Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

አገራዊ መግባባት ለብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ወሳኝ ዕርምጃ ነው! (አበበ ተክለሃይማኖት)

$
0
0

አበበ ተክለሃይማኖት

ባለፉት ሁለት ዓመታት የነበረው ሁኔታ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውጥረትና ሁከት የታየበት፣ የአጭር ጊዜ፣ መካከለኛና ስትራቴጂካዊ የረዥም ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ባለመቻሉ ፖለቲካዊ ችግሩ ሄዶ ሄዶ ወደ ደኅንነት ችግር (Security Problem) ተሸጋግሮ አገራችን በአስቸዃይ ጊዜ አዋጅ እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ ለዚያውም ስድስት ወራት ያልበቃው አራት ወራት ጭማሪ የጠየቀ ክስተት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ማለት የገጠመን ችግር አገርን ሊበትን የሚችል፣ የግዛት አንድነቷንና የሕዝቦቿን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ ሊጥል የሚችል የደኅንነት ችግር ነው ማለት ነው።

ጉዳዩን እንዲህ ባለ ከፍታ አጉልተን ስናይ ነው ለመፍትሔው የምናደርገው እንቅስቃሴ እርባና የሚኖረው። በሰላም ወጥቶ በስላም መመለስ ያለመቻል፣ ስለነገ ውሎ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት የሥጋት ኑሮ፣ ኢንቨስትመንትና የሕዝቦች ሀብት በአድማ እሳት የሚበላበት፣ በአንድ ቀን በርከት ያሉ ፋብሪካዎች የሚወድሙበት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶች መውደምና መሽመድመድ፣ ሥራና የቀን ተቀን ግብይት መቆምና የትራንስፖርት ዘርፍ መቆራረጥ ማለት የአንድ አገር አጠቃላይ ደኅንነት አደጋ ውስጥ ወድቋል ማለት ነው።

ሕዝቦች እርሰ በርስ የሚጠራጠሩበትና አንዱ ሌላው ላይ የሚያቄምበት አዝማሚያ የፖለቲካ ችግር ተብሎ በቀላሉ የሚወሰድ ሳይሆን፣ አጠቃላይ የአገርና የሕዝቦች ድኅንነት አደጋ ላይ ወድቋል ማለት ነው። ልማትና ዴሞክራሲ እክል ገጥሞታል ማለት የደኅንነት ችግር ገጥሞናል ማለት ነው። ስለዚህ ፖለቲካዊ ችግሩ ወደ ደኅንነት ችግር ልቆ ተሻግሯል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ሁኔታም ከዚህ አኳያ ነው መታየት ያለበት።

ሰሞኑን መንግሥት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ለማሻሻል እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተነገረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች ለውይይትና ለድርድር ተቀምጠዋል፡፡ አካሄዳዊ (Procedural) ጉዳዮችን አጠናቀው አሁን የውይይት አጀንዳዎችን በመቅረፅ ላይ እንዳሉ በመገናኛ ብዙኃን እየሰማን ነው፡፡ ፖሊሲውን የማሻሻል ሒደትና የፓርቲዎች ውይይትና ድርድር ለየቅል የሚሄዱ ሒደቶች ናቸው እንዴ? ፓርቲዎች የሚደራደሩበት ዋነኛው አጀንዳ ምን መሆን አለበት? በዝርዝር ጉዳዮች ወይስ የፖሊሲዎች ቁንጮ በሆነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ? በሌላ አነጋገር ከሕገ መንግሥቱ ቀጥሎ ከፍተኛ ጠቀሜታ ባለው የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ወይስ በቅርንጫፍ ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ ነው መወያየት ያለባቸው? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎችን መዳሰስ ተገቢ ነው፡፡

ፓርቲዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉዋቸው ውይይቶችና ድርድሮች በብሔራዊ ደኅንነት መግባባትን ለመፍጠር ከሆነ ይዘቱ ብቻ ሳይሆን ሒደቱ ጭምር በጣም ወሳኝ ነው፡፡ በአንድ በኩል ጥናትና ምርምርን መሠረት ያደረገ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሒደቱ አሳታፊ (Participatory)፣ እንዲሁም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት (Stakeholders) የሚያቅፉ (Inclusive) እንዲሆን ምን መደረግ አለበት? የሚለው መመለስ አለበት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን የማዳን ድርድር ከሆነ መግባባት የሚያስፈልገው በተጋረጠብን ከፖለቲካዊ ችግር በላይ ጎልቶ በወጣው የደኅንነት ሥጋታችን ላይ መሆን ያለበት ይመስለኛል።

ከጥቂት ዓመታት በፊት “የኢትዮጵያ የውጭና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ግምገማ” የሚል የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሱን የሚዳሰስ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፡፡ የፖሊሲው መሠረታዊ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ምን መደረግ አለባቸው? የሚለውን ንድፍና ጽንፈ ሐሳባዊ ማዕቀፎች (Concepts and Theories of Security) መሠረት አድርጎ የተጻፈ ነበር፡፡ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አዛምዶ ለጋዜጣ በሚሆን መልኩ ያለኝን አስተያየት ለመዘርዘር ነው፡፡ የደኅንነት ጉዳይ ከፖለቲካ በላይ ቁንጮ በመሆኑ ለፓርቲዎች ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ መላው ኢትዮጵያውያን እንደየአቅማችን እንድንሳተፍ ይጠይቃል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማም በጉዳዩ ዙሪያ የግል አስተያየት በመሰንዘር ሌሎችም እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ነው፡፡

ጽሑፉ አገራዊ መግባባት ስንል ምን ማለታችን ነው? በሚለው ይጀምርና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ለምን የሁሉም ፖሊሲዎችና ሕጎች ቁንጮ እንደሆነ ያብራራል (ከሕገ መንግሥቱ በመለስ):: ቀጥሎም የ1994 ዓ.ም. የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ይገመግማል፡፡ በመጨረሻም ምን መደረግ አለበት? የሚለውን የግል አስተያየት ያስቀምጣል፡፡ የሕዝቦቻችንና የአገራችን ደኅንነት የሚጠበቀው ፈጣን ልማት ሲረጋገጥና የዴሞክራሲ መስተዳደር በቀጣይነት መሠረት ሲጥል ነው፡፡ ከዚህም ተነስቶ ዋናው የደኅንነት አደጋ የዴሞክራሲ እጥረት ነው ይላል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህት፣ ጠባብነት፣ ወዘተ. የሚሉት ቅርንጫፎችና አጫፋሪዎች ችግሮች ቢሆኑም ከዋናው ችግራችን ማለት ከዴሞክራሲ እጥረት ሊያዛንፉን አይገባም፡፡

መሠረታዊ ችግሮቻችን ሕገ መንግሥታችን በግልጽና በተሟላ መንገድ ያስቀመጠውን የሦስት ትውልድ መብቶች (Three Generations Of Human Rights) አለመተግበር ነው፡፡ መላውን ኅብረተሰብ የሚመለከት ቢሆንም ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ልዩ ቦታ አላቸው፡፡ ትምክህትና ጠባብነት ማምለጫ መሆን የለባቸውም፡፡ በ1990 የኤርትራ መንግሥት ባልተዘጋጀንበት ለምን እንደወረረን ሌሎች ምክንያቶች ቢኖሩም፣ በዋናነት የተደራጀ የደኅንነት ፖሊሲና አስተዳደር ባለመኖሩ መሆኑን አጠር ባለ መንገድ ያስቀምጣል፡፡ በ2008 ዓ.ም. የተከሰተው አመፅ ለምን እንደ አገር ዱብ እዳ ሆነብን? አመፅ እየመጣ መሆኑን ከወዲሁ ለመገመት ለምን አልቻልንም? በ2008 ዓ.ም. ኅዳር አካባቢ የተከሰተው የኦሮሞ ተቃውሞ እንዴት የመጀመርያ ዙር መሆኑን ለማወቅ ተሳነን? እንዴት አመፅ ከመምጣቱ በፊት ልንከላከለው አልቻልንም? አሁንስ እንደዚያ ዓይነት ነገር አመፅ እንዳይከሰት መሠረታዊ መፍትሔዎች አስቀምጠናል ወይ? በሒደት ይዳሰሳሉ፡፡

አገራዊ መግባባት ስንል?

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንል በውሳኔ አሰጣጥ ባለድርሻ አካላት በአገሪቱ ዋና ዋና ጉዳዮች (በየደረጃው) በፖሊሲ ሕግ በይዘቱ ይሁን በውሳኔ አሰጣጥ ሒደት የሚመለከት ነው፡፡ ሕዝቦች በቀጥታ ይሁን የሚወክላቸው አደረጃጀት (ፍላጎታቸውን) የሚያንፀባርቁና የሚገልጹዋቸው (Articulate) የሚያደርጉባቸው ፓርቲዎች፣ ማኅበራት፣ ወዘተ. ፖሊሲው ሕጉን እንዲያውቁትና እንዲተቹት፣ ሐሳባቸውን የሚያሳርፉበት፣ በቀጣይነት ተሳትፏቸውን የሚያረጋግጡበት ሒደት መግባባትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሒደቱ ከይዘቱ አይተናነስም የሚባለውም ለዚህ ነው።

የፖሊሲ/ሕጉ አመንጪዎች (ከፍተኛ አመራር) ጭምር በመግባባት የሚጀምር የአብላጫው ሐሳብ ብቻ ሳይሆን፣ የውህዳን ድምፅ (Minority’s Voice) በሚገባ የሚሰማበት ሒደት ነው:: በፖሊሲው/ሕጉ የተወሰነ አንቀጾች ልዩነት ቢኖርም አጠቃላይ ይዘቱና በውሳኔ አካሄዱ ዴሞክራሲዊ ከሆነ ሁሉም በየኔነት ስሜት ለተግባራዊነቱ የሚረባረቡበትና መሻሻል ያለባቸው ላይ ቀጣይ ትግል እንደሚያስፈልገው አምነው፣ ባለድርሻ አካላት መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ብሔራዊ መግባባት ደረጃ በደረጃ እየተረጋገጠ ነው እንላለን፡፡ በብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ብሔራዊ መግባባት ለምን አስፈለገ የሚለውን ቀጥሎ እናየዋለን?

ብሔራዊ የደኅንነት ፖሊሲ የሁሉም ፖሊሲዎች ቁንጮ ነው ለምን?

በተለምዶ አስተሳሰብ ብሔራዊ ደኅንነት ማለት በዋናነት ውጫዊና ወታደራዊ አድርጎ ማሰብ የተለመደ ነው፡፡ ሉዓላዊነት (Sovereignty) እና የግዛት አንድነት (Territorial Integrity) በውጭ ሥጋት የሚሽከረከር እንደ ታሪካዊ ጠላቶችን ዓይነት አስተሳሰብ ገዥ ሐሳብ አድርጎ ቆይቷል፡፡ ባደጉ አገሮች አሁንም ወሳኝ አስተሳሰብ ነው፡፡ ያደጉ የምዕራብ አገሮች በብዙ ምዕተ ዓመታት የአገር ግንባታ ሒደት (State Building Process) የሕዝባቸውን መሠረታዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶች አሟልተናል ስለሚሉ፣ በሌላ በኩል ዴሞክራሲ በማረጋገጥ የአገርና የባንዲራ ፍቅር እንደ መንግሥት ያላቸው እምነት ጥሩ ነው ብለው ስለሚያስቡ፣ ከውስጥ የሚነሳ አደገኛ የሕዝብ ተቃውሞ አይኖርም ብለው ስለሚያምኑና ከግሎባላይዜሽን የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆንና ተፅዕኖቻቸውን ለማሳደግ ዋናው የደኅንነት ሥጋት ከውጫዊ አድርገው ያስቀምጡታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተለይ በሦስተኛ ዓለም አገሮች ይህ የተለምዶ አስተሳሰብ እንደገና ከሁኔታቸው ጋር አዛምደው ማየት የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በሽግግር ላይ ያሉና የተከፋፈለ ኅብረተሰብ (Divided Society) ያላቸው አገሮች ዋናው የብሔራዊ ደኅንነት ሥጋት ውስጣዊና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መዋቅር (Structure) የፈጠረውና በኅብረተሰቡ ኋላቀር አስተሳሰብ የሚታጀብ በተለይ ብቃት ባለው የዴሞክራቲክ አስተዳደር እጥረት የሚነሳ ነው፡፡ ስለዚህ በዋናነት ውስጣዊ ነው፡፡

የውጭ ጠላቶች ይህን ተንተርሰው የራሳቸውን ፍላጎት ለመጫን መሞከራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከውጭ የሚገኘውን በጎ ዕድል (Opportunity) ለመጠቀምና ሥጋት (Threat) ለመከላከል ከፍተኛ ሥራ መሥራት ቢኖርብንም፣ ዋናው ዕድልና ለደኅንነት የሥጋት ምንጭ ግን የውስጣችን ሁኔታ ነው፡፡ እኛ ስንደክም ነው የውጭ ጠላቶችም ለማጥቃት የሚቃጡት፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የመጀመርያው ክፍል በዋናነት የሕዝቦቻችን ስስት ትውልድ ሰብዓዊ መብቶች ዕውቅና ሰጥቶ በግልጽና በተሟላ አኳኋን ያስቀምጣል፡፡ ሁለተኛው ክፍል እነዚህን መብቶች ለማረጋገጥ አገር (State) እና መንግሥት  (Government) እንዴት መደራጀት እንዳለበትና ተዛማጅ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ያስቀምጣል፡፡ በሌላ አገላለጽ አገር/መንግሥት በዚያ መልክ እንደ ደረጃ የተደረገው የሕዝቦቻችን የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ መብቶች ለማረጋገጥ ነው፡፡ ከዚያ የዘለለም ከዚያም ያነሰም ዓላማ የለውም፡፡

በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍላጎቶች የአገራችን ጥቅሞችና ያሉንን ሰብዓዊና ተፈጥሯዊ እሴቶችን አጣምሮ ሰላምና ልማት፣ ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ ከውስጥ ሆነ ከውጭ የሚገኙትን ዕድሎች/ፀጋዎች በሚገባ አጢኖ፣ የሕዝቦችን ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ ለማደፍረስ ከውስጥ ሆነ ከውጭ የሚገኘውን ሥጋቶች አንጥሮና ቀምሮ የአገራችን፣ የአካባቢያችንና ዓለም አቀፋዊ አካባቢውን በጥናት አረጋግጦ እንዴት ሥጋቶችን መቀነስ እንደሚችልና መከላከል የሚያስችል ስትራቴጂዎችን ያቀፈ በመሆኑ፣ ከሕገ መንግሥቱ ቀጥሎ ለሁሉም የአገራችን እንቅስቃሴዎች አቅጣጫ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ነው የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ የፖሊሲዎች ሁሉ ቁንጮ የሚያስብለው፡፡ ለፖለቲካዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችም አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳይ በጥቂት ጄኔራሎች፣ የደኅንነት ባለሙያዎች (Experts) እና በሥልጣን ላይ ባሉ ፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆን የመላው ኅብረተሰብና የኅብረተሰብ የተለያዩ አመለካከት የሚያንፀባርቁና የሚገልጹ ፓርቲዎች፣ ሲቪልና ፕሮፌሽናል ማኅበራት ጉዳይ የሚሆነው፡፡ በብሔራዊ የደኅንነት ፖሊሲ መግባባት ማለት የአገራችንን ዕድሎችና ሥጋቶች መሠረት አድርጎ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የወታደራዊና የደኅንነት ክፍል እንዴት መመራትና መደራጀት እንዳለበት በአጠቃላይ መስማማት ማለት ነው፡፡ ፖለቲካዊ የኛው የሁላችን፣ ኢኮኖሚያዊ የኛው የሁላችን፣ ወታደራዊና ደኅንነት ክፍሎች የኛው የሁላችን ናቸው ብለን በአጠቃላይ ተስማምተናል ማለት ነው፡፡ የሚያለያዩን ጉዳዮች መኖራቸው አይቀርም፡፡ የሚታዩት ግን በዚህ ማዕቀፍና የተመቻቸ ሁኔታ ስላለ በሰላምና በሰላም ብቻ ለመታገል የምንችልበት የጋራ አስተሳሰብ አለ ማለት ነው፡፡ ከፅንፈኞች በስተቀር፡፡

የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ የአመለካከት አቅጣጫ ለውጥ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ አገር በቀልና ከደኅንነት አኳያ ያሉት በቂ ዕድሎች/ፀጋዎችና ሥጋቶች ዋናዎቹ ውስጣዊ መሆናቸውንና ድህነትና ኢዴሞክራሲያዊነት የአገሪቱ ህልውና ከሚፈታተኑን ሥጋቶች ዋናዎቹ መሆናቸውን በማያሻማ መንገድ ያስቀምጣል፡፡ የአገርና የሕዝብ ፍላጎትን አስተሳስሮ የአገር የመበታተን አደጋ የሚያጋጥመው በዋናነት በውስጣችን ባሉት ችግሮች መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ ደኅንነት ጥቂቶች ባለሥልጣናት/ጄኔራሎች የደኅንነት ባለሙያዎች ብቻ አለመሆኑናቸውን የመላው ሕዝቦች አጀንዳ ሆኖ እንደ ፖሊሲ ያላስፈላጊ ሚስጥርነት ድባብ ያገለለ (በሚስጥር የሚጠበቁ እንዳሉ ሁሉ) መለያው ነው፡፡ የደኅንነት የድብብቆሽ ሥራን ድባቅ የመታ ለውጥ ነው ያሳየው።

የደኅንነት ጽንሰና ንድፈ ሐሳባዊ ማዕቀፎችን በዓለም ዕውቅ ከሆኑ አስተምህሮዎችን (Schools of Thoughts) ቀደም ብሎ በዘውዳዊ ሥርዓትና በወታደራዊ አገዛዝ ሥርዓት ከነበሩት ፖሊሲዎች አንፃር ሲታይ፣ መሠረታዊ የአቅጣጫ ለውጥን (Paradigm Shift) የሚያመላክት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍላጎትና ተስፋ ከፈጣን የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተጠቃሚ መሆን ማለትም ከደኅንነት፣ ከኋላቀርነት፣ ከመሃይምነትና ከበሽታ የፀዳ ሕይወት መኖር ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላትን ኢትዮጵያ በመፍጠር የቡድንና የግለሰቦችን መብት ማስከበር፣ መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥና ለኑሮና ለሥራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው ብሎ ያስቀምጠዋል፡፡ የብሔራዊ ጥቅም (National Interest) በማያሻማና በተሟላ መንገድ እንዲህ ያቀርበዋል፡፡ “ብሔራዊ ጥቅም ማለት የሁሉም ሕዝብ ጥቅም ማለት ነው፡፡ ከዚህ ያነሰም የበለጠም ማለት አይደለም” (16) ትንተናው ልዑላዊነትና የድንበር አንድነት (Sovereignty and Territorial Integrity) ከሕዝቦች ፍላጎትና ጥቅም ጋር ብቻ አቀናብሮ ያየዋል፡፡ ከእነዚህ ጽንሰ ሐሳብ ውጫዊ አመለካከት ቋንቋዎች (External-looking Orientations) ይለያል፡፡ ፖሊሲው እየደጋገመ እንደሚያሰምረው ፈጣን የኢኮኖሚ ልማትን፣ ዴሞክራሲና ሰላምን ማምጣት በከፍተኛ ድህነትና ኋላቀርነት ለምትገኝ አገር መሠረታዊ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

በአጠቃላይ የፖሊሲው ስትራቴጂዎች ከላይ የተጠቀሱትን ወሳኝ የደኅንነት አካባቢ መፍጠር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ብሔራዊ ኩራትን (ነፃነታችን ጠብቀን መኖራችንን) እንደ አንድ እሴት፣ ድህነታችን (Poverty) እንደ አሳፋሪ ታሪክ አስቀምጦ፣ የተለዋዋጩ ምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ እንደ መልካም ዕድልና ሥጋት፣ ሉላዊነት (Globalization) ለልማትና ለዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸውን ተፅዕኖ እንደ መልካም ዕድልና የሥጋት ምንጭ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ መካከለኛው ምሥራቅን በተመለከተ ፖሊሲው እንዲህ ይላል፡፡ “መካከለኛው ምሥራቅ በእኛ ሰላምና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በእኛ ኢኮኖሚ ላይ በእጅጉ ተፅዕኖ ያደርጋል፣ ለዚህ ነው የመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ በእኛ በኩል ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡” (ኢውጉብደፓ፡ 46)

የመከላከያ መዋቅርን (Military Establishment) በተመለከተ ስትራቴጂዎችን ሁሉን አቀፍና የተቀናጀ (Comprehensive and Coherent) ሆኖ የአገሪቱን የልማት እንቅስቃሴ መሠረት አድርጎ የሚገነባና በጥልቅ የአደጋ ትንተና ላይ የተመሠረተ አቅም ግንባታ ላይ ሲሆን፣ ብቃት ያለውና ዘመኑ የደረሰበት የመረጃ መረብ ዕድገትን በማቋቋምና የሰው ልማት ላይ በማተኮር የሚታነፅ መሆን አለበት ይላል፡፡ ይህ ማለት በሁለት ተመሳሳይ የቴክኖሎጂ አቅም ያላቸው ኃይሎች መካከል ጦርነት ቢነሳ ወሳኝ ልዩነት የሚፈጥረው ሰው ነው፡፡ (ኢውጉብደፓ፡ 43) በሚል ነው፡፡ የአፍሪካን ትልቁ ሠራዊት ከመገንባት የደርግ እብደትና ድንፋታ ተወጥቶ ከአገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ተዛምዶ በልክ (Right Size) ሠራዊት ለመገንባት የሚቀነቅነው ሐሳብም ሌላው የአቅጣጫ ለውጥ ነው፡፡ ፖሊሲው የፋይናንስ ሀብትን በጥንቃቄ መጠቀምን በኢኮኖሚያዊና በመከላከያ ወጪ መካከል ቁርኝትን፣ የሠራዊቱና የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማቶች አቅም ግንባታ ከኢኮኖሚ ልማት አንፃርና ከአደጋዎች ጋር ያለውን ትስስር በሚገባ ያስቀምጠ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በጠመንጃ ወይም ቅቤ (Gun or Butter) ያለውን ግጭት ለመፍታት የታሰበለት አማራጭ ያስቀመጠ ይመስላል፡፡

ፖሊሲው ስለጠንካራ የማስፈጸም አቅም ግንባታ በሚመለከት “በትክክል የተቀረፀ የውጭ የአገር ውስጥ ፖሊሲዎች ዓላማዎች፣ ግቦች ፕሮግራሞች ስትራቴጂዎች በአግባቡ ተግባር ላይ ካልዋሉ የትም ሊያደርሱ አይችሉም፣ ለዚህም ነው ውጤታማ የማስፈጸም ብቃት እንደ መሠረታዊ ስትራቴጂ የሚታየው፤” (ኢውጉብዴፓ፡ 49):: ይህ አንድ ቁልፍ ነገር ነው። ፖሊሲው ከዘውዳዊውናና ከወታደራዊው አገዛዝ በተለየ ከበባ አስተሳሰብ (Siege Mentality) ወጥቶ “ታሪካዊ ጠላቶቻችን” የሁሉም ችግሮቻችን ምንጭ እንደሆነ በቀጣይነት ከማላዘን አልፎና በተቻለ መጠን የሥጋት ምንጮችን በመቀነስና ትብብርን የማስፋት አቅጣጫ ተከትለዋል፡፡ “የትኞቹ ጥቅሞቻችን አስፈላጊ እንደሆኑና የትኞቹ ኃይሎች ፍላጎታቸውን ለማስጠበቅ እንደሚፈልጉ በሚጠቅም አቅምና ኃይል ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ከግንዛቤ በመነጨ አደጋዎችን መጋፈጥና በትብብርና ገንቢ በሆነ መንገድ የሥጋት ምንጮችን ማስወገድ አስፈላጊ ነው፤” ይላል የፖሊሲ ሰነዱ በገጽ 33፡፡ በአጠቃላይ ፖሊሲዎቻችን ጥልቅ በሆነ ጥናትና ምርምር መቅረፅ እንዳለባቸው እያስቀመጠ እየተመላለሰ አጽንኦት የሚሰጠው ግን፣ “ለእኛ ዋነኛው የደኅንነት ሥጋት ምንጭ ውስጣዊ ነው፡፡ የድህነት መስፋፋት የአገሪቱ ህልውና አደጋ ሊሆን ይችላል፡፡ የመልካም አስተዳደር ዕጦት የዴሞክራሲ አለመኖር ወደ ደም መፋሰስና ጥፋት ሊከተን ይችላል፤” (91)፡፡ ሆኖም ፖሊሲው አጠቃላይ የአቅጣጫ ለውጥ የሚያመለክት ቢሆንም ቀጣይነት (Consistency) እና ሙሉዕነት (Comprehensiveness) ይጎድለዋል፡፡

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትና ኅብረ ብሔራዊነት እንደ መልካም ዕድል በሚገባ አያስቀምጥም፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት እጅጉን መሠረታዊና ፋውንዴሽናል (Very Basic and Foundational) የግጭቶች መሠረታዊ የአፈታት አቅጣጫዎች በመተንተን ውስጣዊ ደኅንነት የሚረጋገጥበት ሁኔታን አመቻችተዋል፡፡ በተሟላ ሁኔታ መብቶችን በማወቅ ሕገ መንግሥቱ አንድነት ማራኪ ያደረገ ብቻ ሳይሆን፣ አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብን የመፍጠር ሒደትም አመቻችቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ ማኅበራዊ ቡድኖች (Societal Groups) ተጨባጭ የሆነ ፍላጎታቸውን ለማጠናከርና ተጨባጭ ያልሆኑትን ሊሟሉ የማይችሉ ፍላጎቶች መሆኑን ለመገንዘብ የሚያስችል ሒደት አቀናጅቷል፡፡

ፖሊሲው ለደኅንነት አካባቢ (Security Environment) ሕገ መንግሥታዊ ዓውደ ጽሑፍ (Context) ከማስቀመጥ አኳያ የሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው፡፡ ብዝኃነት በአጠቃላይ የኅብረ ብሔራዊነት እሴት በተለየ፣ በዋጋ የማይተመን ሀብት መሆኑንና ለአገር ግንባታ ሒደትና ሁሉን አቀፍ ልማትን ለማፋጠን ያሉትን አዎንታዊ የልማት፣ የዴሞክራሲና የሰላም ሐሳቦች፣ መልካም ዝንባሌዎች የጋራ ልምዶች የግጭት መቆጣጠርና የአስተዳደር ዘዴዎች እንደ ዋነኛ አቅም አድርጎ አያስቀምጥም፡፡ ከዓለም አቀፍ የሚገኘውን የቴክኖሎጂና የቁስ ድጋፍ በከፍተኛ ድጋፍ ደረጃ ሲያደንቅና አስፈላጊነቱን ሲያስረግጥ፣ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊነትን የመሳሰሉ ፀጋዎችን በመርሳት “የኢትዮጵያ ሕዝቦች” የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ወደ ጎን በመተው፣ “የኢትዮጵያ ሕዝብ” የሚለውን ሐሳብ ሲያራምድ ከላይ የተገለጸውን የአቅጣጫ ለውጥ ስንኩል ያደርገዋል፡፡ ይህ የቃላት ጨዋታ ሳይሆን የራሱ ጥልቅ ፖለቲካዊ ትርጉም ያለው ነገር ነው። የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ መሠረታዊ የሆነ ከውስጥ የሚነሱ ፀረ ዴሞክራሲ ሥጋቶችን ችላ ያለ ነው፡፡ የአገራችን ደኅንነት ዋናው ውስጣዊ ነው ብሎ ለሚነሳ አስተሳሰብ የዴሞክራሲ ግንባታ በድህነት ማስወገጃ ትግል ሒደትን ሊያኮላሹ የሚችሉትን በውስጥ ተቋማት፣ ኃይሎችና ዝንባሌዎች ምንም ነገር ሳይል ማለፍ የሚያስገርም ነው፡፡ ዴሞክራሲን ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የውስጥ ተቋማት፣ ኃይሎችና ዝንባሌዎች በአዎንታዊ ይሁን በአሉታ ውስጥ መሆንን እንደታወቀ ያለመጥቀሱ አሁንም ያስተዛዝባል፡፡ በመንግሥት ይሁን በኅብረተሰቡ ሁልጊዜ በከፍተኛ ውጥረት (Tension) የሚኖሩት የፍፁም አንድነትና የመበተን ኃይሎች (Centripetal and Centrifugal Forces) መሳሳብ ቀጣይነት ያለው የደኅንነት ሥጋት መሆናቸውን የተገነዘበ አይመስልም፡፡

የፌዴራሊዝም ሥርዓት መሠረታዊ የደኅንነታችን ዋስትናና መሠረት ቢሆንም፣ እንደ ማናቸውም ሥርዓት የራሱ ተግዳሮቶች ያሉት አደረጃጀት ነው፡፡ ማይክል በርጊስ የተባለ ምሁር የፌዴራል መዋቅርን አስቸጋሪነት በጽሑፍ “In Seymour and Gugnoned” (2012፡24)  እንዲህ ሲል ያብራራል፡፡ “የፌዴራል አገር ግንባታ በተፃራሪዎች ችግሮችና አደጋዎች የተሞላ በመሆኑ ከመጀመርያው በጭንቀትና በውጥረት የተሞላ ሊሆን ይችላል፡፡ “በመቀጠልም ትራዱን (1968፡12) በመጥቀስ “እንደ የራስ ዕድልን በራስ የመወሰን ሐሳብ ፌዴራሊዝም እንዲኖር ቢያስገድድም እዚያ ሳለ የፌዴራል ሥርዓቱን ያልተረጋጋ ያደርጋል፤” ይላል፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔርና ብሔረሰቦች ከሰላም፣ ከልማትና ከዴሞክራሲ መሠረታዊ ጥቅሞቻቸው የሚረጋገጥ ቢሆንም፣ ተጨባጭ ሁኔታው ግን የተለያየ ትርጉምና አመለካከት (Perceptions) እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከፈጣን የኢኮኖሚ ልማት የሚያገኙት ድርሻ በተግባርም ይሁን በአስተሳሰብ የተለያዩ ባህሎችና የሕዝብ ብዛት ላላቸው አካሎች የተለያዩ ትርጉም ያለው ነው ወይም ሊኖረው ይችላል፡፡ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ብሔሮች ወይም ብሔረሰቦች በሕገ መንግሥታዊ ዲዛይን፣ በምርጫ ሥርዓቱና በመንግሥት ተቋማት አወቃቀር፣ በተለይም በሥራ አስፈጻሚና በደኅንነት ኃይሎች ብሔራዊ ተዋጽኦ (National Composition of the Executive, Military and Security Forces) ላይ ቅሬታ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ የታላላቅ ብሔሮች ልሂቃን (Elites) ባለው የፖለቲካ ሥርዓት ያልተሟሉ ፍላጎቶች ሊኖራቸው ሲችል፣ ትንንሽ ብሔሮች መሬታቸውን፣ ሀብታቸውንና ማንነታቸውን የማጣት ሥጋት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡

እነዚህ ክስተቶች ቀጣይነት ባለው ሰፊ ጥናትና ምርምር መሠረት አድርጎ በሕዝቦች መካከል ቀጣይነት ያለው ሰፊ ዴሞክራሲያዊ ውይይት በማድረግ መስተካከል ያሉበትን በወቅቱ መሟላት፣ የማይቻለውን በማስረዳት የሕዝቦች አንድነት ብሎም የአገሪቱ ደኅንነት ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡ ትምክህትና ጠባብነት ከሚባሉ አጫፋሪ ሐሳቦች በየጊዜው መውደቅ ያባብሰው እንደሆነ እንጂ የሚፈይደው የለም፡፡ አሁንም መፍትሔው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር በማጠንከርና የሕዝቦችን ሁለንተናዊ መብቶች በማስከበር ሁለንተናዊ ጥቅሞቻቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ በ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ እነዚህ ተግዳሮቶችን በዝምታ ለምን እንዳለፍናቸው ለመረዳት ያስቸግራል፡፡

ከደኅንነት አንፃር ወደብ የለሽዋ ኢትዮጵያ ሊያጋጥሟት የሚችሉ የደኅንነት ተፅዕኖዎችን የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ በዝምታ ነው ያለፈው፡፡ ነገር ግን ዘመናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ ብቃት ያለውና ወጪ ቆጣቢ ዓለም አቀፍ ግብይትን ይጠይቃል፡፡ የባህር በር ዕጦት የኢኮኖሚ ብሎም የደኅንነት ማነቆ ሊሆን ይችላል፡፡ ግጭት በማይጠፋበትና ራሳቸውን ለመቻል በትግል ላይ ያሉ መንግሥታት ባሉበት የአፍሪካ ቀንድንና ቀይ ባህርን ለመቆጣጠር ላይና ታች የሚሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ቀጣይ እንቅስቃሴ ባለበት ሁኔታ፣ የባህር በር ዕጦት የሚፈጥረውን ሥጋት ቸል ማለት አይገባም፡፡  

አጥንትና ሥጋ እንጂ ደም የሌለው ፖሊሲ

ፖሊሲው አገር በቀል የመሆኑን ያህል አዲስ የአቅጣጫ ለውጥ በማምጣት በደኅንነት ዙሪያ መሠረታዊ የአመለካከት አረጋግጧል፡፡ ሆኖም የአቅጣጫ ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ የተተነተነ ባለመሆኑ ከላይ የተገለጹትን መሠረታዊ ድክመቶችም ያዘለ ነው፡፡ ፖሊሲው በሰፊ ጥናትና ምርምር እንዲታጀብ በቂ አቅም በመፍጠር አስፈላጊነትና አገራዊ መግባባት እንዲኖር ቢያውጅም ይህን ለማስፈጸም የሚችለው የተሟላ የደኅንነት አስተዳደር (Security Governance) በሚመለከት ዝምታን መርጧል፡፡ አንድ ፖሊሲ የተሟላ ቢሆንም ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር በጥበብ አዛምዶ ለመተግበርና ለማበልፀግ፣ ጉድለቶች ካሉትም ለማረም የግድ ጠንካራ አስተዳደር ያስፈልገዋል፡፡ ቀጣይነት ያለውና የተሟላ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚከሰቱትን ዕድሎችና ሥጋቶች ቀጣይነትና ሰፊ በሆነ ጥናትና ምርምር ለማጎልበት የተደራጀ የደኅንነት አስተዳደር ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ ጽሑፍ ሲባል አጥንትና ሥጋ የምንለው የደኅንነት አካባቢ (Security Environment) እና Hardware ጨምሮ አጠቃላይ የደኅንነት ቅርፅ (Security Posture) ሲሆን፣ “ደም” ደግሞ የፖሊሲው ስስ ‹Software› ነው፡፡ የደኅንነት ቅርፅ ያለ “ስስ” ደም የሌለው አጥንትና ሥጋ ይሆናልና፡፡ እንደ ታዋቂዎቹ የደኅንነት ምሁራን አዘርና ሙን (Azar and Moon 1988) ገለጻ፣ “የደኅንነት አካባቢ ሥጋቶችና ዕድሎችን ከቁሳዊ አቅሞች (ወታደራዊ ኢኮኖሚያዊ ኃይል) እና ተጨባጭ የፖሊሲ መሠረተ ልማት፣ ወታደራዊ ዶክትሪን የኃይል አወቃቀር (Force Structure)፣ መረጃ (Intelligence)፣ የመሣሪያ አመራረጥ፣ ወዘተ. የሚያካትተው የደኅንነት ቅርፅ (Security Posture) “ደም” (Software) ከመጨረሻው የፖሊሲ ውጤቶችና አጠቃላይ የፖሊሲ አፈጻጸም የሚያስተሳስር ነው፤” ይላል። በሌላ አገላለጽ የፖሊሲው ዶክመንት ወደ ተግባር/መሬት ለማውረድ የሚያስችል “ለአጥንቱና ሥጋ” ሕይወት የሚዘራ ደም ነው ሶፍትዌር የሚባለው፡፡

የደኅንነት አስተዳደሩ ፖሊሲው የተሟላና ዘላቂ ቅቡልነት (Legitimacy) እንዲያረጋግጥ፣ የሁሉም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኃይሎችና የደኅንነት ክፍሎች ቅንጅት/ውህደት (Integration) እንዲኖር የሚያረጋግጥና የፖሊሲው አቅም በቀጣይነት ለመገንባት የሚያስችል ነው፡፡ ፖሊሲው በትክክል ያነጠረው የአገሪቱ ህልውና ዋናው ሥጋቶች ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በሌላ አገላለጽ ፈጣን ልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ባረጋገጥን ቁጥር የአገራችን ህልውና የሚያስተማምን መሠረት እየተጣለ ይሄዳል ማለት ነው፡፡

ቅቡልነት ለማረጋገጥ “የመጀመርያ ቅቡልነት” (Prema-facie Legitimacy) ማንፀባረቅን ይጠይቃል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ብሔራዊ ተዋጽኦ፣ የአመራሮቹ ብቃት፣ የሕዝብ ባህል/ወግ የማክበርና አመርቂ ሕገ መንግሥትን ይጠይቃል፡፡ ቅቡልነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሕገ መንግሥቱን የመተግበር ህያው ፖለቲካ ለመምራት የሚወጡት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጥራትና የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ሥርዓቱ እኛን ይወክላል፣ ፍላጎታችን ቀስ በቀስ እያሟላ ይሄዳል፣ በአገራችን ጉዳይ እኩል እየተሳተፍን፣ ወዘተ. የሚል አመለካከት (Perception) ካለ “አጥንቱና ሥጋ” ነፍስ ለመዝራት ህያው ሆኖ እንዲተገብር የመጀመርያው ፈተና አልፏል ማለት ነው፡፡ ቅቡልነት የሚባል ደም፡፡

በእውነትም ይሁን በተሳሳተ መንገድ “የአንድ ብሔር የበላይነት አለ”፣ “የሚገባን ሥልጣን እያገኘን አይደለም”፣ “በበጀት አድልኦ አለ”፣ “ፍትሕ የለም” የሚባል ሰፊ አስተሳሰብ ካለ ሕይወት የሚዘራ ደም መሆኑ ቀርቶ “አጥንትንና ሥጋውን” የሚፈጅ እሳት ይሆናል፡፡ ሕግ ካልተስተካከለ አገሪቱ ባልፈነዳ እሳተ ጎመራ ላይ እንደተቀመጠች ሊቆጠር ይችላል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው የደኅንነት አስተዳደር ካለ ቀጣይ በሆነ ጥናት እያካሄደ ቅቡልነት የሚያሰጡ እውነተኛ ምክንያቶችን ያለማወላወል በማስተካከል፣ በተሳሳተ አመለካከት (Perception) በግልጽ ከሕዝቦች ወኪሎች ጋር እየተወያዩ ረመጡን በጊዜው በማጥፋት ቅቡልነት እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል ውህደት (Integration) የሚባለው “ደምም” በብዛትና በጥራት መገኘት ይኖርበታል፡፡ በአገራችን ሁኔታ ዴሞክራሲ ያለ ፈጣን ልማት፣ ልማት ያለ ዴሞክራሲያዊ ምኅዳር መረጋገጥ አይችሉም፡፡ ልማቱን እናፋጥነው ዴሞክራሲው ቢቆይም ቀስ ብሎ ይደርሳል ማለት የዋህነት ነው፣ ወይም ደግሞ አውቆ አጥፊነት ነው፡፡ የፈጣን ልማት ጉዞና ዴሞክራሲያዊ ግንባታ መዋሀድ ይኖርበታል፡፡ ፖለቲካው ከኢኮኖሚ፣ የውጭ ሥጋት ከውስጥ፣ ሲቪል አስተዳደሩ ከወታደሩ፣ ፌዴራል መንግሥቱ ከክልል ካልተዋሀደና መነጣጠል ከመጣ፣ የተለያዩ ማኅበራዊ ኃይሎችን ወደ አንድ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ለመምጣት ካልተቻለ የአደጋ ምልክት ነው፡፡ የፖለቲካው መበታተን በአገር አደጋ እንዲያንዣብብ ያደርጋል፡፡ የውህደት ደሙ ካልደረቀ ወይም መሳሳት ካሳየ፣ ወይም ከቆሸሸ አጥንቱ ይጎብጣል ሥጋው ይበሰብሳል፡፡

የፖለቲካዊ ሥርዓቱ ቅቡልነትና ውህደት እየተረጋገጠ ሲሄድ (ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ) የዴሞክራሲ ትውልድን ዕድገት ያፋጥናል፡፡ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን እንደሚሉት የ“ቁቤ ትውልድ” (Qubee Generation) የኦሮሞ ሕዝብ ትግልን ውጤት መሠረት አድርጎ አዲስ ታሪክ በመጻፍ፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመሆን ዴሞክራቲክ ሥርዓትን ለመገንባት ወይም በትግራይ እንደሚባለው “ሳልሳይ ወያኔ” ትውልድ ማለት የሁለተኛው ወያኔ ድል መሠረት አድርጎ አመራሩን በመንጠቅ፣ ፖለቲካዊ መንሸራተቱን ከሌሎች ወጣቶች ሆነው ለመፍታት የሚሞክር በሌሎች ሕዝቦችም ተመሳሳይ ምሳሌዎች ሊጠቀሱ ይችላል፡፡ ተቀባይነትና ውህደት ለማረጋገጥና የግድ ፖሊሲውን የማስፈጸም አቅም (Policy Capacity) ይጠይቃል፡፡ አቅም ለመገንባት የጠራ አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ተቀባይነትና ውህደት እያረጋገጠ የሚገነባ አቅም፡፡ የዴሞክራሲያዊ ትውልዱ፣ የቴክኖሎጂ ትውልድ፣ የአፍላ ጉልበት ትውልድ መሠረት አድርጎ መገንባት ይጠይቃል፡፡

ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ፖለቲካዊ ሳይንቲስቶች፣ ኢኮኖሚስቶች፣ የፀጥታ ባለሙያዎች. . . ወዘተ. ማእከል ያደረገ የአገራችን የውስጥ ዕድሎችንና ሥጋቶች ከአፍሪቃ ቀንድ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከግሎባላይዜሽን ጋር አስተሳስሮ ፖሊሲው ያስቀመጠውን አቅጣጫ በተሟላ መንገድ የሚረዳና የሚያጎለብት፣ አጥንቱና ሥጋው ከበቂ የደም ጥራት ጋር አዋህዶ የደኅንነት አቅሞችን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅሞ ሥጋቶችን በቀጣይነት በመቀነስ፣ በፈጣን ዕድገት ዴሞክራሲያዊ ምኅዳሩ እየሰፋ የተረጋጋች አገራችንን የሚገነባ አቅም መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ የተሟላ የደኅንነት ቅርፅ (Security Posture) እንዲኖር ተቀባይነት፣ ውህደትና የፖሊሲ አቅም እያዳበረ እንዲሄድ የሚያስችል አደረጃጀት ያስፈልገዋል፡፡ በተለምዶ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስል (National Security Council) እየተባለ የሚጠራውና በሥሩ በጣም ጠንካራና የተሟላ የደኅንነት ሴክሬተሪያት (Secreteriat) እንዲኖር የግድ ነው፡፡

የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ ስለ ካውንስሉና ሴክሪታሪያቱ ዝምታ መርጧል፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስል ደኅንነትን የሚመለከት ከፍተኛው የሥራ አስፈጻሚው አካል ሲሆን፣ በየጊዜው እየተሰባሰበ ወሳኝና ስትራቴጂካዊ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍና ተግባራዊነቱ በሴክሬታሪያቱ በኩል የሚከታተል ነው፡፡ ሴክሪታሪያቱ በቁጥር ሆነ በብቃት ከሁሉም ዘርፍ የተውጣጡ በቂ ባለሙያዎችን ያካተተ ሆኖ በራሱ ዘርፈ ብዙ ጥናት የሚያካሄድ መሆን አለበት፡፡ የመከላከያና የውስጥ ደኅንነት ጥናቶች፣ መረጃዎችና የአገሪቱ ከፍተኛ የትምህርትና የዲፕሎማሲያዊና ፕሮፌሽናል ተቋማትን ተጠቅሞ የውስጥም ሆነ የውጭ ሥጋቶችንና ዕድሎችን መሠረት አድርጎ የተለያዩ ቢጋር/ቢሆኖች (Scenarious) በማደራጀት፣ ለውሳኔ ወደ ካውንስሉ የሚያቀርብና ተግባራዊነቱን የሚከታተል ነው፡፡  

የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስል ይሁን ሴክሪታሪያት ተቀባይነትን (ውህደትን) አቅሙን በሚያረጋግጥበት መንገድ መዋቀር ይኖርበታል፡፡ ብሔራዊ ተዋጽኦ አገሪቱን የሚያንፀባርቅ፣ በተለምዶ ደኅንነት (ወታደራዊ ደኅንነት) የሚባሉትን ብቻ ሳይሆን ዋናው ሥጋት ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት በመሆኑ የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊና የዴሞክራቲክ ተቋማትን ጭምር በማሳተፍ ውህደት የሚያረጋግጥ፣ በከፍተኛ ደረጃ ሁሉን አቀፍ ባለሙያዎችን (በተለይ ሴክሪታሪያቱ) መሠረት ያደረገ አቅም ፈጣሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ካውንስልና ሴክሪታሪያት በማናቸውም አደረጃጀት ሊተካ አይችልም፡፡ የመከላከያ ተቋም ዋናው ተልዕኮ አገሪቱን ከውጭ ጥቃት መከላከል ነው፡፡ የውስጥ ደኅንነት ክፍሉ በውስጥ ፀረ ኢትዮጵያና ሽብርተኛነትን ተከታትሎ የሚያድን እንጂ፣ አጠቃላይ ከድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት የሚነሱት ሥጋቶችን ለመከታተል የተደራጀ አይደለም፡፡ ስለዚህም ይህ ቀዳዳ ካልተሞላ እስካሁን የከፈልነው ሳይበቃ ከውስጥም ከውጭም ለከፍተኛ ጥፋት ልንዳረግ እንችላለን፡፡

በጠንካራ ሴክሪታሪያት እየታገዘ የሚንቀሳቀስ ካውንስል መኖሩ ፖለቲካዊ ትርጉሙ ከፍተኛ ነው፡፡ የሲቪሎች አመራር (Civilian Administration) ወሳኝነት በመከላከያና የውስጥ ደኅንነት ክፍል የሚያረጋግጥበት መንገድ ጭምር ነው፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስሉ እንደተቋቋመ ይታወቃል፡፡ መሪነቱን እስከምን ድረስ እያረጋገጠ ነው? የሚለው በጥናት የሚታይ ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ የሚመራ ቡድን በጣም ጥቂት አባላት ቢኖሩትም፣ የሴክሪታሪያት ሚና ለመጫወት ይችል ይሆን እንዴ? እያሉ የደኅንነት ባለሙያዎች ጥያቄዎች እያነሱ እያለ፣ በ2009 ዓ.ም. በተደረገው አዲስ የመንግሥት አደረጃጀት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማካሪዎች ቡድን ሲፈርስ የደኅንነት አማካሪ ቦታ በተለይ መልሶ ሳይደረግ ቀሩ፡፡ ከድጡ ወደ ማጡ ይሏል ይኼ ነው!

የጠራ የደኅንነት ፖሊሲ ባለመኖሩ፣ እንዲሁም ተቀባይነት፣ ውህደትና የፖሊሲ አቅም የተላበሰ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስልና ሴክሪታሪያት ባለመኖሩ በ1990 ብዙ ምልክቶች እያሉም የኤርትራ መንግሥት ስትራቴጂካዊ ድንገተኝነት አግኝቶ አገራችንን ወረረ፡፡ መጨረሻው በኢትዮጵያ አሸናፊነት (ከዚያ በላይ ድሉ ሊሰፋ ይችል ነበር ወይ? የሚለውን ለጊዜው ትተን በተለይ አሁን ካለው ‹ወይ ሰላም ወይ ጦርነት› ካለመኖር ጋር ተያይዞ) ቢረጋገጥም፣ የከፈልነው መስዕዋትነት በሰው ሕይወትም በንብረትም ከፍተኛ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ አገራችን ተያይዛ ከነበረው የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ለጥቂት ዓመታት ቢሆንም ያደረሰው ኪሳራ ከፍተኛ ነው፡፡ ከኤርትራም ሆነ ከሌሎች አገሮች ጋር የሚኖረን በፖሊሲ ለውጥ በአዋጅ እናጠናዋለን እየተባለ ሳይሆን፣ የካውንስሉ ሴክሪታሪያት ዋናውና በቀጣይነት የሚሠራ ነው መሆን የነበረበት፡፡ የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ ማሻሻል ከተፈለገ ጊዜያዊ ኮሚቴ በማቋቋም ሳይሆን፣ ከምንም ረቂቅ  አዘጋጅቶ ለባለድርሻ አካላት ለውይይት ማቅረብ ይገባ ነበር፡፡ ያ ተቋም ወሳኝ ነው፡፡ የ2008 ዓ.ም. ግርግርና ጥፋት፣ እሱ ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት አገራችንን ወደ መበታተን ሊያደርሱ የሚችሉ ወሳኝ ሥጋቶች ናቸው የሚለውን በተግባር ያሳየን ሁነት ነው፡፡ ኃይላችንን ሳንበታትን በእነሱ ላይ በመረባረብ የተረጋጋ ሰላም፣ የበለፀገችና ዴሞክራሲያዊት አገር እንገንባ፡፡ ይህን ለማድረግ በብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲና አመራሩ መግባባት ይፈጠር፡፡

በተለይ የዴሞክራሲያዊ ምኅዳር እየጠበበ መሄድ ከሁሉም በላይ የሚያሳስብ ነው፡፡ ምኅዳሩ የመጥበብ ጉዳይ የጥቂት ፓርቲዎች መሳተፍ አለመሳተፍ፣ የጥቂት ሰዎች የመጻፍና ያለመጻፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ምኅዳሩን እንዴት እናስፋው? ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥቱን ብቻ ማዕከል አድርገው እንዴት በተግባር ይዋሉ? የሥራ አስፈጻሚውን አምባገነንነት እንዴት እንቆጣጠር? ፓርቲ፣ መንግሥት (Government)፣ አገር (State) በተመለከተ የሚታየውን መዘባረቅ እንዴት እንቀንሰው? በአጠቃላይ ሕገ መንግሥታችን በፖለቲካው የበላይት የሚያገኝበት፣ ብሎም ግልጽነትና ተጠያቂነት የነገሠበት ምኅዳር ለማንገሥ መረባረብ ይኖርብናል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት ከድህነትና ከዴሞክራሲያዊ እጥረት የሚመነጩ በፈጣን ዕድገትና ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ብቻ የሚሸነፉ ናቸው፡፡

በተለይ ትምክህትና ጠባብነት የሚባሉ ጉዳዮች ዴሞክራሲን ማዕከል በማድረግ ካልታዩ አደገኞች ናቸው፡፡ የአመራሩ ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን የጎንዮሽ ግጭት (Horizontal Conflict) የማስፋትና የትችት ትኩረትን ወደ ውጭ የማዞር (Externalization) ሥልት ሊሆን ይችላል፡፡ ኅብረተሰቡ ወደ ላይ አንጋጦ በአመራሩ ያለውን ችግር እንደ ዋነኛ አድርጎ እንዳይረባረብ እርስ በርሱ እንዲገማገም ለማድረግ የታሰበ እንዳይሆን፡፡ እስኪ ይግረማችሁ አስተማሪ በሙያው ሳይሆን እርስ በርሱ በትምክህትና በጠባብነት ሲገመገም፣ ድስት ስታቁላላ ወጥ ያረረባት ሠራተኛ የማረሩ ምንጭ በትምክህትና በጠባብነት ምክንያቱ እየተፈለገ ነው፡፡ በኪራይ ሰብሳቢነት ሆነ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ወይም በጠባብነትና በትምክህት በላይኛው አመራር ላይ ስለተወሰደ ዕርምጃ የምናውቀው የለም፡፡ የተሰጠን መልስ ማስረጃ የለም ነው፡፡ ፖለቲካዊ ሙስና ባለበት ሁኔታ የገንዘብ/ኢኮኖሚ ሙስና እንዴት ማስረጃ ሊገኝበት ይችላል?

በተለይ ጠባብነትና ትምክህት የሚባሉት የአጫፋሪ ቃላት አባዜ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እየታየ ያለውን የብርሃን ጭላንጭል እንዳይገድለው መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ ብቃት ያለው ካቢኔ ለመመሥረት “የኢኮኖሚክ አብዮት” መጀመርና በራሱ ተማምኖ መወሰን (Assertiveness) የጠንካራ ክልላዊ መንግሥት ምልክት እያየን ነው፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በቅርቡ ባላሀብቶችን ሰብስበው ሲያናግሩ፣ “የምንወስንባቸውና ልንወስንባቸው የማንችልባቸው ሥልጣኖች አሉን፣ የተገደበ ሥልጣን ነው ያለን፣ እኔ በግልባጭ አልወስንም፤” ብለው የፀና ፌዴራሊስት አቋማቸውን ገልጸዋል። ይበል የሚያስብል ነው። ጠንካራ የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት መኖር ለጠንካራ ኢትዮጵያ መሠረት ስለሆነ በጉድለቶቹ ላይ ተንተርሰን ደካማ ጎን እየፈለግን አናራግበው፡፡

ምክር ቤቶቻችን በትምክህትና በጠባብነት ምክንያት አልተሽመደመዱም፣ ፍትሕ የታጣው በትምክህትና በጠባብነት ምክንያት አይደለም፡፡ በ2008 ዓ.ም. የነበረው ተቃውሞ በዋናነት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው (ጠባብነትና ትምክህት ቢያጅበውም)፡፡ ወጣት ፖለቲካል ሳይንቲስቱ ናሁሰናይ በላይ አስገራሚ ሐሳብ አለው፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ “በዲሞክራሲ ዕጦትና በኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳስብና ተግባር መካከል ያለው መስተጋብር ልክ እንደ ዝንብና ቆሻሻ አድርገህ ማየት ይቻላል፤›› ይላል፡፡ በመቀጠልም፣ ‹‹ቆሻሻ (የዴሞክራሲ እጥረቱ) በሌለበት አካባቢ አንድ ሁለት ዝንቦች (የኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት አስተሳሰብና ተግባር) ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ድምፅ ካልሰማህ መኖራቸውን አታውቅም፡፡ ከዝንብ ነፃ የሆነ አካባቢ ያለህ ይመስልሃል፡፡ ከፍተኛ ቆሻሻ በሚከማችበት ግን የዝንብ መዓት አያስቀምጥህም፤›› በማለት የሁለቱን ምክንያታዊ ጥምረት ያብራራል፡፡ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ረገድ ችግር በሚኖርበት ጊዜ እነዚህ ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ ልሂቃን ያለምንም ከልካይ ወይም ሃይ ባይ ወለል ያለ ሜዳ ስለሚያገኙ እንደፈለጉ ይጋልቡበታል ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁኔታዎች ሁሉ አደገኛ ይሆናሉ፡፡ መፍትሔውም ዝንቦች (የኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት) ከማስወገድ በላይ፣ ቆሻሻውን ማስወገድ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ማለት ነው፡፡ ፀረ ዴሞክራቲክ አስተዳደር የሚባል ቆሻሻ፡፡

ማጠቃለያ

አገራችን የገጠማት ችግር ተራ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳይሆን፣ እንደ አገር ቆሞ የመቀጠልን ሥጋት የጋረጠ ከፍተኛ የደኅንነት አደጋ መሆኑን ዓይተናል። ለዚህም ሲባል አገራዊ ችግራችን በአገራዊ መግባባት መፍታት ካለብን፣ መወያያትና መነጋገር ያለብን ከሕገ መንግሥቱ በታች የፖሊሲዎች ቁንጮ በሆነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ (ኢውጉብደፓ) ዙርያ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲም ጥልቅ ተሃድሶ ሲል የፓርቲ ተሃድሶ ነው? ወይስ የመንግሥታዊ መዋቅር ተሃድሶ? የሚባለውን በቅጡ ለይቶ መንቀሳቀስ አለበት። የደኅንነታችን ዋና የሥጋትም የኩራትም ምንጭ ውስጣዊ የዴሞክራሲና የልማት ሁኔታ መሆኑ በመገንዘብ፣ የችግሩን ሥረ መሠረት ትቶ አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተንጠላጥሎ የሚመጣ ለውጥ ሊኖር እንደማይችል መረዳት አለበት። እያጠናሁት ነው የሚለው የፖሊሲ ክለሳም ሆነ ጥልቅ ተሃድሶ የአገሪቱን መሠረታዊ ችግር የሆነውን የድህንነት ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ አካሄድ መከተል አለበት። ይዘቱ ብቻ ሳይሆን ሒደቱም ለአገራዊ መግባባት ወሳኝ ነው፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ያሉንን አቅሞች አሟጦ፣ ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት እንደ ዋነኛ የውስጥ ሥጋት አድርጎ፣ አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት እንዴት የአገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ እናረጋገጥ? የሚለው አጥንትና ሥጋ ከደም ጋር አዋህዶ የሚያስተማምን ፖሊሲ መቅረፅ የግድ ነው፡፡ ፖሊሲው በኢሕአዴግና በኢሕአዴግ ዙሪያ ባሉት ሰዎች ብቻ ተረቆና ውይይት ተደርጎበት መፅደቅ የለበትም፡፡ የፖለቲካዊ ፓርቲዎች፣ የሲቪልና የሙያ ማኅበራት፣ የክልል ምክር ቤቶች፣ ወዘተ. ተሳትፎና የተለያዩ አስተያየቶች ተጨምሮበት መሆን ይገባዋል፡፡ ባይሳካም ደቡብ ሱዳንን በተመለከተ ከጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ የሰማሁትን ላካፍላችሁ፡፡

የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ለማርቀቅ አንድ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች ተሰጠው፡፡ በመጀመርያ ረቂቅ ተዘጋጀ፡፡ ከፖለቲካዊ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ተደረገበት፡፡ ከዚያም ወደ አሥሩ ክልሎች ኮሚቴው ተሰማርቶ፣ የየክልል ሕገ አውጭንና ሕግ አስፈጻሚውና ሲቪል ማኅበረሰቡ የመጀመርያው ረቂቅ ቀርቦለት ለየብቻ ሰፋፊ ውይይት ተደረገበት፡፡ ብዙ ግብዓት ተገኘበት፡፡ ኮሚቴውም ግብረ መልሶችን እንደ ግብዓት በሚገባ አሰባሰበ እንደገና መሥራት ጀመረ፡፡ ይዘቱም ዳበረ፡፡ በመሀል ግርግሩ ተፈጠረ፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የኅብረተሰብ ወኪሎች በስፋት መሳተፋቸው የፈጠረው የእኔነት ስሜት በብሰባው ይታይ ነበር፡፡ ውጤቱን ለማየት አልታደሉም፡፡

ኢውጉብደፓ ከውጭ ወደ ውስጥ ይመለከት የነበረው የደኅንነት አስተሳሰብ በግልጽ አሳይቶታል፡፡ አልቀጠለበትም እንጂ፡፡ አሁንም ስላልረፈደ አሳታፊ በሆነ መንገድ ሁሉም ኃይሎች የሚሳተፉበትና የእኔነት ስሜት በሚፈጥር መንገድ ዴሞክራሲና ፈጣን ልማት የዋስትናችን መሠረቶች መሆናቸው በተግባር መግባባት ግድ የሆነበት ሰዓት ላይ መድረሳችን ታውቆ፣ ዕርምጃችን በዚህ ቅኝት ቢሆን መልካም ነው እያልኩ ጽሑፌን በዚህ ልቋጨው።

**************

The post አገራዊ መግባባት ለብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ወሳኝ ዕርምጃ ነው! (አበበ ተክለሃይማኖት) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


መቀሌ ደም በዋንጫ እየጠጣች ነው! – ልዩ ፈንታ

$
0
0

ከባህርዳር ለስፖርት ብለው ርቀው ወደ ትግራይ መቀሌየተጓዙ ስፖርተኞች እና ደጋፊዎቻቼው የጨካኙ የህዋህት ደጋፊ በሆኑ በህዝብ ደም ሲጨፍሩ ዉለው በሚያደሩ ካድሬዎች እማካኝነት ተደበደቡ ። ሜዳው በአማራ ልጆች ደም ታጠበ።

እንዲህ ነው እንጂ በህዝብ ደም ከሰከሩ አይቀር ጥሩ አደርጎ በዋንጫ መጎንጨት።
ኦ! መቀሌ የደም መሬት

The post መቀሌ ደም በዋንጫ እየጠጣች ነው! – ልዩ ፈንታ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የብሪታኒያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ ግፊት እየተደረገበት ነው

$
0
0

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009)

የብሪታኒያ መንግስት ባለስልጣናት በሃገሪቱ በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በሚመከረው አለም አቀፍ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ የኢትዮጵያ መሪዎች ጋር በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ዙሪያ እንዲመክሩ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሃሙስ ጥሪ አቀረበ።

በለንደን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ ጉባዔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሳታፊ ሲሆኑ ከብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ ጋር ውይይትን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁንና የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይን ወክሎ የሚገኘውና የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሪፕሪቭ የብሪታኒያ መንግስት በዚሁ ውይይት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በሚለቀቁበት ጉዳይ ዙሪያ እንዲመክሩ አሳሰቧል።

የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት የሃገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በቂ ጥረት እያደረገ አይደለም ሲሉ ባለፈው ወር ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወሳል።

የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና ግለሰቦች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ በማሰባሰብ መንግስት ዕርምጃ እንዲወስድ ዘመቻ መክፈታቸውም አይዘነጋም።

በሪፕሪቭ ተቋም ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሃሪት ማክ-ኩሎች የብሪታኒያ መንግስት ለዜጋው መብት መከበር ቅድሚያን በመስጠት በለንደን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ጋር የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲመክሩ አሳስበዋል።

በለንደን በመካሄድ ላይ ባለው የሶማሊያ አለም አቀፍ ጉባዔ የኢትዮጵያና የተለያዩ ሃገራት ተወካዮች ተሳታፊ ሲሆኑ ሃገሪቱ ሰላሟን በምታገኝበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ እንደሚገኝ ታውቋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅትና በብሪታኒያ መንግስት አስተባበሪነት በተዘጋጀው በዚሁ አለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ሶማሊያ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ውስጥ አስተማማኝ እንድታገኝ ሰፊ ውይይት እየተካሄድ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ሃይልን አሰማርተው የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ተወካዮች በለንደኑ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ጨምሮ የዩጋንዳ፣ የኬንያ፣ የማላዊ፣ የብሩንዲና የጅቡቲ የሰላም አስከባሪ ሃይሎች በሶማሊያ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ከ22 ሺ የሚበልጡ ሰላም አስከባሪዎች ሰላምን ለማስፈን ጥረት እያደረጉ ይገኛል። ይሁንና የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ አሁንም ድረስ የሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ሆኖ ይገኛል።

The post የብሪታኒያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ ግፊት እየተደረገበት ነው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ለአለም ጤና ድርጅት ቀጣዩ ዋና ዳይሬክተር ለመሆን እየተወዳደሩ ባሉት በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ በርካታ ተቃውሞዎች እየቀረበባቸው ነው

$
0
0

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009)

ለአለም ጤና ድርጅት ቀጣዩ ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ከመጨረሻዎቹ ሶስቱ ተፎካካሪዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከበርካታ ኢትዮጵያ ዘንድ እየቀረበባቸው ያለው ተቃውሞ ተጠናክሮ መቀጠሉን ግሎባል ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የተሰኘ ጋዜጣ ዘገበ።

የአለም ጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት በቅርቡ ቀጣዩን የድርጅቱ ሃላፊ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እያሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም የተቃውሞ ቅስቀሳን እያካሄዱ እንደሚገኝ ጋዜጣው አስነብቧል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳይመረጡ ዘመቻን እያካሄዱ ያሉት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ተፎካካሪው በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በአፈናው የቆየ ታሪክ ያለው የገዢው የኢትዮጵያ መንግስት ዋነኛ ተዋንያን መሆናቸውን እየገለጸ መሆኑን ግሎባል ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል።

የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰጥ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊ ሪፖርትና በተለያዩ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጭምር ሲቀርብ መቆየቱ ይታወሳል። ይኸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ ተቃውሞን እያሰሙ ያሉ ኢትዮጵያውያን የአለም ጤና ድርጅት ተቃውሞአቸውን እንዲሰማ እያደረጉ እንደሚገኝ ጋዜጣው አብራርቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያን የአለም ጤና ድርጅት ዋና ሃላፊውን ለመምረጥ በሚያደርገው ልዩ ጉባዔ ወቅት በዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከተማ የተቃውሞን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሄዱ የሰልፉ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል።

የአለም ጤና ድርጅት አባል ሃገራት ከግንቦት 15 ፥ 2009 አም ጀምሮ ለአንድ ሳመንት በሚካሄደው አመታዊ ጉባዔ ቀጣዩን የድርጅቱ ሃላፊ ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይሁንና በዕለቱ ተቃውሞን ለማሰማት በዝግጅቱ ያሉ የሰልፉ አስተባባሪዎች ዶ/ር ቴዎድሮስ በገዢው የኢህአዴግ መንግስት ውስጥ ያላቸው የቆየ አስተዋፅዖ ተጠያቂ የሚያደርጋቸው በመሆኑ፣ የአለም የጤና ድርጅት ጉዳዩን እንዲረዳ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል።

ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር የብሪታኒያና የፓኪስታን ተወካዮች ለመጨረሻ እጩነት ቀርበው የሚገኙ ሲሆን፣ የጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት በሚስጥር በሚሰጡት ድምፅ ቀጣዩን ዋና ዳይሬክተር ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

The post ለአለም ጤና ድርጅት ቀጣዩ ዋና ዳይሬክተር ለመሆን እየተወዳደሩ ባሉት በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ በርካታ ተቃውሞዎች እየቀረበባቸው ነው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

በሮናልድ ሬገን ውስጥ ቴዲ ኣፍሮ – ንጉሤ አዳሙ

$
0
0
የዚህ ጽሁፍ ጽንሰ ሃሳብ ቴዲ አፍሮ ወይም ቴዎድሮስ ካሳሁን በቪኦኤ የአማርኛዉ ፕሮግራም ላይ ካደረገዉ  ቃለመጠይቅ ላይ መሰመር ያለበትን ሃሳብ ለመጠቆም ነው፥ ይህ ጨዋና ኣርቆ ሳቢ የሆነ ወጣት:-
” ኢትዮጵያዊነት ኣደጋ ላይ የወደቀበት ሰኣት ላይ ነን እንዳለመታደል ሆኖ የዚህ ችግር ደግሞ እኛ ወጣቶች ላይ  የተጋፈጧል ብሎል።”
ይህ ኣንደበተ ርእቱ የዘመናችን ወጣትና የብዙሃን ድምጽ የሆነው ቴዲ ኣፍሮ በመቀጠልም
“መቻቻል፥ መከባበር፥ መስማማት፥ የሃገራችንን ህልውና ከራስ ህልውና ጋር በማጣመር ለሃገራችን የሚበጀውን መሞከር ብቻ ሳይሆን ማድረግ ኣለብን ብሏል።”
በዚህ ጠንካራ ኣቆሙ ነው ቴዲ ኣፍሮን ከሊሎች የሙዚቃ ባለሙያወች እኩል ልንተቸው ኣይገባም ተብሎ ስንከራከርለት የከረምነው።
ቴዲ አፍሮ ከፖለቲከኞቻችን በተሻለ፤ ከታሪክ ኣዋቂቀቻችንን በበለጠ፥ ከምሁራን በላቀ መልኩና ከሃይማኖት መሪወች በተሻለ ኢትዮጵያዊነትን ትክሻው ላይ የተሸከመ  የዚህ ዘመንና ትውልድ ልሳን ነው።
እያንዳንዱ ትውልድ የራሱ የሆነ የትውልድ ልሳን እንዳለው ሁሉ ቴዲም የዚህ ዘመን ምሳሌ ነው፤ ልዩነቱ ግን እንደ ቴዲ ኣይነት ለማግኘት ከ፻ ኣመት በላይ ፈላጊ መሆኑ ኣያጠያይቅም።
ረጋ ባለ ልቡና ካሰብነው ኢትዮጵያ የሚለውን መንፈስ መልሶ ለመፍጠርና ለመገንባት ስንት ፖለቲከኞች ኣቦኩት፥ ስንት የታሪክ ጻህፍት ተቀኙበት፤ ከ26 ኣመት በላይ ብሄርተኝነት የተዘራብን ትውልድ በቀዬው ብቻ እንዲደናቆር ወያኔ ቀን ከለት መሰሪ ተግባሩን ዘራ፤ የሃገራችን ባንዲራ ዝቅ ብላ የብሄርተኝነት ባንዲራ ምድራችንን ኣጥለቀለቃት፤ ባለፉት 26 ኣመታት ያደጉት ወጣቶች ጀግና ማለት ሃየሎም ኣረኣያ፤ መለስ ዜናዌ፤ ቴወድሮስ አድሃኖምና እነ ገብረ-ጽቡቅ ብቻ ናቸው ተብሎ ተተረከላቸው።
ህዝባችን በጠባቦች እጅግ ተመርዞ ክፉኛ ኣደጋ ባንዣበበብን ሰኣት ቴዲ ኣፍሮ ከትፍ ኣለና የኢትዮጵያን ባንዲራ ሰማያ ጥግ ስር ሰቀላት። ማንም ተነስቶ ሊያወርዳት በማይችል ሁኔታ ባንዲራችንን አሳየን። የ አጤ ቴዎድሮስ ራይ እውን ይሁን ኣለ። ትውልዱ ሁሉ ስለ አጤ ተወድሮስ የተጻፉትን መጸሃት ጠላሸት ከወረሰዉ መደርደሪያ ዉስጥ ስቦ ማገላበጥ ጀመረ። ራሱን የሚመረምር ትውልድ ገነባን። የተከፋፈለ የሚምስልን ትውልድ በኣንድ ሃገር በኣንድ ባንዲራ እንባ እያራጨ ኢትዮጵያ.. ኢትዮጵያ.. ኢትዮጵያ.. ኢትዮጵያያያያያያያያን ተዘመረ። ከለፈዉ ይበልጥ መጭዋ ኢትዮጵያ ታለመች። አንድነት፥ እኩልነት፥ መቻቻልና የህግ የበላይነት የሰፈረባት ሃገራችን ታሰበች።
እንግዲህ ሮናልድ ሬገን ይህኔ ትዝ አለንና በቴወድሮስ ካሳሁን ላይ ያለምነዉ።
  ሮናልድ ሬገን የሚባል ኣሜሪካዊ የሆሊውድ ፊልም ባለሙያ ነበር በዘመኑ ጉደኛ የተባሉ የሆሊውድ ፊልሞችን ሰርቶ በችሎታው ድንቅ የተሰኘም ነው።
 ከ14 በላይ ፊልሞችን ሰርቶ ኣንቱ የተሰኘ ኣርቲስት መሃል ነበር። ይህ ድንቅ ባለሙያ በወቅቱ የነበረውን የሃገሩን ሁኔታ በማጤን ፖለቲካ ዉስጥ ገባና ለካሊፎርኒያ ስቴት ገዥ በመሆን ተመረጠ በመቀጠልም 40ኛው የኣሜሪካን ፕሬዘዳንት በመሆን ለ8 አመታት ኣግልግሏል። ከሚነሳለት በርካታ በጎ ምግባሮቹም ኣንዱ ከሶቬት ህብረት ወይም ራሺያ ጋር የነበረውን የቀዝቃዛውን ጦርነት በመቋጨት ይታወቃል።
የዚህ ሰው መነሻው ፊልም ነበር ጥበብ።
ቴዲ ኣፍሮም ተመሳሳይነት ኣለው። በኢትዮጵያ ወጣቶች ልብ ውስት ክፉኛ ዘልቆ ገብቶል። ለብዙወቻችን ሙሴ ነው፤ ኢትዮጵያዊነትን ይዞ ከባህር ሊያሻግረን የሚችል ድንቅ የዘመናችን ፈርጥ ነው።
ሮናልድ ሬገን ከፊልም ተነስቶ ኣሜሪካንን ከመራ ቴዲስ ምን ያንሰዋል? በርግጥ የዚህ መልስ ያለው ራሱ ቴዲ ላይ ነው፤ ወደፊት የምናየውም ይሆናል።
በኔ እምነት ግን….
 ኣንደበተ ርእቱነቱ፣ ትእግስቱ፣ ታሪክ ኣዋቂነቱ፣ ለይቅርታ ያለው ጽኑ እምነቱ፣ ለህዝባዊ ወገንተኝነት ያለው ፍቅር እና ሃገር ወዳድነቱን ሳይ የሮናል ሬገንን ፈለግ በተከተለ ብየ እመኝለታለሁ።
ቸር ያባጀን እና አናያለን ብሎል ራሱ ቴዲ እና እናያለን፦
ንጉሤ ነኝ!

The post በሮናልድ ሬገን ውስጥ ቴዲ ኣፍሮ – ንጉሤ አዳሙ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ገድለህ ማረው

$
0
0

የሰራህን በዓይንህ አይተህ
ሲወሻክት ወይም ሰምተህ
ልታቆመው ብትነሳ
በዝምታ ፊት ብትነሳ
አፍሮ ይተው እንዳይመስልህ
ስምህን ነው ሚከትፍልህ

ከዛ – ይልቅ
ነገርህን አ’ርገህ ድብቅ
ትንሽ ጊዜ ብትጠብቅ
እንደወትሮው ሱሱን ሊያደርስ
ካ’ንዱሊቀምስ
ካ’ንዱ ሊልስ
ከሰው ጋራ ሲቀላቀል
ባልታሰበ የፊት ተንኮል
ተይዞልህ ፊትህ ሲቀል
መፋረጃህ ያን ጊዜ ነው
ተቀላቅለህ አብረህ በለው
ወይንም በዓይንህ ገድለህ ማረው

(ወለላዬ ከስዊድን)

ፍትህን ሰቀለው በፍትህ ስም የፕሮፓጋንዳ ዳንኪራ – የጨለማው ሳምንት!!

$
0
0

የ“ፍትህ” ወይስ የጨለማ ሳምንት?

(ርዕሰ አንቀጽ)

“ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ጸጥ ይላል!” ይህ የተጻፈው በአንድ የጎንደር እስር ቤት ውስጥ ነው። የተጻፈው በግድግዳ ላይ ሲሆን በብዕር ወይም በቀለም አይደለም። ፍትህ ከተጓደለባቸው አንዱ የእጁን ጣት በመብጣጥ በደሙ ነው። ፍትህ የተዛባባቸው ይህንኑ አባባል ልክ እስር ቤት እንደገቡ ይሳለሙታል። በብዙ የአገሪቱ ማጎሪያዎች ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት ገላጭ ሃረጎች ይጻፋሉ። ፍትህን አደባባይ ሰቅለው በምስኪኖች ህይወት ለሚጫወቱ ይህ ሁሉ ስላቅ ነው። ፍትህን አደባባይ ሰቅለዋት፣ በፍትህ ስም እየማሉ በድግስ ሊያሽካኩ ይወዳሉ።

ፍትህ የዜጎች ሁለንተናዊ ህይወታቸው ትርጉም የሚያገኝበት ውድ ጉዳይ ነው። ይህንን ሃቅ የበረሃው አባዜው አልለቅ ያለው ህወሃት ጥንቅቆ ያውቀዋል። ሊክደውም አይችልም። ለዚህም ነው “ህገ መንግስት፣ ህግ፣ አዋጅ፣ የሰብዓዊ መብት፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት…” እያለ ህግ ሲያረቅና አዋጅ ሲያመርት የሚኖረው። በተግባር የሚታየው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ “ፍትህ” የህወሓትን ልዕለ ሥልጣን ለመጠበቅ የተቋቋመ መሳሪያ፣ በ“ህግ” እና “አዋጅ” ስም የጠሉትን መምቻ፣ የተቃውሞ ድምጽ ማፈኛ መሆኑ ነው። ኢ-ፍትሐዊነት በ“ፍትህ” ካባ ጀቡነው የዓይነ ደረቅ ጨዋታ መጫወት ይሏል ይህ ነው። ይህ እንደ ሚዲያ እኛ የምንለው ሳይሆን ህዝብ በአደባባይ በየቀኑ የሚታዘበው እውነት ነው።

ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ዘውጋዊ መድሎንና የዘር ማጽዳትን የተገበረ፣ ያለተጠያቂነት የአገሪቱን የፍትህ ሥርዓት በፓርቲ ፖለቲካ ታማኝነት የጨፈለቀ፣ ሙስናን በአደባባይ ያነገሰ፣ በገዛ ዜጎቹ ላይ ጦርነት አውጆ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃንን ከገጠር እስከ ከተማ የረሸነ፣ የአካል ጉዳተኛ ያደረገ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በጅምላ ቀፍድዶ የሚያሰቃይ፣ በእስረኞች ላይ ዘግናኝ የምርመራ ወንጀል የሚፈጽም፣ አውሬያዊነት የተጠናወተው አገዛዝ፤ . . . አገሪቱን በኦፊሴል ወደ ወታደራዊ የአፈና መዋቅር አሻግሯት ባለበት በዚህ ዘመን “የፍትህ ሳምንት” ለማክበር በሚል መጀመሩን የፕሮፓጋንዳ አታሞ በሚደልቅባቸው ሚዲያዎቹ አዋጅ እያስደለቀ ነው።

አገር እንድትበታተን የሚጋብዙ የፖለቲካ አጀንዳዎች በስትራቴጂ ደረጃ ቀርፆ የሚሰራው ህወሓት፤ ትግራይን እንደአገር እየሰራ፣ ዳሩን መሀል እያደረገ፤ መሀሉን እያፈረሰ ባለበት ሁኔታ “የህግ የበላይነት ለዘላቂ ሰላምና ለህዝቦች አንድነት” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን የ“ፍትህ” በዓል (ከሚያዚያ 30 – ግንቦት 06) ማክበር ጀምሯል። በቀደመው ዓመትና በያዝነው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ወራት በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአገዛዙ ቅልብ ወታደሮች በተተኮሱ ጥይቶች ጎዳናው ላይ የወደቁ ንፁሃን ዜጎች፣ ለአካል ጉዳት የተዳረጉ ወገኖች፣ በእስር የማቀቁና የሚማቅቁ ኢትዮጵያዊያን ፍትህ ባላገኙበት ሁኔታ አገዛዙ የሚያከብረው የ“ፍትህ” ሳምንት ለመከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ “የጨለማ ሳምንት ክብረ በዓል” ቢሆን ህወሃትን ይመጥነዋል። ለጠጣው ደምና ለበላቸው ንጹሃን ዜጎችም ደግ መታሰቢያም በሆነ ነበር

እኛ እንደ ሚዲያ፣ ዜጎች እንደ ህዝብ የአንድ ሥርዓት ምቹነት መመዘኛው የፍትሃዊነት መኖር ወይም ያለመኖር ጉዳይ ስለመሆኑ አያከራክርም። አገርን የሚያስተዳድር መንግስት ካለ ፍትህ ከቶውንም ሊጓድል አይገባም። ቢጓደልም አሁን ባለበት ደረጃ ሊሆን አይችልም። ፍትህን ላልተገባ ወይም ለፖለቲካዊ ዓላማ ማዋል ከወንጀሎች ሁሉ የከፋው ወንጀል ነው። ህወሃት ይህንን እያደረገ ያለና ግብሩ ሁሉ ፍትህ ላይ ቆሞ የመደነስ በመሆኑ እንዲህ ያለውን የሚያበራ መሪ ቃል ተሸክሞ ህዝብ ፊት ስለ ፍትህ ሊናገር አይችልም። ሞራል የለውም እንጂ ስለ ፍትህ ሲያወራ ሃፍረት የጨው ዓምድ ባደረገው ነበር።

የሕጎችና አዋጆች መጽደቅ ዋናው ግብ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒው ሲተገበር መመልከት ለኢትዮጵያዊያን እንግዳ ክስተት አይደለም። በቁጥር የበዙ ኢትዮጵያዊያን ህግ እነርሱን ለማጥቃት እንጂ ለመከላከል እንዳልቆመ በውል ያውቃሉ። በተለይም ከመንግስታዊ “ክሶች” አኳያ “ህግ” የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም መጠቀሚያ ሲሆን ማየት የፍትህ ሥርዓቱን መበስበስ አመላካች እንደሆነ በጽናት እናምናለን። ይህ እምነታችን ደግሞ በደፈናው ወይም በቅጽበት የመጣ ሳይሆን የህወሃት ግብር አስረግጦ ያስተማረን ነው።

የህግ የበላይነት ተጨፍልቆ ጥቂቶች ከህግ የበላይ ሲሆኑ መመልከትም የአንድን አገዛዝ ፍፃሜ አመላካች ነው። ከጥንቶቹ ገናና መንግስታት እስከ ቅርቦቹ ድረስ፣ አገዛዞች መውደቂያቸው ሲቃረብ የፍትህ ሥርዓታቸው የተበላሸ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል። ከታላቁ የሮማውያን ግዛት ጀምሮ እስከ አረቡ የፀደይ አብዮት ድረስ የህዝብ ማዕበል ጠራርጎ የወሰዳቸው አምባገነን መንግስታት የአወዳደቃቸው መንስኤ የአገዛዙ ተጠቃሚዎችና አባላት ህግጋቱን ለገዛ (ግላዊና ቡድናዊ) ፍላጎታቸው በማዋላቸው ነው። የዘፈቀደ ጅምላ እስርና ግድያ መለያው የሆነው ህወሓት/ኢህአዴግ ከዚህ የተለየ ዕጣ እንደማይገጥመው ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።

ከሩብ ክፍለ ዘመን የአገዛዙ ጉዞ የታየው እውነታም አገዛዙ “እታመንለታለሁ” በሚል ከሚመፃደቅበት “ሕገ – መንግስቱ” ላይ የተቀመጡትን ህጎች በአደባባይ ከመጣስ ጀምሮ በተለያዩ አዋጆች የገዛ ዜጎቹን እስከመበቀል ደርሷል። በምርጫ 97 ድንጋጤ ማግስት፣ የአገዛዙን ምሰሶ የነቀነቁትን ዘርፎች ለማሽመድመድ በሚል ያወጣቸው የተሻሻለው የፕሬስ አዋጅ፣ የፀረ-ሽብር አዋጅ፣ የበጎ አድራጎት (መያዶች) አዋጅ አተገባበር የአገሪቱን የፍትህ ስርዓት በማሽመድመድ ተጠቃሽ አዋጆች ናቸው።

እነዚህ አዋጆች በረቂቅ ደረጃ እንዳሉ በብዙ ምሁራንና ፖለቲከኞች እንደተገመተውም ተቃዋሚውን ኃይልና ሞጋቹን ማህበረሰብ ለማፈንና ለማዳከም በማጥቂያነት የተቀመሩ በመሆናቸው፣ ዛሬም ድረስ ያለ አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ ከነዚህ የማጥቂያ አዋጆች ቀዳሚ የሆነው የፀረ ሽብር አዋጁ እየተጠቀሰባቸው ወደ አስከፊ እስር የሚወረወሩ ዜጎች በርክተዋል። ከሁሉም በላይ የከፋውና ዜጎችን የባይተዋርነት ስሜት ውስጥ የሚከተው ድርጊት፣ በተጠርጣሪነት በተያዙበት ሁኔታ ውስጥ ህጉ ያስቀመጠላቸውን መብቶች መነፈጋቸው ነው። የሽብርተኝነት ታፔላ እየተለጠፈባቸው ወደ እስር የሚጋዙ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ሞጋች ወጣቶች፣ . . . ከመሰረታዊው በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አንስቶ እስከ ዋስትና መከልከል እንዲሁም የቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም በኃይማኖት አባትና በጠበቃ እንዳይጎበኙ ክልከላ ማድረግ፣ በእስር ቆይታ የከፋ አያያዝ እና በድብደባ ማሳመን የመሳሰሉ ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊ በደሎች ይፈፀሙባቸዋል። ከዚህ አልፎ ተርፎም ድራማዊ የሆኑ የሐሰት ምስክሮች ይዘጋጁባቸዋል። የካንጋሮው ፍርድ ቤት የሚቀርቡለትን “መንግስታዊ ክሶች” በሙሉ ከባባድ የፍርድ ውሳኔዎች በመስጠት ወደ ማጎሪያ ይወረውራቸዋል።

ቁጥሩ የበዛ ኢትዮጵያዊ ለፍትህ ተቋማትና አገልጋዮች ያለው አመኔታ ተሟጥጦ አልቋል። በእስከአሁኑ ተሞክሮ ህወሓት/ኢህአዴግ በወንጀል ጠርጥሮ ካሰራቸው ግለሰቦች መካከል በፍርድ ክርክር ሂደት ነፃ ተብሎ የተለቀቀ አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የለም። ከእስር ጀምሮ ያሉ የፍርድ ቤት ክርክሮች በህወሓት አቃቢያነ ህግ የበላይነት የሚደመደሙ ናቸው። “ተለቀቁ” ተብለው ሲፈቱም በተፈለገ ቀን ወደ እስር ቤት ለመክተት የሚያገለግል “ወንጀል” በአደራ ተቀምጦ ነው።

ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” ብሎ ያሰራቸው ግለሰቦች ፍትህ እናገኛለን ከሚሏቸው የፌዴራልም ሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ በቀላሉ ሲሰጥ ማየታቸው ከእነርሱ አልፎ ሌሎች ዜጎች በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ያላቸው አመኔታ ወደዜሮ የወረደ እንዲሆን አድርጎታል።

ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” ብሎ ያሰራቸው ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ሞጋች የህብረተሰብ ክፍሎች፣ … የፍትህ ሥርዓቱን መበስበስ እየወቁ እንኳ ጠበቃ ከማቆምና ከመከራከር ሲሰንፉ አንመለከትም። እንዲህ ያለው ጉዳይ በዶ/ር መረራበቀለ ገርባለወልቃይት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የኮሚቴ አባላትና በመሰል የ“ሽብር ወንጀል” ለታሰሩ ዜጎች የተሰወረ እውነት ባይሆንም ጠበቃ የማቆም አስፈላጊነት የህወሓት/ኢህአዴግን ኢፍትሃዊነት በኢትዮጵያ የታሪክ ምዕራፍ በጉልህ መዝግቦ ለማስቀረት እንደሆነ የቀደሙት ግፉአን የፍርድ ሂደት የሚነግረን እውነት አለ።

አንደበተ ርትዑው ፖለቲከኛ፣ አንዷለም አራጌ የህወሓት/ኢህአዴግን ሃሳዊ “የሽብር ወንጀል የክስ ሂደት” ጠበቃ አቁሞ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ለማመን በሚከብድ ፖለቲካዊ “የፍርድ ውሳኔ” የዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት የተፈረደበት ዕለት፣ ከፍርዱ በፊት የፍርድ ማቅለያ ሃሳብ እንዳለው በካንጋሮው ፍርድ ቤት ሲጠየቅ “እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው። በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ፍትህን ለምኜ ስነፈግ ይሄ የመጀመሪያዬ አይደለም። ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ፅዋ በፀጋ ከመጠጣት ውጭ ባልፈፀምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናዬ ስላልተቀበለው አልጠይቅም…” ማለቱን እናስታውሳለን። የአንዷለምን ምርጫ የሚጋሩ ብዙ ግፉአን ፍርደኞች የኢትዮጵያን እስር ቤቶች አጣብበውታል።

እንደ እኛ እምነት የኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓት ሲበዛ በስብሷል። በጉልበተኛ ገዥዎች መዳፍ ስር የወደቀው የፍትህ ሥርዓት አገዛዙ ሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ከቶውንም ሊቃና አይችልም። የፍትህ እጦት አመጽ መውለዱ አይቀሬ ነበርና በቀደመው ዓመት የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬ ላይ በረድ ያለ ቢመስልም በደፈጣ የጦር መሳሪያ ጥቃት የታጀበ አገዛዛዊ ውድመት ወደ ማድረስ ተሸጋግሯል።

ለኢትዮጵያ የሚበጀው ሰላማዊ ሽግግር መሆኑን አጥብቀን እናምናለን። ደርግ ኢ-ፍትሃዊ ነው በሚል “ብሶት ወለደኝ” ያለው የያኔው የደፈጣ ተዋጊ ቡድን ዛሬ ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ ከጣለው አገዛዝ በላይ የከፋ ሆኖ ተገኝቷል። የደርግን መደባዊ ጭፍጨፋ ወደ ዘውጋዊ ጭፍጨፋና የዘር ማጽዳት ደረጃ ያሻገረው ህወሓት ኢ-ፍትሃዊነትን በፍትህ ካባ ሸፍኖ የገዛ ዜጎቹን መበቀያ መሳሪያ አድርጎታል።

የዘፈቀደ ግድያና አፈና በ“ህግ” ሽፋን “ፍትህን የማስፈን” ዕውቅና ይቸረው ከጀመረ በአገዛዙ ዕድሜ ዘመን ልክ ይቆጠራል። ሰላማዊውን መንገድ “የፍርሃት” አድርጎ የሚቆጥረው ህወሃት “ጦርነትን መሥራት እችላለሁ” እያለ ቢደነፋም በሕዝባዊ እምቢተኝነት የተነሳው ተቃውሞ ከገጠር ተጋድሎ ወደ ከተማ አብዮት የመቀየር ፍንጮችን በገሃድ እያሳየ ነው። ከራሱ ተሞክሮ እንደሚያውቀው ይህ ዓይነቱ አካሄድ  ሥርዓተ አገዛዙን በመናድ ዕድሜውን የሚያሳጥር ብቸኛ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል።

ይህ ሳምንት ለህወሓታዊያን “የፍትህ ሳምንት” በሚል የፕሮፓጋንዳ አታሞ መምቻ ሲሆን፤ ለግፉአን ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በአገዛዙ ወደር የለሽ የጭካኔ ተግባር በሞት ያጣናቸውን፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን፣ የደረሱበት ያልታወቁትን፣ በማዕከላዊ እስር ቤትና ለህዝብ ይፋ ባልሆኑ ድብቅ ማጎሪያ ቤቶች በአሰቃቂ የእስር ምርመራ እየማቀቁ ያሉ ውድ ወገኖቻችንን ስቃይ ይበልጥ የምንጋራበት የጨለማ ሳምንት ነው።

ፍትህ የህገ-ኅልዮት ሰንደቅ ነች!

ፍትህን ይኖሯታል እንጅ አይነግዱባትም!

ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

ደባርቅ ከተማ ላይ ግፉ ቀጥሏል… – አስናቀው አበበ

$
0
0

ጥጋበኛ የወያኔ ልዩ ሀይሎች አንድን ሰላማዊ የደባርቅ ወጣት በጩቤ ወግተውዋል፡፡
ዛሬ 03/09/09 2:00 ከምሽቱ የተፈፀመ ግፍ ነው፡፡ ተጎጅው ወጣት ልዮ ሀይሎቹ የሰፈሩን ሌላ ወጣት ሲደበድቡ አይቶ ለምን ብሎ በመጠየቁ ብቻ በከባድ ሁኔታ በሳንጃ ወግተውት አሁን ሆስፒታል ውስጥ በከፍተኛ ሰቃይ ይገኛል፡፡ ጥጋበኞቹ በጩቤ መውጋታቸው አልበቃ ቢላቸው በጥይት ሊመቱት የተከታተሉት ቢሆንም በሌሎች የሰፈሩ ልጆች እርዳታ ሊያመልጥ ችሏል፡፡
መቸ ይሆን ግን ይሔ ሁሉ የሚያበቃው? መቸ ይሆን በሀገራችን በነፃነት ወጥተን የምንገባው ይላሉ በቁጭት የደባርቅ ወጣቶች። በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ንዴትና ቁጭት የፈጠረ ጉዳይ ነው። በዚህ ሰዐት በደባርቅ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ እልህና ቁጭት ፈጥሯል። ደባርቅ ውስጥ ውጥረቱ ጨምሯል። በዛሬው እለት ብዛት ያላቸው የወታደር ኦራል መኪኖች በወልድያ ጎንደር መስመር የደብረታቦርን ከተማ አልፈው በፍጥነት መጓዛቸውን አስመልክተን ለጥንቃቄ ስንል መዘገባችን ይታወቃል። 11ኛ ወሩን የያዘው ሐምሌ 5 2008 በጀግናው ኮሎኔል ደመቀ እምብይ እጀን አልሰጥም ባይነት ጎንደር ላይ የተጀመረው ህዝባዊና ፍትሃዊ ትግል ስልቱን እየቀያየረ መቀጠሉ ለወያኔ እራስ ምታት ሆኖበታል። በዝግ ስብሰባቸውም ጎንደር ከእጅ ወጥታለች ማለታቸው ይታወቃል።

The post ደባርቅ ከተማ ላይ ግፉ ቀጥሏል… – አስናቀው አበበ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


የፍቅር እስከ መቃብር – ፍቅረኞች (በጥበቡ በለጠ)

$
0
0

የዛሬ ፅሁፌን እንዳዘጋጅ የገፋፉኝ ሁለት ነገሮች ናቸው። አንደኛው በፍቅር እስከ መቃብር ላይ ተመርኩዞ የተሠራው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ደብረማርቆስ ከተማ ላይ የተሠራው የታላቁ ደራሲ፣ ዲፕሎማትና አርበኛ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁ ሐውልት ነው።

ቴዲ አፍሮ /ቴዎድሮስ ካሣሁን/ ፍቅር እስከ መቃብርን መሠረት አድርጐ ግሩም የሆነ ሙዚቃ አቀንቅኗል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ርዕሠ ጉዳዮችን በተለይም ገፀ-ባህሪያቱን፣ ደራሲውን እና ተራኪውን ወጋየሁ ንጋቱን ሳይቀር ለዛ ባለው ሙዚቃው ሌላ ፍቅር ሰርቶላቸዋል። ፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ወደር የማይገኝለት ልቦለድ ታሪክ ነው። ፍቅር እስከ መቃብር ዘመን አይሽሬ /Eternal/ ብለን የምንጠራው የጽሑፎች ሁሉ ቁንጮ ነው። ታዲያ ወደዚህ መጽሐፍ ንባብ የገባ ሰው ሁሉ በመጽሐፉ ፍቅር ተሳስሮ እንደሚቀር ይታወቃል። ፍቅር እስከ መቃብር መፅሐፍ በውስጡ ያለው ታሪክ ሲነበብ፣ አንባቢውን ራሱ በፍቅር ወጀብ አላግቶ፣ አላግቶ የፍቅር እስረኛ የሚያደርግ ተአምረኛ መጽሐፍ ነው። ቴዲ አፍሮም በመጽሐፉ ፍቅር ወድቆ ይህን የመሰለ ግሩም ዜማ አቀነቀነ። ከራሳችን፣ ውስጣችን ካለው ታሪካችን ላይ መሠረት አድርጐ ሙዚቃ መስራቱ አንዱ ስኬቱ ነው። እንዲህ ዓይነት ግዙፍ ኢትዮጵያዊ ቅርሶችና ታሪኮች ላይ መሠረት ተደርገው የሚቀርቡ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የታዳሚን ቀልብ በቀላሉ የመውሰድ አቅም አላቸው። ከዚህ ሌላም ከያኒው ራሱ በሀገሩ ታሪክ ላይ ተመስጦ የጥበብ ስራዎቹን ማቅረቡም ምን ያህል የዕውቀት አድማሱም ሰፊ እንደሆነ ማሳያም ነው። አንድ ከያኒ የአገሩን እና የሕዝቡን ታሪክ ሲያውቅ በሕዝቡ ውስጥ ግዙፍ ሆኖ ብቅ ይላል።

ቴዲ አፍሮ ፍቅር እስከ መቃብርን ሲዘፍነው የመጀመሪያው አቀንቃኝ አይደለም። በ1995 ዓ.ም እጅጋየሁ ሽባባው /ጂጂ/ መጽሐፉን መሠረት አድርጋ “አባ ዓለም ለምኔ” የተሰኘ ውብ ዜማ አቀንቅናለች። በዚህ መጽሐፍ ላይ መሠረት አድርጐ ዜማ ማቀንቀን እንደሚቻል ያሳየች ቀዳሚት ባለቅኔ ነች።

ጂጂ ለቴዲ አፍሮ፣ የታላላቅ ርዕሠ ጉዳዮች መነቃቂያው /inspiration/ የሆነች ይመስለኛል። ምክንያቱም ፍቅር እስከ መቃብርን እርሷ 1995 ዓ.ም ተጫውታዋለች። እርሱ ደግሞ በ2009 ዓ.ም ተጫወተው። አባይን በተመለከተ ጂጂ ከ15 ዓመት በፊት አቀንቅናለች። ቴዲ አፍሮ ደግሞ በቅርቡ ተጫውቶታል። አድዋን በተመለከተ ጂጂ በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ ድንቅ አድርጋ አዜመችው። ቴዲ አፍሮ ደግሞ እርሷ ካቀነቀነች ከ13 ዓመት በኋላ አድዋን ውብ አድርጐ ሠራው። ብዙ ነገሮችን ሳይ ጂጂ የቴዲ መነቃቂያ ትመስለኛለች። እርግጥ ነው ሁለቱም አቀንቃኞች የአንድ ዘመን ወኪሎች ናቸው። እነርሱ በተፈጠሩበትና ባደጉበት አስተሳሰብ ውስጥ ነው ማቀንቀን የሚፈልጉት። የርዕሠ ጉዳይ ምርጫቸውም ተመሳስሎ ማሳየቱ ከፈለቁበት ሕዝብና አስተሳሰብ ውስጥ ይመነጫል። ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ እንዳሉት “ነበልባል ትውልድ እየመጣ ነው። ከነዚህም ውስጥ እጅጋየሁ ሽባባው /ጂጂ/ እና ቴዲ አፍሮ ናቸው። የኢትዮጵያን ሙዚቃ ባልተጠበቀ ፍጥነት ወደ ላይ አመጠቁት” ብለው ነበር። ኃይሌ ገሪማ ለጂጂ ሙዚቃ የነበራቸውን ፍቅር ሳስታውስ ወደር አላገኘሁላቸውም።

