Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

አቡነ ቀውስጦስ: መ/ር ዘመድኩንን ወቀሱ፣ አወደሱም፤ በ‘መቀባባቱ’ ጉዳይ ተቃውሞውን ይጋራሉ፤ ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ መሰከሩ፤ በኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ አቋማቸውን አብራሩ

$
0
0
  • አባ ተክለ ሃይማኖት፥ ያለተወዳዳሪ መቅረባቸውን በመቃወም፣ የሲኖዶሱ ሕግ እንዳይፈርስ አሳስቤያለሁ፤
  • በክልሉ መንግሥት ማሳሰቢያ ከመረጥን፥ ቤተ ክርስቲያንን ይጎዳል፤ ቅ/ሲኖዶስም እንደሌለ ያስቆጥራል፤
  • “አስመራጩ ክፍል፥ ማሳሰቢያውን አልተቀበለውም፤ ተሰርዟል” የሚል መልስ ሲሰጠኝ፣ ዝም ብያለሁ፤
  • ማሳሰቢያዬ፥ ቤተ ክርስቲያኔን መጠበቅ እንጂ መካድ አይደለም፤ የሚያስመሰግነኝ እንጂ አያስተቸኝም፡፡

******  

  • በዶ/ር አባ ኃ/ማርያም ምርጫ፥ እንዳንሳሳት ወይም ጥራት ያላቸውን እንዳናጣ የመጠንቀቅ አቋም ነበረኝ፤
  • በሰዓሊተ ምሕረቱ ጉዳይ፣ ባለሥልጣናቱን ትቶ በዶ/ሩ ላይ ያነጣጠረው ተቃውሞ፣ ግራ አጋብቶኝ ነበር፤
  • በሃይማኖት የማይገናኙን፣ ከቢሮ ወይም ከአዳራሽ ውጭ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲገቡ አይፈቀድም፤
  • ቢገቡ፥ ቀኖና ይጣሳል፤ ምእመናንም ቢቃወሙ አይፈረድባቸውም፤ እኔም ተቃውሟቸውን እጋራለሁ፤
  • የሰዓሊ ምሕረቱ [ቀኖናዊ ጥሰት]ወደፊት እንዳይደገም እንወያይበታለን፡፡

 ****** 

  • ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ የክህነት አባታቸው ነኝ፤ ቅስናም ኾነ ቁምስና በኢየሩሳሌም የተቀበሉት ከእኔ ነው፤
  • የአሁኑን ምርጫ እግዚአብሔር በዕጣ ለተወዳዳሪያቸው ሰጠ፤ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደሚሾሙ ተስፋ አለኝ፤
  • ለቅዱስ ሲኖዶሳችን ጥንካሬ የሚሰጡ ተጠያቂ ሊቅ በመሆናቸው፣ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ይፈልጋቸዋል፡፡

 ****** 

****** 


(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፱፻፲፩፤ ቅዳሜ፣ ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)

ባለፉት ሳምንታት በብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ላይ የተላለፉ መጣጥፎችን አንብቤ ስለነበር፤ ብፁዕነታቸውን ልጠይቃቸው ወደድሁ፡፡ ቀርቤም መስቀል ከተሳለምሁ በኋላ፥ ጥያቄ አለኝ፤ አልኋቸው፡፡ ስለ ምን ጉዳይ? አሉኝ፡፡ ባለፉት ሳምንታት እርስዎን በሚመለከት የተላለፉ መጣጥፎች ነበሩ፤ ሰምተዋቸው ከሆነ፡፡ እውነቱንና ሐሰቱን ሊያብራሩልኝ ይፈቅዳሉን? አልኋቸው፡፡ እርሳቸውም ሳያንገራግሩ፥ እንዴታ! ምን ከፋኝ፥ በሰፊው እገልጽልሃለሁ፤ ብለው ንግግራቸውን በእግዚአብሔር ቃል ጀመሩ፡፡ “ቃሉም ብፁዕ ውእቱ ዘኢተዐቅፈ ብየ = በሐሰት ምስክር በእኔ ያልተሰናከለ ብፁዕ ነው” (ማቴ.11፥5)፤ “በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመሰክር፤ ይላል እግዚአብሔር የሚል ነው፡፡ ዘጸ.20፥16

ንግግራቸውንም በማራዘም ሲናገሩ፤ “እኔ አባ ቀውስጦስ፣ የሰሜን ምዕራብ ሸዋ – ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በመሆኔ፥ በሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ሐሳብ የመስጠት መብት አለኝ፡፡ ስላለኝም በአስመራጭ ኮሚቴ የቀረቡ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት፣ እንደ ነገ የምርጫ ድምፅ ልንሰጣቸው ተዘጋጅተን ሳለን፥ በዋዜማው የስም ማጥፋት ዘመቻ የጀመሩ ሰዎች እንዳሉ ሰማሁ፤ በእጅጉ አዘንሁ፡፡ እንዳንሳሳት፤ ለቤተ ክርስቲያናችንም ጥራት ያላቸውን ሰዎች እንዳናሳጣት በማሰብ፣ በማግሥቱ ጉባኤው በጸሎት እንደ ተከፈተ እጄን አውጥቼ ማሳሰቢያ ሰጠሁ፡፡

የመጀመሪያ ማሳሰቢያዬ፦ ለኑፋቄው ማረጋገጫ ያለበትን ተጠርጣሪ አንድ ላይ ሆነን እናስወግደው፡፡ ያለማረጋገጫ የንጹሐን አባቶችን ስም አጥቁረን እናስወግድ ብንል ግን፤ ቤተ ክርስቲያንን ብቁ ሰው ማሳጣት ይሆንብናል፤ ጠመንጃ ተኩሶ ሰው እንደ መግደል ያስቆጥርብናል፡፡ በንጹሕ ደም ውስጥ እጃችንን እንዳናስገባ እንጠንቀቅ፤ የሚል ነው፡፡ ይህ፣ ራሳችንን ከፍርድ ለማዳን፤ ቤተ ክርስቲያንንም እግዚአብሔር በሚወደው መንገድ ለመምራት የሚያስችል ሐሳብ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን መካድ አይደለም፡፡

ሁለተኛው ማሳሰቢያዬ፦ አባ ተክለ ሃይማኖት ያለተወዳዳሪ ቀርበዋል፡፡ ተቀምጦ የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ ይቸግራል፤ እንደሚባለው ነገ ከነገ ወዲያ ወገን ያለው ያለተወዳዳሪ ልመረጥ ቢል የሲኖዶሱን ሕግ ያፈርስብናል፤ አንድ ተወዳዳሪ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተለይ በክልሉ መንግሥት በቀረበ ማሳሰቢያ ወይም ጽሑፍ የምንመርጥ ከሆነ፤ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጎዳል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስንም እንደሌለ ያስቆጥራል፤ ስል፤ የአስመራጩ ክፍል፥ “ጽሑፉን አልተቀበለውም፤ ተሰርዟል፤” የሚል መልስ ሲሰጠኝ ዝም ብያለሁ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ እንጂ መካድ አይደለም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ማሳሰቢያዬ የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስተች አልነበረም፡፡

ነገር ግን፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለኝን ተቆርቋሪነት የጠላብኝ ጥንተ ጠላቴ ሰይጣን፣ ፍልስጣ፣ የጽድቅ ጠላት የቀናውን ሐሳቤን አጣምሞ፥ ያላልኩትን አለ፤ ብሎ በሐሰት መስክሮብኛል፡፡ በዚህም ጠላት ሰይጣን ብዙ ምእመናንን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ አድርጓል፡፡ ይህንንም የሐሰት ምስክርነቱን አጠናክሮ የገደል ማሚቶ ላደረገው፥ ዘመድኩን ለተባለው ሰው አስተላልፎለታል፡፡ ይህ ግለሰብ ከጠላቴ የተላለፈለትን የሐሰት ምስክርነት ልዋል ልደር ላጣራ ሳይል ስሜን አጥፍቶ አሰራጭቷል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ባለው በሰማንያ አንድ ዓመታት ዕድሜዬ ስለ ቤተክርስቲያን ህልውና በመጨነቅ የተጓዝሁበትን የተጋድሎ ጎዳና ሳይሸሽግ ስለ መሰከረልኝ አመሰግነዋለሁ፡፡ የሚገርመው ግን ደቂቃ ሳይቆይ ቃሉን ለውጦ በመቃብር ውስጥ ሆኖ “ቤተ ክርስቲያንን ክዷል” ብሎ በሐሰት መመስከሩ ነው፡፡

እውነት ለመናገር፣ ለአንተ ለጠያቂዬ መልስ ልሰጥህ ፈቃደኛ የሆንሁት፤ ሃይማኖቴን ስለነካብኝና፤ ልጆቼ ምእመናን ይህን ሰምተው እንዳይሰናከሉ፤ እርሱም እውነትና ሐሰቱን ለይቶ እንዲያውቅ እንጂ፤ ሌባ፣ ወንበዴ፣ ቀጣፊ፣ አጭበርባሪ፣ ሴሰኛና ነፍሰ ገዳይ ቢለኝ ኖሮ፤ ከምንም ባልቆጠርኹት ነበር፤ ምክንያቱም፣ በዜና አበው ላይ እንዳነበብኹት፦ “አንድ ቅዱስ አባት ቆመው ሲጸልዩ፥ አንድ ክፉ ሰው ሰይጣናዊ ፈታኝ፦ ሌባ፣ ወንበዴ፣ ቀጣፊ፣ ሴሰኛ፣ ነፍሰ ገዳይ አላቸው፡፡ እርሳቸውም ዝም አሉት፡፡ መናፍቅ ከሐዲ ቢላቸው ግን፤ “አይደለሁም አይደለሁም” ብለው ጮሁ፤ ይላል፡፡ ይህም የሚያሳየው የሰው ልጅ ከምንም በላይ ሃይማኖቱን እንደ ዓይኑ ብሌን ጠብቆ መኖር እንደሚገባው መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም እኔም ሃይማኖቴን ከሚነኩብኝ ጨፍጭፈው ቢገድሉኝ ምርጫዬ ነው፡፡ እንደሰማሁት፣ ዘመድኩን የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ተቋም ምሩቅና ተቆርቋሪ እንደሆነ ተነግሮኛል፡፡ እንዲህ ከሆነ፣ እኔ ቤተ ክርስቲያንን ሳልክድ፤ ሁለተኛም፥ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተናገርኩትን ተገኝቶ ሳይሰማ ሳያውቅ ከእኔም ጠይቆ ሳይረዳ በእኔ ላይ የሐሰት ምስክርነት መስጠት ሰዎችም የተሳሳተ ግንዛቤና እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ የለበትም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያንም ልጅ ከሆነ በዚህ ንስሐ እንዲገባ እመክረዋለሁ፤” ሲሉ መልሰውልኛል፡፡

ጥያቄዬን በመቀጠል፣ ብፁዕ አባታችን፥ ከላይ የተዘረዘረው ቸግር መነሻው በሰዓሊተ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ የተባለው ችግር ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር ካለ አሁንም ቢገልጹልኝ አልኋቸው፤

ብፁዕነቸው ሲመልሱም፦ እኔ፣ ተፈጸመ የተባለውን ነገር አላውቅም ነበር፤ ነገር ግን፣ ለኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ ሁለትና ሦስት ቀን ሲቀረው በዶክተር አባ ኃይለ ማርያም ላይ የተቃውሞ ድምፅ ተሰማ፤ ምክንያቱ ወይም መነሻው ምንድን ነው? ብዬ ስጠይቅ፤ አባ እንግዶቹን ሲቀቡ፣ ከእንግዶቹ አንዱም አባን ሲቀባቸው የሚያሳይ ምስል ታየ፤ ተባለ፤ ቆይቶ፤ ደግሞ ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራንና ሌሎችም ባለሥልጣናት ከእንግዶቹ ጋር በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ቆመው ለእንግዶቹ በሳፋ ውኃ ቀርቦላቸው እየቀዱ ሲያፈሱ የሚያሳይ ምስል ታየ፤ ተባለ፡፡ ይህ የተንኰለኛ ቅንብር ይኹን አይኹን ባላውቅም አስደነገጠኝ፤ በእጅጉም አሳዘነኝ፡፡ ተቃዋሚዎችም፣ የሃይማኖት ልዩነት ያላቸውን ሰዎች አጅበው የገቡትን ባለሥልጣናት ትተው ዶክተሩን ብቻ ሲቃወሙ ከመሰማታቸው(ከመደመጣቸው) በቀር ሌሎችን ባለመቃወማቸው ግራ ተጋባሁ፤ ምክንያቱም፣ ቤተ ክርስቲያናችን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አባል መሆኗ ባይካድም፤ ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ጋር ግኑኝነታችን ቢቻል በኢኮኖሚ ለመረዳዳት ተቻችሎ ኑሮን ለመግፋት አንዱ የሌላውን መንጋ እንዳይነጥቅ ተመካክሮ በሰላም ለመኖር እንጂ፤ በሃይማኖት ግኑኝነት የለንም፡፡ ከቢሮ ወይም ከአዳራሽ ውጭ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲገቡ አይፈቀደም፡፡ በውጭ አገር ግን አብያተ ክርስቲያናት የሃይማኖት ልዩነት ሳይገታቸው፤ አልፎ አልፎ ይገናኛሉ፡፡ ይህም በኢየሩሳሌም እንደሚደረግ ዐውቃለሁ፡፡ በአገራችን ግን ይህ አልተለመደም፤ ምእመናን ቢቃወሙ አይፈረድባቸውም፤ እኔም ተቃውሟቸውን እጋራለሁ፤ ምክንያቱም መናፍቃን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ከገቡ የቀኖና ጥሰት ይከተላል፤ ሃይማኖትንም ይጎንጣል፤ ወደፊት እንዳይደገም እንወያይበታለን፤” ብለዋል፡፡

እኔም ጥያቄዬን ስላልጨረስሁ፣ ብፁዕ አባታችን፥ መጣጥፉ አባ ኃይለ ማርያም ከእርስዎ ቤት እንደሚገቡ እንደሚወጡ ሌሊትም ከእርስዎ ጋር እያደሩ እንደሚመክሩ ይናገራል፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት ነው? አልኋቸው፡፡

ብፁዕነታቸው በመገረም ሲመልሱ፦ “ይህ ፍጹም ውሸት ነው፡፡ አባ ኃይለ ማርያም ከእኔ ቤት የሚገቡበትና የሚወጡበት፣ ከእኔ ጋርም እያደሩ የሚመክሩበት አንዳችም ምክንያት የላቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ በአጋጣሚ ከመንገድ ላይ እንኳን ተገናኝተን አናውቅም፡፡ ወደ ፊት በአገልግሎት ብንገናኝ፥ በእርሳቸውም ሆነ በእኔ ላይ ማዕቀብ የሚጥል የለም፡፡ ለመሆኑስ ከሰው እንዳይገናኙ ያወገዛቸው ነፃነታቸውን የገፈፈው ማነው?” ብለዋል፡፡

ስለ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራስ ምን ይላሉ? አልኋቸው፤ ሲመልሱም፦ “ለሊቀ ሊቃውንት አባ ዕዝራ ከኔ የሚቀርባቸው ወንድም ወይም አባት ያለ አይመስለኝም፡፡ ዕድል ገጥሞኝ፤ በኢየሩሳሌም ቅስናም ሆነ ቁምስና የተቀበሉት ከእኔ ነው፡፡ የክህነት አባታቸው መሆኔን በሕይወት ታሪካቸው ላይ አቅርበውታል፡፡ የአሁኑን ምርጫ እግዚአብሔር በዕጣ ለተወዳዳሪያቸው ሰጥቷል፡፡ እርሳቸውም ጉባኤያቸው እንዳይመክን ተተኪ መምህር ያዘጋጁ እንጂ፣ ለሲኖዶሳችን ጥንካሬ የሚሰጡ ተጠያቂ ሊቅ በመሆናቸው ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ይፈልጋቸዋል፡፡ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደሚሾሙ ተስፋ አደርጋለሁ፤” ሲሉ ለጥያቄዬ መልስ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ስለ ምእመናን ያላቸውን አስተያየት ሲገልጹ፦ ምእመናን ተዋሕዶ ሃይማኖታቸውና ቀኖና ቤተ ክርስቲያናቸው እንዳይዛባ በቤተ ክርስቲያን ያልተለመደ ሥራ ወይም ሥርዓት ሲያዩ ተቃውሞ ማሰማታቸው የሚደገፍ ነው፤ በእጅጉም ያስመሰግናቸዋል፡፡ በተጓዳኝ ደግሞ፣ መናፍቃን ባቀናበሩት ሤራ አንዳንዶች ምንም በማያውቁት መንገድ ሰይጣን ዲያብሎስ የዘራውን የሐሰት ምስክርነት አምነው የንጹሐን አባቶቻቸውን ንጹሕ ስም እያጠፉ፥ መስቀላቸውን አንሳለምም፤ አባቶቻቸንም አንላቸውም፤ እያሉ በድፍረት ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡

መስቀሉ የክርስቶስ ነው፤ እኛም ልጆቻችን የምንላቸው አማኞችን እንጂ ከሐዲዎችን አይደለም፤ ባይሳለሙም አባቶቻችን ባይሉንም ጉዳቱ የራሳቸው ነው፡፡ እኛ እኮ ቀደም ሲል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ “ክፉ ስም ያወጡላችኋል፤ ደስ ይበላችሁ” ስላለን፤ አይከፋንም፡፡ እነሱ ግን የሚጎዱት ባለማወቅ ስለሆነ እናዝንላቸዋለን፡፡ ስለዚህም፣ “በወንድምህ ላይ በሐሰት አትመስክር” ብሎ ሕግ የሠራ እግዚአብሔር እንዳይፈርድባቸው በሐሰት ከመመስከር ይጠንቀቁ፡፡ በማያውቁት ነገር በመናፍቃን ቅጥረኞች እየተገፉ ሌላውን ኰንነው በሥራቸውም ሆነ በእምነታቸው እንደ ፈሪሳዊ አይመጻደቁ፥ ፈርዶ የሚኮንን፣ ፈርዶ የሚያጸድቅ እግዚአብሔር መኖሩን ይወቁ እላለሁ፤” ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

እኔም በበኩሌ የብፁዕነታቸውን ምክር ተቀብለን እንጠቀምበት እላለሁ፡፡

************

መምህር ዘመድኩን በቀለ፣ ስለ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ተጋድሎ ከሰጠው ምስክርነት መካከል፣ በፀረ ማርያም – ሰባክያን ነን ባይ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰርጎ ገቦች ላይ ያላቸውን ጽኑ አቋም በታወቀው ርቱዕ አንደበት በመግለጽ፣ ቀናዕያን ኦርቶዶክሳውያን ከመድረክ እንዲያስወግዷቸው ያስተላለፉትን ጥብቅና ቆራጥ አባታዊ መመሪያ የሚያስታውሰው ይገኝበታል፡፡

ጊዜው፥ ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲኾን፤ ወቅቱም፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 34ኛው ዓመታዊ ስብሰባ የሚያካሒድበት ሦስተኛ ቀን ውሎ ነው፡፡ የዕለቱ የስብሰባው መክፈቻ የነበረውና በአጠቃላይ ጉባኤው የጋራ መግለጫ ላይ የሰፈረው የብፁዕነታቸው ትምህርት፣ በቅዱስ ጳውሎስ የሮሜ ክታብ ምዕ. 8 ላይ የተመሠረተ ሲኾን፤ መልእክቱም የሚከተለው ነበር፡-


ቅዱስ ሲኖዶስ/ሰበካ ጉባኤ የተመሠረተው በሐዋርያት ነው፤ ለሃይማኖቱ ቀናዒና አስተዳደር ዐዋቂ የነበረው ቅዱስ እስጢፋኖስም ተሹሞ ሰፊ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ እርሱን ቢገድሉትም፣ ፰ሺሕ ተከታዮቹ ተነሥተው፣ የበለጠ ተደራጅተው አገልግሎቱን አስፋፍተዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን በ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የራሷ ፓትርያርክ ኖሯት፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ሰበካ ጉባኤ ተጀምሮ፣ በ፶ ሳንቲም የተጀመረውን አስተዋፅኦ፣ ዛሬ በመቶ ሚሊዮን መቁጠር ችለናል፡፡ ይህን ብር ግን፣ ቤተ ክርስቲያን ትገልገልበት፤ ትክክለኞቹ አገልጋዮቿም ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

ሰበካ ጉባኤ የሚጠናከረው በስብከተ ወንጌል ነው፡፡ ስብከቱን ደግሞ ምስጢር ዐዋቂዎች ሊሰብኩት ይገባል፡፡ “ክርስቶስን እንሰብካለን”፤ “አባት የሌለው አባት አብ ብቻ ነው”፤ ምስጢረ ሥጋዌው ሳይገባቸው፣ ዕውቀቱ ሳይኖራቸው፥ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንረከባለን፤ የሚሉ በየበረንዳው የሚያንዣብቡ ሰባክያን ነን ባዮች፣ በፍጹም ቤተ ክርስቲያንን ሊደፍሯት አይችሉም፡፡ እስከ ደም ጠብታ እንታገላለን፤ ቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ነች፤ ማርያምን የማይሰብክ/የሚቃወም/ ሰባኪ ካለ ከመድረክ እንድታስወግዱት በእግዚአብሔር ስም አደራ ብዬ እማፀናችኋለኹ፤” ሲሉ ለጉባኤው ትምህርተ ወንጌል እና አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

The post አቡነ ቀውስጦስ: መ/ር ዘመድኩንን ወቀሱ፣ አወደሱም፤ በ‘መቀባባቱ’ ጉዳይ ተቃውሞውን ይጋራሉ፤ ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ መሰከሩ፤ በኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ አቋማቸውን አብራሩ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


በባህርዳር መግቢያ መውጫወች በተለይ በጎንደር መስመር ከፍተኛ ወታደራዊ ፍተሻ እየተደረገ ነው !!

$
0
0

ይህ የወያኔ ፍተሻ የሚያገኘው ነገር ኖሮ ሳይሆን በህዝቡ ላይ የፍርሃት ቆፈን በመጫን የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ያለመ ነው።
ህወሓት /ወያኔ ውርደቱን ለመሸፋፈን ያዙኝ ልቀቁኝ አብዝቷል። የደረሰበት መተረማመስና መፈረካከስ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ አላደረገውም። የነፃነት ሃይሎች ያልተጠበቀና ምንም መረጃ ባልወጣበት የሚፈፀም ጥቃት ፋታ ነስቶታል። ወደ ጎጃም እየገሰገሰ የሚገኘው የነፃነት ትግል ፋና የውስጡን አለመረጋጋት እና ጎራ ለይቶ እርስ በርሱ በጥርጣሬ መተያየቱን በጉልህ ጥርሱን አግጥጦ እንዲታይ አድርጎታል። በባህርዳር አየር ማረፊያ የተያዘው ተቀጣጣይ ፈንጂ ደግሞ የነፃነት ትግሉ አድማሱን ማስፋቱና ከእጁ እየወጣ የሚገኘው የቀጠናው የነፃነት ታጋዩች እንቅስቃሴ በወታደር ብዛት መግታት እንዳልቻለ ያረጋገጠ ትልቅ ስጋት ሁኖበታል።በዚህም የራሴ የሚላቸውን ሰወች በመጠራጠር እስከ ማሰር እንደደረሰ መረጃወች ይጠቁማሉ። በቀጣይ ይደርስብኛል ብሎ ከሰጋቸው አንኳር ጥቃቶች በመነሳት በለሊት ማንኛውንም የስራ መኪና እንቅስቃሴ በሰሜኑ ቀጠና እስከማገድ እና በኬላወች ለፍተሻ በማስቆም እንዲያድር ያደርጋሉ።
በዛሬ ዕለተ ረዕቡ ሰኔ 28/2009 ዓ.ም አነጋግ የጀመረው ፍተሻ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች (ባለማዕረግተኞች)በስምሪት የተሳተፉበት ነበር። በትናንትናው ምሽት በበግ ተራ አካባቢ ሰወች እየታደኑ ይያዙ እንደነበር የአይን እማኞች ይናገራሉ። በወታደሮች እየተያዙ የተወሰዱ ሰወች ትክክለኛ ማንነትና ቁጥር እስካሁን ለማረጋገጥ አልተቻለም።
ይህ በህወሓት ወንበዴ ቡድን የሚፈፀም ድንገተኛ የተጋነነ ወታደራዊ ሰልፍና ፍተሻ በመውጫ መግቢያወች ምንም የሚያገኘው ኑሮ ሳይሆን በነዋሪው ህዝብ ላይ የፍርሃት ቆፈን በመደረብ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ያለመ ውርደቱን መሸፈኛ ካባ ነው ።
ስነልቦናው እንደ አለት በጠነከረ ህዝብ ላይ ጫና ለመፍጠር መሯሯጥ ትርፉ መላላጥ ብቻ ነው።
ድል ድል ይሸታል አየሩ ፣
ትርምስምስ ብሏል ጠላት መንደሩ ።
ድል ምንጊዜም የህዝብ ነው !!
@እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

Jan Tirar to ኢትዮጵያዬ

The post በባህርዳር መግቢያ መውጫወች በተለይ በጎንደር መስመር ከፍተኛ ወታደራዊ ፍተሻ እየተደረገ ነው !! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

“የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር” ለማቋቋም እና ለአባላት ምዝገባ የቀረበ ጥሪ

$
0
0

“የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር” ለማቋቋም እና ለአባላት ምዝገባ የቀረበ ጥሪ

ጣና ሃይቅን የወረረዉን እንቦጭ አረም (Water Hyacinth) ለመከላከልና ሃይቁን በዘላቂነት ለመጠበቅ የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር ለማቋቋም የቀረበ የመነሻ ሃሳብ በደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)፣ በባዳዩ የተቀናጀ ዉሃ ሃብት አስተዳደር ረ/ፕሮፌሰር

መግቢያ

ሃሩርና ሃሩር ቀመስ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ የዉሃ አካላት አንዱና ዋነኛ ችግራቸዉ በዉሃ ላይ በሚንሳፈፍ የእንቦጭ አረም (Water Hyacinth) ወይም በሳይንሳዊ ስሙ (Eichhornia crassipes) መወረር ነዉ። አረሙ በመጀመሪያ ከደቡብ አሜሪካዉ የአማዞን ወንዝ እንደተገኘ የሚታመነዉ ይህ ዝርያ በአሁኑ ወቅት በሃሩርና ሃሩር ቀመስ በሆኑ የአለማችን አካባቢዎች ማለትም በደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን፣ በአፍሪካ፣ በደቡብ ምስራቅ እስያና በፓስፊክ አካባቢ ሃገራት በስፋት ተዛምቶ ይገኛል። በሃገራችን ኢትዮጵያም እንቦጭ አረም ባለፉት አምስት አመታት ዉስጥ በጣና ሃይቅ ላይ ተከስቶ ሃይቁን በመዉረር ላይ ሲሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከሦሥት አመት በፊት ባካሄዱት ጥናት መሰረት 50,000 (ሃምሳ ሺ) ሄክታር ወይም 500,000,000 (አምስት መቶ ሚሊየን) ካሬ ሜትር ስፋት ያለዉን የሃይቁን አካል ሸፍኖ እንደሚገኝ ሪፖርት አቅርበዋል።

አረሙ በተዛመተባቸዉ አካባቢዎች የመስፋፋት ፍጥነቱ ከፍተኛ ሲሆን ለዚህ ዋነኛ ምከንያቱ ደግሞ ከእርሻ መስፋፋትና የማዳበሪያ አጠቃቀም መጨመር ጋር ተያይዞ ከተፋሰሶች በጎርፍ ተጠርጎ ወደ ሃይቆች የሚገባዉና በዉሃ አካላቱ ዉስጥ የሚገኙ ንጥረ-ነገሮች (nutrients) በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር (eutrophication) ሲሆን አረሙ ተፈጥሮአዊ አጥቂ ጠላት አለመኖሩም ለመስፋፋቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።

በተለያዩ አገሮች ዉስጥ በተሰሩ ምርምሮች ላይ በስፋት እንደተረጋገጠዉ በስነ-ህይወታዊ ዘዴ አረሙን መከላከል ከሌሎች አማራጮች የተሻለ ዉጤታማና ተመራጭ ነዉ። ለምሳሌ በአዉስትራሊያ Neochetina eichhorniae እና N. bruchi የተባሉ ዕፅዋት ተመጋቢ ጥንዚዛዎችን እንዲሁም the moth Sameodes albiguttalis የተባለ የነፍሳት ዝርያን በመልቀቅ እምቦጭ አረምን ዉጤታማ በሆነ መንገድ መቆጣጠር ተችሏል። እነዚህ መንገዶች በሌሎች የደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ አገሮች ላይም ተሞክረዉ በተመሳሳይ ዉጤታማ እንደሆኑ ተረጋግጧል።

በብዙ አገሮች እንደሚታየዉ ሁሉ በጣና ሃይቅ ላይ ያለዉ የአረሙ መስፋፋት በጣም ፈጣን ስለሆነና በአሁኑ ወቅት ከጅምር ያለፈ በቂ የሆነ የስነ-ህይወታዊ የመቆጣጠር ስራ እየተከናወነ አይደለም። እነዚህን የመቆጣጠሪያ መንገዶች ለመጠቀም በቅድሚያ የጎንዮሽ ጉዳታቸዉን የተመለከቱ ምርምሮችን ማካሄድ አስፈላጊ ነዉ። ስለዚህ የአጭር ጊዜ ርምጃዎችን በመዉሰድ አረሙን የመቆጣጠር ስራ መስራት እንደሚገባ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል። የአጭር ጊዜ የመቆጣጠር ስራዎች በአንድ በኩል አረሙ አሁን ያለዉን ፈጣን መስፋፋት ለመቆጣጠር፤በሌላ በኩል ደግሞ ወደፊት ለሚከናዎኑ ስነ-ህይዎታዊ የቁጥጥር ስራዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ በሚል ታሳቢ ነዉ።

በጣና ሃይቅ ላይ ያለዉን አረም ለመከላከል መደረግ ከሚችሉ የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች መካከል በአካላዊ (በማሽነሪ ወይም በሰዉ ጉልበት በእጅ) ዘዴ ማስወገድ እና ፀረ-አረም ኬሚካሎችን መጠቀም ይገኙበታል። ሁለቱንም ዘዴዎች በተለይ በታዳጊ አገሮች ለመተግበር ተግዳሮቶች ይኖራሉ። በማሽነሪ ለማስወገድ ማሽነሪዎችን ወይም ሃርቨስተሮችን መግዛት የሚያስፈልግ ሲሆን ብዙዎቹ አንድም ዉድ ናቸዉ ወይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች በሃገር ዉስጥ ገበያ አይገኙም። አረሙን በእጅ በሰዉ ጉልበት ማስወገድ ደግሞ ብዙ የሰዉ ሃይልና ጉልበት ይፈልጋል። የታዳጊ አገሮች መንግስታት ለዚህ የሰዉ ሃይል የሚሆነዉን የጉልበት ክፍያ የመክፈል አቅም ወይም ቁርጠኝነትና ፍላጎት ላይኖራቸዉ ይችላል። አረሙን እንደ ቱ-ፎር-ዲ እና ግላይፎሴት አይነት ኬሚካሎችን በመጠቀም መቆጣጠር በአንዳንድ አገሮች አዋጭ ቢሆንም ደሃ አገሮች ይህን ማድረግ አዋጭ ላይሆን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ኬሚካሎችን በዉሃ አካላት ላይ መርጨት በዉሃ አካላት ብዝሃ-ህይወት ደህንነትና ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያደርሱ በብዙ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ ይተቻሉ።

ስለዚህ የችግሩን ግዝፈት ከግምት ዉስጥ በማስገባት በዘላቂነት በጣና ሃይቅ ዙሪያ የሚከናወኑ የእንቦጭ አረምና መሰል ወራሪ ዕፅዋትን ለመከላከል የበጎ ፈቃደኛ ምሁራን፣ ባለሃብቶች፣ ወጣቶች፣ የማህበረሰብ ድርጅቶችንና ሃላፊነት የሚሰማቸዉን ተቆርቋሪ ዜጎች ለማስተባበር የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የማህበሩ ዓላማና ግብ

ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ ሲሆን ለአባይ ወንዝም ዋነኛዉ የዉሃ ፍሰት ምንጭ ነዉ። ሃይቁ ለቱሪስት መስህብነት፣ ለሃይል ማመንጫ፣ለመስኖ እርሻ፣ለመጓጓዣ እንዲሁም ለአሳ ምርት ምንጭ በመሆን ለአካባበዉ ማህበረሰብም ሆነ ለሃገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ይህንን የሃይቁን አስተዋጽኦ በዘላቂነት ለማስቀጠል የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ጎን ለጎን የተደራጁ የማህበረሰብ ድርጅቶች (ሲቪል ሶሳይቲዎች) ጠቃሚ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የበጎ አድራጎት ማህበራት ምዝገባ ክፍል ለማጣራት እንደተሞከረዉ ከዚህ በፊት ሁለት ድርጅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ለመስራት ፈቃድ ቢወስዱም እሰከአሁን ድረስ አጥጋቢ እንቅስቃሴ አላደረጉም። ስለዚህ የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር በሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች ዙሪያ ጠንካራ እንቅስቃሴ ለማድረግ አስቧል፤

1) በጣና ሀይቅ ላይ የተዛመተዉን እንቦጭ አረምና ሌሎች ወራሪ ዕፅዋቶችን የመቆጣጠር ስራን ማገዝ

2) የሃይቁን ጥበቃና እንክብካቤ አስመልክቶ የአድቮኬሲና የማህበረሰብ ትምህርት መስጠት፣

3) ለጣና ሃይቅ ጥበቃና እንክብካቤ በጎ አድራጊ ባለድርሻ አካላትን ማስተባበርና ተያያዥ ስራዎችን መስራት

4) በጣና ሃይቅ ላይ የሚከናወኑ የተቀናጀ የዉሃ ሃብት አስተዳደር ስራዎችን መደገፍ ናቸዉ። ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች በማሳካት የሃይቁ የዉሃ ጥራትና መጠን ተጠብቆ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲሸጋገር ማድረግ የማህበሩ ግብ ነዉ።

የማህበሩ ህጋዊነትና አደረጃጀት

የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህግ መሰረት እንዲቋቋም የሚደረግ ሲሆን የሚከተሉት አደረጃጀቶች ይኖሩታል፤

1) ጠቅላላ ጉባዔ

2) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

3) የማህበሩ አባላት

4) የማህበሩ አማካሪና ስራ አመራር ቦርድ

የማህበር ምስረታ ጥሪ

ማህበሩን ለማቋቋም የማህበሩ መመስረቻ ረቂቅ አጀንዳ (7-ገፅ) ፣ መተዳደሪያ ደንብ (14- ገፅ) ፣ የጊዜያዊ ስራ አስፈፃሚ አመራሮች የህይወት ታሪክ ፎርም (1-ገፅ) እንዲሁም የማህበራት ምዝገባ ማመልከቻ ቅፅ (4-ገፅ) አዘጋጅተናል። ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን የማህበሩን ዓላማ የሚደግፍና ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ የአካባቢዉ ተወላጆች፣ ምሁራን፣ ባለሃብቶች፣ ወጣቶችና አርሶ አደሮች እንዲሁም ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለመስራች አባልነት እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።

ለምዝገባና ለማንኛዉም ጥያቄ ወይም አስተያየት፡-

በተንቀሳቃሽ ስልክ (+251) 918 764 279 ፡- ደሳለኝ ጫኔ ወይም
በ Email: cdessalegn@yahoo.com ወይም
በ Facebook መልዕክት (ለ Dessalegn Chanie Dagnew)

ሙሉ ስም፣ ፆታ፣ ዕድሜና ስልክ ቁጥር በመላክ መመዝገብ ይቻላል።

ማህበሩ በይፋ የሚመሰረትበት ቀን ወደፊት በስልክና በፌስቡክ ይገለጻል።

 

The post “የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር” ለማቋቋም እና ለአባላት ምዝገባ የቀረበ ጥሪ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ጣና ዓባይና አባ ባህሩ አንድም ሶስትም – በላይነህ አባተ

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

አባ ባህሩ እየወደቁ እየተነሱ ከዋሻቸው ፀሎት ሲያደርሱ የቅኔ ተማሪያቸው ዲያቆን ፈጣን ኮቴ አቋረጣቸው፡፡ የዲያቆኑ ፈጣን ኮቴ ያልተለመደ ስለነበር “በደህንነት ነው?” ሲሉ ጠየቁ፡፡ ዲያቆኑም “ይቅርታ ያድርጉልኝ እየንታ! ስክለፈለፍ ጸሎትዎን አቋረጥኮዎ! በኃላ እመጣለሁ!” ብሎ ተሸማቆ ሊመለስ ሲል “ና! ና! ምንድነው ችግሩ?” ብለው መለሱት፡፡ “ችግሩማ ጣና ነው እየንታ!” ብሎ ሳይጨርስ! “ጣና ምን ሆነ!” ሲሉ ጮኹ በጢም የተሸፈነ ፊታቸውን ከዝሆን እንደተጣላ አንበሳ ከዲያቆኑ ጥደው፡፡ ዲያቆኑ እንደተቆጣ አንበሳ የጋለው ፊታቸው ለምጥጦት መሬት መሬቱን እያዬ “ቁራሽ ልለምን ሰፈር ለሰፈር ተውሻ ስታገል ሕዝቡ “ጣና ሊደርቅ ነው! እያለ ሲበሻጭ ተመለከትኩ” ብሎ ሳይጨርስ “ጣና እየደረቀ! እውነትህን ነው? በትክክል ተመልክተኻል?” ሲሉ እንደገና አፈጠጡበት፡፡ “እውነት ነው እየንታ! ተሕዝቡም በተጨማሪ ተውጪ በሚሰራጩ ራዲዮኖችና ገጠ-ብራናዎች ተላልፏል” አለ ፌስ ቡክን ገጠ-ብራና ብሎ ተርጉሞ፡፡  የተላለፈው እውነት መሆኑን እንዴት አረጋገጥክ ሲሉት “አረም የለበሰው አዲሱ የጣና መልክ ይኸው እየንታ” ብሎ ቁራሽ ከዘከሩት አንዱ የሰጠውን ፎቶግራፍ ሲያሳያቸው አባ ባህሩ ጾም ተቆፈረው ያይናቸው ዳገት እንባቸውን እንደ ፏፏቴ አወረዱት፡፡ የአባ ሐዘን ቅስሙን የሰበረው ዲያቆንም “ለዓባይና ለጣና ያለወት ፍቅር፤ ስለ ዓባይና ጣና ያስተማሩን መንፈሳዊ ትምህርት አይምሮዬን እንደ ድቡቅ አደፍርሶት በምሽት ላረዳዎ መጣሁ” አለ የእናትና ያባትን ሞት እንደተረዳ እርሱም እንባውን የተኳለ ከሚመስለው የዓይኑ ክፈፍ እንደ በልግ ዝናብ ዱብ ዱብ እያደረገ፡፡

የዲያቆኑን ጥልቅ ሐዘን ያስተዋሉት አባ ባህሩ ቅዱሳን መጻሕፍትን እየተጠቀሱ ስለ ዓባይና ጣና ያስተማሩት ከለም መሬት መብቀሉ አስደሰታቸውና በዱካቸው እየሄደ ያለውን ዲያቆን ፀጉር እንደ እናት እየዳሰሱ “ለመሆኑ ስንት ዘመን የተጠማ እርኩስ መንፈስ ጣናን ጨለጠው? የትስ ሄዶ ሸናው?” ብለው በግዕዝ ሲጠይቁት ዲያቆኑ “ምንት ምንትስ” ብሎ ባስተማሩት ግዕዝ “ቀዩን ባህር ገንጥሎ የበላው ሰማያዊውን ባህር ማወራረጃ አርጎ ተንጋሎ በሆዱ ሸናው” ሲል፡፡ በተማሪያቸው ቅኔ አዘራረፍ የረኩት አባ ባህሩ “ይበል ብለናል” ብለው አደነቁና “ሳጥናኤል ጣናን ለመጨለጥ ምን ተጠቀመ!” ሲሉ ጠየቁ፡፡ “አረም፣ መስኖ፣ ግድብ፣ ደን ጭፍጨፋ፣ ምቀኝነት፣ ተንኮል… እያለ ሕዝቡ ይናገራል” ብሎ ሲመልስ “አገራችንን እሚያጠፉ ፍልፈሎች ተዓባይ ተማይዋሰኑት ያገሪቱ ክፍሎች ይነሳሉ” ተብሎ የተተነበየው ተፈፀመ” አሉና ዓይናቸውን ከማያዩት መሬት ተክለው እንደ ጣና በሰፋና እንደ ዓባይ በረዘመ ትካዜ መዋኘት ጀመሩ፡፡፡

የአባ ባህሩ ትካዜ በሰባት ዓመታቸው ጣና ጥልቂያ የገጠማቸውን ጓደኛቸውን አስታወሳቸው፡፡ በዚህ ከጓደኛቸው ጋር ባደረጉት የጨዋታ ጥልቂያ መጀመሪያ ጓደኛቸው ጭንቅላታቸውን ረምዶ ሲደፍቃቸው በኋላ ግን ኃይላቸውን አሰባስበው ከትክሻው ቆመው ደጋግመው ያሰመጡት ትዝ አላቸውና የላይኛውን ከንፈራቸውን እንደ ስስ እንጀራ ተጠንቅቀው ጠቅልለው “እህ….እህህህ…” ብለው ዓይናቸውን ተምድር ተክለው በሳቅ ሲፈነዱ ዲያቆኑ ያበዱ መሰለውና “ያባይና የጣና ነገር መቼም አይሆንላቸው፤ እየንታ መቀወሳቸው ነው?” ብሎ ተጨነቀ፡፡ የአባ የልጅነት ትዝታ ያፈነዳው ሳቅ ከመቅጽበት እንደ ጤዛ ረግፎ ያምላክ በረከት፤ ያገሪቱም ሞገስና ግርማ የሆነው ጣና አረም ለብሶ  ታያቸውና “በስመ አብ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ! ይኸንን ሳታሳይ ውሰደኝ” ብለው የንዳድ በሽታ እንደነደፈው ተንቀጠቀጡና ወደቁ፡፡

የአባ ባህሩን፣ የዓባይንና የጣናን አንድነትና ሶስት እማያውቅ፤ በጣና እየተነከረና እየተንጨቧረቀ ላላደገ፣ የጪስ እሳትን ፉጨት ሲያዳምጥ ላልኖረ፣ ያባይን እንጉርጉሮና  የእረኛውን ዋሽንት ጣዕም ሲያንቆረቁር ላቅመ ሔዋን ወይም አዳም ላልበቃ አለዚያም ዓባይና ጣናን እንደ ሥጋውና ነፍሱ ለማይቆጥር “ያባይና የጣና መድረቅ አባን አንቀጥቅጦ ጣላቸው” ብሎ ለማመን ያስቸግረው ይሆናል፡፡ አባ ባህሩ ግን የጣናን መድረቅ በህሊናቸው ሲስሉት ተንቀጥቅጠው ወደቁ፡፡ አባ ባህሩ የዓባይና የጣና ውሀ ደማቸው፣ የረግረጉ ፊላና እንግጫ ስጋቸው፣ የገዳሙ ዜማ መንፈሳቸው፣ የዋሽንቱ ጣዕምና  የጪስ እሳት ፉጨት ነፍሳቸው ስለሆኑ የእነዚህ መጥፋት ሲያስቡ ተዝለፍልፈው ወደቁ፡፡ ከወደቁበት ሳይነሱ “የቁንዝላን አፈር በጣና ውኃ አላቁጠህ ሥጋዬን ሰርተህ፣ ተራስ ደጀን፣ ተበላያ፣ ታመዳሚት፣ ተጣራ ገዳምና ተጮጬ ተራሮች እሚነፍሰውን አየር እፍ ብለህ ነፍሴን ዘርተህ፤ በሁለተኛው ወንዝ በግዮን በተከበበችው ኤደን እንድኖር የፈጠርከኝ አምላክ ሐይቃችንንና ወንዛችንን ተማይጠረቃውና በቃኝን ተማያውቀው ሳጥናኤል እንድንከላከል የመንፈስና ያካል ጥንካሬ ስጠን!” እያሉ ደጋግመው ሲጮኹ ቆዩና ሲደክማቸው ጸጥ አሉ፡፡ ዲያቆኑም ” የማላውቀው በሽታ ነበረባቸው ወይስ ስክለፈለፍ መጥቼ ገደልኳቸው?” ብሎ ተጨነቀና እስተንፋሳቸው መኖሯን ለማረጋገጥ የቀኝ ጆሮውን ወደ አፍንጫቸው ዘንበል አድርጎ ሲያዳምጥ “እ…ህ ፉው… እ…ህ ፉው…” እሚል ድምፅ ሰማ፡፡ “ተመስገን ነፍሳቸውስ አለች! እንቅልፍ እየወሰዳቸው ነው!” አለና ደበሎውን በጋቢያቸው ደርቦላቸው ከአጠገባቸው ጸሎት ማድረስ ጀመረ፡፡

አባ ባህሩ አካላቸው ቢተኛም አይምሯቸው በትዝታ ባህር መዋኘቱን ቀጠለ፡፡ ከሶስት ዓመታቸው ጀምሮ “ሀ ግዝ፣ ሁ ካይብ፣ ሂ ሳልስ፣ ሃ ራበ …” እያሉ ሆሄ የቆጠሩባት ቁንዝላ ከአቡጊዳ እስከ ስንክሳር ከዚያም እስከ መጽሐፈ ትርጓሜ ያስተማረቻቸው የተዋህዶ ቤተክርስትያን ባይምሯቸው እንደ መንፈስ ተመላለሱባቸው፡፡ ዳዊትን ሲጨርሱ የተፈተኑበት “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” እሚለው የግዕዝ ቅኔ ትዝ አላቸው፡፡ በግዕዝ “ምንትስ ምንትስ” ብለው “የፍጥረት መጀመሪያዋ፣ የኦሪትና የሀዲስ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታለች” ሲሉ “ተዘረጋች ሩብ ክፍለ-ዘመን አለፋት” አለና መለሰ ዲያቆኑ በእውናቸው ሲያስተምሩት እንደሚያደርገው፡፡ ዲያቆኑ ለመልሱ የተለመደውን የሙከሻ ወይም የነቀፋ አስተያየት ከአባ ባህሩ ሲያጣ በእንቅልፍ ልባቸው እየተናገሩ እንደሆነ ትዝ አለውና “ህ…” ብሎ በሐፍረት ፈርጠም አለ፡፡

አባ እንቅልፋቸው ሕልም እሚታለምበት ደረጃ ሲደርስ አቡኑ፣ ጳጳሳቱ፣ ቀሳውስቱ፣ ቆመሳቱና  ዲያቆናቱ ካባ እንደ ግራር ቅርፊት ለብደው፣ ቆብ እንደ ጉልላት ቦጅረው፤ መስቀል እንደ ድሪ አንዠርገው ዓባይንና ጣንን በጣሳ እየቀዱ ሳጥናኤልን ሲያጠጡ አዩና “ሰ አሊለነ ቅድስት” ብለው ደንብረው ተነሱ፡፡ ከዚያም “በስመ አብ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ!” እያሉ በአራቱንም አቅጣጫ አማተቡ፡፡  “ምነው እየንታ ምነው!” አለ ዲያቆኑ የድንጋጤ አነሳሳቸው እርሱንም አስደነገጠውና፡፡ “የሳጥናኤል አገልጋዮች እንቅልፍም ነሱኝ! አሉ፡፡ “የሳጥናኤል አገልጋዮች እነማን ናቸው” ብሎ ዲያቆኑ ሲጠይቅ “ዓባይና ጣናን በጣሳ የሚግቱት ናቸዋ!” አሉት፡፡ ዲያቆኑም አሁንም በግዕዝ “ምንትስ ምንትስ” ብሎ “በአብ የመጣ በወልድ መጣ! ሳጥናኤልን ጋቾች እኔንም እንቅልፍ ነሱኝ” ብሎ ሲመልስ “እንቅልፍ እንደነሱን እንቅልፍ እንነሳቸዋለን! ጭንፉር በልና በጧት እድትሸኘኝ!” አሉት፡፡ “የት ሊሄዱ እየንታ?” ሲል ጠየቀ፡፡ “ወደ ጪስ ዓባይና ጣና ጉዞ እንጀምራለሁ” ሲሉት “አብሬ እሄዳለሁ!” አለ በሲቃ፡፡ ጉዞው ቀናት ይፈጃል! ልጅም ስለሆንክና ልምዱም ስለሌለህ ያቅትሃል!” ሲሉት “የሰሌን አኮፋዳ ሸጬ ያጠራቀምኳት ትንሽ ገንዘብ አለችኝ በመቺና እንሄዳለን” አለ፡፡ “ተመቺና ተሰቅዬ አላውቅም!” አሉ፡፡ “ለቅኔ ዋሽራ፣ ጎንጅ፣ ዲማ፣ ደብረወርቅ፣ ዋድላና ድለንታ፤ ለዜማ ጎንደር የሄዱት በእግርዎ ነበር” ብሎ ሲጠይቅ እንደ አቡኑና ጳጳሳቱ ድሃ ተልጇ ጉረሮ እየሞለቀቀች ለማርያምና ለገብርኤል ባስገባቸው ስለት የሮቢላ ካርኒ ገዝቼ ጮማ እየቆረጥኩና ጠጅ እየጠጣሁ መስሎህ ነበር?” ብለው ሲያፌዙ ተሳሳቁና በጧት ለመነሳት አቅደው ተኙ፡፡

ያህያ ሆድ ሲመስል አባ ባህሩና ዲያቆናቸው አብርሃና አፅብሃ የቀደሱባትን መርጡ ለማርያም ተሳልመው ጸሎታቸውን አደረሱና አራት ዓይናው ጎሹ ብሉይ ኪዳንን፣ ሀዲስ ኪዳንን፣ መጽሐፈ መነኩሳትንና መጽሐፈ ሊቃውንትን አኝከው በልተው እንደ ባውዛ እሚያበሩ አራት ዓይኖች ያወጡባትን የሞጣን መልከአ-ምድር እየቃኙ ለሃያ አራት ዓመታት የተለዩአቸውን ዓባይና ጣናን ባይኗ በብረቷ ሊያዩ አኮፋዳ ያንጠለጠለውን ዲያቆናቸውን አስከትለው መቋሚያቸውን እንደ ሙሴ ዘንግ ተከል ነቀል እያደረጉ የእግር ጉዞ ጀመሩ፡፡ “የግዮን ጋራ ይታይኻል?!” አሉ እንደ ኢትዮጵያ አርበኞች ደረታቸውን ነፍተው ወደ ተጀነኑት የዓባይ ጋራዎች እጃቸውን ዘርግተው፡፡ “ተጅንኖቹ ጋርዎች ድረስ ሄጃለሁ! የቋጉሜ ሩፋኤል እየሄድን ዓባይ እንጠመቅ ነበር” አለ ዲያቆኑ፡፡ “የግዮን ወዲህና ወዲያ ማዶ ሕዝብ በገመድ የሚገናኝበትን ሰባራውን ድልድይስ አይተኸዋል?” ብለው ሲጠይቁት “በስም እንጅ ሰባራውን ድልድይስ አይቸው አላውቀም! እርስዎ ጎንደር ለዜማ ሲሄዱ በዚህ ገመድ ነበር የተሻገሩ” ሲል ጠየቀ፡፡ “በኔ ልጅነት እንኳን ወንዱ ሴቷም ልጅ በሙላት እሚያጓራውንና እሚያገረሸውን ግዮንን በዋና ሰንጥቃው ትሄድ ነበር፡፡ እኔና ጓደኞቼም ተዋሸራ፣ ተጎንጅ፣ ተዲማና ደብረ ወርቅ ያኘክነውን ቅኔ በዜማ ልናወራርድ በነሐሴ ወር ቤገምድር  ስንሄድ ልብሳችንን በራሳችን ጠቅልለን የውኃ ጠብታ ሳናስነካ ቀንጥሰነው ተሻግረናል”! ሲሉት “እስጢፋኖስ እውነትንና ጥበብን ፍለጋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ!” ብሎ በግዕዝ ሲቀኝ “በደናቁርትና በሐሳውያንም ተቀጠቀጠ” ብለው ቅኔውን አሰሩት፡፡

የቅኔው ማሰሪያ ዲያቆኑን አረካውና “የዜማና የአቋቋምን ጥበብ ፍለጋ ህይወቱን ለግዮን አሳልፎ የሰጠ በየትኞቹ ደናቁርትና ሐሳውያን ተቀጠቀጠ!” ብሎ በግዕዝ ሲጠይቅ “በበርባኖችና በይሁዳዎች እግርና እጁን ታስሮ ጣና ተወረወረ” ብለው መለሱ፡፡ ዲያቆኑ በጉዞም የግዕዝና የቅኔ እውቀቱን ለማለዘብ ብሎ ሲጠይቃቸው የመለሱት መልስ ገረመውና “እውነትዎን ነው?” ሲል ኮስተር ብሎ ጠየቀ፡፡ “እውነት ነው!” አሉና ትረካውን ቀጠሉ፡፡ “ያይምሮ ምግብ ፍለጋ የድፍን ጎጃምና ጎንደርን የአብነት ትምህርት ቤቶች አድርሼ ለመሪጌትነት እንደበቃሁ “ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ለብዙ ዓመታት በመሪጌትነት አገለገልኩ፡፡ ተሩብ ክፍለ ዘመን በፊት አሕዛብ ቅድስት አገራቸውን የከዱ እንደ በርባን ያሉ ዘራፊዎችን ቤተመንግስት ሲያስቀምጡና እንደ ይሁዳ ቤተክርስቲያንን አሳልፈው የሰጡ ከሀዲያንም በሰማእታት ስሞች እየተሰየሙ በቤተ-ክርስቲያናችን ሲሾሙ” ብለው ሐሳባቸውን ሳይጨርሱ “እግዚኦ መሐርነ-ክርስቶስ የበግ ለምድ ለብሰው ተሚመጡ ነጣቂዎችና ተኩላዎች ተጠንቀቁ እሚለው የማቴዎስ ወንጌል ተፈጠመ” አለ ዲያቆኑ ራሱን ይዞ፡፡ “ትክክል! ማቴዎስ ምዕራፍ ሰባት አንቀጥ ባንቀጥ ቃል በቃል ተፈጠመ፡፡ ቤተመንግስቱን የወረሩት ባርባኖች ያገሪቱን ሐብት ሲዘርፉ ቤተከርስትያንዋን የወረሩት ይሁዳዎች ቤተክርስቲያኗን በመንፈስም በቁስም አራቆቷት፡፡ ሰላዩን፣ ወታደሩን፣ ሆዳሙንና አመንዝራውን እያመነኮሱና እያቀሰሱ እንደ ጅብ ለቀቁባት፡፡ እነዚህ ጅቦችም ሥጋዋን በሉት ደሟንም ሰረበቁት፡፡ ይኸንን በቤተክርስትያንና ባገሪቱ እሚፈጠመውን ደባ በአደባባይ በመቃወሜ በአንድ ምሽት እንዳልናገር አፌን በጨርቅ ጠቅጥቀውና እጄን ተግሬ አስረው ጣና ወረወሩኝ” ብለው ሳይጨርሱ “እንደ ሙሴ!” ሲል ጮኸ ዲያቆኑ፡፡ “ሙሴ ውኃ ውስጥ የተጣለው አንደኛ በህጻንነቱ ሁለተኛም ተሞት እንዲተርፍ ነበር፡፡ እኔ ውሀ ውስጥ የተጣልኩት ግን አንደኛ በጎልማሳነቴ ሁለተኛም እንድሞት ነበር፡፡ በጣሉኝ ሰዎች ግንዛቤ ዛሬ በህይወት የለሁም፤ ሞቻለሁ!” ሲሉ “ጣንና ተሚያህል ባህር ታስረው ተወርውረው እንዴት ተረፉ?” ሲል ጠየቀ የሚመልሱትን ለመስማት ተቻኩሎ፡፡ “ጣና ደጎባ ሳለሁ ጀምሮ እንደ ወላጅ እያጠበ ያሳደገኝ፣ እንደ ዳክዬ እያንሳፈፈ ዋና ያስተማረኝ፣ በገዳማቱ ዜማና በዋሽንቱ ጣዕም መንፈሴን ያነጠኝ ሥጋና ነፍሴ ነው፡፡ ጣና በምን ልቡ  እንደ ይሁዳ ይከዳኛል? ጣና በምን አንጀቱ እንደ በርባን ነፍሴን ይዘርፈኛል? ጣናማ እጅግ ረዳኝ! ስንቱ ቆብ ደፊ፣ ስንቱ ጠምጣሚና ስንቱ ካባ ደራቢ ሲከዳኝ ጣና አብሮኝ ቆመ፡፡ ጣናዋ የታሰርኩበትን ጉንጉን እንደ ጥጥ ሲያለሰልስልኝ በጥርሴ ቦጨኩና የምናውቅብኝ በሚል ወኔ እንደ ዳክዬ ተንሳፍፌ ወጥቼ አንተን ወዳገኘሁበት ዘወር ያለ ቦታ መጣሁ” ብለው ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካቸውን ሲነግሩት “እንደ ሙሴ ተውሀ የተገኘ” ሲል በግዕዝ ተቀኘ፡፡

አባ ባህሩ የሚገርም ታሪካቸውን ለዲያቆናቸው እየተረኩና እግረመንገዳቸውንም እያስተማሩት ስንቱን ሜዳ ተጉዘው፣ ስንቱን ዳገት ወጥተው፣ ስንቱን ጅረት አቋርጠው፣ ስንቱን ቀን ዉለው፣ ስንቱን ሌሊት አድረው፣ ከስንት ውሻ ታግለው፣ ከስንቱ ደጅ ቁራሽ ለምነው ጪስ ዓባይ ደረሱ፡፡ አባ ባህሩ ገና የፏፏቴውን ጫፍ ሲያዩ “መስቀላቸውን መጀመርያ ከጭንቅላታቸው ወደ ደረታቸው ከዚያም ከግራ ወደ ቀኝ ትከሻቸው ከወሰዱ በኋላ “አፈር አላቁጠህ ሥጋዬን የሰራህበትን ውኃ እንደገና እንዳየው የፈቀድክልኝ አምላክ ክብርና ምስጋናህ ይብዛ” ብለው ከምድሩ ሲደፉ “አሜን!” አለና ዲያቆኑም አብሮ ተምድር ተደፋ፡፡ ከተደፉበት ተነስተው ወደ ፏፏቴው እየቀረቡ ሲሄዱ በሁለት መስመር እንደ ትንሽ ጅረት የሚፈስ ውሀ በማየታቸው “እውነትም እየደረቀ ነው!” የሚል መንፈስ መጣባቸውና እግራቸው እየተብረከረከ እጃቸውን ወደ ሰማዩ ዘረጉ፡፡ “ፈጣሪ ሆይ! ሰማይና ምድርን ስትፈጠር ባርከህ የፈጠርከውን ሐይቅ ዘላለማዊ አድርገው፡፡ ገነትን እንዲያጠጣ ያመነጨኸውን ወንዝ እንዲነጥፍ አትፍቀድ!” እያሉ መጮኽ ጀመሩ፡፡ ጩኸታቸውን ሳይጨርሱ ማእበል ያመጣው ውሀ መጣያውን ሞልቶ “እሹዋዋዋ….እሽዋዋ!” ብሎ ሲፈጠፈጥ አዩትና ሲቃ ይዟቸው “ተመስገን… ተመስገን….እንዲህ ነው እንጅ….ተመስገን!” ብለው መጨዋቻ እያሳዩ “እ..ን..ግ..እእ…” እያሉ እንደሚያጫውቱት ህጻን ፈገግ አሉ፡፡ ማዕበሉ ሲያልፍና የዓባይ ፏፏቴ ተመልሶ ትንሽ ጅረት ሲመስል መጨዋቻውን እንደተነጠቀ ህጻን ፊታቸውን አኮሳተሩና ሊያለቅሱ ዓይናቸው በእንባ ደመና ሸፍነው “ራሳቸውን እንደ ቅንቡርስ አወፍረው አንተን በምን ክር አቀጠኑህ ግዮን?” ሲሉ ዓባይን ጠየቁት፡፡ ዓባይ ግን እሮሮውን በሰነነ የውሀ ቋንቋ እያንጎራጎረ መጓዙን ቀጠለ፡፡ በሰነነ እንጉርጉሮውን ያዘኑት አባ ባህሩም “አወይ ግዮን! ባዕዳን ልጓም ልከውብህ ከሃዲዎች ለጉመውህ አንበሳው ግዮን መናገርም ተሳነህ!” አሉና እንባቸው ያወፍረው ይመስል ዓይናቸውን የጋረደውን ዳመና አዘነቡለት፡፡

አባ ባህሩ አሞታቸው ኮስታራ፣ ልባቸው ደንዳናና እምነታቸው የጠነከረ ቢሆንም የዓባይና የጣና ጉዳይ ሲነሳ መንፈሳቸው ይረበሻል፡፡ የዓባይና የጣና ጉዳይ ሲነሳ እኒያን የሚያህሉ ሊቅ፤ እኒያን የሚያህሉ መምህር፣ እኒያን የሚያህሉ ፈላስፋ፣ እኒያን የሚያህሉ መንፈሳዊና እኒያን የሚያህሉ አባት ሆዳቸውን ባርባር ይለዋል፡፡ የዓባይን፣ የጣናንና የእርሳቸውን ግንኙነት ለማወቅ ወይ ዓባይን፣ ወይ ጣናን አለዚያም እርሳቸውን መሆን ይጠይቃል፡፡ ዓባይና ጣና ለአባ ባህሩ የፍጥረታት ምንጭ ናቸው፡፡ ዓባይና ጣና ለአባ ባህሩ አጥንታቸው፣ ስጋቸው፣ደማቸው፣መንፈሳቸውና ህሊናቸው ናቸው፡፡ ዓባይና ጣና እርሳቸውን ከፈጣሪ የሚያገናኙ የእትብት ገመዶች ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት “ዓባይና ጣና ችግር ገጠማቸው!” እየተባለ በተነገራቸው ቁጥር አጥንታቸው እየተገነጣጠለ ሲወድቅ፣ ሥጋቸው እየተቆራረጠ ሲጣል፣ ደማቸው እየተንደቀደቀ ሲፈስ፣ መንፈሳቸው እየቀለጠ ሲወርድ ይሰማቸውና “የጥፋት ውሀን ያስቆምክ፤ ሶዶምና ገሞራን ያበረድክ አምላክ በዓባይና በጣና የመጣውን አደጋም መልስ” እያሉ ሲጸልዩ ውለው ያድራሉ፡፡ ይኸንን ጸሎት በዚህ እለትም ጪስ ዓባይ ሲጸልዩ አድረው በነጋታው ሆዳቸውን ባርባር እያለው ወደ ጣና ጉዞ ጀመሩ፡፡

“ጣና ለመድረስ ብዙ ይቀረናል?” ሲል ጠየቀ ዲያቆኑ፡፡ “አሁንማ ተጠግተናል፤ ብዙም አይፈጅብንም!” ብለው ሳይጨርሱ “ጣናን ለማየት ቸኩያለሁ!” አለ ዲያቆኑ በስም እንጅ በአካል አይቶት ስለማያውቅ፡፡ “ዓባይና ጣና የሕይወት መጀመሪያዎች ናቸው! ዓባይና ጣና የእምነት መጀመሪያዎች ናቸው! ዓባይ የሙሴን ጥላት አንከብክቦ ጣና ሲያደርስ ባለማተቡ ጣናም የተረከበውን ጥላት ለሺህ ዘመናት ጠብቋል፡፡ በጣና ገዳማት ቤተምኩራቦችንና የኦሪት አምልኮት ጽዋዎችን ዛሬም ታገኛለህ፡፡ በጣና ገዳማት የሃይማኖት ሊቃውንትን፣ የፍላስፎችንና የነገስታትን የብራና ጥሑፎች ታገኛለህ፡፡ በጣና ገዳማት የኖኅን መርከብ የሚመስለውን የዳጋ እስጢፋኖስ ቤተከርስትያን ታያለህ፡፡ በጣና አካባቢ በጥፋት ውሀ ዘመን ኖኅ ለዘር የመረጣቸውን እንሰሳት፣ እጸዋትና ሰዎች ታጋኛለህ፡፡ ባጠቃላይ ዓባይና ጣና የእግዚአብሔር ዕደ ጥበቦች ናቸው” እያሉ ሲያስተምሩት ዲያቆኑ “እግዚአብሔር ይፈጥራል ሳጥናኤል ያጠፋል” ብሎ የተማረውን በግዕዝ አሰረው፡፡

አባ ባህሩ ዲያቆናቸውን ስለ ዓባይና ጣና እያስተማሩት ሁለት ቀናት ተጉዘው ባህርዳር እንደ ደረሱ የጊዮርጊስ ቤተክርስትያንን ተሳለሙና ጣናን ሊያዩ ተግዮን ሆቴል ጀርባ ሄዱ፡፡ አረም የለበሰ ፎቶግራፉን ያዩት ጣና ፍንትው ያል ብልኮውን ደርቦ አንቱ እንደተባሉ ሽማግሌ ሲኩነሰነስና ሲጎማለል ስላዩት “ክብሩ ይስፋ መድሃኒዓለም” ብለው የምስጋና ፀሎት አደረሱ፡፡ በነጋታው ዲያቆኑ የሰሌን አኮፋዳ ሸጦ ባጠራቀመው ገንዘብ የደንገል ጀልባ ተከራይተው ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ሄዱ፡፡ የዳጋ እስጢፋኖስ መነኩሳት እንደ ተለመደው እግራቸውን አጥበው ከገዳም አሳደሯቸው፡፡ በማግስቱ ረፋዱ ላይ አባ ባህሩ ከጣና ዳር ቆመው ወደ ደንበያ ሲመለከቱ አረንጓዴው መርዝ ዘንችሮት እሳት እንደነካው ላስቲክ ጣና ተኮማትሮ ሲያዩት “እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ!” ብለው ዓይናቸውን ሲጨፍኑ እንቅፋት መታቸውና ወደቁ፡፡ ተወደቁበት ተነሱና አሁንም “እግዚኦ መሀርነ ክርስቶስ! እግዚኦ መሀርነ ክርስቶስ!” እያሉ ባራቱም አቅጣጫ አማትበው “አገር ጉድ በል! ዓለም ጉድ በል” ብለው በሐይል ጮኹ፡፡ “እብድ ይጮኻል!” እያለ የገዳሙ ሰውና ጎብኝው ሲወጣ! ወደ መጣው ሕዝብ ዘወር አሉና ” ጣናን ይኸንን ያህል አረም ሲመጠው ገላጋይ ያጣው ምን ሸር ቢዘረጋለት ነው? ያባይን ኮረንቲ ለባዕዳን ሊሸጡ የቋመጡት ባህሩ ኩሬ ሲሆን ምን እያደረጉ ነው! ተጣና ገዳማት የሚታለበው ወተት እሚናጠው የት ነው? በቤተክርስትያናችን የሚነግደው ወገብ ሰባቂና መቋሚያ ነቅናቂ ካህን አስራቱንና ስለቱን ጣናን ለማሳከም እማያውልበት በምን መተት ታስሮ ነው? ጣና እየደረቀ ነው! ዓባይም ሊቆም ነው! ሳጥናኤል የመለኮትን ዕደ ጠበብ እየሰባበረው ነው! የመለኮትን ዕደ ጥበብ ሳጥናኤል ሲሰበር የተባበረ ወይም በችልታ የተመለከተን ገዝቻለሁ! ገዝቻለሁ! ገዝቻለሁ!” እያሉ ላባቸው እስቲንጠፈጠፍ  ጮኹ፡፡ ያባ ባህሩን ግዝት የተቀበሉ አንዲት መነኩሲት “እልልል!! እልልል! እልልል! በመጨረሻም የፍጥረትን መጀመርያ ጣናንና ዓባይን እሚታደግ  መልእክተኛ ላከልን!” ሲሉ ሕዝቡም ተከተሎ “እልልልል… እልልል… እልልል…” እያለ እልልታውን ለአምስት ደቂቃዎች አቀለጠው፡፡

እልልታው ሲታገስ አባ ባህሩ የደረቀውን ጉረሯቸውን በሰጧቸው ውኃ አረጠቡና “ሕዝብ ሆይ! ተስራኤላውያን ስህተት ትምህርት እንውሰድ! መታገል ሀገርን ተመነጠቅ በፊት ነው! መታገል እግዚአብሔር ፍጡራንን መፍጠር የጀመረበት ባህርና ወንዝ ሳይደርቅ ነው!” ሲሉ “ልክ ነው! እውነት ነው!” እያለ አድማጩ አጨበጨበ፡፡ ጭብጨባው ሲታገስም “ጪብጨባ በሥራ መታዬት አለበት፡፡ ያዕቆብ በሥራ ያልታዬ እምነት ሙት እንደሆነ አስተምሯል! በግብር የማይታይ ጪብጨባም ሆነ ጸሎት ጭንጋፍ ነው! በሥራ ያልተደገፈ ፀሎት የእግዚአብሔርን በር አይከፍትም፡፡ የእግዚአብሔርን በር የሚከፍት ማንኳኳት እሚችል ሰራተኛ ነው፡፡ እግዚአብሔር እሚሰራ እንጅ ሰነፍ አይወድም! እግዚአብሔር ፈሪም አይወድም! እግዚአብሔር ተመንታ መንገድ የቆመን አይወድም፡፡ እግዚአብሔር አስመሳይና ሆዳምም አይወድም!” እያሉ እንደ ከበሮ መቺ አንዴ ጉልበታቸውን ሸብረክ ሌላ ጊዜ በጥፍራቸው እየቆሙ ሲያስተምሩ “ተማር ካህን፣ ተማር ምዕመን፣ ተማር ውሀው፣ ተማር መስኩ፣ ተማር ተራራው” አሉ አንድ በአባ ባህሩ ትምህርት የረኩ መነኩሴ፡፡ አባ ባህሩም መነኩሴው ተራራው ሲሉ ተራራዎች ትዝ አሏቸውና አንዴ ወደ ራስ ደጀን ሌላ ጊዜ ወደ በላያ ተራራ እየተመለከቱ “አንተ የሲና ተራራ ስንቱን ግፍ በዝምታ አሳለፍክ! ሙሴ በዘንግ የከፈለው ባህር ሲሄድ ዝብለህ ተመለከትክ! አንተኑ ሲሰርቁም ዝም አልክ! አሁንም የዘፍጥረቱ ባህር ሲደርቅና ኤደንን እሚያጠጣው ወንዝ እንደ ክር ሲቀጥን ታደፍጣለህ፡፡ እስተመቼ ታደፍጣለህ? እስተመቼ ዝም ትላለህ? ዝምታህን እምተሰብረው መቼ ነው? ድምፅ እምታሰማው መቼ ነው?” እያሉ ሲጠይቁ “ዛሬ ነው! ዛሬ ነው! ዛሬ ነው” እያለ ሕዝቡ ተራራው የተጠየቀውን ጥያቄ መለሰው፡፡

የሕዝቡ ያልተጠበቀ መሰባሰብ እጅግ ያሳሰበው የበፊቱ ሻምበል ብሉፅ ያሁኑ አባ ገሪማ “የሙን እብዱ ነው እሙቦጠቡጠው!” ሲል “ጣናን አድኑ ማለት መበጥበጥ ነው!” ብሎ መለሰ አንድ ጀልባ እሚነዳ ጎበዝ፡፡ “ቡኣ! ጣና ደረቀ እያለ እሙጮህ ውሀውን አያይም? እውር ነው!” ሲል አባ ገሪማ አሁንም ጀልባ ነጂው “አንተስ ውሀ መጣጩ አረንጓዴ መርዝ ማዶ አይታይህም?” ብሎ ሲጠይቅ አባ ገሪማ የለበጣ ሳቅ ሳቀና “አሩንጓዴውማ ልማት ነዋ፤ አሁንስ የማልወደውን መንግስቱ ኃይለማርያምን ልታስታውሱኝ ነው! ደርግ መንግስቱ ወርቅ ሲያነጥፉላችሁም ፋንድያ ነው ትላላችሁ ብሎ ነበር፡፡ እናንተ ትምክተኞችም የለማላችሁን ልማት አሩንጓዴ መርዝ ትላላችሁ! መሬቱም ውሀውም ሲለማ አትወዱም ልበል ቡኣ” እያለ ሲደነፋ “ሐይቅ እሚያደርቅ ልማት?” ብላ አንድ ጎብኝ ሴት አባ ገሪማን አፋጠጠችው፡፡ “ውሀ መቺ ደረቀ! ይኸው መንጋ ውሀ አለ!” አለ አባ ገሪማ በባህርዳር ገጥ ያለውን ጣና እየጠቆመ፡፡ “ጣና ድሮ እንደዚህ ትንሽ ነበር” ብሎ ሌላ አንድ ጎብኝ ሲጠይቀው “ኩሬ የሌላቸው ክልልሎችም አሉ! ላማራ ክልል ይኼ ሲበዛበት ነው ቡኣ” አለ አባ ገሪማ ሕዝቡ በጥያቄ ሲያዋክበው ተናዶ!

አባ ባህሩ “እንኳን የራሳችን የዓለም ሕዝብ ጣናን እንዲያድን የእግዚአብሔር አደራ አለበት!” እያሉ በርትኡ አንደበታቸው ስብከታቸውን ሲቀጥሉ የገዳሙና ጎብኝው ሕዝብ እየተጠራራ በነቂስ ወጣ፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት አባ ገሪማ የሚል ስም ተሰጥቶት ደቀ እስጢፋኖስን  እንደ ፈርንጅ ላም እንዲያልብ የተላከው ሻምበል ብሉፅ ለስለላ ያሰማራቸው መነኩሴ ካድሬዎችም ተሯሯጡ፡፡ ከሰላሳ ደቂቃዎች በኋላ አንዱ ሰላይ መነኩሴ ወደ አባ ገሪማ ጆሮ ጠጋ አለና “ይህ ሰው ተሃያ አራት ዓመታት በፊት እንዲሞት እጅና እግሩን ታስሮ ጣና ተወርውሮ የነበረ ሰው ነው! በታምር ተርፏል” አላቸው፡፡ አባ ገሪማ በመገረም “ለምንድን ነበር የተወረወረው” ብሎ ሲጠይቅ “የማይበላ የማያስበላ ገገማ ነፍጠኛ ስለሆነ ነዋ” አለና ገለፈጠ ሰላዩ፡፡ አባ ገሪማ ይኸንን ሰላይ አድንቆና አመስግኖ ፌደራል ፖሊስ ባስቸኳይ እንዲላክለት ባህር ዳር ደወለና አባ ባህሩ ካሉበት ውሀ ዳር ቆሞ የለበጣ ሰላምታ አቀረበ፡፡ አባ ባህሩ ግን ፍየል የቦጠቦጠው ችፍርግ የመሰለውን አባ ገሪማ ዝቅዝቅ አይተው ችላ ሲሉት “ምነው ቹግር አለ?” ሲል ጠየቀ፡፡ “እንደ እባብ ምድር ለምድር እየተሳብክ ባይታይህ እንጅ እዚያ ማዶ ትልቅ ችግር አለ!” አሉ አባ ባህሩ ፊታቸው ሊውጥ የተዘጋጀ አንበሳ መስሎ ከንፈራቸው እየተንቀጠቀጠ፡፡ “ቹግር ቢኖርም በውይይት፣ በምክክር፣ በጥርነፋ፣ በሂስ፣ በግለ ሂስና በዲሞክራሲ ይፈታል” ብሎ ሳይጨርስ የቆመበት ድንጋይ ተንሸራተተና ጣና ውስጥ ወደቀ፡፡ አባ ገሪማ በአቸፈርና በደንበያ ማኛ፤ በጎርጎራና በዳሞት ሰንጋ ቁርጥ የካናዳ ኬሻ የመሰለ ሆዱን ተሸክሞ የእንግላል ሰመጠ፡፡ አባ ገሪማ እንኳን ሊዋኝ እግሩንም ኩሬ ውስጥ ገብቶ ሰለማያውቅ የፊዚክስ ሕግ ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አድርጎ ለመጨረሻ ጊዜ ሊያሰምጠው ሲል ሶስት አሳ አጥማጆች እንደ ዶልፊን ዘለሉና እንደ ክብ ወፈጥ ተሸክመው አወጡት፡፡

ሕዝቡም ጣናን ለጊዜው ረስቶ የአባ ገሪማን ሕይወት ማትረፉ ላይ ሲረባረብ ጣናነሽ የተባለችዋ መርከብ ላውንቸር የደቀኑ የፌደራል ፖሊሶች ይዛ ስትመጣ ከሩቅ ተመለከተ፡፡ የሰው ባህሪ የሌላቸውን የፌደራል ፖሊሶች የተመለክቱ የገዳም ሰዎች አባ ባህሩን እንዲሸሹ ለመኗቸው፡፡ አባ ባህሩ “አልሸሽም! እሚገሉት በእንቅፋት ሊረግፍ የሚችለውን ሥጋዬን እንጅ ነፍሴን አይደልም፤ ተዚህ በፊት ገድለውኝም ተነስቻለሁ!” ብለው ማንነታቸውን ሲገልጡ ዱሮ ያውቋቸው የነበሩ የገዳሙ ሰዎች ባካላቸው ከፍተኛ ለውጥ ሊለዩአቸው ባለመቻላቸው ተገርመው ለአርባ አምስት ሰከንዶች ፀጥ አሉና ከመቅጽበት ደሞ “እልልልል… እልልልል…. እልልል” ብለው ደስታቸውን አቅልጠው “ባህሩ ሞትን ድልነሳ! ባህሩ ሞትን ድል ነሳ!” እያሉ ጨፈሩ፡፡ ወደ ሰማይ እየጓኑ ሲጨፍሩ ከነበሩት ወጣቶች ግሼ ዓባይ ያደገ ሰፈፈ በላይ እሚባል ጀልባ ነጂ “እኒህን ሰውማ አናስነካም!” አለና ተሸክሞ ተጀልባቸው አስቀመጠና ወደ ዘጌ መንዳት ጀመረ፡፡ አባ ባህሩም ሰፈፈ በላይን “ባይሆን እንድዋኝ ፍቀድልኝ!” ሲሉት “ዋና ይችላሉ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ “በጥልቂያ ፈትነኝ!” ብለው ቀለዱና ዘለው ከውሀው ጥቡልቅ አሉ፡፡ እጆቻቸውን ግራና ቀኝ ዘርግተው ባካላቸው መስቀል ሰሩና ውሀውን ብዙም ሳያንቀሳቅሱ ጀልባዋን ቀድመው እንደ አሳ ተንሳፈፉ፡፡ “ሙሴ በዘንጉ የከፈለውን ባህር እየንታ በክንዳቸው ከፈሉት” አለ አብሯቸው የተሳፈረው ዲያቆናቸው፡፡ የአባ ባህሩን ዋና የተመለከቱ ከአዲስ አባባ የመጡ የዳጋ እስጢፋኖስ ጎብኝዎች በዓለም የዋና ውድድር ያንን ዘረጦ ልከው ከሚያዋርዱን አባን ቢልኳቸው ፈረንጅን አስከንድተው የወርቁን ዋንጫ ይዘውት ሸገር ይገቡ ነበር” ሲሉ አገራቸው በመዋረዷ ተቆጩ፡፡ አባ ባህሩ የልጅነት ትዝታቸው እየመጣባቸው አንዴ እንደ ዶልፊን ዘለው እየጠለቁ ሌላ ጊዜ እንደ አሳ እየሰመሙ ሲያስፈልጋቸውም እንደ ዳክዬ እየተንሳፈፉ ሲደክማቸውም ተጀልባው እየወጡ ወደ ዘጌ ነጎዱ፡፡

ፌደራል ፖሊሶችን የጫነችው ጣናነሽ ዳጋ እስጢፋኖስ እስከምትደርስ እነ አባ ባህሩ የዘጌን ጉዞ አጋመሱ፡፡ ፖሊሶች ዳጋ እስጢፋኖስ ከደረሱ በኋላም ለአባ ገሪማ ነፍስ ቅድሚያ እንዲሰጡ ስለታዘዙ ጣናነሽ አባ ገሪማን ይዛ ወደ ባህርዳር እንድትመለስ አደረጉ፡፡ ሌላ ጀልባ እስተሚላክላቸው ገዳሙን መዝረፍና የገዳሙን ሕዝብ መደብደብ ጀመሩ፡፡ አባ ገሪማን እንደ ዶልፊን ዘለው ገብተው ያወጧቸው አሳ አጥማጆች “አባ ገሪማ ገፍትረው ጥለውኛል!” ብለው ተናግረዋል በሚል ወንጀል ተያዙ፡፡ ሁለተኛዋ ጀልባ ለፖሊሶቹ እንደደረሰች ላውንቸራቸውን ደቅነው አባ ባህሩን ለመያዝ ወደ ዘጌ መንዳት ጀመሩ፡፡ ጀልባዋ ግማሹን ጉዞ እንደተጓዘች ስትገለበጥ ከነጂው ከጎርጎራው ልጅ ወሮታው ሙጬ በቀር ሁሉም ፖሊሶች ዋና ስለማይችሉ ሰመጡ፡፡ የጀልባዋን መስመጥ የተመለከቱ አባ ባህሩና ሰፈፈ በላይ ዘጌ አጠገብ ከደረሱ በኃላ ተመለሱና ወሮታውንና የጫነውን መሳሪያ ይዘው ዘጌ ገቡ፡፡

“ወሮታው ገድል ፈጠመ” ሲል ሰፈፈ በላይ ዲያቆኑ ቀለብ አደረገና “ምንትስ ምንትስ … ወሮታ ብሎ” በግዕዝ ተናገረ፡፡ “ይኸንን ገድል በመፈጸምህ ቋንጃዋን የቆረጧት ቤተክርስትያንህና እያደረቋቸው ያሉት ዓባይና ጣና ምን ወሮታ ይክፈሉህ ማለቱ ነው!” ብለው አባ ባህሩ የዲያቆኑን ግዕዝ ሲተረጉሙት ወሮታው “ገና ምን ሰርቼ! ምን ፈጥሜ ወሮታ ይከፈለኛል? የቤተክርስትያኗ፣ የጣናና የዓባይ ብዙ እዳ አለብኝ! የጣና ገዳማትን ዕንቁ ቅርጾችና ጽላቶች ሲዘርፉ እያየሁ ምን አደረኩ! ከሐይቁ፣ ተገዳማቱና ተደሴቶች ቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ሲሞጨለፍ እያየሁ ምን አረኩ? ጣናን አረም አስወርረውና በመስኖ ጠልፈው ሲያደርቁት እያየሁ ምን ፈጠምኩ? ወልቃይት፣ዳንሻ፣ ዳባት፣ ደባርቅ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ጎንደር፣ ቆላድባ፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ጢስ ዓባይ፣አዴት፣መራዊ፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ፣ ፍኖተሰላም፣ ቋሪት፣ ደንበጫ፣ ደብረማርቆስ  ደም እንደ ጅረት ሲፈስ ምን አረኩ? ይልቅስ እኔ ገና ብዙ ወሮታ መክፈል ይጠበቅብኛል!” ብሎ እንባውን ሲያፈስ ሁሉም መቆጣጠር ያልቻሉትን የቁጪት እንባ አብረውት አንዠቀዠቁ፡፡

እንባ ተራጪተው ሰክንዶች እንዳለፉ አባ ባህሩ “ምንትስ ምንትስ…” ብለው በግዕዝ ተናገሩና መልሰው ባማርኛ “የፈሰሰ ደምና እንባ ከንቱ አይቀርም፡፡ የፈሰሰው ደም የእግዚአብሔር ፍጡር ደም ነው፡፡ የፈሰሰው እንባም የእግዚአብሔር ፍጡር እንባ ነው፡፡ እየደረቀ ያለው ባህርም እግዚአብሔር የፈጠረው ባህር ነው፡፡ እየደረቀ ያለው ወንዝም እግዚአብሔር እያቆላመጠ ሁለተኛው ወንዝ እሚለው ግዮን ነው፡፡ እየጠፋ ያለው የእግዚአብሔር ዕደ ጠበብ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዕደ ጥበብ ሲጠፋ አጥፊውን ሐግ እማይል ተሳጥናኤል የተሰለፈ ብቻ ነው፡፡ እኛ ተሳጥናኤል ስላልተሰለፍን የንጹሐንን ደምና እንባ እሚያፈሰውን፤ ባህርና ወንዝ እሚያደርቀውን ሳጥናኤልን እንፋለማለን” ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አድማጮቹ  “አወን! ሰይጣንን እንፋለማለን!” አሉና የተቆጣው ጣና ካሰመጣቸው ሰውበላ ፖሊሶች የማረኩትን መሳሪያ ይዘው ወደ በላያና ቋራ ተራሮች መጓዝ ጀመሩ፡፡ አባ ባህሩም እንደ አድዋ ዘማች ካህን በአንድ እጃቸው መስቀል በሌላኛው መሳርያ ተሸክመው በአእምሯቸው ቤተከርስቲያናቸውን፣ በልባቸው ዓባይን፣ በአንጀታቸው ጣናን አዝለው ተከተሉ፡፡

ሐምሌ ሁለት ዘጠኝ ..

The post ጣና ዓባይና አባ ባህሩ አንድም ሶስትም – በላይነህ አባተ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አማራና መሬት፤ ወያኔና የአማራ መሬት ዝርፊያ – መለክ ሐራ

$
0
0

ሳሚ የሚባሉ ህዝቦች በሰሜናዊ ስካንዲኔቪያ እና ሩሲያ ይኖራሉ፡፡ ሬይንዲር ወይም የበረዶአማ አጋዘን የተባለውን እንስሳ በአንድ ሽህ የተለያዩ ስያሜዎች ይገልጹታል፡፡ ኢስኪሞ የሚባሉት በሰሜናዊ አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ህዝቦች ለበረዶ ከ50 እስከ መቶ የሚሆኑ ስሞች ይሰጡታል፡፡ ማለትም በረዶን በ50 እና ከዛ በላይ የተለያዩ ስሞች በመጠቀም ይገልጹታል፡፡ በአረብኛ ቋንቋ ግመል አንድ ሽህ ስሞች አሉት፡፡ በአፋር ግመል ወደ 13 ስሞች አሉት፡፡ እነዚህ ህዝቦች ለተዘረዘሩት ነገሮች ብዙ ስም የሰጡበት ምክንያት ህይወታቸው በቀጥታ በእነሱ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፡፡ ለሳሚዎች የበረዶ አጋዘን ማለት ጠቅላላ ህይወታቸው የተመሰረተበት ነው፡፡ ስለዚህም ከእሱ ውጭ ህይወት የማይታሰብ ነው፡፡ ለዛም በተለያዩ ስሞች ይጠሩታል፡፡ ለኢስኪሞ ወይም ኢኑይቶች ህይወት ያለበረዶ ምንም ነው፡፡ በረዶ ቤታቸው፤ መጠጣቸው፤ የአደን ቦታቸው፤ መዋኛቸው..ወዘተ ነው፡፡ ግግር በረዶ የለም ማለት እነሱ የሉም ማለት ነው፡፡ አረብና ግመል በቀጥታ የተያያዙ ስለሆነ አንድ ሽህ ስሞች የተሰየመበት ምክንያት የግመልን አስፈላጊነት የሚያመለክት ነው፡፡ ለአረብ ግመል ህይወት ነው፡፡ ለአፋርም እንደዚሁ፡፡ ግመል በአፋር ህይወት ውስጥ እጅግ መሰረታዊ ከመሆኑ የተነሳ በ13 የተለያዩ ስያሜዎች ይጠሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ያለግመል ህይወት ለአፋር አስቸጋሪ ነች፡፡

የአማራን የህይወት ትስስር ስናይ መሬትን በቅድሚያ እናገኛለን፡፡ አማራ ያለመሬት ምንም ነው፡፡ መሬት በጣም ትልቁ ዋጋ ያለው ነገር ነው፡፡ ማንም አማራ ለመሬት የሚሰጠውን ዋጋ ለምንም አይሰጥም፡፡ በዚህም ምክንያት አማራ መሬትን በብዙ ስሞች ይጠራዋል፡፡ አማራ መሬትን መሬት፤ ምድር፤ ባድማ፤ ኩራ፤ ወጀድ፤ ጓሮ፤ ማሳ፤ ጥማድ፤ እርሻ፤ መስክ ወይም ሜዳ፤ ርስት፤ ጉልት፤ አገር፤ ሀገር፤ ውርስ፤ ድንጅ፤ ቀየ፤ መንደር፤ ዙሪያገባ፤ እትብት የተቀበረበት፤ ጉልማ፤ ድንበር ፈሰስ፤ ዞታ ወይም ይዞታ፤ ዲበ ቀብር፤ አጥቢያ፤ ግድም፤ ምሪት፤ እና ወዘተርፈ ብሎ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡ ከዚህም በመነሳት መሬት በአማራ ህይወት ውስጥ እጅግ መሰረታዊ እና ወሳኝ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ከዚህም በመነሳት ርስት በሽህ አመቱ ለባለቤቱ ይባላል፡፡ ምንም ይሁን ምንም ርሰትህን ከሽህ አመት በኋላ ቢሆን ተከራክረህ ማስመለስ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ርስቱን ተቀምቶ የቀረና ያላስመለሰ በማህበረሰቡ እንደሰው ስለማይቆጠር እና ቀሪ ዘመኑን የተዋረደ ሆኖ ስለሚኖር፡፡ ርስት በሽህ አመቱ ለባለቤቱ የሚለው ብሂል በአማራ ውስጥ የመሬትን አስፈላጊነት የሚያመለክት ነው፡፡ የጨዋ ልጅና ድንች ከባድማው አይጠፋም የሚለው ንግግር ራሱ ትልቅ መልእክት ያለው ነው፡፡ ድንች መዘራት ከመጀመረ ከብዙ አመት በኋላ ድሮ ተዘርቶበት የነበረው ቦታ ላይ ከሌላ ማሳ ጋር ይበቅላል፡፡ እናም ዘሩ የማይጠፋ እህል ነው፡፡ አማራም በቀጥታ የዚህን ምሳሌ ነው ለጨዋ ልጅነት መታወቂያ ያዋለው፡፡ ልክ እንደ ድንች ሁሉ የጨዋ ልጅ ከአባቱ ባድማ አይጠፋም፡፡ ከባድማ ወይም ከመሬት አለመጥፋትም የጨዋ ልጅነት ምልክት ነው፡፡ ይህም የመሬትን ላቅ ያለ ዋጋ ያመለክታል፡፡

እናም አማራ ከመሬት ጋር እጅግ የተቆራኘ ህዝብ ነው፡፡ በባህሉም በትንሽ የድንበር መገፋፋት ራሱ እርስ በእርስ ሊጨካከን የሚችል ነው፡፡ ድንበር ክቡር ናት፤ መሬት ህይዎት ናት፡፡ በሚስትና በርስት ቀልድ የለም ሲልም ለንግግር ማሳመሪያ ብቻ አይደለም፡፡ በተግባር የሚገለጽ ነው እንጅ፡፡ የመሬት ጉዳይ ቀልድ ሆኖ አያውቅም፡፡ መሬት ከጠቅላላ ህይዎቱ ጋር ስለተሳሰረ አማራና መሬትን ነጣጥሎ ማሰብ አያችልም፡፡ አማራ ያለመሬት ህይወቱን አስቧት አያውቅም፡፡ ጠቅላላ ማህበረሰባዊ መሰረቱም መሬትና በመሬት ዙሪያ የተገነባ ነው፡፡

እናሳ? እናማ ወያኔ የዚህን ህዝብ ከመሬት ጋር በጥብቁ የተቆራኘ ትስስር ለማጥፋት እና ለማዳከም ቆርጦ ተነሳ፡፡ የአማራ ማንነቱ የተሳሰረው እና ሀብቱ የሚመነጨው ከመሬት ነው፡፡ ፖለቲካዊ፤ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማህበራዊ መሰረቱ መሬት ነው፡፡ ወያኔም መሬትና የአማራን መሰረቶች ለመናድ መፍጨርጨሩን ተያያዘው፡፡ ብዙ ጊዜ ይገርመኝ የነበረው ነገር መለስ አገር ማለት ህዝብ እንጅ መሬት አይደለም የሚለው ለበጣ ነበር፡፡ ፊት ለፊት አግኝቶ የሚያወራው ወሬ ፍሬ ከርስኪ መሆኑን መንገር ነበር እያልኩ ስመኝ ነበር፡፡ መሬት አገር አይደለም፤ አገር ማለት ህዝብ ነው ብሎ ሲያላግጥ እሱን ተከትለው የሚነፍሱ ሰዎች ብዙ ጊዜ አይቻለሁ፡፡ የተከራከርኳቸውም አሉ፡፡ ግን እደትልቅ መገለጥ ቆጥረውት ከመደጋገም እና ከመደነቅ ውጭ ምን ማለት ነው ብለው ሲያስቡት አላየኋቸውም፡፡

ግን የመለስና የወያኔዎች መሬት ሳይሆን አገር ህዝብ ነው የሚል ስላቅ በመሰረቱ የዜሮ ብዜት ነው፡፡ መጀመሪያ የተፈጠረው መሬት ነው፤ ሰውም፡ መለስን ጨምሮ፡ ከአፈር ነው የተፈጠረው፡፡ መሬት ሳይረግጥ አየር ላይ የሚኖር የለም፡፡ ስለሰው ለማውራት መጀመሪያ ማረፊያ ቦታ ያስፈልጋል፡፡ ምንም እንኳ ከሰው ቀድሞ የተፈጠረው መሬት ቢሆንም አንዱን ከአንዱ ማበላለጥ አያስፈልግም ነበር፡፡ በእርግጥ መሬት ያለ ሰው ሊኖር ይችላል፤ ሰው ግን ያለመሬት አይኖርም፡፡ ሰው ይኖር ዘንድ መሬት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ መሬት ይኖር ዘንድ ግን ሰው አስፈላጊ አይደለም፡፡ በዚህም እሳቤ ሰው የመሬት ጥገኛ ነው እንላለን፡፡ የመለስ ፍልስፍናም እዚህ ላይ እርቃኗን ቆማ ትታይ እና ማሰብ በሚችል አእምሮ ውስጥ ትከስማለች፡፡

መለስ ግን መሬት ሳይሆን አገር ማለት ህዝብ ነው ሲል በእርግጥ ህዝብ እየወደደ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እሱ በውስጡ የሚወደው መሬትን ነው፡፡ መሬት ላይ ገንዘብ ይታፈሳል፡፡ ኪስና ሆድም ይሞላል፡፡ በዚህ በኩል ወገኖቹን የሌላ ብሔረሰቦች መሬት በማደልና በመሸጥ ኪሳቸውን ይሞላል፤ በዛ በኩል መሬት እኮ ምንም ማለት አይደለም ይላል፡፡ ቅድሚያ ህዝብ እያለ ያላግጣል፡፡ መሬት ህዝብ ካልሆነ ታዲያ የወሎን፤ የጎንደርን መሬት ህዝቡን እየጨፈጨፉ መውሰድ ለምን አስፈለገ? የጋምቤላን እና ጉምዝን መሬት መዝረፍ ለምን አስፈለገ? ከጎንደርና ወሎ መሬትና ህዝብ መሬት በልጦ ነው ህዝቡ የተጨፈጨፈው እግዲህ፡፡ ይህንን ግን ገልብጠው መሬት ለምኔ ህዝብ እንጅ እያሉ ያላግጣሉ፡፡ እዚህ ጋር አንድ ታሪክ ታወሰኝ፡፡ መለስ ለብቻው ይኖርበት የነበረውን እና አሁን ወያኔዎች በቡድን የሚኖሩበትን የዳግማዊ ምኒልክ ቤተመግስት የአያቴ ይዞታ ነው ይመለስልኝ ብሎ የሚከራከር ሰው እንዳለ ሰምቻለሁ፡፡ ታዲያ በቤተ መንግስት አጠገብ ባለፍኩ ቁጥር ትዝ የሚለኝ ያ ግፉአን ሰው ነው፡፡ መለስ ግን ተራራና ወንዝ፤ ሜዳና ሸለቆ አልፈልግም ብሎ ሲያበቃ ምናለብት የዚህን ሰውየ መሬት ቢመልስለት እላለሁ፡፡ የሰው ጉብታ ላይ ተጎልቶ መሬት ምን ያደርጋል ህዝብ ነው እንጅ እያለ ያላግጣል፡፡

ወያኔዎች መሬትን የጠሉበት እንግዲህ ከአማራ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ትግል ሲጀምሩ አማራ ብዙ መሬት ይዟል፤ ፊውዳል ነው፤ የመሬት ከበርቴ ነው ብለው ነው፡፡ ስለዚህ አማራ መጥፋት አለበት ብለው ሲደነግጉ የአማራ ሀብት የሆነውን መሬት ሁሉ ጨምረው ነው፡፡ መሬት ለአማራ የኩራቱ ምንጭ ነው፡፡ ስለዚህ የመሬትን አፋዊ ዋጋ በማኮሰስ የአማራን ኩራት መግደል አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ፡፡ ከመሬቱ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላለውም አማራን የማጥፋቱ ሂደት ከባድ ሆነ፡፡ ስሆነም እየደጋገሙ መሬት ዋጋ እንደሌለው፤ አገር ማለት ህዝብ እንደሆነ በመለፈፍ አማራውን ከመሬቱ ጋር የስነልቡና ፍች እንዲያደርግ ጣሩ፡፡ አማራው ስለመሬት ያለው ጠንካራ ግንዛቤና ትስስር ከላላ በቀላ ማፈናቀልና ያንን መሬት መውረስ ይቻላል፡፡ ልክ በጎንደርና ወሎ እንደሚያደርጉት፡፡ መሬት አያስፈልግህም፤ አንተ ብቻ ኑር ይልህና ቀና ስትል መሬትህን ወስዶ አንተን ዘበኛ አድርጎሀል፡፡ ይህች ናት የመለስ ህዝብ ማት፡፡ ይህች ናት የወያኔ ህዝብ ማለት፡፡

መለክ ሐራ

The post አማራና መሬት፤ ወያኔና የአማራ መሬት ዝርፊያ – መለክ ሐራ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የጣና ሐይቅም ይደርቃል የጢስ እሳት ፏፏቴ ተሰርቋል

ኢትዮጵያና የቴክኖሎጂ ዕድገት ፈለግ ! የተጻፈ ባለ 337 ገጾች መጽሀፍ። በአቶ ታደሰ ንጋቱ – ትችት፣ በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

$
0
0

በአቶ ታደሰ ንጋቱ የማቴሪያል ሳይንቲስት ባለሙያ፣  በመጋቢት ወር 2016ዓ.ም የተጻፈ ባለ 337 ገጾች መጽሀፍ።

ትችት፣ በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ የስልጣኔ ተመራማሪ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለሙያና ለሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ታጋይ !

በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

አቶ ታደሰ ንጋቱ በመጽሀፉ የመጀመሪያው ሽፋን ላይ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለአቆዩዋት የቴኮኖሎጂ ባለሙያዎች ያበረከቱትን አስተዋጽዖ ለማመስገንና ለማስታወስ መጽሀፉን ለመጻፍ እንደተነሳሳ በዚህ መልክ ያስቀምጠዋል። ብረትን በእሳት፣ ሸክላን በውሃ፣ መሬትን በማረሻ፣ እንጨትን በስለት፣ ጥጥን በማዳወሪያ፣ ሙዚቃን በማሲንቆ፣ እየገሩ ነባራዊና ስነ-ልቦናዊ የህይወት ቁሳት በማምረት አገራችንን እንደ አገር ያቆዩልንን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቻችንን ለመዘከር „  የተጻፈ መጽሀፍ መሆኑን ይነግረናል።

መጽሀፋ በ20 ምዕራፎች የተከፈለና በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣ ደራሲው የሰው ልጅ አሳቢና ተንቀሳቃሽ ፍጡር እንደመሆኑ መጠን ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ቀስ በቀስ፣ በማየት፣ በልምድና በሙከራ እንዲሁም ከስህተቱ በመማር እንዴት ወደተወሳሰበ የህብረተሰብ ዕድገት ደረጃ ላይ ለመድረስ እንደቻለ ነው የሚያስተምረን።

ደራሲው በመንደርደሪያው ላይ ለማሳየት እንደሚሞክረው፣ የሰው ልጅ ህይወትና ቲክኖሎጂ የተሳሰሩ ሲሆኑ፣ የሰው ልጅ ማንነትና የኑሮ ትርጉም ሊገለጽ የሚችለው በቴክኖሎጂ አማካይነት ብቻ  እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጣል። የሰው ልጅ ቀስ በቀስ ቴኮኖሎጂን በማፍለቅና በማዳበር የምርትን ዕድገት ማፋጠኑ ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን ከበሽታ ለመከላከልም ሆነ፣ አንድ በሽታ ከያዘው በኋላ ደግሞ ለመዳን የሚችለውና፣  ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚጓዘው በቴክኖሎጂ አማካይነት ብቻ ነው።  የባቡር ቴክኖሎጂ፣ የአውሮፕላን ስራና በአየር ላይ በመብረር ሰውን በብዙ ሺሆች የሚቆጠር ኪሎሜትር አጉዞ የተፈለገው ቦታ ማድረስ፣ የመርከብ ስራና ሰውንና ዕቃን እንደዚሁ ራቅ ያሉ ቦታዎች ማመላለስ፣ እንዲሁም በዛሬው ዓለም በስልክና እንዲያም ሲል በኢንተርኔት አማካይነት ወሬንና ኢንፎርሜሽኖችን ፊት ለፊት ሳይተያዩ መለዋወጥና የሃሳብ ተካፋይ መሆን፣ እነዚህ ሁሉ የሰው ልጅ የማሰብ ኃይል ውጤቶች እንደሆኑ ከመጽሀፉ መረዳት ይቻላል።

ደራሲው ስለቴክኖሎጂ ምንነት ሲገልጽ በዚህ መልክ ያሰፍረዋል። ቴክኖሎጂ በአንድ በኩል እንደቁሳቁስ የሚይታይ ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ ምርትን ለማምረት፣ ዕቃንና ሰውን የምናቀሳቅስበትና እንዲሁም ኢንፎርሚሽን የምንለዋወጥበት በዐይን የሚታይና በእጅም የሚዳሰስ ነው።

በሁለተኛ ደረጃ ቴክኖሎጂ ጥበባዊም እንደሆነ ምሁሩ በደንብ ያስረዳናል።ይህም ማለት በቴክኖሎጂ አማካይነት ማንኛቸውንም ነገሮች ማለትም የህንጻ ስራን፣ የመብራት ኃይልን፣ የኢንጂነሪግንና ሌሎች ቴክኒካዊ ነገሮችን ሁሉ እንድናጠናበትና እንድንመረምርበት ያገለግለናል።  ስለሆነም ቴክኖሎጂ ሚዛናዊ ግምትን ለመውሰድ፣ ምርምርን ከሙከራና ከስህተት ጋር በማገናዘብ ወደ ተፈላጊው ውጤት እንድንደርስ የሚረዳን ልዩ ዐይነት ጥበባዊ ኃይል ነው። በመሆኑም ቴክኖሎጂ የአሰራር ዕቅድን ቅደም ተከተል በሚገባ ማጤን የሚያስፈልግ እንደመሆኑ መጠን አንድ ውጤት ላይ ለመድረስ ከተፈለገ  የግዴታ የቅደም ተከተልን ህግ ማጥናት ያስፈልጋል። አንድ ቴክኖሎጂ ከጥቅሙ ባሻገር ጉዳትም ለማድረስ የሚችል እንደመሆኑ መጠን የአንድን ቴክኖሎጂ አፈጣጠርና ዕድገት ከሁሉም አቅጣጫ ማጥናት ጉዳትን ለመቀነስ እንደዚሁ ከፍተኛ ምርምር እንደሚያስፈልግ ያሳያል። በተጨማሪም ቴክኖሎጂ የህይወታችን አንዱ አካል እንደመሆኑ መጠን በየጊዜው እንክብካቤ ያስፈልገዋል።፡ በሌላ አነጋገር፣ ቴክኖሎጂ ህይወት የሌለው ቢመስልም ልዩ ልዩ ነገሮችን በጥልቀት ማየት የምንችለውና የምንመረምረው እንዲሁም ልዩ ውጤት ላይ የምንደረሰው ቴክኖሎጂ ህይወት ያለው ነገር መሆኑን የተረዳን እንደሆን ብቻና በየጊዜውም ተሃድሶ ወይም ጥገናና መሻሻል የሚያስፈልገው መሆኑን የተረዳን ብቻ ነው።

በሶስተኛ ደረጃ ቴክኖሎጂ  የተግባር መግለጫ እንደሆነ ደራሲው ያስተምረናል። በእሱ አገላለጽ

„ እውቀትን ከራእይ ጋር አዋህዶ ወደ ጠቃሚ ቁሳቁስነት መቀየር የሚቻለው በተግባር(በስራ) ነው።

በማለት፣ በተለይም በአሁኑ ዘመን አንድን ለጥቅም የሚውል ቴክኖሎጂ ለማፍለቅ የግዴታ የምርምር ስራን፣ ፈጠራን፣ ቅየሳን፣ ዲዛይንን፣ የማነጽ ስራን፣ የማምረትና ተግባራዊ ማድረግም የተያያዙ መሆናቸውን  ደራሲው ያትታል። ይህም ማለት በአለንበት ዘመን እንደጥንቱ ዘመን በዘለማድ ሳይሆን፣ ሳይንሳዊ ምርምርና የቴክኖሎጂ ፈጠራና፣ ቀስ በቀስም አስፈላጊውን የዕድገት ደረጃዎች አልፎ ተግባራዊ መሆን የግዴታ የተያያዙ መሆናቸው ወንድማችን ቁልጭ አድርጎ ያስረዳናል።

በአራተኛ ደራጃ፣ ስለሆነም ይላል የማቲሪያል ሳይንቲስት ተመራማሪውና፣ በዚህ ሙያ ከስላሳ ዐመት በላይ ልምድ ያለው ኢትዮጵያዊው ምሁር፣ ፍላጎታችንን፣ ርዕያችንና ህልማችንን ዕውን በማድረግ ሰው መሆናችንን ማረጋገጥ የምንችለው በቴክኖሎጂ አማካይነት ብቻ ነው።  ቴክኖሎጂ ከላይ ዱብ የሚል ሳይሆን ከጭንቅላት የሚፈልቅና ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በብዙ ሰዎች ተሳትፎ ዕውን የሚሆን የሰውን ልጅ ኑሮ የሚያቃልልና ሊታለፍ የማይችለው የስልጣኔና የአንድ ህብረተሰብ ዋናው የዕድገት ቁልፍና መለኪያ እንደሆነ ውድ ወንድማችን ያስተምረናል።

ከዚህ በመነሳት አቶ ታደሰ ንጋቱ የሰው ልጅ የአለፈባቸውን የቴክኖሎጂ የዕድገት ጉዞዎች ደረጃ በደረጃ በዝርዝር ያስረዳናል። እንደሚታወቀውና በምሁሩም ዕምነት በአጠቃላይ ሲታይ የሰው ልጅ በሶስት የቴክኖሎጂ ዕድገት ውስጥ እንዳለፈና ዛሬ በመጨረሻው በሶስተኛው የዕድገት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያስቀምጣል። እነሱም፣ 1ኛ) ጥንታዊ የዲንጋይ ዘመን፣ 2ኛ) አዲሱ የዲንጋይ ዘመንና፣ 3ኛ) የስልጣኔ ዘመን በመባል እንደሚገለጹና፣ የሰው ልጅም በእነዚህ የዕድገት ደረጃዎች እንዳለፈና እንደሚገኝም መረዳት ይቻላል።

