ ከቼልሲ ጋር እየተነጋገሩ ነው

የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከስታንፎትምርድ ብሪጁ ክለብ ጋር አዲስ ስምምነት ማድረግ ሰለሚችሉበት ሁኔታ እየተነጋገሩ ይገኛሉ።

ምንጭ: ደይሊ ኤክስፕሬስ

ስፐርሰች ሉኬ ሻውን ምርጫቸው አድርገውታል

ቶተንሃም ሆትስፐሮች ሉኬ ሻው በመጪው ክረምት ከማንችስተር ዩናይትድ እንዲወጣ የሚያድረገው የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡለት ይችላሉ።

ምንጭ: ደይሊ ሚረር

ኤልኤ ጋላክሲ ቴሪን ፈልጓል

የአሜሪካን ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ በመጪው ክረምት ጆንቴሪን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል።

ምንጭ:  ዘ ሰን

የዩናይትዱ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በኦልትራፎርድ የመቆየት ፍላጎት አለው። የ35 ዓመቱ ስዊድናዊ የእግርኳስ ህይወቱን መቀጠል የሚያስችሉት የዝውውር ጥያቄዎች ከወደቻይና፣ ዩናይትድ ስቴስትና አውሮፓ ቀርቦለታል።  (ደይሊ ሚረር)

 

Daily Mirror

የደይሊ ሚረር ጋዜጣ የዕለተ ሃሙስ ዕትም በጀርባ ገፁ ዝላታን ኢብራሂሞቪችን ይዞ ወጥቷል

ኢንተር ሚላን የ47 ዓመቱን የቼልሲ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከስታንፎርድ ብሪጅ እንዲለቁ የሚያደረጋቸው በዓመት 10 ሚ.ፓ ክፍያ አቅርቦላቸዋል። (ደይሊ ሚረር)

ምንም እንኳ የ26 ዓመቱ ቪክቶር ሞሰስ ከሰማያዊዎቹ ጋር አዲስ ስምምነት ለመፈራረም ቢስማማም አንቶኒዮ ኮንቴ ግን በመጪው ክረምት የክንፍ ተከላካይ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።  (ደይሊ ቴሌግራፍ)

አርሰናል አማካኞቹን የ25 ዓመቱን ጃክ ዊልሼርና የ23 ዓመቱን አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይንን እንዲሁም የ27 ዓመቱን ተከላከዩን ኪራን ጊብስን የማጣት አደጋ ተደቅኖበታል። መድፈኞቹ የኮንትራት ስምምነታቸው በ2018 ክረምት ለሚጠናቀቀው ለእነዚህ ሶስት ተጫዋቾቹ እስካሁን መደበኛ የሆነ የኮንትራት ጥያቄ አላቀረበላቸውም። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

ጁቬንቱስ የ28 ዓመቱን የአርሰናል አጥቂ፣ አሌክሲ ሳንቼዝን ለማሰፍረም ሲል የ25 ዓመቱን አጥቂውን፣ ሲሞኒ ዛዛን እና የ20 ዓመቱን ኪንግስሌይ ኮማንን ለመሸጥ ተዘጋጅቷል። (ቶክ ስፖርት ቱቶ ስፖርትን ጠቅሶ)

መድፈኞቹ “የወደፊቱ አሌክሲ ሳንቼዝ” ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የ17 ዓመቱን ቺሊያዊ ተጫዋች ለማስፈረም የሙከራ ጊዜ ሰጥተውታል። ማርሴሎ አለንዴ የተሰኘው ይህ ተጫዋች የሁለተኛው ዲቪዮን ክለብ፣ ሳንታ ክሩዝ ተጫዋች ነው። (ሰን)

የሌስተር ሲቲ ደጋፊዎች ሮይ ሆጂሰን ቀጣዩ የክለባቸው አሰልጣኝ እንዲሆኑ አልፈለጉም። የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ክለብ ከ69 ዓመቱ የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋር መደበኛ ያልሆነ ንግግር እያደረገ ይገኛል። (ሌስተር ሜርኩሪ)