ወደ ርዕሰ ጉዳዬ ልመለስ። ፍቅር እስከ መቃብር ብዙዎችን በፍቅር የጣለ መጽሐፍ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዲፓርትመንት ውስጥ ላለፉት 50 ዓመታት የጥናትና ምርምር ፅሁፎች ሲሰሩበት የኖረ መጽሐፍ ነው። አያሌ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የድግሪ፣ የማስተርስ እና የዶክተሬት ድግሪያቸውን ለማግኘት ፍቅር እስከ መቃብር ላይ የምርምር ፅሁፎቻቸውን አቅርበዋል። ሌሎች ምሁራን ተመራማሪዎችም ፍቅር እስከ መቃብርን በልዩ ልዩ ርዕሠ ጉዳዮቹ ላይ ተመርኩዘው ጥናት ሠርተዋል። የውጭ አገር ሰዎች ሳይቀሩ መጽሐፉ ላይ ተመራምረዋል። መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ቋንቋም ተተርጉሟል። በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ፍቅር እስከ መቃብር የአያሌዎችን ቀልብ በመሳብ ወደር አይገኝለትም። ይህን መጽሐፍ በጥናትና በምርምር ፅሁፎቻቸው ከፍ ከፍ አድርገው የሰጡን ምሁራን ሁሉ ሊታወሱ ሊመሰገኑ ይገባል።

በርዕሴ ላይ “የፍቅር እስከ መቃብር – ፍቅረኞች” ያልኩትም እነዚህን አካላት ሁሉ ለመጠቃቀስ ፈልጌ ነው። በዚህ መፅሐፍ ታሪክ ውስጥ ከሁሉም በላይ “ፍቅር” ናቸው ብዬ የማስበው ደራሲውን ክቡር ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁን ነው። ይሄን የሁላችንም ፍቅር የሆነውን መጽሐፍ 1958 ዓ.ም ያበረከቱልን የደራሲነት ግዙፍ ስብዕና ሐዲስ ዓለማየሁ እፊቴ ተደቀኑ። አቤት ትዝታ! ትዝ አሉኝ።

በህይወት ዘመኔ እስካሁን በሠራሁበት የጋዜጠኝነት ሙያዬ ቃለ-መጠይቅ ካደረኩላቸው የዚህች አገር ፈርጦች መካከል በእጅጉ ደስ የሚለኝ ከእርሳቸው ዘንድ ሄጄ ስለ ብዙ ነገር ያጫወቱኝ ወቅት ነው። ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁን በ1994 ዓ.ም እና በ1995 ዓ.ም ቃለ-መጠይቅ ያደረኩላቸው ሲሆን፤ ለሦስተኛ ጊዜ ለሌላ ቃለ-መጠይቅ ቀጠሮ በያዝንበት ቀን ህይወታቸው አለፈች። ክቡር ሐዲስ ሆይ ታላቅነትዎ፣ ከሁሉም በላይ ትህትናዎን ፈፅሞ አልረሳውም።

ውድ አንባቢዎቼ፤ እስኪ አንድ ነገር እንጨዋወት። በዚሁ መፅሐፍ ውስጥ ሦስቱን ዋና ዋና ገፀ-ባህሪያት አስቧቸው። ሰብለ ወንጌልን፣ በዛብህን እና ጉዳ ካሣን። እነዚህ ሦስት ገፀ-ባህሪያት አንድም ሦስትም ናቸው። አንድ የሚያደርጋቸው፣ ባሰቡት አቋማቸው፣ ለወደዱት ጉዳይ ፍፁም ራሳቸውን መስጠታቸው፣ በፍቅርና በዓላማ ተገማምደው እስከ ወዲያኛው ማለፋቸው፣ በአንድ ጉድጓድ መቀበራቸው አንድ ያደርጋቸዋል። ፍቅር እስከ መቃብሩም እሱ ነው። ሦስት የሚያደርጋቸው ደግሞ ሦስቱም ከየራሳቸው የኋላ ማንነት እና ተፈጥሮ አመጣጣቸው የተለያየ መሆኑ ነው። እነዚህ ከሦስት ማንነት ውስጥ የወጡ የሐዲስ ዓለማየሁ ፍጡሮች የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ ዋልታና ማገር ሆነው እነሆ 50 ዓመታት ሙሉ ተገዳዳሪ ሳይኖርባቸው ብቻቸውን ውብ ሆነው እንዳማረባቸው አሉ።

ሰብለና በዛብህ በሁለት ሰብአዊያን መካከል የሚንበለበል የፍቅር እቶን ውስጥ የተቀጣጠሉ ቢሆንም ከዚያ ባለፈ ደግሞ የሁለት ዓለም ሰዎችን ወክለው የአንድን ማኅበረሰብ አወቃቀር የሚያሳዩ ናቸው። ሰብለ ከባላባት ወገን፣ በዛብህ ከአነስተኛው ማኅበረሰብ ክፍል። የነዚህ ሁለት ዓለም ሰዎች ፍቅር ውስጥ የሚመጣ ጉድ የተባለ ግጭት ፍጭት አለ። እናም ሐዲስ ዓለማየሁ ያንን የማኅበረሰብ አወቃቀር ልዩነትና አንድነት ሊያሳዩን ፍቅር ፈጠሩ። በፍቅር ውስጥ ያለ ማኅበረሰባዊ እቶን ሲፈነዳ ሲቀጣጠል አሳዩን። ጉዱ ካሣ የተባለ ጉድ ፈጥረውም ማኅበረሰቡን የሚያርቅ፣ የሚተች፣ የሚያሄስ፣ ችግሩን ነቅሶ የሚያሳይ እና መፍትሄ የሚሰጥ የሊቆች ሊቅ ወለዱ። የጐጃሙ ዲማ ጊዮርጊስ የቅኔ ዩኒቨርሲቲ ያፈራው ጉዱ ካሣ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ፣ በሥርዓት እንድትገነባ እንዲህ ብሎ ነበር፡-

“የማኅበራችን አቁዋም የተሰራበት ሥርዓተ-ልምድ፣ ወጉ ሕጉ እንደ ሕይወታዊ ሥርዓተ-ማሕበር ሳይሆን ህይወት እንደሌለው የድንጋይ ካብ አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦ የላይኛው የታችኛውን ተጭኖ፣ የታችኛው የላይኛውን ተሸክሞ እንዲኖር የተሰራ በመሆኑ ከጊዜ ብዛት የታችኛው ማፈንገጡ ስለማይቀርና ይህ ሳይሆን ህንፃው በሙሉ እንዳይፈርስ እንደገና ተሻሽሎ ሰውን ከድንጋይ በተሻለ መልክ የሚያሳይ የህያውያን አቁዋም ማኅበር እንዲሰራ ያስፈልጋል።”

/ፍቅር እስከ መቃብር፤ ገፅ 122/

ለመሆኑ እንደ ጉዱ ካሣ አይነት ማኅበረሰባዊ ፈላስፋ አለን ወይ? አንዱ ሌላውን ተጭኖ መኖር እንደሌለበት የሚነግረን። አንዱ ሌላኛውን ከተጫነ ከጊዜ ብዛት የታችኛው እምቢ ብሎ ይወጣል። የታችኛው ሲወጣ ካቡ ይፈርሳል፤ ሀገር ይፈርሳል እያለ በውብ ምሳሌ ኢትዮጵያን የሚያስተምር የዲማ ጊዮርጊሱ ጉዱ ካሣ ጠቢብ ነበር።

እናም ሐዲስ ዓለማየሁ እንዲህ አይነቶቹን ገፀ-ባህሪያት ፈጥረው፣ የፍቅር ልቦለድ የሆነ መነፅር ሰክተውላቸው ኢትዮጵያን እንድናያት፣ እንድንመረምራት እና የሚያስፈልጋትን ሥርዓት እንድንገነባላት እኚህ ጉደኛ ደራሲ ከ50 ዓመታት በፊት በውብ ድርሰታቸው ነግረውናል። ማን ይስማ!?

1994 ዓ.ም እቤታቸው ሄጄ ቃለ-መጠይቅ ሳደርግላቸው በውስጤ ብዙ ነገር ተመላለሰብኝ። ፍቅር እስከ መቃብር። በዛብህ ሞተ። ሰብለ ከበዛብህ ሌላ ፈፅሞ መኖር አትፈልግም። መነኮሰች። ቆብ ጫነች። እሷም ሞተች። አጐቷ ያ ታላቅ ፈላስፋ ለዕውነት ብሎ የኖረና የሞተው ጉዱ ካሣም ተቀላቀላቸው። እነዚህን ገፀ-ባህሪያት የፈጠሩት ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ እድሜና ጤና ተጫጭኗቸው በተንጣለለው ሳሎናቸው ውስጥ በተዘረጋው የማረፊያ አልጋ ላይ ጋደም ብለዋል። ትክ ብዬ አየኋቸው። ፍፁም ትህትና፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የመቅረብ ተፈጥሯቸው ይሄው እፊቴ ላይ ዛሬም አለ። ይታየኛል።

ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ባለቤታቸው ወ/ሮ ክበበፀሐይ ከሞቱ በኋላ ምንም ዓይነት ትዳር አልመሰረቱም። ብቻቸውን ከቤተሰባቸው ጋር ነው የሚኖሩት። ሳያገቡ፣ የአብራካቸውን ክፋይ ሳያዩ አረጁ። ደከሙ። እናም ገረመኝ። ግን ጠየኳቸው። “ጋሽ ሐዲስ፤ ባለቤትዎ ወ/ሮ ክበበፀሐይ ካረፉ በጣም ረጅም ዓመታት ተቆጠሩ። በነዚህ ዓመታት ግን እርስዎ ምንም ዓይነት ሌላ ትዳር አልመሰረቱም። ይህ ለምን ሆነ? ምክንያትዎ ምንድን ነው?” አልኳቸው።

ጋሽ ሐዲስ የግራ እጃቸውን ከፍ አደረጉልኝ። እጃቸው ላይ ቀለበት አለ። ግራ ስጋባ እንዲህ አሉኝ። ይህን ቀለበት ያሰረችልኝ ክበበፀሐይ ነች። እኔም ለእሷ አስሬያለሁ። እሷ ድንገት አረፈች። እዚህ ጣቴ ላይ ያለው እሷ ያሰረችልኝ ቀለበት ነው። ቀለበቱን አልፈታችውም። ሳትፈታው አረፈች። ስለዚህ ይህን ቀለበት ከኔ ጣት ላይ ማን ያውልቀው? ካለ እሷ፣ ካለ ክበበፀሐይ ይህን ቀለበት ከጣቴ ላይ የሚፈታው የለም አሉኝ።

ለመሆኑ ከዚህ በላይ ፍቅር እስከ መቃብር አለ ወይ? ሐዲስ ዓለማየሁ ማለት የፍቅር እስከ መቃብር መፅሐፍ ዕውነተኛ ገፀ-ባህሪ ነበሩ። የፃፉትን ልቦለድ በእውናቸው የኖሩ የፍቅር አባት ናቸው። ሰብለወንጌል፣ በዛብህ እና ጉዱ ካሣ ማለት ሐዲስ ዓለማየሁ ናቸው። ፍቅርን ፅፈው ብቻ ሳይሆን ኖረውት ያለፉ እውናዊ ፍጡር! ጋሽ ሐዲስ፤ አቤት የስብዕናዎ ግዝፈት! እንዴት አድረጌ ልግለፀው?

የፍቅር እስከ መቃብር ፍቅረኞች በጣም ብዙ ናቸው። በዋናነት ራሳቸው ሐዲስ ዓለማየሁ ናቸው። ሌላው ይህን ታሪክ በጥብጦ ያጠጣን ተራኪው ወጋየሁ ንጋቱ ነው። መፅሐፉ ላይ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ሊቃውንትም የመፅሐፉ ፍቅረኞች ናቸው። ጂጂ እና ቴዲ አፍሮም በመፅሐፉ ፍቅር ወድቀው እኛንም ጣሉን። ፍቅረኛው በጣም ብዙ ነው።

የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሁፍ ጣሪያውን ያሳዩን ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ደብረ-ማርቆስ ከተማ ላይ ሐውልታቸው ከሰሞኑ ቆመ። ምስጋና ለደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ! ይህች ደብረማርቆስ ሌላ እጅግ አስደናቂ ደራሲም ወልዳለች። ተመስገን ገብሬ ይባላል። በብዕሩም ሆነ በዕውቀቱ በዘመኑ ሊቅ የነበረ አርበኛ ነው። ተመስገንን ስጠራ ዮፍታሔ ንጉሴ መጣብኝ። ባለቅኔው፣ ተወርዋሪ ኮከቡ ዮፍታሔ ከዝህቺው ደብረማርቆስ ዙሪያ ሙዛ ኤልያስ ተወልዶ ያደገ የዚህች አገር የቴአትር፣ የመዝሙር፣ የግጥም ሊቅ የሆነ አርበኛ ነው። መላኩ በጐ ሰው የተባለ ልክ እንደ ዮፍታሄ ገናና የነበረ ሊቅም ከደብረማርቆስ ወጥቷል። የዛሬው ትውልድም ሐውልት ብቻ የሚሰራ እንዳይሆን የነዚህን ታላላቅ ሰብዕናዎች ማንነት መከተል ይገባዋል።

በትውልድ ውስጥ እየተቀጣጠለ የሚሄድ ፍቅር የሰጡን ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ በሙዚቃው ጂጂን እና ቴዲ አፍሮን ቀልብ ወስደው ዛሬም እንደ አዲስ ፍቅር እስከ መቃብር ያሰኙናል። አቶ ሐዲስ ከአርበኝነቱ እና ከደራሲነቱ ባሻገር የሰሩትን መልካም ነገር ላስተዋውቅና የዛሬ ጽሁፌን ላብቃ።

ሐዲስ ዓለማየሁ በድርሰት ስራዎቻቸው በኢትዮጵያዊን ዘንድ እጅግ ጎልተው ወጡ እንጂ መተዳደሪያቸው የመንግስት ስራ ነው። የኢትዮጵያን መንግስት በአምባሳደርነት እና በሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው። ከኢጣሊያ ወረራ በኋላ በተቋቋመችው ኢትዮጵያ ማለትም ከ1937 ዓ.ም እስከ 1938 ዓ.ም ድረስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ አምባሳደር ነበሩ። ቀጥሎም በአሜሪካን ሐገር በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ሌጋሲዮን ውስጥ ከራስ እምሩ ጋር ሆነው በአምባሳደርነት ለአራት ዓመታት ሰርተዋል። ኒውዮርክ ውስጥም የኢትዮጵያ አምባሳደር ነበሩ። ቀጥሎም ከኒውዮርክ መልስ ማለትም ከ1953-1958 ዓ.ም በለንደን እና በኔዘርላንድስ ውስጥ አገልግለዋል። ስለዚህ ሐዲስ በዋነኛነት አምባሳደር ነበሩ። በዚህ የአምባሳደርነት ስራቸው ደግሞ የዋሉትን ውለታ ዛሬ እንዘክረዋለን።

የፊታችን ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም 54ኛ ዓመቱን የሚያከብረው የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫው ኢትዮጵያ እንደሆነ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። ለዚህም ደግሞ በተከታታይ የመጡት የኢትዮጵያ መሪዎች አስተዋፅኦም ከፍተኛ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ከመመስረቱ አራት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ነው። ይህ መ/ቤት ታህሳስ 20 ቀን 1951 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ተቋቋመ /ተመሰረተ/።

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እንደ ዋነኛ ዓላማ አፍሪካን ለማጠንከርና ለማጎልበት ኢኮኖሚ ወሳኝ በመሆኑ በጋራ ትስስር ሐገሮች ወደ አንድ አህጉራዊ ህልም መምጣትን የሚያመቻች ተቋም ሆኖ አገልግሏል። ይህም የአፍሪካ ሐገሮች በጋራ ለሚያቋቁሙት የአፍሪካ ሕብረት እንደ መሰረታዊ የመአዘን ድንጋይ ሆኖ አስተዋፅኦ አድርጓል። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሆን የደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር የሕይወት ታሪካቸው ያወሳል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከመቋቋሙ በፊት ሐዲስ ዓለማየሁ ኒውዮርክ ውስጥ በአምባሳደርነት ይሰሩ ነበር። እዚያ ሆነው አንድ ነገር አሰቡ። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመሰረት። ይህን ሃሳባቸውን ለንጉሥ ኃይለስላሴ ፃፉ። በወቅቱ ንጉሡ በጉዳዩ ወዲያውኑ አልተስማሙም ነበር። ሐዲስ ዓለማየሁም ስለ ጉዳዩ ጠቀሜታነት በተከታታይ ደብዳቤ ይፅፉላቸው ነበር።

 

ንጉሥ ኃይለሥላሴ ለምን ወዲያው ሀሳቡን አልተቀበሉትም? አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ውስጥ ከሆነ የበርካታ ሐገር ዜጎችም አዲስ አበባ ውስጥ የስራ ቦታቸው ይሆናል። በዚህ የተነሳ ሁሉንም የሚታዘብ የውጭ ተመልካች ይመጣብናል። ስለዚህ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ይፋ ይሆናል። ይሔ ደግሞ ለመንግስት ስርዓት አመቺ አይሆንም በሚል ምክንያት እንደሆነ ይገልፃሉ። በኋላ ግን በአዲስ አበባ ውስጥ እንዲቋቋም ጃንሆይ ፈቀዱ።

ዓፄ ኃይለሥላሴ ከመስማማታቸው በፊት ግን አራት ሐገሮች ጽ/ቤቱ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር። ከእርሳቸው ለአንደኛቸው ሊሰጥ በጥናት ላይ ነበር። በኋላ ኢትዮጵያ ስትጠይቅ ተሰጣት። እንዴት ተሰጣት የሚለውም ሌላው ጥያቄ ነበር።

እንደ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ገለፃ ኢትዮጵያ ጽ/ቤቱ እንዲሰጣት ያደረገችው በዘዴ ነው። ጉዳዩ እንዲህ ነው። ጽ/ቤቱን ገንዘብ አውጥቶ በቋሚነት የሚሰራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነው። የሀገሮች ምላሽ ደግሞ ለጽ/ቤቱ መስሪያ የሚሆን ቦታ መስጠት ብቻ ነው። ሐገሮቹ የመስሪያውን ገንዘብ አያወጡም። ኢትዮጵያ ዘግይታ ጥያቄውን ስታቀርብ ግን አንድ መላ ቀይሳ ነበር። ይህም ቦታውን በነፃ እሰጣለሁ፤ የሕንፃውን ማሰሪያ ወጪም እራሴው እችላለሁ። የተባበሩት መንግሥታት ገንዘቡን አያወጣም አለች። በዚህ ምክንያት ከኋላ የመጣችው ኢትዮጵያ የጽ/ቤቱ ምስረታን በአሸናፊነት ተቀበለች። ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁም በሕይወት ዘመናቸው እጅግ ደስ ያላቸው የዚያን ቀን ነው። ምክንያቱም ከበስተኋላ ሆነው የዚህ ሐሳብ ጠንሳሽም ግፊት አድራጊም እርሳቸው ስለነበሩ ነው።

ዛሬም ከአዲስ አበባ ከተማ ውብ ሕንጻዎች መካከል አንዱ የሆነው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ጽ/ቤት የተመደበው ቦታ 26ሺ ሜትር ካሬ ነው። ስለዚሁ ኪነ-ሕንፃ አሰራር አቶ በሪሁን ከበደ በፃፉት መጽሐፍ እንዲህ ይላሉ¸

ሕንጻው የተለያዩ ክፍሎች አሉት። አንድ የጉባኤ አዳራሽ ፣ የኮሚቴ መሰብሰቢያዎች፣ ስድስት ክፍሎች ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሲዮን ሠራተኞችና ከዚህ ኮሚሲዮን ጋር የሥራ ግንኙነት ላላቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት ለጽ/ቤቶች የሚያገለግሉ 140 ክፍሎች፣ ከነዚህ ሌላ ለባንክ፣ ለፖስታ፣ ለቴሌግራፍና ለአየር መንገድ የሚያገለግሉ ክፍሎች አሉት። ዋናው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የዝግጅቱ ፕላን ለሊቀ መናብርቶቹ የመቀመጫዎች ብዛት 8 ለዋና መልዕክተኞች 86፣ ለመልዕክተኞች 168፣ ለታዛቢዎችና ለልዩ ልዩ ወኪሎች 58፣ ለፀሐፊዎች 16፣ ለተርጓሚዎችና ለኦፕሬተሮች 16፣ ለልዩ ልዩ እንግዶች 37፣ ለጋዜጠኞች 106፣ ለተመልካች ሕዝብ 220 በድምሩ 715 መቀመጫዎችን የያዘ ነው።

 

ይህን ለመስራት የወሰደው ጊዜ 18 ወር ብቻ ሲሆን የጨረሰውም ገንዘብ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ብር እንደሆነ አቶ በሪሁን ከበደ “የአፄ ኃይለስላሴ ታሪክ” በተሰኘው መጽሀፋቸው በገፅ 470 ውስጥ ገልፀዋል። በፅሁፋቸው ውስጥ እንዳብራሩት የጉባኤው አዳራሽ የተቀመጠበት ቦታ 3ሺ 600 ሜትር ካሬ፣ ለጽ/ቤቶቹና ለስድስቱ ኮሚቴዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ ስድስት ክፍል የፈጀው ቦታ 5500 ሜትር ካሬ፣ ለባንክ፣ ለፖስታ ቤት፣ ለቴሌግራፍና ለአየር መንገድ መ/ቤት የተሰራበት ቦታ 4500 ሜትር ካሬ እንደሆነ ጽሁፉ ያስረዳል።

ይህን ትልቅ ስራ ያከናወነችው ኢትዮጵያ ናት። ከበስተጀርባ ሆነው ታላቁን ሕልም እውን ያደረጉት ደግሞ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ናቸው። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ታህሳስ 20 ቀን 1951 ዓ.ም ተከፈተ።

ያ ወቅት ለብዙ የአፍሪካ ሐገሮች ጨለማ ነበር። ምክንያቱም ከቅኝ አገዛዝ ገና አልወጡም። በመከራ ውስጥ የሚዳክሩበት ነው። ከነርሱ ውስጥ ዘጠኝ ሀገሮች ብቻ ነፃ ወጥተው ነበር። እነርሱም

1-  ኢትዮጵያ፣

2-  ላይቤሪያ፣

3-   የተባበሩት አረብ ሪፐብሊክ (ግብፅ) ፣

4-   ሊቢያ፣

5-   ሱዳን፣

6-   ሞሮኮ፣

7-   ቱኒዚያ፣

8-   ጋና፣

9-   ጊኒ ነበሩ።

 

ለነዚህ ዘጠኝ ሀገራት የምታበራይቱ ፀሐይ ለሌሎም በቅኝ ግዛት ስር ለሚዳክሩት እንድታበራ ትግላቸውን ቀጠሉ። ሀገሮች ነፃ መውጣት ጀመሩ። ተበራከቱ። አፍሪካ ከባርነት ነፃ የወጣች አዲስ አህጉር ሆነች። ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ.ም ላይ ነፃ የወጡ 32 የአፍሪካ ሐገሮች አዲስ አበባ ላይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን አቋቋሙ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከዚህም አልፎ የብዙ አስተሳሰቦችና ፍልስፍናዎችም ድምር ውጤት ነው።

 

ለምሳሌ የፓን አፍሪካኒዝም ፍልስፍናዎችን የሚያራምዱ እነ ማርክስ ጋርቬይ፣ ኢትዮጵያዊው የህክምና ሊቅ ዶክተር መላኩ በያን እና ሌሎም ከ1920ዎቹ ጀምሮ የሚያቀነቅኗቸው አስተሳሰቦች እየሰፉ መጥተው የደረሱበት ደረጃ ነው። የአፍሪካ ህብረት! ጉዞው ገና ይቀጥላል። ፓን አፍሪካኒዝም ይመጣል። “United States of Africa” ይመጣል ተብሎም ይጠበቃል።

 

እነ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ሀሳቡ ጽንስ እንዲሆን አድርገዋል። ፅንሱም ተወልዶ እያደገ ነው። በ50 ዓመታት ውስጥ ሁሉም የአፍሪካ ሐገሮች ከቅኝ አገዛዝ ስርዓት ወጥተዋል። ቀጥሎም ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ፖለቲካቸውን፣ ኢኮኖሚያቸውን እያስተሳሰሩ መሔድ እንዳለባቸውም አውቀዋል።

 

የአፍሪካ ሐገሮች ትልልቅ ህልሞችን አልመው ነበር። ለምሳሌ በ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ለ25 ዓመታት የሚቆይ ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴሮቻቸው በኩል አቅደው ነበር። ይህም መሐይምነት ከአፍሪካ ምድር በ25 ዓመት ውስጥ እንዲጠፋ። ምክንያቱም በቅኝ የመገዛቱ አንዱ ምክንያት መሐይምነት ስለሆነ ነው። ግን ይሄ የ25 ዓመታት እቅድ አሁንስ እምን ደረጃ ላይ ነው ብሎ ማየት ከአፍሪካ ሐገራት ይጠበቃል።

 

ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ግን ለንጉሥ ኃይለሥላሴ እዲህ አሏቸው፡- መሐይምነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የትምህርት ሚኒስቴር በጀት በጣም ትንሽ ነው። መጨመር አለበት እያሉ በጣም ተከራከሩ። ሳይጨመርም ቀረ። በወቅቱ ሐዲስ የትምህርት ሚኒስቴር ነበሩ። በጀቱ አልስተካከል ሲል ሐዲስ ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ። በኋላም ወደ ለንደን አምባሳደር ሆነው ተላኩ። ሐዲስ ከሄዱ በኋላ የጠየቁት በጀት ተለቆ ነበር። የሚገርም ነው።

አፍሪካ የብዙ ነገሮች ሀብት ባለቤት ነች። ይህን ሐብቷን ተጠቅማ የበለፀገች አህጉር እንድትሆን የህብረቱ ትልቅ የቤት ሥራ ነው። ደራሲ ሐዲስም ከአስር ዓመታት በፊት እንደገለፁት ትምህርት ላይ ብዙ መስራት ተገቢ ነው።

በድርሰቶቻቸው የምናውቃቸው እኚህ ደራሲ ታላቅ ዲፕሎማት እንደነበሩ በጥቂቱም ቢሆን የዛሬው ፅሁፌ ያስረዳል። ሐዲስ ዓለማየሁ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። ከዚያም በምክትል ሚኒስትርነት ማዕረግ ሰርተዋል። በአምባሳደርነት አገልግለዋል። ግን አነሳሳቸው ከቆሎ ተማሪነት፣ ወደ መምህርትን፣ ከመምህርነት ወደ የቴአትር ፀሐፊነት፣ ከፀሐፊነት ወደ አርበኝነት ከአርበኝነት ወደ ዲፕሎማትነት እና ታላቅ ደራሲነት የመጡ ናቸው።

 

በድርስት ዓለም ውስጥ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ፅፈዋል። ለምሳሌ

1.  የትምህርትና የተማሪ ቤት ትርጉም 1948 ዓ.ም

2.  ፍቅር እስከ መቃብር ልቦለድ ታሪክ 1958 ዓ.ም

3.  ወንጀለኛው ዳኛ (ልቦለድ) 1974 ዓ.ም

4.  የእልምዣት (ልቦለድ) 1980 ዓ.ም

5.  ትዝታ 1985 ዓ.ም

 

ከነዚህም ሌላ ኢትዮጵያ ምን አይነት ስርዓት እንደሚያስፈልጋት እና ልዩ ልዩ ቴአትሮችን ከሰላሳ ዓመታት በፊት ሲፅፉ ኖረዋል።

እኚህ ደራሲና ዲፕሎማት በኢጣሊያ ወረራ ዘመን በአርበኝነት ሲታገሉ በፋሽስቶች ተማርከው ወደ ኢጣሊያ ሀገር ተግዘው ታስረዋል። ጣሊያን እስር ቤት ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያ ከፋሽስቶች ወረራ ተላቀቀች። ግን ሐዲስ ከእስር አልተፈቱም ነበር። ሐገራቸውና ህዝባቸው ነፃ ሲወጡ ሐዲስ ገና ነፃ አልወጡም ነበር። በኋላ እንግሊዞች ጣሊያንን ሲወሩ ሐዲስ ዓለማየሁን እና ጓደኞቻቸውን እስር ቤት አግኝተዋቸው ለቀቋቸው። ወደ ሐገራቸው መጥተው የዲፕሎማትነት እና የደራሲነት ስራቸውንም የቀጠሉት ከዚህ በኋላ ነበር።

 

ሐዲስ ዓለማየሁ ከትንሽ ተነስተው ትልቅ ቦታ የደረሱ የትውልድ ተምሳሌት ናቸው። “አባታቸው አለማየሁ ሰለሞን ከጎጃም ክፍለ ሐገር መተከል ወረዳ ኤልያስ ከተባለ የትውልድ አምባቸው ተነስተው ወደ ጎዛምን ወረዳ እንዶደም ኪዳምህረት ድንገት አቀኑ። በዚያው ከወ/ሮ ደስታ ዓለሙ ጋር ተገናኙ። ወ/ሮ ደስታ እንዶዳም ተወልደው፣ እንዶዳም አድገው፣ በኋልም ለወግ ማዕረግ በቅተዋል። ከአቶ ዓለማየሁ ሰለሞን ጋር ትዳር የመሰረቱት በዚሁ ቦታ ነው። በትዳራቸውም ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም የበኩር ልጃቸውን ሐዲስን ወለዱ” ብዙም አብረው ሳይቆዩ ተለያዩ፡ ፈጣሪ ያገናኛቸው ታላቁን ደራሲና ዲፕሎማቱን ሐዲስ ዓለማየሁን እንዲወልዱ ብቻ ነበር። እንኳንም ወለዱት!

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 1951 ተመስርቶ፣ ከዚያም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 1955 ዓ.ም እንዲመጣ ብዙ ውለታ ውለዋል። ዛሬ ሐዲስን የጠቀስነው ከዚሁ አምድ ጋር የተገናኘ በመሆኑ ብቻ ነው። ለምሳሌ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ታህሳስ 20 ቀን 1951 ዓ.ም የተመሰረተ እለት ጉባኤውን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡት ክቡር አቶ አበበ ረታ ናቸው። በኋላ ደርግ የረሸናቸው ሰው ናቸው። ስለ እርሳቸውም ምንም አልተባለም። ሌሎችም ነበሩ። እነ ከተማ ይፍሩ፣ እነ ክፍሌ ወዳጆ እና ሌሎችም።

ደራሲ ሐዲስ አለማየሁ ኢትዮጵያ ምርጥ ደራሲዎችሽን ጥሪ ስትባል ከፊት የሚሰለፉ፣ ኢትዮጵያ ምርጥ ዲፕሎማቶችሽን ጥሪ ብትባል ከፊት የሚመጡ፣ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞችሽን ጥሪ ብትባል ከነግርማ ሞገሳቸው ብቅ የሚሉ የታላላቅ ሰብዕናዎች ባለቤት ነበሩ። ግን ጭንቅ የሚለኝ አንድ ነገር አለ። እንደነ ሐዲስ አለማየሁ አይነት ሰዎችን እያፈራን ነው ወይ? ኢትዮጵያ ሆይ እንደነ ሐዲስ አለማየሁ አይነት ሰዎችን ውለጂ፣ ማህፀንሽም የተባረከ ይሁን።

The post የፍቅር እስከ መቃብር – ፍቅረኞች (በጥበቡ በለጠ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ጠብመንጃና አማራ ምንና ምን ናቸው? – ጋሻው መርሻ

$
0
0

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን እከታተላለሁ። እውነት ለመናገር ሃገር ውሥጥ ካሉት ሚዲያዎች ለህዝብ የቀረበ ነገር በማቅረብ አማራ ቴሌቪዥንን የሚደርሥበት የለም። ጋዜጠኞቹ እሾህ ላይ ቁመውም ቢሆን ማሥተላለፍ የሚፈልጉት ነገር እንዳለ መረዳት ይቻላል። በጣቢያው ከሚተላለፉ ፕሮግራሞች መካከል “አንድ ለአንድ (የክልሉን ባለሥልጣናት በጥያቄ የሚያፋጥጥ ፕሮግራም ነው)፣ ምክር ከአበው፣ የከተሞች መድረክ እና የወጣቶች ፕሮግራም ትንሽ መሻሻል ቢደረግባቸው ለክልሉ ብሎም ለሃገሪቱ እንደ አማራጭ ሚዲያ ማገልገል፣ ለጣቢያውም የመታየት እድሉን ያሠፋለታል ብየ አሥባለው። በተለይ እንደ አድዋ ድል፣ የአርበኞች የድል ቀን የመሣሠሉትን ሃገራዊ ክብረ በዓላት የሚዘክሩበት ርቀት ይበል የሚያሠኝ ነው። ከዚህ የተነሣም ነው የትግራይ ብሄርተኞች የአማራ ቴሌቪዥንን ሃገር ውሥጥ ያለ ኢሣት ሲሉት የሚደመጠው። ያው ሃገር ውሥጥ ያሉ ጣቢያዎች ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ትተው መንግሥታዊ የፕሮፖጋንዳ ማሽን እንዲሆኑ የመፈለግ ጠቅላይነት ክፉ ልክፍት።
.
ህጻናት እያለን በክረምት ከብት ሥናግድ በሠፈር እረኛ የሌላቸውን ሠወች ከብቶች ጨምረን እናግድ ነበር። ታዲያ በነጻ አይደለም። በቀን 10 ወይም 15 ሣንቲም እየተከፈለን እንጅ። ሌላው ደግሞ ከብት በምናግድበት አካባቢ ያለን ማሣ በክፍያ አረም በመንቀል፣ በመኮትኮት፣ እህሉን በማጨድ ትንንሽ ክፍያ እናገኛለን። እንዲሁም ዘመድ አዝማድ ቤተሠብ ሊጠይቅ ሲመጣ ስሙኒም ሃምሣ ሣንቲምም ይቸረናል። ሌላው ደግሞ ከበግ ጸጉር ኮፍያ ሠርተን በመሸጥ፣ ከሠኔል ወይም ግራምጣ ገሣ በመሥራት ሣንቲም እናገኛለን። ይህን ሣንቲም ታዲያ አጠራቅመን ከረሜላ አንበላበትም ወይም ለእሥክብሪቶ ወይ ለእርሣሥ አናወጣውም። ይልቁንም ሥናጠራቅም ከርመን መሥከረም ሲጠባ ጥይት እንገዛበታለን እንጅ። ጥይቱ ከአባታችን ወይም ከወንድማችን ሊሆን ይችላል የምንገዛው። ያኔ እኔ የምገዛው ከአባቴ ሲሆን አንድ የአብራረው ጠብመንጃ ጥይት 1 ብር አካባቢ ነበር። ታዲያ ባጠራቀምነው ሣንቲም ሁለት ሶሥት ጥይት እንገዛለን። የመሥቀል እለትም የገዛነውን ጥይት በቤተሠቦቻችን ጠብመንጃ እንደ ፈንድጃ እናጣጣዋለን። የመሠቀል እለት መንደሩ ከታች በደመራ ከላይ በጥይት እሣት ይንቦለቦላል። የአካባቢያችን ጋራዎች ድምጹን ተቀባብለው ለማዶው ሠው ያሠሙታል። የእዛኛው ማዶ ጋራም ለእኛ ያሠማል። ከዚያ በኋላ የአተኳኮሥ ጀብዱአችን እሥከ ቀጣይ መሥቀል ድረሥ ሥንተርክ እንከርማለን። በሠርግና በሃዘን ጊዜም ጠብመንጃ ማድመቂያው ነው። የእያንዳንዱ አማራ ከጠብመንጃ ጋር ያለው ቁርኝት እንደዚህ ነው የሚጀምረው። ይሄ የሁላችንም የአማራ ልጆች ታሪክ ነው ብየ አሥባለሁ። በአጭሩ ነው ለመተረክ የሞከርኩት። ሌላ ጊዜ በሠፊው እመለሥበታለሁ!! በአዲሥ መሥመር ወደ ዋናው ጉዳየ ልግባ።

 

የአማራ ቴሌቪዥን ትናንት ማታ ያሥተላለፈውን “ፍለጋ” የተሠኘ ድራማ ተመለከትኩት። ድራማው አንድ ወጣት ልጅ የሆነች ልጅ ወዶ እንዴት የራሡ ማድረግ እንዳለበት፣ አንድ ሌላ ሠው ደግሞ ሠው በድሎት ምን ማድረግ እንዳለበት ዘዴ ሲያፈላልጉ የሚያትት ነው። ታዲያ በመካከል አንደኛው ልጅ ጠብመንጃ መግዛት እንዳለበት ለሌላኛው ይነግረዋል። ሌላኛው ግን ጠብመንጃ ለወጣት ብሎም በዚህ ዘመን የማያሥፈልግ ዕቃ እንደሆነ ሊያሥረዳው ይታትራል። በመካከል ሁለቱም ወደ ሌላ ጓደኛቸው ዘንድ ይሄዳሉ። ቤቱ ሲደርሡ ጓደኛቸው ጠብመንጀ ፈትቶ እየወለወለ ይደርሣሉ። ከዚህ በኋላ ያለው የድራማው ክፍል ነው የሚያናድደው!! ወጣቱ ልጅ ጓደኛው ጠብመንጃውን በእጁ እንዲያሥነካው ሲለምነው ያሣያል። ተመልከቱ! ለአንድ የአማራ ወጣት ጠብመንጃ በእጅ መንካት ብርቅ ሲሆን። ባለጠብመንጃውም ጠብመንጃ ከሚገዛ በሬ እና ላም ቢገዛ የተሻለ እንደሚሆን ሊያሥረዳው ይሞክራል። በመካከል ጠብመንጃውን ወልውሎ ከገጠመ በኋላ ሲሞክረው(ሙከራው ያለ ጥይት ነው) ያ ጠብመንጃውን እንዲያሥነካው ሲለምነው የነበረው ልጅ በጣም ይደነግጣል። ድንጋጤው ከአንድ አማራ ወጣት የሚጠበቅ አይደለም። የምር ያናድዳል። ማንኛውም አማራ ለጠብመንጃ አዲሥ አይደለም። ከላይ የጠቀሥኩት አሥተዳደጋችን ለጠብማንጃ አዲሥ እንዳልሆንን የሚያሥረዳ ይመሥለኛል። ታዲያ የዚያ አማራ ወጣት ያን ያክል ለጠብመንጃ መደንገጥ ምን አመጣው? ያልን እንደሆነ ነው ቁምነገሩን የምናገኘው። መንግሥት አማራን ከምድረ ገጽ አጥፍቸ አማራ አልቦ የሆነች ሃገር እመሠርታለሁ ብሎ በያዘው ሥትራቴጅይ መሠረት አማራን ለማንበርከክ ልጆቹን ጠብመንጃ ጠል ማድረግ የመጀመሪያ ሥራው ነው። የዚህ ድራማ ዋና አጀንዳም ይሄው ነው። አማራን ከጠብመንጃው ጋር ማራራቅ፣ ጠብመንጃ የፋራ ነው የሚል መልዕክት መሥጠት፣ ያኔ አማራን እንደፈለጉ አርቆ (ር ጠብቆ ይነበብ) መግዛት ይቻላል ብሎ ከማሠብ የተሠራ አጉል ሥሌት። ልብ አድርጉ አማራ ራሡንና ሃገሩን አሥከብሮ የኖረው በነፍጠኛነቱ ነው። የታጠቀን ህዝብ ማንም እንደፈለገ ሊሸልልበት አይችልም። ህዝብ ራሡን እንዲያሥታጥቅ የሚፈለገውም ለዚህ ነው። አማራ ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት ሲባል ከሚወዳት ጠብመንጃው ጋር ወደ ጦር ሜዳ ይዘምታል። በዚህ አዋጅ ጊዜ ማንም ወሥልቶ አይቀርም። ጠብመንጃ ለአማራ ህልውናው ነው፣ ማንነቱ ነው፣ የአማራነቱ ምልክት ነው። ለአማራ ጠብመንጃ በብቸኝነቱ ጊዜ የሚያነጋግረው ጓደኛው ነው። በክፉውም በደጉም ጊዜ የማይለየው የእሡነት የአጽም ፍላጭ ነው። አማራ ያለ ጠብመንጃ ምንም ነው..! አማራ ጠብመንጃን ፈርቷር አያውቅም!! ይልቁንሥ እንዴት እንደሚያናግራት ያውቃል እንጅ!! እንዲህ እንዝጋው..!
አማራ እና ጠብመንጃ ምንና ምን ናቸው፣
የጆሮ ጉትቻ የአንገት ማተብ ናቸው።
.
በመጨረሻም እደግ ተመንደግ፣ ክፉ አይንካህ ብለን እንትፍ እንትፍ ያልንበት የአማራ ቴሌቪዥን ምራቃችን ሣይደርቅ እንዲህ አይነት ዋልጌ ፕሮግራሞችን ከማሥተላለፍ ቢቆጠብ ለነገው እድገቱ ይጠቅመዋል ሥንል እንመክራለን። ከዚህ በኋላም እንዳይደገም ይሁን!! አማራነትን ዝቅ የሚያደርግ የአማራ ቴሌቪዥን ማየት አንሻም!!

The post ጠብመንጃና አማራ ምንና ምን ናቸው? – ጋሻው መርሻ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሰበር ዜና! … በምእራብ ትግራይ ዉጥረት ነግሶአል! – ልኡል አለሜ

$
0
0

በትግራይ በተለይም በምእራቡ ክንፍ አካባቢ ተሰማርተዉ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ጥሪ እና ትእዛዝ ወደ ጀርባ እንዲያፈገፍጉ መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል በ ዌልቂ፣ ሻምቡካ፣ ባድሜ እና ኢሮብ፣ ኣህፈሮም ድንበሮች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ የድንበር መከላከልና አሰሳ ምድብ የጥበቃ መረባቸዉን አላልተዉ ወደ ጀርባ ተወርዉረዋል፤
በተያያዘ መረጃ 15 የሚጠጉ የመከላከያ አባልት
1. ወ/ር ዘመድኩን ሳሙኤል
2. ወ/ር ቢሆነኝ አጥናፉ
3. ወ/ር ዘገየ ሳሳሁልህ
4. ም/መቶ አለቃ ዘረብሩክ ሰንበቴ
5. ወ/ር ጌጡ አበራ
6. ወ/ር ግርማይ በረካ
ከምእራቡ የመከላከያ ኮማንድ ክንፍ በማፈንገጥ የት እንደገቡ ያልታወቀ ሲሆን የተቀሩት ኍአሃት እራሱ እንደጠለፋቸዉ የሚጠረጠሩ የመከላከያ አባላት የደረሱበት አለመታወቁን ታማኝ ምንጭ ጠቅሰዋል።
በቅርቡ የምእራቡ ትግራይ ድንበር ላይ ጥቃት ከተፈጸመ ወዲህ ከፍተኛ ትርምስምስ ዉስጥ የገባዉ የትግራዩ አንጋች ሰራዊቱን በግምገማና በመልሶ መቁዋቁዋም እያንገበገበዉ ይገኛል፤
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

ልኡል አለሜ

The post ሰበር ዜና! … በምእራብ ትግራይ ዉጥረት ነግሶአል! – ልኡል አለሜ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሰበር ዜና……አሁን በደረሰን መረጃ በሁመራ ከተማ ወያኔ የአማራ እና የትግራይ ሽማግሌዎች እርቅ በማለት በየወረዳው ሰዎችን መርጦ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል!!

$
0
0

ጉልላት ደጀኔ

ስለሆነም ህዝባችን ይህ የወያኔን ፖለቲካዊ “ቁማር ተረድቶ ስብሰባውን ለማክሸፍ አስፈላጊውን ተግዳሮት እንዲተገብር ለማሳወቅእንወዳለን ። በሌላ ዜናም ወያኔ ጠገዴን ከሁለት ጠገዴ ና ፀገዴ ብሎ በመክፈል በድንበር ጉዳይ ህዙቡን ያጋጨው ወያኔ በአሁኑ ሰዓት የሁለቱን አካባቢ እርቅ አውራጅ ሽማግሌዎች ባህርዳር መሰብሰቡ ታውቋል ይሁን እና በእርቅ እና በማይሆን ሽንገላ የሚቀለበስ ጥያቄ እንዳልሆነ ያነሳነው እንድታወቅ በአፅንኦት ማስታወስ እንሻለን ። ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ነው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ!!!!!!
ከዚህም ባሻገር መረሳት የለለበት ነገር ቢኖር ደምን የሚያነፃው ደም እንጅ የወያኔ የይስሙላ የእርቅ ቱሪናፋ እንዳልሆነ እንዲታወቅልን እንወዳለን በተለይም ይህ ጉዳይ በቀጥታ የትግራይ ህዝብ ከወዲሁ ሂሳቡን ለማወራረድ እንዲዘጋጅ የማንቂያ ደውል ነው ።
ወላ በይቅርታ ወላ በማሃላ የሚቀለበስ ጥያቄ አይደለም የጠየቅነው ጥያቄው የህልውና ጉዳይ ነው የሞት ሽረት!!
አማራነት ይለምልም

#ታሪክ ምስክር ነው ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ አማራ ነው
#ትግሬ እንጂ ትግራይ ተከዜ ተሻግራ አታውቅም!!!!!!!

ጉልላት ደጀኔ

The post ሰበር ዜና……አሁን በደረሰን መረጃ በሁመራ ከተማ ወያኔ የአማራ እና የትግራይ ሽማግሌዎች እርቅ በማለት በየወረዳው ሰዎችን መርጦ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል!! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ከፖለቲካ ነፃ የሆነ አንድም ሰው የለም ፣ በሀገር ጉዳይ ገለልተኛ መሆን አይቻልም!

$
0
0
በቶማስ ሰብስቤ
ሀገር የፖለቲከኞች ብቻ አይደለም።በአንድ ሀገር ከፍተኛ ድርሻ ያለው ህዝብ ነው።ከህዝብ የተውጣጣ ፖለቲከኛ ደግሞ አደራ የሚወጣ አካል ነው።ህዝቦች ሀገራቸው ሁሌም በቅርበት የመከታተል ግዴታ አለባቸው።የትኛውም ህዝብ በሚኖርበት ድንበር ውስጥ በሚፈጠር የትኛውም ነገሮች የመጀመሪያ ሰለባ ነው።ሀገር ስትጠቀም ህዝብ ይጠቀማል  ፤ ሀገር ስትከስር ህዝብ ኪሳራ ያወራርዳል።ይህን እውነታ ወደ ጎን ትቶ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ማለት አደጋው ከፍተኛ ነው።ማንም ሰው በአንድ ሀገር የሚወጣው ህግ የሚጎዳው ቢሆን ነፃ ነኝ ያለ ሁላ ከመጎዳት አይድንም።የሚመራው መንግስት ሀገር አፍራሽ ፖሊሲ ቢያወጣ ነፃ ነኝ ያለውም ይቀምሳል ገፈቱን።እርስ በእርስ የሚያፋጅ ሰርአት እየመጣ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ቢሉ ከስቃይ  አያመልጡ።
በሩዋንዳው የእርስ በእርስ እልቂት ያለቁት ከ800  ሺ በላይ ሰዎች ፖለቲከኞች አይደሉም ፣ ንፁሃን ሰዎች እንጂ።በእልቂቱ ወቅት ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ያለ ከጭፍጨፋው አልተረፈም።ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ይውጣም አልተባለም።ምን አገባኝ ፖለቲካ ያለም ፣ያላለም አለቀ።
ዮጎዝላቪያ ስትበታትን ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ያለ ከችግር እና ከሰቆቃ አልተረፈም።ሀገሩ ዪጎስላቪያ ትንንሽ ሀገር ሆና ስትቆረስ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ እዚው ይኑር አልተባለም።ሰባት ቦታ ከመከፋፈል አላመለጠም።አንድነትን የፈለጉ ዮጎዝላቪያዊያን በፖለቲከኛ መሪዎቻቸው ተቆራርጠው ዛሬ ያቺ ሀገራቸው የለችም።ዮጎዝላቪያ ምድር ላይ ጠፍታለች።አንድ ሀገር ነበረች ተብሎ ነው የሚተረተው።ዛሬ ዮጎዝላቪያዎች ኮሶቮ፣ቦሲኒያ፣ሰርቪያ፣ክሮሺያ በሚሉ ትንንሽ ሀገራት ተወክለዋል።ትልቅ ሀገራቸው ጠፍታለች እንደ ዳይኖሰር።ታዲያ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ፣ስለ ሀገሬ ገለልተኛ ነኝ ያሉ ዮጉዠላቪያኖች አሁን የት ናቸው? ከመከፋፈል ተረፉ? ከፖለቲካ ነፃ መሆናቸው ከመጣው ችግር ነፃ አደረጋቸው?……ከፖለቲካ ነፃ ነን ባሉበት አንደበታቸው አልቅሰዋል ፣ተሰደዋል ፣ሞተዋል።የረፈደ እንባ ስለሆነ የአንድነት ሰአቱ አልቆ ያው ተበትነዋል።
ከፖለቲካ ነፃ መሆን ሀገር ያለመውደድ ነው።ሀገር የአንድ ህዝብ ህልውና ነው።ህዝብ ለመቀጥል የሀገሩ ክብር እና አንድነቷ መጠበቅ እና ማስቀጠል አለበት።አለበለዚያ ማንምን ስለሚያፈራው ልጅ መጨረሻ አያውቅም ፣ማንምን ነገር እርግጠኛ ሆኔ ማደር አይችልም ፣ማንም ነገ የሚመጣው እሳት መቆጣጠር አይችልም።በፍርሃት እና ያለዋስትና መሬት መርገጥ ነው ኑሮው።የነገ ልጁን ፣የነገ ቤተሰቡን እና የትላን ሀገር ክብር እና ዳር ድንበሩን ለማስጠበቅ ከፖለቲካ ነፃ መሆን የለበትም። ማንኛወወም ህዝብ በሚኖርበት ሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለው የሀገር ህልውናን የሚንድ እና ሀገሩን ከሚያጠፋ ነገር ሲያይ መነሳት አለበት።ሀገሩን በቅርበት መጠበቅ ግዴታው ነው።
የትኛውም የመንግስት ፖሊሲ ላይ ጥልቅ የሆነ ሀሳብ ባይኖረውም ሀገሩ ላይ እየተከናወነ ያለው ደባ ባየ ጊዜ መጠየቅ ፣መቃወም እና መነሳት ግድ ይለዋል።ሀገሩ እየተበተነች ፣ሀገሩ ላይ ሽር እና የነገ ጥፋት እየተዘራ እየተመለከተ ምን አገባኝ ያለ ችግሩ ሲመጣ ከፖለቲካ ነፃ ነው ተውት አይባልም ነገ።በሀገራችን ምንም ስለ ሀገሩ ፖለቲካ ሳያውቁ በዘር ፖለቲካ ግጭት ፣በድንበር ይገባኛል ግጭት ፣በብሄር ማንነት ግጭት ህይወታቸው ያለፈ ህፃናት ፣ሴቶች ፣አረጋዊያን አሉ።ከፖለቲካ ነፃ መሆናቸው ከሞት አላተረፋቸውም ። ሁሉም ሰው የፖለቲካ ፓርቲ አይመሰርትም ፤ ሁሉም ሰው የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይሆንም ነገር ግን ሁሉም በሀገሩ የነገ ቀጣይነት ላይ ግን ፖለቲከኛ ነው።በሀገር የነገ አንድነት ፣በጋራ ተቻችሎ እና ተዋዶ አንድ ሀገር ማስቀጠል ላይ ህፃን ፤ አዋቂው ፖለቲከኛ ነው።እዚህ ጋር ገለልተኛ ሆነ ነፃ ሰው የለም።ሁሉም ያገባዋል።
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት የሚመጣን ሁሉ ማቆም ፣ምላሽ መስጠት እና አያገባኝም የምንለውን አቁመን ማሸነፍ አለብን።ኢትዮጵያዊነት እየወደቀ እና እየጠፋ ከፖለቲካ ነፃ ሰው የለም።ሀገራችንን እያጠፋ ካለው ፀረ ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ ህግ እና ተግባራት ለማሸነፍ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን የለብንም።ኢትዮጵያን ወደ ትንንሽ ሀገር ለመቀየር የሚሰራ መንግስትንም ፣ተቃዋሚንም ማጥፋት አለብን።ልካቸው ለማሳየት በእያለንበት መስራት ይጠበቅብናል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለውን የዘር ፣የሀይማኖት እና የቋንቋ ልዮነት መከባበር እና መቻቻል አለበት።በፍቅር ልዮነታችንን አንድ ማድረግ ይጠበቅብናል።ነገር ግን ዘራች እና አንደበታችን ልዮነት መሰበኪያ እና የጎሳ ፖለቲካ መፍጠሪያ መሆን የለበትመ።ይህም የሆነበትን የአሁኑኑ ስርአት እምቢ ማለት ይኖርብናል።ልዮነታችን ለእራሳችን የግል እና የቡድን ጥቅም ይሁን እንጂ ከሀገር ለመለየት ምልክት አይሆንም።ሀገራችን የሁላችንም ስለሆነች ያገባናል።ነፃ የሆነ ሰው የለም።አሁን ያለው የጎሳ ፖለቲካ ዝም ብለነው ረጅም አመት ከቀጠለ እኛም ዘረኛ ሆነን እጅጉን ከሄድን ከ፣ከሀገር በላይ የዘር ድንበር እና የዘር ታሪክ ካስጨነቀን ፣ከሀገር በላይ እርስ በእርስ ካልተስማማን ፣ሀገርን ትተት በጎሳ መደራጀቱ ካዋጣን ነገ የሚመጣወወ እሳት ከባድ ነው።
የጎሳ ፖለቲካ ነገ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጭፍጨፋ ቢያመራ የሚተርፍ የለም።ከፖለቲካ ነፃ ነበርኩ ብትል ባትል የጭፍጨፋው ስለባ ከመሆን አተርፍም።ስለዚህ እንደ ሀገር ለመቆም ነፃ ነኝ ከፖለቲካ ያልን ሁላ ቆም ብለን ነገን አስበን ለሀገራችን አንድነት የበኩላችንን እንወጣ።ገለልተኛ እና ነፃ መሆን ከሀገር አይቻልም።በልዮነት ጥላቻን እንተው።አንድነት ለሁላችንም እንዲበጅ አድርገን እንነሳ።ልዮነታችን  ለመራራቅ አንጠቀምበት።በእርስ በእርስ ጭፍጨፋ እና የጎሳ ፖለቲካ ደም እንጂ ፉሪደም የለም።ማንም ጀግና ብሄር የለም ፣ማንም የሚገደል ብሄር አይኖርም።ትልቁም ትንሹም  አንድ ሀገር ብሎ ከኖረ ትልቅ ነው።አንድ ሀገር ለማፍረስ የሚሰራ ገዢ መንግስት ሆነ ተቃዋሚ ትንሽ ሀሳብ ስለያዛቹ ትንሽ ትሆናላቹ።ኢህአዴግ ካመጣህው የጎሳ ፖለቲካ ውጣ ፣ ህዝብን አሰቀድም እና ውረድ።የተቃዋሚ ሰፈር ደሞ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመራ ጭንቅላት ይዘህ የራስህ ትውልድ አና ሀገር አድን ፖሊሲ ይኑርህ።
ከፖለቲከኛ ነፃ ነኝ የምትል ፣የምትይ ሁላ ግን ወደድሽም ጠላሽም ከፖለቲካ ነፃ አይደለሽም።ኢትዮጵያዊ ውስጥ አሁን በተፈጠረው የዘር ፖለቲካ እልቂት ቢጀመር ከፖለቲከኛ ነፃ ነኝ ያልሽ ሁላ የምተርፊ ይመስልሻል? ያገባኛል በሉ!!
ኢትዮጵያ አንድ ሀገር ፣ኢትዮጵያ ሁሌም ትቅደም

The post ከፖለቲካ ነፃ የሆነ አንድም ሰው የለም ፣ በሀገር ጉዳይ ገለልተኛ መሆን አይቻልም! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ዘረኝነት—የሐይማኖት መሪዎች መለዮ! – በዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ*

$
0
0

በምድረ ኢትዮጵያ ዘረኝነት የሚሉት ወረርሽኝ ከምንም ጊዜ በላይ ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። በተለይ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ያለ ምንም በቂ ምክንያት አንድን ሕዝብ ወይም ብሔር አብዝተው የሚጠሉበት ሁኔታ በግልጽ እያየንና እየሰማን እንገኛለን። እንድህ ዓይነቱን ኃላ-ቀር እና የወረደ አስተሳሰብ አጥብቀን መዋጋት ይኖርብናል። ምላሱን አዳጠው መሰለኝ የሆነ ቀን አንድ ሰውዬ፡-

‹‹እነኝህ ለማኝ ትግሬዎች ችግር አለባቸው!›› ስል በገዛ ጆሮዬ ሰምቼ ኖሮ፤

‹‹ችግር ያለው ትግሬ፣ ካምባታ፣ ኪኩዩ፣ ኦሮሞ፣ ዶርዜ፣ አማራ፣ ሃድያ፣ ጉራጌ፣ ሉዎ፣ አሻንቲ….አይደለም! ችግር ያለው የሰው ልጅ ራሱ ነው፤ የሰው ልጅ ራሱ ለራሱ ጥያቄ ነው፤ ጭፍን ጥላቻ የበለጠ ያራርቀናል እንጅ የትም አያደርሰንም! የጥቂት ሰዎች ድርጊት የአንድ ብሔር ማንነት መገለጫ ሊሆን አይችልም፤ ለምሳሌ፡- አማራ—ነፍጠኛ፣ ኦሮሞ—ወራሪ፣ ጉራጌ—አጨበርባሪ…ወዘተ እያሉ ሕዝቡን ግራ የሚያጋቡ ሰዎች አሉ፤ አንድን ሕዝብ ስብናውን መወረፍ አግባብነት የለውም፤ እናም የቅድመ-ጥቅላሎት ሕፀፅ ፈጽመሃል…›› አልኩት!

እንዳለጌታ ከበደ ይህንን ጉዳይ እንድ ስል ነበር የታዘበው፡-

‹‹አንዳንዱ የዚህ ትውልድ አባል- ከአባቶቻችን ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው መሰረት ልበል?) የስድብ ሃብታም ነው፤ የሚተርበው ብሔር አያጣም፤ ሌላውን አሳንሶ አስጐንብሶ ካላሳየ እሱ ቀና ቢል እንኳን የሚታይ አይመስለውም፤ ልቡ በነቀፌታ የተሞላ ነው፤ አንዳች የስድብ መንፈስ-በየቤቱ- በየቤተመንግስቱ- በየቤተ ክርስትናውና በየቤተ እስልምናው ሰፍኗል፤ የሆነውን ብሔር ለይቶ፣ የሆነውን ወገን አግልሎ፤ ‹እኛ ካልተሳተፍንበት የልማት እስክስታው አይሰምርም፤ እኛ ካልደሰኮርንለት አምላክ ቸርነቱን አያዘንብም› ማለት የተለመደ እየሆነ ነው! ለመጪው ትውልድ ‹በደም› የሚመለስ የቤት ስራ እየተውን ያለ ይመስለኛል፤ የመጪው ትውልድ አባላት እኛ በመጣንበትም ሆነ አባቶቻችን በተመላለሱበት የመሰዳደብ መንገድ ባይሄድ እንመርጣለን፤ እኛ ፈትለንና ገምደን ያቆየነው፣ አለባብስን ያረስነው ነገር ነገ ከነገ ወዲያ ‹… ያልተዘጋ ፋይል አለ!› ብለው በጥይት ቋንቋ እንዲነጋገሩ መፍቀድ የለብንም- ሰርተን በቆየንላቸው መንገድ ደም እንዳያጐርፍበት፤ ሰርተን ባቆየንላቸው ተቋማት ስድብ እንዳይፈበረኩበት ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል፡፡ አዎን፤ ሁላችንም ስድቦች ወደ መጡበት የሚመልስና ወደሚመለከተው ክፍል የሚያዘዋውር ጽ/ቤት በየህሊናችን ልናቋቁም ይገባል፤ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በብዙዎች ልቦና ላይ የማይታይ ቁስልና ሰንበር እንዲታተም አድርገናልና!››

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን የእግዝአብሔርን ሕዝብ እናገለግላለን የሚሉ የኀይማኖት አባቶች የችግሩ አካል በመሆን ‹ወንገልን› በ‹ወንጀል› ለውጦታል። እነኝህ ፈርሳዊያን እና የሕግ መምህራን ፓስታ እየበሉ ወይንም ቢራ እየተጐነጩ ይህንን ጉዳይ ፈጽሞ አይወያዩበትም ማለት አይቻልም፤ ጠንቅቀው ነው የሚያውቁት—የእኛ አድርባዮች! ነገር ግን፣ እስከ ዛሬ ድረስ ዘረኝነትን በግልጽ ለመተቸት አይደፍሩም። አንድ የኀይማኖት መሪ የወጣለት ዘረኛ ሆኖ እያሌ ዓይኑን በጨው ታጥቦ እንዴት ‹‹እግዝአብሔር ፍቅር ነው›› በማለት ይሰብካል? ያሳፍራል እኮ! አንድ ቄስ ወይም ፓስተር በአጠገቡ ካለው ወንድሙ ጋር ሠላም ሳይፈጥር ‹‹የእኛ እግዝአብሔር የሠላም አምላክ ነው!›› ብሎ ክላሽ ማንጣጣት ነውር አይደለም እንዴ!? የጥምቀት ውሃ ከሰው ልጅ ባህል ‹በላይ› መሆኑን ያልተቀበለ/ያላመነ አንድ አገልጋይ ‹‹ሁላችንም በምስጢረ ጥምቀት የእግዝአብሔር ልጆች ሆነናል›› ብሎ ቤተ-መቅደስን ማጣበብ ስበዛ ሌብነት፣ ሲያነስ ደግሞ ድንቁርና ነው! ሌብነት ይብቃን አቦ!

ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ በሃይመኖት ተቋማት ውስጥ ያለአግባብ መበልጽግ ባሕል ከሆነ ፤ የመልካም አስተዳደር እጦት ከተንሰራፋ ፤ የውሸት ባሕል ከነገሰ፤ አድሏዊነት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ጨቋኝነት ሥር ከሰደደ፣ በገዳማት ውስጥ በሠላምና በፍቅር አንድ ላይ አብሮ መኖር ካልተቻለ፣ መደማመጥና መነጋገር ጠፍቶ መናናቅ ብቻ ከሆነ፣ የአብሮነት መንፈስ የሚባል ነገር ከጠፋ፣ ሥራ የሚከፋፈለው በዝምድና እና በዘር ከሆነ ቤተ-ክርስቲያንን የሌቦች ዋሻ ሆናለች ማለት ነው!
ስለዝህ፣ ዘረኝነት በግልጽ መተቸት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል። ለምን ይዋሻል! ሕዝቡ ቆንጨራ እስከሚያነሳ መጠበቅ የለብንም! በሩዋንዳ ምድር በተደረገው የዘር ጭፍጨፋ የቄሶች (እኔ መቀሶች ነው ሚላቸው!) እጅ ነበረበት። በእርግጥ እነኝህ የኀይማኖት መሪዎች ትምህርት ቤት ተመላለሱ እንጅ አልተማሩም፤ መጽሐፍና ማንበብ የቻለ ሁሉ ‹ተምሯል› ማለት አይደለም! እንዴታ! የሰባት ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርት የአንድን ሰው አስተሳሰብን ካልቀየረ እኮ የጭንቅላት ጥቅም ለ‹ቆብ› ብቻ ነው የሚሆነው! አርስጣጣልስ (Aristotle) ልክ ነበር— ‹‹ልብን ሳያስተምሩ ጭንቅላት ብቻ ማስተማር ዋጋ-ቢስ ነው!››
የሆነ ሆኖ አጐስቲን ካሬኬዝ (Augustine Karekezi) የሚባል አንድ ኢየሱሳዊ ቄስ (a Jesuit priest) የሩዋንዳውን አሳዛኝ ክስተት በምገርም ሁኔታ እንደሚከተለው አስፍሮ ነበር፡-

“My faith as a Christian has been affected seriousely, in the sense that I cannot realize that such evil could happen in a country where so many people are Christians and where there are so many Catholics, over sixty five perecent, with such influence in education. What have we been doing as Christians and as priests? How can we preach the love of God, the compassion of God, in this situation? All these questions derive from an experience of the deep mystery of evil, evil that is so consistent and so strong that its power is prevailing”

ስለዝህ፣ የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ኋላፍነት አለባቸው! ሕዝቡ በቆንጨራ እየተጨራረሰ ዝም የሚትሉ ከሆነ፣ በፈጣሪና በሕግ ፊት ተጠያቅዎች ናችው። እምነትና ፀሎት ብቻ በቂ አይደለም። ሰይጣንም እኮ እግዚአብሔር የዘለዓለም ኗር መሆኑንና ታላቅ አምላክ መሆኑን ያምናል። ግን መልካም ሥራ የለውም፤ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው! የእግዝብሔር ቃልም የሚላችው ይህንኑ ነውና፤ “ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።” (አሞጽ 5፤ 22-24) ይህ ማለት፣ አንድም፣ የሚተሰብከውን ኑር እንጅ፣ ፈሪሳዊ አትሁን፤ ሁለትም፤ ‹‹ከመጠምጠም መልካም-ሥራ ይቅደም›› ማለት ነው። ‹‹ፂም በማሳደግ ቢሆን ፍየል ትሰብክ ነበር›› እኮ!!

 

አዎን! በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ውስጡን ዘረኝነት የሚሰብኩ ወይም የሚያቀነቅኑ ቀጣፊ ቄሶች አሉ፤ እንድ ዓይነቱን የአስተሳሰብ ሽርሙጥና ከወድው በቆራጥነት መዋጋት አለብን፤ አዎን! እነኝህ አስመሳይና አድርባይ ‹መቀሶች› እሳት ከሚተፋው የፍልስፍና ብእር ማምለጥ አይችሉም! እየተከታተልን እናጋልጣለን!

ሠላም፣ ፍቅርና አንድነት ለሀገራችን ኢትዮጵያ እያልኩኝ፣ በሃይለመለኮት መዋእል ግጥም ልሰናበታቸው!

 

ምን ጠቀመዉ ቃየልየመሳሪያ ቋንቋ
ሰጠመ ጠፋ እንጂባቤል ደም አረንቋ
መኢኑም አባተሰመረ መረሳ
ኦቦንግ አብዱል ከሪምጋቸኖ ቶሎሳ
አብረኸት ምንትዋብኛዳክም ጋዲሴ
በላህ በነብዩበሶስቱ ስላሴ
ሰይፉም ዶማ ይሁንሞርተሩም አንካሴ

 

*Yoseph Mulugeta Baba (Ph.D.) can be reached at:

kankokunmalimaali@gmail.com

 

The post ዘረኝነት—የሐይማኖት መሪዎች መለዮ! – በዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ* appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሰበር መረጃ . …የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ልኡካን ቡድን ጀርመን

$
0
0

ግንቦት 7/ 2009
የምጡ ሰሃት ደርሷል . .
ህወሃት እያማጠች ነዉ የዉጭ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነቷ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ደብዛዉ እየጠፋ አስተማማኝ
ማረጋገጫዎች ፍንትዉ ብለዉ እየወጡ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻዉም።
የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ልኡካን ቡድን ጀርመን መግባቱን ተንተርሶ የዉጭ ጉዳይ፣
የደህንነት ክፍል ዘርፎችና የሐገር ዉስጥ እንዲሁም ከፍተኛ የዉጭ ጉዳይ አመራሮች፣ ወታደራዊና ከወታደራዊና
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጋር ግንኙነት አላቸዉ የሚባሉ ግለሰቦች በሙሉ በብሔራዊ መረጃ ቅጽር ዉስጥ የጭንቅ ዉይይት
ተቀምዋል።
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ደንብና ህግ የጀርመንና የሌሎች አዉሮጳ ሐገራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አያካትትም ወይ
የሚሉ መጠይቆች እየተነሱበት የሚገኘዉ ይህዉ ስብሰባ እነዚህ ከአጸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እያደረጉ የሚገኙ
ሐገራቶች በደብዳቤም ይሁን ህዝብን አስተባብሮ ሰላማዊ ሰልፍ በማስወጣት እንዲወገዙ በማድረግና ኢንባሲዎቻቸዉን
በማገድ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በማቋረጥ እርምጃ ለምን አይወሰድባቸዉም የሚሉት ሐሳቦች አጀንዳዉን
አጨናንቀዉታል።
ይሁንና አንድና አንድ ያለን አማራጭ ኤርትራ የሚገኘዉን አርበኞች ግንቦት 7 የተባለውን ድርጅት ማስወገድ ነዉ
የሚለዉ መንጥረ ሐሳብ በሙሉ ድምጽ ተሰምሮበት በአስቸኳይ መመሪያ ዛሬ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ተወስኗል።
ስብሰባዉን በቁጭት ሲመሩ ከነበሩት መካከል ጄ/ ሳሞራ እና የብሔራዊ መረጃዉ ጌታቸዉ አሰፋ እንባ ሁሉ
እየተናነቃቸዉ እንደነበር የደረሰን መረጃ አረጋግጧል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

ልኡል አለሜ

The post ሰበር መረጃ . …የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ልኡካን ቡድን ጀርመን appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


የዐማራ ተማሪዎች ስቃይ በዓለማያ ዩንቨርሲቲ- ተማሪ ሀብታሙ ጌታቸው እንደማሳያ – ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0

ተማሪ ሀብታሙ ጌታቸው ይባላል፤ ትውልዱና እድገቱ ከወደ ጎጃም ሲሆን የሁለተኛ ዓመት የሕግ ተማሪ ነው፤ ከዲፓርትመንቱ በውጤት እሱን የሚስተካከል ተማሪ የለም፡፡ ባለፈው ዓመት ጀምሮ ውጤቱን አስጠብቆ መሔዱ ያናደዳቸው ጠባብ ብሔርተኞች ከትምህርቱ እንዲሰናከል ወይም እንዲያቋርጥ ጥረት ማድረግ የጀመሩት ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤት ከታየ በኋላ ነበር፡፡ ሀብታሙ የሚደርስበትን ትንኮሳና ዛቻ ከምንም ሳይቆጥር ትኩረቱን ትምህርቱ ላይ አደረገ፡፡

ግንቦት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ቤተ መጽሐፍት ሲያነብ ቆይቶ ወደ መኝታ ክፍሉ በመመለስ ላይ ሳለ አራት ከሳሽና መስካሪ ሊሆኑ የሚችሉ ወንጀል አቀናባሪዎች አብረውት መንገድ ጀመሩ፤ አንደኛዋ ሴት ናት፡፡ ሁለቱ በኤርፎን ሙዚቃ ያዳምጣሉ፤ አንደኛው ማዳመጫውን ነቅሎ ሙዚቃውን አስጮኸው፡፡ የሚሰማው የቴዲ አፍሮ አዲሱ ሙዚቃ ነበር፡፡ ከመካከል ሴቷ ልጅ ‹‹ስለምን የነፍጠኛ ዐማራ ሙዚቃ ታዳምጣለህ›› የሚል ሀሳብ ታነሳለች፤ አካሔዳቸው ሀብታሙን ማናደድና ወደ ጠብ መገፋፋት ቢሆንም ሀብታሙ ጌታቸው ግን ዝም ብሎ ንቋቸው መንገዱን ቀጠለ፤ እነርሱ እረፍት ሳይሰጡት ግልጽ የሆነ ስድብ ይሰድቡት ጀመር፤ አሁን በዚህ ሳይናደድ ገብቶ ተኛ፡፡

ወዲያውኑ ብዛት ያላቸው ፖሊሶች መጥተው ሀብታሙን እየደበደቡ አፍነው ወሰዱት፡፡ ለምን ብለው የጮኹ ጥቂት የዐማራ ተማሪዎች በጥይት አስፈራሯቸው፡፡ ሌሊት በመሆኑ ብዙ ልጆች መሰባሰብ አልቻሉም ነበር፡፡ ሀብታሙ ጌታቸው ትምህርቱን አቋርጦ በዓለማያ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ሲደበደብ ከሰነበተ በኋላ ‹‹የትምከተኝነት›› ክስ ተመሰረተበት፡፡ ተማሪ ሀብታሙ በቀጣይ ሰኞ ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ›ም ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሏል፡፡

በዓለማያ ዩንቨርሲቲ የዐማራ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሰብአዊ መብት ረገጣ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ እንደሔደ በዩንቨርሲቲው የሚማሩ ተማሪዎች በተደጋጋሚ ይገልጻሉ፡፡ የኦሮሞና የትግሬ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ማኅበር አላቸው፡፡ የትግሬ ተማሪዎች በዩንቨርሲቲው ተደግሶላቸው ከአንድ ሳምንት በፊት በዓል አዘጋጅተዋል፡፡

ሚያዚያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በዩንቨርሲቲው በነበረው የባሕል ፌስቲቫል የዐማራ ተማሪዎች ባሕላቸውን ካዘጋጁ በኋላ የትኽምከተኛ ባሕል በዩንቨርሲቲያችን አይቀርብም ተብሎ የሌሎች ብሔሮች ሲቀርብ የዐማራው ተለይቶ ቀርቷል፡፡ ለምን ብለው የጠየቁ ተማሪዎችም ታስረዋል፡፡

በዩንቨርሲቲው የዐማራ ተማሪዎችን ቸግር ሊፈታ ወይም ሊያዳምጥ የሚችል አንድም አካል አለመኖሩም ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል ብለውናል፡፡

The post የዐማራ ተማሪዎች ስቃይ በዓለማያ ዩንቨርሲቲ- ተማሪ ሀብታሙ ጌታቸው እንደማሳያ – ሙሉቀን ተስፋው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የቤተ ክርስቲያንን የዳኝነት ሥርዓት መልሶ በማደራጀት ጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት በገለልተኝነት እንዲዋቀር ተጠየቀ

$
0
0

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ያለውን የፍትሕ ሥራ በማቀናጀት ተግባሩን ይወጣል
  • የፍትሕ ዕጦት የተንሰራፋው፣ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ የይስሙላ መዋቅር በመኾኑ ነው
  • ከፓትርያርኩና ከጠቅ/ቤተ ክህነቱ ክፍሎች ጣልቃ ገብነት እንዲጠበቅ ይደረጋል ተብሏል
  • ለፓርማው የተላከው የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ ዐዋጅ፣ ውሳኔ አላገኘም

መንበረ ፓትርያርክ ከኾነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጀምሮ፣ በቤተ ክርስቲያናችን የተንሰራፋውን የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ የሥነ ምግባርና የውሳኔዎች አስፈጻሚ ማጣትን ችግሮች ለመቅረፍ፣ የቤተ ክህነቱን መዋቅር መልሶ በማደራጀት ማሻሻል እንደሚገባ በመሠረታዊ ችግሮች ላይ የተካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

መዋቅሩን መልሶ ከማደራጀት ጋራ በተያያዘ፣ ወጥ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት፣ ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ተልእኮዋን በብቃት እንድትወጣ ለማድረግ የሚያግዙ ሕጎች፣ ደንቦችና የአሠራር ሥርዓቶች የሚያስፈልጓትና ያሉትም ተሻሽለውና ተስተካክለው እንደገና መጻፍ እንዳለባቸው ጥናታዊ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

በዐዲስ መልኩ እንዲወጡ ከተጠቆሙት ሕጎችና ደንቦች መካከል፥ የቤተ ክርስቲያኒቱን የዳኝነት ሥርዓት የሚደነግገው ሕግ የሚገኝበት ሲኾን፣ ከቅዱስ ሲኖዶሱ፥ የፍርድ፣ የሕግና ሥነ ሥርዓት ተግባርን በሚመለከት ያለው ሥልጣን፣ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጽ/ቤት ውጭ በማድረግ፣ በጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት እና በሕግና ሥነ ሥርዓት ኮሚሽን እንዲዋቀር፣ በአማራጭነት የቀረበው መዋቅር ያሳያል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱ የሕግና ሥነ ሥርዓት ኮሚሽን፣ በኮሚሽነር እንዲመራ በማድረግ፦ የሕግ፣ የሥነ ሥርዓት፣ የኦዲት፣ የቁጥጥር፣ የመሳሰሉት ከተጽዕኖ ነጻ በኾነ መልኩ መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚሰማራ፤ የኮሚሽኑም ሓላፊ በቅዱስ ሲኖዶሱ በቀጥታ እንደሚመረጥና ተጠሪነቱም ለቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ እንደሚኾን በአማራጭ መዋቅሩ ተመልክቷል፡፡ በጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱም ኾነ በሕግ፣ ሥነ ሥርዓት፣ ቁጥጥርና ኦዲት ሥራዎች፣ ከፓትርያርኩ፣ ከቋሚ ሲኖዶሱና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ክፍሎች ጣልቃ ገብነት ሊጠበቁ እንደሚገባ ጥናቱ ያስገነዝባል፡፡

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዛሬ፣ ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ የቀትር በፊት ውሎው፣ ጥናታዊ ሪፖርቱንና የከፍተኛ ኮሚቴውን ማብራሪያዎች በማዳመጥ ተወያይቶበታል፡፡ የዳኝነት ሥርዓቱን መልሶ በማደራጀት፣ ጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱን በገለልተኝነት ማዋቀር እንደሚያስፈልግ በጥናቱ የተጠቆመውን በተመለከተ፣ ሰንደቅ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት እትሙ ተከታዩን ዘገባ አውጥቷል፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የሥራ አስፈጻሚውና የዳኝነቱ ሥራ መቀላቀሉ፥ ለአሠራር ሥርዓት ክፍተት፣ ለመልካም አስተዳደር ዕጦትና ለፍትሕ መዛባት ምክንያት እንደኾነ የሚጠቅስ ጥናት ለቅዱስ ሲኖዶሱ የቀረበ ሲኾን፤ የዳኝነቱን ተግባር በገለልተኝነት የሚሠራ ጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት እንዲዋቀር ተጠየቀ፡፡

የቤተ ክርስቲያንን መሠረታዊ ችግሮች አጥንቶ ከመፍትሔ ሐሳቦች ጋራ እንዲያቀርብ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ምልአተ ጉባኤ የሠየመው ከፍተኛ ኮሚቴ ባረቀበው ጥናታዊ ሪፖርትበጠቅላይ ቤተ ክህነት እና በሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ደረጃ የተቋቋመ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ቢኖርም፣ የአሠራር ደንብ ያልተዘረጋለትና ብቁ ባለሞያዎች ያልተካተቱበት የይስሙላ መዋቅር መኾኑን ተችቷል፡፡

ለቅዱስ ሲኖዶሱ ተጠሪ ኾኖ የተቀመጠው መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ፣ የዳኝነትና የፍትሕ ተግባር ከመሥራት ይልቅ፣ በሥራ አስፈጻሚው ጥላ ሥር ኹኖ የአስፈጻሚነት የሚመስል ሥራ መሥራቱ፤ የአስተዳደር በደል ደርሶብኛል የሚለው ካህንና ምእመን፣ ተገቢውን ፍትሕ እና የዳኝነት አገልግሎት እንዳያገኝ ምክንያት መኾኑን ጥናታዊ ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ካህናትና ምእመናን፣ በብዛት እየተሰበሰቡ ውሳኔ ወደሰጣቸው አስፈጻሚና ወደ ዋናው የሕግ አውጭ አካል(ቅዱስ ሲኖዶስ) እንዲኹም ወደ መንግሥት መደበኛ ፍርድ ቤት ለመሔድ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ እንግልትና መንከራተት በሰፊው ተንሰራፍቶ የሚታየው፣ መንፈሳዊ ፍ/ቤቱ፣ ቀድሞ በነበረው ልማድ ያለበቂ ሥራ በመቀመጡ እንደኾነ ጥናቱ አስረድቷል፡፡

በየመዋቅሩ የሚገኙት ሥራ አስፈጻሚዎች በሚሰጡት ውሳኔ ቅር የተሰኘ አካል የሚያቀርበውን አቤቱታና የፍትሕ ጥያቄ የሚተረጉምና የሚዳኝ ሥርዓት ባለመኖሩ፣ የአስተዳደር ሓላፊዎች ሥልጣናቸውን ያለገደብ እንዳስፈለገ የሚተገብሩበት አጋጣሚ በስፋት እንደሚታይ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

የመዋቅራዊ አደረጃጀት ችግር በተለይም፣ የሥልጣን በአንድ ቦታ መከማቸት እና የሕግ አውጭው፣ የሕግ አስፈጻሚውና የሕግ ተርጓሚው አካላት ተለይተው አለመደራጀታቸው፣ የተጠያቂነት ማለትም የእርስ በርስ ቁጥጥርና ሚዛን ሥርዓት እንዳይዳብር ያደረገ፦ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ኹሉ ዋነኛ መንሥኤ መኾኑን ጥናታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

መዋቅራዊ አደረጃጀቱ፥ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ የሚያሳካ፣ ዓላማዎቿንና ግቦቿን ለማስፈጸም በሚያስችል አኳኋን፣ ስትራተጅያዊና መሠረታዊ በኾነ መልኩ መልሶ ሊደራጅና ሊስተካከል እንደሚገባ የጠቆመው ጥናቱ፤ በዐዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት ለመሥራትም፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸውና በአስቸኳይ ሊወጡ ይገባቸዋል ካላቸው ቃለ ዓዋዲዎች መካከል፥ የዳኝነት አካሉን ከነዝርዝር ተግባሮቹ እንዲኹም የመዋቅሩን ተዋረድና የአሠራር ሥርዓቱን የሚገልጽና የሚደነግግ ሕግ ይገኝበታል፡፡

በአጥኚ ኮሚቴው በቀረበው የዐዲስ መዋቅር አማራጭ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ሥልጣን ባለው በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በገለልተኝነት መዋቀር እንዳለበት ነው የተጠቆመው፡፡

ፍርድ ቤቱ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው ሓላፊነትና ሥልጣን፦ የፓትርያርክ፣ የቋሚ ሲኖዶስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ክፍሎች ጣልቃ እንደማይገቡና ሥራውን በገለልተኝነት እንዲሠራ፤ የመጨረሻ የይግባኝ የፍትሕ ዳኝነት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ እንደኾነ በጥናቱ ተገልጿል፡፡ የፍርድ ቤቱ ችሎትና ዳኝነትም፣ በሚወጣው ደንብና መመሪያ መሠረት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ያለውን የፍትሕ ሥራ በማቀናጀት ተግባሩን እንደሚወጣ ተጠቁሟል፡፡

ስድስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ÷ በዛሬ፣ የቀትር በፊት ውሎው፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን አወቃቀር ጨምሮ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች የሚጠቁመውን ጥናታዊ ሪፖርትና የከፍተኛ ኮሚቴውን ማብራሪያ በማዳመጥ፣ የለውጥ ሥራውን በተግባር ለመጀመር የሚያበቃ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምታስተዳድራቸው ካህናት ምእመናን ላይ፣ የመንፈሳዊ ዳኝነት ሥልጣን ያላት ሲኾን፤ ወንጀል ነክ ከኾኑ ጉዳዮች ውጭ፦ ካህናት፣ ኤጲስ ቆጶሳትና ሊቃነ ጳጳሳት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በሚመለከት ቢከሠሡ ወይም ቢከሡ፣ ጉዳያቸው፣ በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ይታያል እንጅ በመደበኛ ፍርድ ቤቶች እንደማይዳኙ ተደንግጓል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ዳኝነት፣ እንደ ክሡ አቀራረብ እየተመዘነ ከሚታይባቸው አካላት መካከልም፣ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አንዱ እንደኾነ በሕጉ ተመልክቷል፡፡

ቤተ ክርስቲያን በ2003 ዓ.ም.፣ “የፌዴራል መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀትና ለማጠናከር የወጣ ዐዋጅ/ቁጥር 2003” በሚል የዳኝነት ሥርዓቷን ለማደራጀትና በኦፊሴል እንዲሠራበት ለማድረግ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቃ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብትልክም፣ ውሳኔው በመዘግየቱ፣ ለአስተዳደር ሥራዋ ልታገኝ የሚገባትን የሕግ ድጋፍ እንዳላገኘች በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ የጋራ መግለጫ አማካይነት ቅሬታዋን ማሰማቷ አይዘነጋም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱም፣ ጉዳዩን ተከታትሎ የሚያስፈጽም አካል እንዲሠይም በመግለጫው መጠየቁ ተወስቷል፡፡

The post የቤተ ክርስቲያንን የዳኝነት ሥርዓት መልሶ በማደራጀት ጠቅላይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት በገለልተኝነት እንዲዋቀር ተጠየቀ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አዎ!  አማራ ተኝተሃልና በመቀሌ ከተማ  በልጆችህ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይገባሃል!   (አድማሱ በጋሻው)

$
0
0

በመጀመሪያ በመቀሌ  የእግር ኳስ ጨዋታ  በባህር ዳር ከተማ ተጫዋቾች ላይ  ግፍ ሲፈጸምባቸው  የሚያሳየውን ፎቶ  በአይነ ህሊናዎ ይመልከቱ!

አዎ! አማራ ትዕግስትህ ከሚገባው በላይ ሆኖ ወደ ፍርሃት አድጓልና   ይህ በአለቆችህ   ልጆች በልጆችህ ላይ የተፈጸመው ዱላ ሲያንስ ነው! ለነገሩ በፎቶ ላይ ተጫዋቾቹ ሲደበደቡ ስላየን  ተቃጠልን   አንጅ በየአስር ቤቱ  ቄራ ግቢ  ውስጥ  ቁልቁል  ተዘቅዝቆ እንደሚታረድ በግ እየታረዱ ያሉትን ልጆችህን መቸ ደረስክላቸውበአጋዚ ወታደር በየቤትህ እየገባ ሲፈልግ አንተን፤ ሲፈልግ ልጅህንና  ሚስትህን ሲደበደብና ሲገድል መቸ  ! ብለህ ተነሳህ?

እናት አባቶችህ ያስረከቡህን የወንድሞቸህ  እና አባቶች አጸም ያረፈበትን ዳር ደንበር ህወሐት ትግሬ   የሚፈልገውን ያህል ለራሱ  ዘርፎ  የተረፈውን ለባዕድ ሀገር ሲሰጥ መቸ በጋራ በቃ ብለህ ተነሳህ!  ለወደፊቱ እንዳይራቡና እንዲመክኑ በየጤና ጣቢያው በክትባት ስም ህወሓት ልጆችህን   ሲያመክናቸው መቸ በቃኝ አልህ?

ወገንህን በወያኔና  በአጋሮቹ ከቀያቸው ሲባረሩ፤ አይናቸው እያየ ወደ ጉድጓድ ሰወረወሩ፤ እርጉ ሴት እህቶችህ እና  ልጆችህ   ሆድ እቃቸው   በቢለዋ  ተተርትሮ  ጽንሳቸው ሲወጣ  ከዚህ በላይ ውርደት የለም ብለህ  በጋራ መቸ ተነሳህ?  በደል መቸ በቃህ?  በባህርዳር፤ ከተማ የልጆችህ ደም እንደጎርፍ ሲፈስ ከዚህ በላይ ሌላ ግፍ ማስተናገድ አልችልም  ብለህ  ለፃነትህ መቸ  ቆርጠሀ በጋራ ተንቀሳቀስህ?

አመራ  ከእንቅልፉ በቶሎ  ተነስቶ  በአንድ ላይ ባንዳወች አይቀጡ ቅጣት እስካልቀጣ ድረስ  ሊከሰተ የሚችለው ግፍ እጅግ ዘግናኝ እንደሚሆን መጠራጠር አይኖርበትም፤ ለዚህም ኃላፈነቱ የእያንዳንዱ አማራ ተወላጅ ነው፤ ከአሁን በኃላ ነፃነት እያንዳንዱ አማራ በሚከፍለው ዋጋ የሚገኝ እንጅ ከዳር ቆሞ በመመልከት ሊገኝ የማይቻል  መሆኑን ልንረዳ ይገባል፡፡

አዎ! የዋንዛ ልጅ ጉል እንደሚባለው ሆኖ ነው እንጅ  እንዴት የቴዎድሮስን፤ የሚኒልክንና የአባ ኮስትር ባለይን ልጆች  የባንዳ ልጆች መጫወቻ ይሆኑ  ነበር?

ይህ በመቀሌ የተፈጸመው  የማነ አለብኝነትና ወራዳ ተግባር  በስፖርት ሚዳ ላይ ሁሌ እንደሚከሰተው የስፖርት ስነምግባር ጉድለት ተብሎ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ጉዳዩ  የፖለቲካ ጉዳይ ነው፤ ጉዳዩ የብሄረ ጉዳይ ነው፡፤ በጨዋታው ላይ የተነሱት ዘረኛ  ስድቦች  የሚመሰክሩት ይህን ነው፡፡ ችግሩ እንደ ማነኛውም  በስፖርት ላይ እንደሚከሰቱ ችግሮች ቢሆን ኑሮ የመቀሌው መንግስት ተጫወቾቹ መደብደባቸው ሳያንስ ይቅርታ ጠይቁ አይልም ነበር፡፡ ጉዳት የደረሰበትን የባህርዳር ከተማ ተጫዋች  የቀይ መስቀል ሰራተኞች (ልብ በሉ የቀይ መስቀል ሰረተኞች) ወርውረው በግፍ መሬት ላይ አይጥሉትም ነበር፡፡ የዘር ጉዳይ ባይሆን ኑሮ ሆስፒታል ውስጥ  ለተጎዱ የባህርዳር ከተማ  ተጫዋቾች የህክምና እርዳታ እየሰጠ የነበረውን የአማራ ብሄር ተወላጅ( አስተውሉ ይህን ተግባር   ከህክምና ስነ ምግባር ጋር)   አፍነው አይወስዱትም ነበር፡፡

ይህ ማለት ትግሬ የሆነ የህክምና ሰራተኛ ሁሉ የተጎዱ የባህርዳር እግር ኳስ ተጫዋቾችን ለመርዳት ፈቃደኛ አልነበርም፤ ከነሱ ውጭ ሌላ ሀኪም  የተጎዱ ተጫዋቾችን እንዲረዳ አይፈልጉም ነበር ማለት ነው፡፡  ታዲያ  እንዲህ ያለውን ዘርኝነት በናዘ መነጸር ካልሆነ በስተቀር በምን ሊገለጽ ይችላል? ከዚህ አሳዛኝ ክስተት ጋር አያይዘነ ስናየው ከዘረኛ አስተሳሰብ ነፃ የሆነ ትግሬስ አለ ማለት ይቻላል?

 አዎ! ለዚህ  የህወሓትና  የደጋፊዎቹ  እብሪት ዋናው ምክንያት የአማራ መተኛት ነው፡፡ስለሆነም መሳረጊያየ፤  አዎአማራ አሁንም እንደተኛህ  ነውና  ትልቅ የውርደት ካባ ይጠብቀሃል ነው፡፡

 

 

The post አዎ!  አማራ ተኝተሃልና በመቀሌ ከተማ  በልጆችህ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይገባሃል!   (አድማሱ በጋሻው) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ዶ/ር ቴዎድሮስ የኮሌራ በሽታ እንዳይታወቅ ደብቀዋል ተብለው በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ክስ ቀረበባቸው

$
0
0

ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009)

ኢትዮጵያን በመወከል ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩ ጊዜ በሃገራቸው የተከሰቱ ሶስት የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታዎች ለህዝብ እንዳይታወቅ አድርገዋል የሚል ቅሬታ በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ቀረበባቸው።

የጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት የመጨረሻ እጩ ሆነው ከቀረቡ ሶስት ተፎካካሪዎች መካከል አንዱን ለመምረጥ የሳምንት ዕድሜ በቀራቸው ጊዜ ዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የቀረበው ቅሬታ በምርጫው ሂደት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን ሊያሳድርባቸው ይችላል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።

በአሜሪካ በሚገኘው የጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ የኦ ኔል ኢንስቲትዩት ፎር ናሽናል ኤንድ ግሎባል ኸልዝ ሎው ዳይሬተር እና የብሪታኒያው ተፎካካሪ የሆኑት ሎረንስ ጎስተን የአለም ጤና ድርጅት በሃገሩ የበሽታ መከሰትን በደበቀ ተፎካካሪ የሚመራ ከሆነ ተቋሙ ተአማኒነቱን ያጣል የሚል ስጋት ስላደረባቸው ሁኔታውን ይፋ ማድረግ እንደተገደዱ ገልጸዋል።

መረጃውን ይፋ ባደረጉ ጊዜ አማካሪ የሆኗቸውን የብሪታኒያውን ተፎካካሪ ዶ/ር ዴቪድ ናባሮው በጉዳዩ እንዳላማከሯቸው እና ድርጊቱን በሃላፊነት ስሜት እንዲታወቅ ማድረጋቸውን እንደተናገሩ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አስነብቧል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው የቀረበባቸውን ቅሬታ በማስተባበል በመጨረሻ ሰዓት የብሪታኒያ የጤና ሃላፊዎች ከፍተውታል ያሉትን የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዳሳሰባቸው ምላሾን ሰጥተዋል።

የብሪታኒያው ተፎካካሪ ዶ/ር ናባሮው  ቅሬታው በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ እንዲቀርብ የሰጡት ትዕዛዝ አለመኖሩን ለጋዜጣው አስረድተዋል።

የአለም ጤና ባለስልጣናት አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የኮሌራ በሽታ እንዳይታወቅ መደረጉን በአግባቡ የሚያውቁት ጉዳይ ነው ሲሉ ተፎካካሪው አክለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎች በመሞት ላይ መሆናቸውን የተባባሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሲገልፅ ቆይቷል።

የፌዴራል እና የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት ወረርሽኙ በሰው ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ቢያረጋግጡም ምን ያህል ሰው በበሽታው እንደሞተ የሰጡት ዝርዝር መረጃ የለም። ባለፈው አመት ክረምት ወቅት በአዲስ አበባ ተመሳሳይ መልክ ተከስቶ የነበረው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ በሰው ዘንድ የሞት ጉዳትን ቢያስከትልም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጉዳቱ ለህዝብ መግለፅ ድንጋጤን ይፈጥራል በማለት መረጃው እንዳይሰራጭ አድርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ቅሬታን ያቀረቡት የጤና ባለሙያው ሎረንስ ጎስቲን ኢትዮጵያ የበሽታ ወረርሽኝን በመደበቅ ያላት የቆየ ታሪክ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው ሲሉ አክለው አስረድተዋል።

እነዚሁ የበሽታ ስርጭቶች በዶ/ር ቴዎድሮስ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩ ጊዜ ሁሉ የተከሰቱና የተሸሸጉ ናቸው በማለት የጤና ባለሙያው ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

ለሰባት አመታት ያህል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በተለያዩ አመታት ሶስት ጊዜ ተከስተው የነበሩ የአጣዳፊና ተቅማት በሽታዎች ኮሌራ ሊባሉ የማይችሉ እንደነበሩ ለጋዜጣው በሰጡት ምላሽ ተናግረዋል።

ይሁንና የአለም ጤና ድርጅት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የተከሰቱ በሽታዎችን ሁኔታ በአግባቡ እንደማይገልፁ በግል ቅሬታን እንዳቀረቡም ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል።

የአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በሽታ ከሁለት ሳምንት በላይ መሻሻልን ካላሳየ በሽታው ወደ ኮሌራ የመለወጥ ሂደት እንዳለው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ዘጋርዲያን እና ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣዎች ስማቸው ያልተገለፀ ባለስልጣናት የእርዳታ ድርጅቶች ኮሌራ የሚለውን ቃል እና የታማሚዎችን ቁጥር ከመግለፅ እንዲቆጠቡ ግፊት ያደርጉ እንደነበር መዘገባቸውንም ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አውስቷል።

ይሁንና ከኢትዮጵያ ውጭ በተካሄደ የላብራቶሪ ምርመራ በሽታው የኮሌራ ባክቴሪያ ተገኝቶበት እንደነበር ጋዜጣው ዘግቧል። የአለም ጤና ድርጅት አባል ሃገራቱ በሽታዎች ሲከሰቱ ሁኔታዎችን በግልፅ ይፋ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ መመሪያና ደንብ ያለው ሲሆን፣ አባል ሃገራት የበሽታ ስርጭትን በአግባቡ ሳያውቁ ሲቀር በድርጅቱ ተአማኒነት እንደማያገኙ ይነገራል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተፎካካሪያቸው የዶ/ር ናባሮው ደጋፊዎች የቅኝ ገዢነት አስተሳሰብ ያላቸውና የታዳጊ ሃገራት ተወካይን ዋጋ የማሳጣት አላማ ያላቸው ናቸው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ፣ የብሪታኒያና፣ የፓኪስታን ተፎካካሪዎች የመጨረሻ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን፣ የጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት በቀጣዩ ሳምንት ምርጫን ያካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

The post ዶ/ር ቴዎድሮስ የኮሌራ በሽታ እንዳይታወቅ ደብቀዋል ተብለው በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ክስ ቀረበባቸው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ክሱን እንዲከላከል ብይን ሰጠ

$
0
0

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ

ፍርድ ቤቱ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ክሱን እንዲከላከል ብይን ሰጠ፤አብርሃ ደስታ ታስሮ እንዲቀርብ ተባለ!!!
(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
በእነ ዘላለም ወርቅአለማሁ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው በነፃ የተሰናበቱት አቶ ዳንኤል ሽበሺ እንዲከላከሉ ተበየነባቸው፡፡የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በነፃ እንዲለቀቁ የሰጠውን ብይን በመቃወም የፌደራል ዓቃቢ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገቡን በድጋሜ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት መምራቱ ይታወቃል፡፡ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ዳንኤል ሺበሽ ክሱን እንዲከላከል ጉዳዩንም ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡በዚሁ መዝገብ የተከሰሰው አቶ አብረሃ ደስታ በዛሬው ቀጠሮ ባለመቅረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ለግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም ታስሮ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ ለብይን ተቀጥሮ የነበረው አራት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮች ማለትም አቶ በቀለ ገርባ፣አቶ ደጀኔ ጣፋ፣አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ አያኖ ጉርሜሳን ጨምሮ 22 ተከሳሾች መዝገብ በድጋሜ ተቀጠረ፡፡ብይኑ ያልተሰጠው ያልተያያዘ መረጃ በመኖሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጧል፡፡መረጃውን አያይዞ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም በድጋሜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

The post የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ክሱን እንዲከላከል ብይን ሰጠ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live