ጆን ማጉፉሊ ይባላሉ የዛሬ ወር ነበር ስልጣን የተረከቡት ታዲያ በአንድ ወር ውስጥ ያረጉትን ይመልከቱ…
1. የመጀመሪያ እርምጃቸው የታንዛኒያ የነፃነት ቀን በዓል እንዳይከበር ማድረግ ነው፣ ለምን? በርካቶች በኮሌራ በሽታ እየሞቱ የነፃነት ቀን ማክበር ነውር ስለሆነ ለበዓሉ የሚወጣውን ወጪ ብሄራዊ የፅዳት ቀን ተብሎ ሁሉም አካባቢውን በማፅዳት እንዲጀምር አዘዋል። በዚህም መሰረት ከትላንት በስቲያ December 9 በታንዛኒያዊያን የነፃነት ቀን ታንዛኒያዊያን ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ አካባቢያቸውን ሲያጸዱ ውለዋል
2. ሙሂምቢሊ የተባለ ሆስፒታልን ከጎበኙ በኋላ ባዩት አስቸጋሪ ሁኔታ ለፓርላማ አባላት የሚወጣውን የመዝናኛ ዝግጅት ገነዘብ ለዚህ ሆስፒታል እንዲውል አዘዋል፣ ታዲያ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሆስፒታሉ 300 አዳዲስ አልጋዎች ተገዝተዋል እንዲሁ የማይሰሩ የሆስፒታሉ መሳሪያዎች በታዘዘው 200Million Shilling ተጠግነዋል።
3. ስልጣን በያዙ በሶስተኛው ቀን የመንግስት ባለስልጣናት ወደ ውጭ ሀገር የሚያረጉትን ጉዞ ሰርዞ በምትኩ ወደ ገጠር ከተሞች ተጉዘው የህዝቡን ችግሮችን እንዲከታተሉና መፍትሄ እንዲያመጡ አዘዋል። ውጪ ሀገር የሚያስኬዱ ጉዳዩች ሀገሪቱዋን ወክለው ውጪ ባሉ አምባሳደሮች እንዲፈጸሙ አዘዋል።
4.ከፕሬዝዳንቱ፤ ከምክትል ፕሬዝዳንቱ እና ከጠቅላይ ሚንስተሩ ውጪ ያሉ ባለስልጣናት የአውሮፕላን ጉዞ ሲያደርጉ ከፍተኛ ማዕረግን እንዳይጠቀሙና አብዛኛው ህዝብ በሚጠቀመው በመደበኛ ማዕረግ እንዲጠቀሙ አዘዋል
5.የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስብሰባዎችን እና ወርክ ሾፖችን ውድ በሆኑ ሆቴሎች ካሁን በኋላ እንዳያደርጉ አስታውቀዋል በየሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ያሉት ክፍሎች በቂ እንደሆኑ አስታውቀዋል
6. እቃ የጫኑ 350ኮንቴኖሮች በዳሬሰላም ወደብ መጥፋታቸውን ተከትሎ የታንዛኒያን የገቢዎች ሀላፊ ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሀላፊዎች አባረዋል
7.አዲሱን ፓርላማ ለመክፈት ወደ ዶዶማ 600ኪሜ በመኪና ነው የሄዱት፤ በፓርላማው መክፈቻም ላይ ባለስልጣናት ነገሮች እንደድሮ ይሆናሉ ብለው እንዳይጠብቁ እና ህዝቡ የመረጣቸው ንግግር እንድናደርግ ሳይሆን ችግሮቻቸውን እንድንፈታላቸው ነው ብለዋል
8. ለበአለ ሹመታቸው ይወጣ የነበረውን $100,000(2 ሚሊዮን ብር) ብር ወደ $7000(140,000) በመቀነስ የቀረውን ለሆስፒታል ሰጥተውታል
ለሌሎች ሀገሮችም መሪዎች ምሳሌ ለሚሆኑት ለታንዛኒያው አዲሱ ፕሬዝዳንት ላይክ በማድረግ አድናቆቶን ይግለጹ
The post አዲሱ የታንዛኒያ ፕሬዘዳንት ስልጣን በያዙ በጥቂት ቀናት ውስጥ እነዚህ አስገራሚ ነገሮች አድርገዋል። appeared first on Medrek.