Daily Star

የዕለተ ሃሙስ የደይሊ ስታር ጋዜጣት ዕትም ማንችስተር ዩናይትድ ሃሪ ኬንን ሊያስፈርም እንደሚችል የሚገልፅ ዘገባ ይዞ ወጥቷል

ሊቨርፑል ለሳንቶሱ የ17 ዓመት ተጫዋች፣ ሮድሪጎ የዝውውር ጥያቄ ቢያቀርብም ታዳጊው ግን ወደአውሮፓ የመሄዱ ጉዳይ እያሳሰበው ይገኛል። (ግሎቦስፖርትን ጠቅሶ ደይሊ ኤክስፕሬስ)

የቀዮቹ አለቃ የርገን ክሎፕ የ25 ዓመቱ የፊት ተጫዋች ሎሬንዞ ኢንሲኚ ከናፖሊ ጋር ያለው ኮንትራት በእንጥልጥል መቆየቱን ተከትሎ የወደፊቱ የዝውውር ዕቅዳቸው ሊያደርጉት ይችላሉ። (ካልቾመርካቶ)

ዌስትሃሞች ለ26 ዓመቱ ሁለገብ አማካኝ ተጫዋች ሚካኤል አንቶኒዮ ሳምንታዊ ደመወዙ 70,000 ፓውንድ ሊደረስ የሚችል አዲስ ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።  (ደይሊ ስታር)

የ31 ዓመቱ የማንችስተር ዩናይትድ የቀኝ መስመር ተከላካይ፣ አንቶኒዮ ቫሌንሺያ የሆዜ ሞሪንሆው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት ስለመሆን ማሰብ መጀመሩን ተናግሯል። (ደይሊ ቴሌግራፍ)

የ37 ዓመቱ የሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ጋሪ ሞንኮ የተሰናባቹ አሰልጣኛቸው ማርክ ዋርበርተን ምትክ ይሆኗቸው ዘንድ በሬንጀርሶች ተፈልገዋል።  (ደይሊ ስታር)

የ35 ዓመቱ የብሪስቶል ሲቲ አሰልጣኝ ሊ ጆንስ ቅዳሜ በአሽተን ጌት ስታዲየም በሚደረገው ጨዋታ ቡድናቸው የሻምፒዮንሺፑ ተቀናቃኛቸውን በርተንን የማያሸንፉ ከሆነ የስንብት ዕጣ ይገጥማቸዋል። (ብሪስቶል ሲቲ)

የ48 ዓመቱ የፉልሃም አሰልጣኝ ስላቪሳ ጆካኖቪች በክለቡ ስኬያማ የሚሆኑ ከሆነ በሻምፒዮንሺፑ ለ10 ዓመታት ሊቆዩ እንደሚችሉ ተናግረዋል። (ለንደን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ)

በመጨረሻም

በዝቅተኛው ሊግ ተሳታፊ የሆነው ሊንኮን ሲቲ ደጋፊዎች በኤፍኤ ዋንጫው ሩብ ፍፃሜ ከአርሰናል ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ትኬት ለመቁረጥ ሲሉ ሽያጭ ከሚጀምርበት 7 ሰዓታት ቀድመው ሰልፍ ጀምረዋል። ሊንከኖች ቅዳሜ መጋቢት 2፣ 2009 ዓ.ም ለሚደረገው የኤመራት ጨዋታ 7,000 ትኬት ተመድቦላቸዋል። (ሊንከንሻየር ኢኮ)

የስፓርታ ሞስኮው ተከላካይ ዲሚትሪ ኮምባሮቭ ለአምስት አመቷ ሴት ልጁ የልደት ክብረ በዓል አንበሳ ቀጥሮላታል። (ደይሊ ሚረር)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles