Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የወያኔዉ አገዛዝ በዚህ ዓመት ያቀደዉ የዉጭ ኢንቨስትመንት ማሽቆልቆሉን ብሉምበርግ ዘገበ

$
0
0

ናትናኤል ኃይለማርያም

የኢትዮጵያ የዉጭ አገራት ኢንቨስትመንት እያሽቆለቆለ መሔዱን ብሉምበርግ ባወጣዉ ዘገባ አስታወቀ። በኢትዮጵያ በተቀጣጠለዉ ሕዝባዊ አመፁን ተከትሎ በተለይ በዉጭ አገር የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ በደረሰዉ አደጋ ምክንያት በተያዘዉ የበጀት ዓመት የዉጭ አገራት ኢንቨስትመንት በ6 ወራት ጊዜያት ዉስጥ በ 20%(ፐርሰንት) ማሽቆልቆሉን ብሉምበርግ በዘገባዉ አመልክቷል።

ባለፈዉ በ2015 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የ1.5 ቢሊዮን የዉጭ ኢንቨስትመንት ገቢ የነበራት ኢትዮጵያ በዚህ ባሳለፍነዉ የ2016 ዲሴምበር መጨረሻ የዉጭ ምንዛሬዉ ወደ 1.2 ቢሊዮን እንደወረደ የኮሚሽነሩ መሥሪያ ቤት አስታዉቋል።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ከአዲስ አበባ ባደረገዉ የስልክ ቃለ መጠይቅ ከወያኔዉ አገዛዝ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነሩን በማነጋገር ባገኘዉ መረጃ በዚህ ዓመት የወያኔዉ አገዛዝ ያቀደዉ የ3.5 ቢሊዮን ዶላር የዉጭ ኢንቨስትመንት እንደነበርና ይኽ የታሰበዉ ኢላማ በእቅዱ መሠረት ማግኘት እንዳልተቻለ አቶ ፍፁም አረጋ ለብሉም በርግ መግለፁን አስፍሯል።

በአማራ እና በኦሮምያ ከ2015 ጀምሮ የመሬት ነጠቃዉ፤ የፖለቲካዉ አለመረጋጋት እና መንግስት በአካባቢዉ የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ በአካባቢዉ ላይ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት መፈጠሩን ምክንያት በማድረግ የወያኔም አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ አካባቢዉ የፖለቲካ አለመረጋጋቱን ማሳያም ጭምር ከመሆኑም ባሻገር የናይጄሪያዉ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴን እና የደች የፍራፍሬ ማሸጊያን ጨምሮ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸዉም ታዉቋል። ይኽንንም ተከትሎ 600 ንጹሐን ዜጎች በወያኔ ደህንነት መገደላቸዉን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ማሕበር ማሳወቁን ብሉምበርግ በዘገባዉ አካቷል።

ይኸዉ የኮሚሽነሩ መሥሪያ ቤት አገር ዉስጥ ካሉት የአገር ዉስጥ ኢንቨስተሮች 20 የሚሆኑት ካምፓኒዎች ለደረሰባቸዉ ጥቃትና የንብረት ዉድመት ማካካሻ ለማግኘት የጠየቁ መሆናቸዉን ሲገልጽ የዉጭ ካምፓኒዎችም ያቀዱትን እቅድ የሰረዙ ባይኖሩም ነገር ገን በቆይታ ነገሮችን ለማየት እንደፈለጉ እንዳሉ ግን ኮሚሽነሩ መግለጹ ታዉቋል። እነዚህ ካሳ እንዲከፈላቸዉ የጠየቁት የአገር ዉስጥ ካምፓኒዎች አብዛኞቹ የወያኔዉ ኢፈርት አካል እንደሆኑም አንዳንድ ታዛቢዎች አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles