Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን “ልዩ ጥቅም ” ለመወሰን የወጣ ዓዋጅ፤ ቅንነት ያዘለ የችግሮች መፍቻ ወይስ በማር የተለወሰ መርዝ?

$
0
0

ባይሳ  ዋቅ ወያ   (ጄኔቫ)
ሰኔ 30 ቀን 2017 /

ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ባላፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግሥት ባገሪቷ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49(5) የተደነገገውን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ ብሎ ያወጣው ረቂቅ ዓዋጅ ነው። በኔ ግምት የዓዋጁ ከሁለት ዓስርተ ዓመት መዘግየት በኋላም ቢሆን ዛሬ ይፋ መውጣቱ አዎንታዊ ገጽታ ያለው ቢመስልም መንግሥት በቀና መንፈስ ያደረገው ሳይሆን ባገሪቷ ውስጥ በተከሰተውና በመከሰት ላይ ባለው የፖሊቲካ ቀውስ ተወጥሮ ያደረገው ይመስለኛል። ከዚያም በላይ ዓዋጁ የተደነገገው በሕገ መንግሥቱ ለኦሮሚያ  ክልል ቃል የተገባለትን ጥቅም ለማስጠበቅና የታለመለትን ግብ ለመምታት ሳይሆን የኦሮምያን ክልል ለይቶ የጠቀመ እያስመሰለ በሕዝቦች መካከል መጠራጠርንና ብሎም መከፋፈልን ለማንሰራፋት የተወጠነ በማር የተለወሰ መርዝ ነው ብዬ ብል ከእውነት ያልራቅሁ መሆኔን እርግጠኛ ነኝ። አባባሌን በተጨባጭ ማስረጃ ለማስደገፍ እስቲ የረቂቅ ዓዋጁን ይዘት በጥልቁ እንመርምር። ከዚያ በፊት ግን እንደሁ በቅንፍ ውስጥ ዝቅ ብዬ ለማቀርባቸው አስተያየቶች መሰረት ይሆናሉ ብዬ የማስባቸውን ጥያቄዎች ለማቅረብ እሻለሁ።

 

ያኔ ሕገ መንግሥቱ ሲደነገግ ”የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም“ የተባለው ዓረፍተ ነገር ሲታከልበት በኦሮሚያ ክልልና በፊንፊኔ መካከል ያለው ሕጋዊ ግንኙነት በጥልቅ ውይይት ተደርጎበት ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ወይ? ከሆነስ ያኔ የተደረሰበት ድምዳሜ ፊንፊኔ የኦሮሚያ ከልል ናት ወይስ ራሷን የቻለች ልዩ ግዛት ነበር የሚለው? ለኦሮሚያ ክልል “ልዩ ጥቅም” የተባለው፤ ፊንፊኔ “በኦሮሚያ ክልል መሃል የምትገኝ” እና በኦሮሚያ ክልል ስለተከበበች ተብሎ ነው ወይስ “የኦሮሚያ ከልል አካል ስለሆነች”? ሕገ መንግሥቱስ ሲደነገግ በኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናትና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ግልጽ የሆነና ጣምራ ትርጉም የሌለው አቋም ተወስዶ ነበር ወይ? እነዚህን ጥያቄዎች ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም። ረቂቅ ዓዋጁን አስመልክቶ አሁን በኢትዮጵያውያን መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ውይይት አይሉት መናቆር፤  ሁለት ዱዳና ደንቆሮ የሆኑ ግለሰቦች የሚያወሩትን ያህል በምንም ተዓምር መግባባት ሊደረስበት የማይቻልበት ሁኔታ ላይ የደረስን ስለመሰለኝ ነው።

 

የረቂቅ ዓዋጁ ይዘት፤

 

ረቂቅ ዓዋጁ ገና ከመጀመርያው በአንቀጽ 2 (4) በግልጽ ያስቀመጠው የአዲስ አበባን “በኦሮሚያ ክልል መሃል” መገኘት ነው። ይህ እንግዲህ እያንዳንዱ አንባቢ እንደፈለገው እንዲተረጉመው ተብሎ መሰለኝ። ኦሮሞዎች ፊንፊኔ የኦሮሚያ አካል ናት ሲሉ መንግሥት ደግሞ፤ አይ አይደለም፤ ፊንፊኔ በኦሮሚያ ክልል መሃል የምትገኝ ማለትም በኦሮሚያ ክልል የተከበበች እንጂ የኦሮሚያ ክልል አካል አይደለችም የሚል መሰለኝ። ዓዋጁ “የኦሮሚያን ክልልን ልዩ ጥቅም ለመወሰን” የወጣ ነው ይልና ይጠበቃሉ የተባሉትን “ልዩ ጥቅሞች” ሲደረድር የትምህርት የጤና የባህል ቋንቋና ሥነጥበብ አገልግሎቶች በማለት፤ ይጠቅሳል። በኢሕአዴግ አባባል የተዘረዘሩቱ “ልዩ ጥቅሞች” የተሰጡት የኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ላይ ባለው ሕጋዊ መብት ላይ ተመሥርቶ ሳይሆን መንግሥት በበጎ ፈቃዱ ለክልሉ የቸረው ነው ማለት ነው። ከሕግ ትርጓሜ አንጻር ካየነው ግን እነዚህ የተወሱት ”ልዩ ጥቅሞች“ ፊንፊኔ ከተማ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ዜጋ በእኩልነት ሊያገኛቸው የሚገባ የሰው ልጆች መብት እንጂ መንግሥት ለይቶ ፊንፊኔ ውስጥ ለሚኖሩ  የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ብቻ የሚሰጥ የችሮታ  ዕቃ አይደሉም። እንደሁ መንግሥት በማን አለብኝነት ወይም ”በኃዜኔታ“ ከፊንፊኔ ነዋሪዎች መሃል ለይቶ ሃያ በመቶ የሆኑትን ኦሮሞዎችን ብቻ ልዩ ተጠቃሚ አደርጋቸዋለሁ ካለ ደግሞ፤ ድርጊቱ እውነትም ልዩ ጥቅም ወይም ፈረንጆች እንደሚሉት (preferential treatment) ነው እንጂ የመብት ጉዳይ አይደለም ማለት ነው። “ልዩ መብት” እስካልሆነ  ድረስ ደግሞ በፊንፊኔ የሚኖሩ ኦሮሞች እንደማንኛውም የከተማው ነዋሪዎች፤ ለምሳሌ እንደ ሕንድ፤ የአርመን እና የጀርመን ኮሙኒቲ የኦሮምኛ ትምህርት ቤት፤ ፊልም ቤት፤ ቤተ መዘክር ወይም ቴያትር ቤት ከፍተው እኩል ሊደሰቱ ይችላሉ ማለት ነው። ለዚህ ደግሞ “ልዩ ጥቅምን” የሚደነግግ የተለየ ዓዋጅ አያስፈልግም።

 

መደረግ ያለበት፤

 

በመጀመርያ ደረጃ አሁን በመካሄድ ላይ ላለው አለመግባባት መንስዔው በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተካተተው አንቀጽ 49(5) ግልጽ ሆኖ ያለመቀመጡ ጉዳይ በመሆኑ መንግሥት ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አካላት ጋር በመሆን የማያወላውልና  ቀጥተኛ ትርጉም ባለው አንቀጽ እንዲተካ መደረግ አለበት። ኦሮሞዎች፤ ያኔም አሁንም የሚፈልጉት ፊንፊኔ የኦሮሞዎች ርስት መሆኑ ታውቆ ሕጋዊ ባለቤትነታቸው እንዲረጋግጥላቸው ስለሆነ ይህ የባለቤትነት መብታቸው በሚስተካከለው አዲስ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49(5) በግልጽ መቀመጥ አለበት። ይህ በመጀመርያ ደረጃ መመለስ ያለበት ቁልፍ የሆነ የባለቤትነት ጥያቄ ነው። ለዚህ ቁልፍ ጥያቄ መልስ ከተገኘ ደግሞ የተቀረው ሁሉ በቀላሉ ዕልባት ያገኛል። አለበለዚያ ግን የፌዴራል መንግሥቱ ያለሕጋዊ ባለቤቶቹ በጎ ፈቃድና ስምምነት ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነ መንገድ የከተመበትን መሬት ራሱን እንደ ሕጋዊ ባለቤት ቆጥሮ የልዩ ጥቅሞች “ሰጪ” በመሆን የመሬቱን ሕጋዊ ባለቤቶችን ማለትም ኦሮሞዎችን ደግሞ “ተቀባይ” ለማድረግ መሞከር የሌባ ዓይነ ደረቅ እንደሚሉት ዓይነት ከመሆን የተለየ ትርጉም አይኖረውም።

ክልሎች ሁሉ በየራሳቸው ምርጫ በክልላቸው ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች መርጠው የየራሳቸውን ዋና ከተሞች መሥርተዋል፤ የኦሮሚያ አስተዳደርም በክልሉ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች ሁሉ ፊንፊኔን መርጦ ዋና ከተማው አርጎት ባገሪቷም ሕገ መንግሥት አስጸድቆታል። የፈዴራል መንግሥቱ ደግሞ ባገሪቷ ውስጥ ከክልሎች አስተዳደር ነጻ የሆነ በፈዴራሉ መንግሥት የሚተዳደር ትርፍ መሬት ባለመኖሩ በተለምዶ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ተብላ የታወቀችውን አዲስ አበባን ያለምንም ቅድመ ድርድር ዋና መቀመጫው አርጎታል። እንደ ፌደራል መንግሥት መቀመጫውን ቢፈልግ ሃዋሳ ወይም ሁመራ ወይም ጂማ ማረግ ይችል ነበር። ግን አስፈላጊ አልነበረም። ለወደፊትም ደግሞ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አዲስ አበባን የንግድ መናሀርያ አርጎ የኢትዮጵያን ዋና ከተማ፤ ለምሳሌ የናይጄሪያና የፓኪስታን መንግሥታት እንዳደረጉት፤ አመቺ ወደሆነ ሌላ ከተማ ወይም ቦታ ሊያዞር ይችላል። ይህ ደግሞ ጉዳዩ በሚመመለከታቸው የክልሉ አስተዳዳሪዎች መልካም ፈቃድና ውሳኔ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።

 

ወደድንም ጠላንም ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መዋቅር ፌዴራላዊ ነው። የድኅረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የግዛትና አስተዳደር ሁኔታ ደግሞ በሕዝቦቿ እኩል ተሳትፎና ፈቃድ የሚወሰን ስለሆነ ዛሬ ግምታዊ የሆነ እሰጥ አገባ መጀመር ያለብን አይመስለኝም። እስከዚያው ድረስ ግን ኦሮሚያ ክልል እንደሆነች ትቀራለች፤ ፊንፊኔም የኦሮሚያ አካል እንደሆነች ትቀጥላለች ማለት ነው። ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል አካል ሆነች ማለት ግን በኗሪዎቿ ላይ አንዳችም የግለሰብም ሆነ የቡድን የመብት ጥሰት አያስከትልም። የተለያዩ ብሄረ ሰብ አባላት ቋንቋቸውንና ባህላቸውን ያለምንም ተጽንኦና አድልዖ የማሳደግና የማስፋፋት መብታቸው ይጠበቃል ማለት ነው፤ ዜጎች በሕጉ መሰረት የሚወሰንባቸውን ግብር ይከፍላሉ፤ በሙያቸው ከማንኛውም ዜጋ እኩል ያለምንም መድልዖ ሥራ ያገኛሉ፤ ፊንፊኔ ማንም ከማንም የተለየ ወይም የተሻለ “ልዩ ጥቅም” የማያገኝባትና ሁሉንም እኩል የምታስተናግድ የኦሮሚያም የኢትዮጵያም ዋና ከተማ ሆና ትቀጥላለች ማለት ነው።

 

ዛሬ በአስቸኳይ መፈፀም ያለበት አንድ ዓብይ ጉዳይ አለ። የፊንፊኔ ከተማ ወሰን በአግባቡ ሳይከለል በልማት ሰበብ በመስፋፋቷ በዙሪያዋ ለሚኖሩት ብዙ ኦሮሞዎች ከመሬታቸው መፈናቀልና ለድኅነት መዳረግ ምክንያት በመሆኑ የከተማው ድንበር በግልጽና በማያሻማ መንገድ በአስቸኳይ መከለል አለበት። ከተማው ከድንበሩ ውጭ ተፈጥሮአዊ ዕድገትን ተከትሎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በሰፋ ቁጥር ላስከትለው የሕዝቦች መፈናቀልም ተገቢው ካሳ መክፈል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም እንዳይደገም መንግሥት ዛሬውኑ የማያወላውል እርምጃ መወሰድ አለበት። የፊንፊኔን ወደቀሪው የኦሮሚያ ክፍል መስፋፋት ማንም ሊያቆመው የማይችል የከተሞች ዕድገት ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው። ሕጋዊና ተፈጥሮአዊ የማይሆነው ግን በልማት ሰበብ የዜጎች መሠረታዊ የሰው ልጆች መብት ሲደፈር ነው።

 

በመጨረሻ ለማሳሰብ የምወደው ግን፤

 

ሀ) ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልልና አካል ነች ማለት ሕጋዊ ባለቤትነትን ለማጽደቅ ታስቦ እንጂ ዛሬ የከተማዋ ነዋሪ በሆኑት የተለያዩ ብሄርና ብሄረሰቦች ላይ አንዳችም የጊዜያዊም ሆነ ቋሚ የአኗኗር ወይም የአሰራር ለውጥ ለማስከተል አይደለም። አንድ ብቸኛ ለውጥ ቢኖር የከተማዋ አስተዳደር በፌዴራል መንግሥት መሆኑ ቀርቶ በኦሮሚያ ክልል ሥር ይሆናል ማለት ነው። ይህ ደግሞ በኗሪው ሕዝብ ሥራና ሕይወት ላይ አንዳችም ለውጥ አያወጣም። የፊንፊኔም ኗሪ ሕዝብ ማንነትም (demography) በሰው ሠራሽ ውሳኔ ሳይዛባ የተፈጥሮ ሂደትና ዕድገት ተከትሎ ጉዞውን ይቀጥላል ማለት ነው።

 

ለ) ኢሕአዴግ ዛሬ ሕገ መንግሥቱ ከጸደቀ ከሃያ ዓመት በኋላ ይህንን “ልዩ ጥቅም” የሚለውን ሸፋፋ ሰበብ ከተቆለፈበት መጋዘን አውጥቶ ለኦሮሞ ሕዝብ የተቆረቆረ አስመስሎ ለገበያ ማቅረብ፤ እውነትም የተዛባውን ፍትህና የአላግባብ ባለቤትነትን ዘረፋ ለማስተካከል ብሎ ሳይሆን “ጭር ሲል አልወድም” እንዳለችዋ ዘፋኝ እህታችን ሕዝቡን ለማመስና ብሎም እርስ በርስ ለማጋጨት ታስቦ ስለሆነ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለይም በዲያስፖራ ያሉት ዜጎች ይህንኑ በቅጡ አስተውለው ካላስፈላጊ የጥላቻ ውይይትና አመለካከት እንዲቆጠቡ አደራ እላለሁ። አመሰግናለሁ።

 

 

*******

 

ባይሳ  ዋቅ ወያ 

(ጄኔቫ)

ሰኔ 30 ቀን 2017 /

wakwoya2016@gmail.com

 


አጼ ምኒልክ በሕይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን ድንቅ ተግባራት በደማቅ ብእርና ብራና የተከተቡ ናቸው!

$
0
0

 

አጼ ምኒል

1835 ዓ.ም. ————-ወፍጮ
1882 ዓ.ም. ————-ስልክ
1886 ዓ.ም. ————ፖስታ
1886 ዓ.ም. ————ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ————ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ———-የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ———–ጫማ
1887 ዓ.ም. ————–ድር
1887 ዓ.ም. ————-የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. ———-የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ———-ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. —————ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ————-ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ————–የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ————-ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ———–ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ————-ባቡር
1893 ዓ.ም. ————-ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ————-መንገድ
1897 ዓ.ም. —————ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. —————ባንክ
1898 ዓ.ም. ————-ሆቴል
1898 ዓ.ም. ————-ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ————–ላስቲክ
1899 ዓ.ም. ————አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ———–የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ————-ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ————አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ———–የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. ———–ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. ———የመድነኒት መሸጫ ሱቅ
አጼ ምኒልክ የኢትዮጵያ መሐንዲስ!
ክብር ለቀደሙት አባቶቻችን!

 


Fekrou Kidane

 

 አርባ አመት ቢቀመጥ በደል አያረጅም【 በቶማስ ሰብሰቤ】

$
0
0
የኢህአዴግ ጭቆና እና ታላላቅ የአለም የጭቆና ታሪክ መካከል የመጠንና የአተገባበር ልዮነት እንጂ ጭቆናው ያው ነው።የጭቆና ደግ የለውም።ለተጨቋኝ ህዝብ ሁሉም አይነት ጭቆና ልብ ሰባሪ ነው። ሰባቱ የአውሮፓ ሀገራት አፍሪካን” በቀኝ ግዛት የበላይነት በትር “ሲቀራመቱ በባርነት እጅ የወደቁትን ሚሊየን አፍሪካዊያን የደረሰባቸውን ጭቆና ዛሬም ማንም አይረሳውም።ነጭ በጥቁር በቀለም ልዮነት ብቻ የሚያሳየው የዘረኝነት በደልና ጥላቻ መቼም በመላው ጥቁር ሰው ልብ ይኖራል ፤ አዶልፍ ሂትለርን የሚረሳው እስራኤላው ከቶ የት ታገኝ ይሆን? ጭቆና መቼም በሰው ልጅ ታሪክ ፣ ህሊና ፣ የዕለት ተዕለት ህይወት በቁጭት የሚታወስ ነው።ጨቋኝ ቢረሳም ተጨቋኝ አይረሳም ፤ ተጨቋኝ ይቅርታ ካደረገልህን እንኳን ድጋሚ እሱ ላይ የደረሰው በሌለው ትውልዱ እንዳይመጣ ፍፁም ማሳመኛና ተግባር ይሻል።
ጭቆና በሰው ልጆች መካከል በብዙ ይመዘናል።ለምሳሌ የሴቶች ተሰሚነት ፣እኩልነትና ተጠቃሚነት የሌለበት አንድ ማህበረሰብ ውስጥ የሴቶች ጭቆና አለ ።አካል ጉዳተኞችን ማገለል ፣እንደ ዜጋ አለመቁጠርና መብታቸውን መንፈግ አጭቆና ነው።በየትኛውም ማህበረሰብ በዘር ፣በፆታ ፣በቋንቋና በአሰተሳሰቡ እኩልነቱ ካልተረጋጋጠለት ጭቆና አለ።እኩልነት የሌለበት ህብረተሰብ ውስጥ ጭቆና በሰፊው ይኖራል።ባለፍት 26 አመታት ያየነው በእኩልነት መጋረጃ ውስጥ ያለ ጭቆና ነው።
የኢህአዴግ በእኩልነት መጋረጃ ውስጥ የያዘው ጭቆና
1/በእኩልነት መጋረጃ ውስጥ ያለ የአንባገነንነት ጭቆና
አንባገነነት አያዳምጥም ፤ አንባገነነት የሚያስተዳድረው ህዝብ ስሜት ሳይሆን ስለ ራሱ ሟች ነው ፤ እኔ ሁሉን አውቃለው ይልሃል ፣ ፈሪ ነው ፣ የህዝብ አንድነት ያስፈራዋል ፣ እናተ ከማለት እኔ ያበዛል ፣ ጡራራም ጉረኛ ነው ፣ ሽንፈቱን የማያምን ፣ለእሱ ያልሆነ ህግ በአንድ ቀን ዶግ አመድ የሚያደርግ ፣ከሰው ወርቅ የራሱ መዳብ ትልቅ አርጎ የሚጨፍር በርጣቃ ነው።ኢህአዴግ ስለ ራሱ ብቻ የሚያወራ ፣ ህዝብን የማያደምጥ ፣እኔ አውቅልሃለው የሚል ፣ በአንድ ጤና ጣቢያ የሆስፒታል የሚያቅራራ ፣ሁሌም አሸናፊነኝ የሚል የሆቼሚኒ  ፣ የፓሻ(Ismail Enver Pasha) ፣ የLeopold II ፣ የMao Zedong የአንባገነን ዘር ነው።አንባገነን ሁሌም እሺ በሉኝ ይወዳል።እምቢ ያለ ጣለቱ ነው።ለእሱ የትኛውም ህግ ተገዢ ያደርግሃል።ኢህአዴግ ላወጣው ህግ ካልተገዛህ የሚያደርግ እንደዛው ነው።እሱ ያለው ከተቃወምክ ዲሞክራሲያው ጭቆና ፣ዲሞክራሲያዊ መገደል ፣ዲሞክራሲያዊ ሰበዓዊ መብት ረገጣ ያሳይሃል።
A society is under the thumb of a cruel dictator. Anyone who disagrees with the policies of the dictator can be killed for sharing his opinion and voicing the disagreement. The people of the society who live under the dictator are oppressed. በየትኛውም የኑረ ደረጃ ፣ ቦታ ፣ሰራ ፣ህይወትና መንገድ ሆነህ መንግስ ያወጣው የትኛው ነገር ላይ ልዮነት ካሳየት በስልታው መንገድ የጭቆና ገመድ ውስጥ ትገባለህ።ከዚህ አልፈህ ደሞ ጠናካራ የሰው መብት ጠያቂ ፣ የፍትህ ፣የእኩልነትና የስበዓዊ መብቶች ላይ ፊት ለፊት ከቆምክበት ያኔ አሟሟቴን አሳምርልኝ ማለት ብቻ ነው።
2/በእኩልነት መጋረጃ ውስጥ ያለ የአስተሳሰብ ልዮነት የማያስተናግድ ጭቆና
የአሰተሳሰብ ልዪነት ለጨቋኝ ሞቱ ነው።በጭቆና ስርዓት አንድ ወጥ የሆነ አሰሰተሳሰብ ባይፈለግም የትኛውም አስተሳሰብ ግን ደጋፊ መሆን አለበት።በየትኛውም መንገድ ተናገር የመጨረሻ መልዕክትህ መንግስት የሚያንቆለጳጵስ መሆን ግድ ይለዋል።የመንግስት ደካማ ጎን ስትናገር አስተማሪና ወደ ፊት እንዲታረም አሳይተህ እንድታፈልፍ ነው የሚፈለገው።የትኛው የህዝብ ቅሬታ ፣የህዝብ ልዮነት ፣የህዝብ በደል በየትኛውም መንገድ ስታሰራጭ ችግሩን አሳይተህ በቀጣይ መንግስት እንደሚፈታው የሚያሳይ ተሰፋ መስጠት እንጂ የህዝቡን ሰሜት ተነትናለው ብትል ያኔ በአሸባሪ ስም በቲቢ መስኮት የምታውቃቸው ከአልሸባብና አልቃይዳ ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደነበረህ ይተነትንልሃል።አሉታዊ ዜና በአንባገነን ስርዓት የለም።መንግስት የሚተች የሃሳብ ቢኖርህም በልማታዊ መንገድ መግለፅ አለብህ።ለዚህም ነው ኢህአዴግ ሚዲያን እንደ ልማት መሳሪያ አድርጎት ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው።የሀሳብ ልዮነት በልማታውነት ፤የሀሳብ ልየነት በኢህአዴጋዊነት አራት ነጥብ።
ሚዲያ የህዝብ ነው እያለህ በስልታዊ መንገድ የእሱ ባሪያ ያደርግሃል።በእኛ ሀገር ያሉ ሚዲያዎች የማን ናቸው? የግል የሚባሉት በመንግስት ባለስልጣን ፣ድርጅትና ደጋፊ ሰዎች የሚዘውሩ አልሸሹም ዞር አሉ አይደል እንዴ? ልክ ምርጥ ምሳ እንደ ጋበዘ ሰው ለመንግስት ምስጋና የሚቸር ሚደያ የፈጠረው ኢህአዴግ የሃሳብ ልዮነት መቀበል ሞቱ ስለሆነ ነው።በዚህም ነፃ ፕሬስን አፈር አብልቶታል።ህዝቡም መናገር ፣ መደራጀት ፣ሰላማዊ ስልፍ መውጣት አይችልም።
“A society carefully controls the freedom of speech of all people. The Internet is not accessible to the public, certain books are banned and the media works for the state and is permitted to write only the positive news that the state allows to be printed. This is an example of a society where the people who are under the control of the authority are oppressed.የሃሳብ ልዮነት ያላቸው ጠንካራ ሚዲያ የሚዘጋ ፣ ጋዜጠኛ የሚያስር ፣የመብት ተሟጋችና ተቃዋሚ ፓርቲ የሚያስር ከዚህ በላይ የጨቋኝ ማሳያ አለ እንዴ? ተቃዋሚውም የሚያባር  ደጋፊውን የሚያጎርስ ፤ ተቺውን የሚቀብር አሸርጋጁን  የሚድር ከህውሃት ኢህአዴግ በላይ ያለ መንግስት የለም።
3/በእኩልነት መጋረጃ ወስጥ ያለ ኢ_ፍትሃዊነት
“A society exists where people of a certain race are denied opportunities and equality” ይህ በሁልም በእየቤቱ ያለ ሀቅ ነው።ፍርህ ባለፍት 26 አመታት መጫወቻ ነው የሆነው።ከአሁን ጊዜ  ፍትህ የደርግ ቀይ ሽብር ዘመቻ የሚመርጥ ብዙ ነው ፤ ከአሁን ጊዜ ፍትህ ጋር የሚነፃፀር አፓርታይድ ነው።በዘርና በቀለም ለመጫረስ ያበቃቸው የፍትህ ጥያቄ ነው።እኛም ለሀገራችን ስጋቱ ይሄ ነው።ህዝብን በብሄር ፣በዘርና በቋንቋ መከፋፈሉ ብቻ ሳይሆን ጣጣው ሰውን ከከፋፈሉ በኃላ በእኩል አይን ያለማየት ነው።ከእኛ የዘር ፖለቲካን የከፋ ጨቋኝ የሚያደርገው ፍትህ በህዝቦች መካከል ያለመፍጠር ነው።
ዛሬም ትልቁ ጥያቄ ይሄ ነው።የአንድ ብሄር የበላይነት ማረጋገጥ የሌሎችን ተጨቋኝነት ማረጋገጥ ነው ፣ አንድ ብሄር ሀገር ሙሉ መቆጣጠር ስልታዊ ብቻ ሳይሆን ሌላው ህዝብ እንደ እንስሳ መቁጠር ነው።ዛሬ ሀጎስ ቢሮ ሲገባና ኡባግ ሲገባ ልዪነት የለውም? ዛሬ ሀብታሙ አንድ ቋንቋ የሚያወራ ደሃው አድማጭ አልሆነም? ስልጣኑስ የማን ነው? ተራው ሰው ወታደር አዛዡ ሃጎስ አይደል እንዴ!  ኢህአዴግ ሚኒስትር ህግ አውጪው ህውሃት እንደሆነ እናውቀዋለን? ትልቅና ትንሽ ብሄር የለም ስርታችዋል ፣ተደማጭና የተገለለ የለም እንዴ? ፍትህ ያጣ ደሃ ፣ፍትህ ያጣ ብሄር ፣ፍትህ ያጣ ባንድራ ፣ፍትህ ያጣ ነፃነት ፣ፍትህ ያጣ ተቃዋሚ ፣ፍትህ ያጣ ገበሬ ……ሀገር ምድሩ እረ በህግ! እያለ ሰሚ የለው።ለዚህ ነው ዛሬ እየጨቆንከው ሲጠራህ የማትሰማቅ ከሆነ፤ ዛሬ በጭቆና በትር የምትገርፈው ምን ያደርጋል ኢህአዴግዮ” አርባ አመት ቢቀመጥ በደል አያረጅም”.

ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሐገራቸዉ ከመመለስ ይልቅ «የመጣዉን ለመጋፈጥ» እንዲወስኑ ያስገደዳቸዉ የመጓጓዣ ዋጋ ብቻ አይደለም

$
0
0

ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያዉያን

 ከተመለሱት የሚያገኙት መረጃ ከሁለቱ መጥፎ፤ «የተሻለ» የሚሉትን  መጥፎ እንዲመርጡ ሳያስገድዳቸዉ አልቀረም።በዚሕ መሐል ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መጠቃት፤ አንዳዶቹ መደፈር፤ ሐብት ንብረታቸዉ መዘረፉንም ተናግረዋል።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ከሐገሩ እንዲወጡ የደነገባበቸዉ ኢትዮጵያዉን አሁንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ እያቅማሙ መሆኑ ተነገረ። ጉዳዩን የሚከታተሉ ጋዜጠኛና የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ መሪዎች እንደሚሉት «ሕገ-ወጥ» የተባሉት ኢትዮጵያዉያን ወደ ሐገራቸዉ እንዲመለሱ የተሰጣቸዉ ተጨማሪ ቀነ-ገደብ ቢጋመስም አብዛኞቹ የመመለስ ፍላጎት ያላቸዉ አይመስሉም። ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መጠቃት፤ መደፈርና መዘረፋቸዉን ይናገራሉ። ነጋሽ መሐመድ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
አንዳንድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ያለ ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ እስከ አራት መቶ ሺሕ ይደርሳል።

Saudi Arabien Äthiopien Rückkehrer (DW/S. Shiberu)

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን ጨምሮ «ሕገ-ወጥ» የሚላቸዉ የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ በሰጠዉ የሰወስት ወር የጊዜ ገደብ ሐገሩ የገባዉ ኢትዮጵያዊ ቁጥር ግን መቶ ሺሕ እንኳን አይሞላም።
የመመለሻዉ ጊዜ ባንድ ወር ሲራዘም ደግሞ፤ ጂዳ የሚኖረዉ ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ እንደሚለዉö የሚመለስ ሰዉ ጠፋ። ከብዙዎቹ ምክንያቶች አንዱ መመለስ የፈለገዉ ኢትዮጵያዊ መንገላታቱ ነዉ። ሁለተኛዉ የአዉሮፕላን ትኬት ዋጋ መናር።

በሪያድ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ሊቀመንበር አቶ ሻዉል ጌታሁን «እንግልት» መባሉን አይቀበሉትም። የቲኬቱን ዋጋ መናር ግን አላስተባበሉም።

ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሐገራቸዉ ከመመለስ ይልቅ «የመጣዉን ለመጋፈጥ» እንዲወስኑ ያስገደዳቸዉ የመጓጓዣ ዋጋ ብቻ አይደለም። ከተመለሱት የሚያገኙት መረጃ ከሁለቱ መጥፎ፤ «የተሻለ» የሚሉትን

Saudi-Arabien Abschiebung illegaler äthiopischer Arbeitsmigranten (DW/S. Shibru)

መጥፎ እንዲመርጡ ሳያስገድዳቸዉ አልቀረም።በዚሕ መሐል ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መጠቃት፤ አንዳዶቹ መደፈር፤ ሐብት ንብረታቸዉ መዘረፉንም ተናግረዋል። የሪያዱ የኢትዮጵያዉያን ማሕበረሰብ መሪ አቶ ሻዉል ጌታሁን አቤቱታዉ ደርሷቸዋል።

ጋዜጠኛ ነብዩም መረጃ አለዉ።በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስላ፤ አዲስ አበባ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ዛሬ ቀኑን ሙሉ ደዉለን ነበር። ካንድ ሰዉ በስተቀር ሥልኩን የመለሰ አንኳን አልነበረም። የመለሱት «ስብሰባ ላይነኝ አሉ» በቃ።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

እምዬ ምኒልክ የኢትዮጵያ መሐንዲስ!

$
0
0

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡ Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Join 462 other subscribers

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live