በዚህ መሰረት ማንኛውም ህብረተሰብ ውስጣዊ ኃይል ያለው እንደመሆኑ መጠን እዚያው ባለበት ረግቶ የሚኖር ሳይሆን፣ የሚንቀሳቀስ፣ ከአንድ  ትንሽ ደረጃ በመነሳት፣ እያደገና እየተወሳሰበ በመሄድ የሚለወጥና ከፍተኛ የሆነ በብዙ መልኮች ወይም ገጽታዎች የሚገለጽ ማህበረሰብ መመስረት እንደሚችል ደራሲው በአጠቃላይ ሲታይ ስለሰው ልጅ ዕድገት ያስረዳናል። ይህም ማለት፣ ከእንሳሳ በስተቀር ማንኛው እንደ ማሀበረሰብ ወይም እንደ ህብረተሰብ የሚኖር የሰው ልጅ የግዴታ በመጥፎም ሆነ በጥሩ ነገር እንደየሁኔታው ሊለዋወጥ ወይም ሊቀየር እንደሚችል እንማራለን። ከዚህ በመነሳት ነው ከላይ የተቀመጠው ሶስት የሰው ልጅ የዕድገት ደረጃዎች ሊገለጹ የሚችሉትና ግንዛቤ ውስጥ የሚገቡት።

በደራሲው አቀራረብና በሌሎችም የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች ዕምነት ሁሉቱ የዲንጋይ ዘመኖች፣ ወይም የሰው ልጅ በዲንጋይ እየተጋዘ ኑሮውን ለማሸነፍ የቻለበት ዘመን ወደ ሶስት ሚሊዮን ዐመታት እንደሚያስቆጥር ነው። ዲንጋይን፣ እንጨትንና አጥንትን ወደ መቅረጽና  እንዲሁም ሀረግን በመስራት ማንነቱን ማረጋገጥ እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ውስጥ በሚከሰቱ የተፈጥሮ ቁጣዎች ሰለባ እንደነበረና ቀስ በቀስም ራሱን በማግኘት ዲንጋይን በማሾል፣ እንጨትንና አጥንትን በመቅረጽና ደጋን በመስራት ራሱን ከአደጋ ለመከላከልና በተፈጥሮ ውስጥም የሚገኙ እንስሳዎችን እያደነ መብላትና መኖር የቻለው በእዚህ ዐይነቱ  ራሱ በፈጠራቸው ቴክኖሎጂዎች እየታገዘ መሆኑን እንማራለን።

በአጋጣሚ እሳት ከተገኘ በኋላ የሰው ልጅ ህይወት ከፍተኛ ምጥቀትን ማግኘት ይጀምራል። እሳት ምግብን ለመቀቀያ፣ ለመብራትና ራስን ከአደጋ ለመከላከል፣ ለሰውነት ሙቀት መለገሺያ፣ ለብረት ማቅለጪያና መሳሪያዎችን ለመቅረጽና ለመስሪያ የሚያገልግል ልዩ ኃይል ነው። በእሳትና የኋላ ኋላ ደግሞ ኃይል(Energy)በሚባለው ልዩ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ልጅ የፈጠራ ሀብት አማካይነት ብቻ ነው የሰው ልጅ ከእንስሳ ባህርዩ ለመላቀቅና ቴክኖሎጂዎችን ቅርጽ በመስጠት፣ ሸክላን በማቃጠልና ቤት በመስራት ቀስ በቀስ መንደሮችንና ከተማዎችን በመገንባት ተሰባስቦ ለመኖር የቻለው። ይህም የሚያመለክተው በአንዳች ምክንያት ካልተዘጋ በስተቀር የሰው ልጅ ጭንቅላት ተንቀሳቃሽ የሆነና በማሰብ ኃይሉም ልዩ ልዩ ነገሮችን በመፍጠር ወደ ተወሳሰበና በስራ-ክፍፍል ወደሚገለጽ ማህበረሰብ እንደሚያመራ ነው።

በዚህም መሰረት የሰው ልጅ ከመጀመሪያው የዲንጋይ ዘመን ወደ አዲሱ በመሸጋገር ቀስ በቀስም የእርሻ ቴክኖሎጂን  ያዳብራል።  ቀደም ብሎ በአደንና ፍራፍሬን በመልቀም ይተዳደር የነበረው የሰው ልጅ  አሁን በእርሻ ቴክኖሎጂ አማካይነት መዝራትንና ማብቀልን፣ እንዲሁም ፍሬውን ለቅሞ መመገብን ይማራል። ይህ ዐይነቱ አዲስ ቴክኖሎጂ ደግሞ የበለጠ ምርምርን የሚጠይቅ ሲሆን፣ የሰው ልጅም በመጀመሪያ ደረጃ በማየትና በኢንቲዩሽን ለምግብ የሚያገለግሉትን በመምረጥና  በማባዛት እየዘራ ምርትን በማሳደግ ወደተሻለ የህብረተሰብ ዕድገት ደረጃ ይደርሳል። ከዚህ በመቀጠልም ለመለማመድ የሚችሉ ከብቶችን በማቅረብና በማራባት የስጋና የወተት፣ የአይብና የቺዝ ፍላጎቶቹን ያሟላል።

ደራሲው እንደሚያስረዳን በዚህ ዐይነቱ የአዕምሮ እንቅስቃሴና የማሰብ ኃይል አማካይነት ቴክኖሎጂዎች መዳበራቸው ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ መንደሮችንና ከተማዎችን በመመስረት ወደ ማህብረሰብና ወደ መንግስት ምስረታ ለማምራት እንደቻለና፣ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች አመለካከታቸውን ወደ አንድ አቅጣጫ ለማድረግ የቻሉበትን  ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጣል። ይህም ማለት ስርዓት ያለው ማህበረሰብና መንግስት መመስረት የሰው ልጅ ባህላዊና ታሪካዊ ግዴታዎች እንደሆኑ እንማራለን። በዚህም አማካይነት፣ የሰው ልጅ ከዲንጋይ ቴክኖሎጂ ወደ ብረታብረት ቴክኖሎጂ፣  ወደ ህንጻ ቴክኖሎጂና  የጽሁፍ ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም ወደ ሂሳብና ወደ ጊዜ መቁጠሪያ ቴክኖሎጂ በመሸጋገር ተፈጥሮን ወደ መቆጣጠር እንዳመራ ከደራሲው መማር እንችላለን። ይህ ዐይነቱ የቴክኖሎጂ ምጥቅት ቀስ በቀስ ወደ ተወሳሰበና አንድ ወጥ ወዳልሆነ ማሀበረሰብ ለመጓዝ እንዳስቻለ መረዳት ይቻላል።

በዚህ አማካይነት ደግሞ የግዴታ የተመሰረቱ ማህበረሰቦች እንደቀድሞው በእኩልነት ደረጃ ላይ የሚተያዩ ግለሰቦች ያሉበት ሳይሆን ገዢና ተገዢ፣ በዝባዥና ተበዝባዥ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ የህብረተሰብ ክፍሎች የግዴታ ከህብረተሰብ ዕድገት ጋር የተከሰቱ ሁኔታዎች እንደሆኑ እንመለከታለን። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ ሂደት አንደኛውና ኃይል ያገኘው የህብረተሰብ ክፍል የተፈጥሮን ሀብት እንዲቆጣጠር ሲያስችለው፣ በዚያው መጠንም ህብረተሰብአዊ ዕድገት ሚዛናዊ ከመሆን ይልቅ ዕድገቱ አንደኛውን የሚጠቅም ብቻ እየሆነ ይመጣል። ይህ ዐይነቱ የህብረተሰብ ዕድገት ቀስ በቀስ አስተሳሰብንና ዕድገትን ወደሚያፍን፣ እንዲያም ሲል የሳይንስን ግኝት ወደሚቀናቀን ፊዩዳላዊ ስርዓት ያመራል። ይህ ዐይነቱ የህብረተሰብ ዕድገት በአገራችንና በአውሮፓ ምድር የተከሰተና እንደተፈጥሮአዊ የህብረተሰብ ስርዓት የተወሰደ ሲሆን፣ በአውሮፓ ምድር ሰፋ ባለና በማያቋርጥ ምሁራዊ እንቅስቃሴና የመደብ ትግል ሲገረሰስ፣ በአገራችን ምድር ግን ከስምንት መቶ ዓመታት በላይ በመቆየት ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ዕድገት እንዳይኖር እንቅፋት ሆኗል።

በደራሲውና በሌሎችም ምሁራን ምርምር መሰረት የሰው ልጅ ከፍተኛ ዕድገትን መቀዳጀትና ቴክኖሎጂዎችን ማዳበር የቻለው ባለፉት አምስትና ሁለት ሺህ ዐመታት እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን። በተለይም የኢንዱስትሪ አብዮት ከተካሄደና፣ ከዚያ በኋላ ባለፉት ሁለት መቶ ዐመታት ሳይንሳዊ ምርምር ለቴክኖሎጂ ማግኝያ ዋናው የቁልፍ ዘዴ መሆኑ ከተደረሰበት ወዲህ የሰው ልጅ ከፍተኛ እርምጃን እንዳደረገ መረዳት ይቻላል።

ከዚያ በፊት በአንዳንድ አካባቢዎች በተገለጸላቸው ምሁራን አማካይነት የተገኙት ፍልስፍናዎችና የምርምር ዘዴዎች ለዘመኑ ስልጣኔ ዋናው መነሾዎች እንደሆኑ ደራሲው በዝርዝር ያስረዳል፣ በሜሶፖታሚያ፣ በአባይ በተለይም በግብጽ አካባቢና፣ ይህ ስልጣኔ ቀስ በቀስም ወደ ግሪክ መምጣቱና የተፈጥሮ ፈላስፋዎች በመባል የሚታወቁት መመራመሪያ ዘዴ መሆን ከጀመረ ወዲህ የሰው ልጅ በማያጠራጥር ሁኔታ የስልጣኔውን ቁልፍ ማግኘት እንደቻለ እንማራለን። ስለሆነም የግሪክ የመጀመሪያዎቹ የተፈጠሮ ፈላስፋዎች በመባል የሚታወቁት የተፈጥሮን ልዩ ልዩ ነገሮች፣ ማለትም ነፋስን፣ ውሃን፣ መሬትንና እሳትን የማንኛውም ነገሮች መነሻ መሆናቸውን ከገለጹ ወዲህ የስልጣኔው ቁልፍ እንደተገኘ ይታወቃል። በኋላም የተነሱት ፈላስፋዎች ይህንን መሰረት በማድረግ ወደ ከፍተኛ ምርምር በማምራት የሰው ልጅ በማሰብ ኃይሉ ማንኛውንም ነገር ማፍለቅና ራሱን ማሻሻል እንደሚችል ይደርሱበታል። ይህ የምርምር ዘዴ ለግሪኩ የመጀመሪያውን ስልጣኔ በር የከፈተ ሲሆን ማቲማቲክስ፣ ፊዚክስንና አስትሮኖሚን፣ እንዲሁም ባዮሎጂ የምርምር ዘዴዎች በመሆን ለእነ አርቺመዲስ የመካኒክስ ምርምርና ፈጠራ ስራ መንገዱን እንዳሳዩት መገንዘብ እንችላለን።  በዚህም መሰረት የነፋስና የውሃ ቴክኖሎጂዎች በመዳበር የሰው ልጅ ቴክኖሎጂዎችን ለማንቀሳቀስ የሚችልበትን የኃይል ምስጢር እንዳገኘ እንማራለን።

የግሪክ ስልጣኔም በሮማውያን ከተነጠቀና የተወሰነው ከወደመ በኋላ ሮማውያን ይበልጥ ያደሉት የመሳሪያ ቲክኒክን በማዳበር፣ የካናል ሲስተምን በመስራት፣ ከተማዎችን በልዩ መልክ በማስፋፋት ለአዲሱ የስልጣኔ ዘመን በር ለመክፈት እንደቻሉ እንገነዘባለን። በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የሮማውያን ስልጣኔ ከወደመ በኋላ የጨለማው ዘመን በመተካት ሳይንሳዊ ግኝቶችና የቴክኖሎጂ ምርምሮች በከፍተኛ ደረጃ  ወደ ኋላ የተጓተቱበትን ዘመን ደራሲው ያስቀምጣል። ይሁንና ግን ይህ ዕይነቱ የጨለማ ዘመን የግሪኩን ስልጣኔ መልሶ ማግኘት በመባል በሚታወቀው በሬናሳንስ አማካይነት፣ ቀጥሎም በሪፎርሜሽንና በኢንላይተንሜንት አማካይነት የጨለማው ዘመን እንደተወተገደና የሰው ልጅም በቴክኖሎጂ አማካይነት ከማንኛውም የተፈጥሮ ጭነት መላቀቅ የሚችልበት መንገድ የተከፈተለት ለመሆኑ ከመጽሀፉ መረዳት ይቻላል። በሬናሳንስ ዘመን የእነጋሊሌዮ ምርምር፣ የሬኒ ዴካር ሳይንሳዊ ግኝት፣ ቀጥሎም የኒውተን የግራቪቴሽንና የአስትሮኖሚ ምርምሮች፣ በኒውተንና በላይብኒዝ አማካይነት ካልኩለስ በመባል የሚታወቀው የቲክኖሎጂ ቁልፍ የሆነው የማቲማቲክስ አንድ አካል ከተገኘ በኋላ ሳይሳዊ ምርምርና ቴክኖሎጂያዊ ዕድገትና መሻሻል የተያያዙ መሆናቸውን የዚህ መጽሀፍ ደራሲ በዝርዝርና በግሩም መልክ ያስረዳናል። በእሱ እምነትም አንድ ቦታ ላይ የተጀመረ ምርምርና ቲክኖሎጂያዊ ዕድገት ተከታታይነት ሊኖራቸው የቻለው በማያቋርጠው የጥቂት ሰዎች ያለመስልቸት ጥረትና ትግል እንዲሁም ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደሆነ ከመጽሀፉም ሆነ ከልዩ ምርምሮች መማር ይቻላል። ይህም ማለት በአውሮፓ ምሁር ዘንድ እንደባህል የተወሰደው  የቴክኖሎጂን ግኝት እንደምስጢር መያዝና ማዳፈን ሳይሆን፣ ተከታዩ ትውልድ እንዲያዳብረውና ለሰው ልጅ መጠቀሚያ እንዲያደርገው መንገዱን አሳይቶ ማለፍ ነው። በዚህም መሰረት ተከታታዩ ትውልድ ሳይሰለችና ግዴታው መሆኑን በመረዳትና ኃላፊነቱን በመወጣት ከራሱ ማህበረሰብ አልፎ ለዓለምም ህዝብ መጠቀሚያ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ማዳበርና ማሻሻል እንደቻለ መገንዘብ እንችላለን።

ደራሲው የማቴሪያል ቴክኖሎጂ ተመራማሪ እንደመሆኑ መጠን ዛሬ የምንጠቀምባቸው በቴክኖሎጂ አማካይነት የተገኙ የተፈጥሮ ውጤቶችና፣ እንዲሁም አንደኛውን ከሌላው ጋር በማቀናጀትና በማዋሃድ ልዩ ዐይነት ባህርይ ያለውና ጠቀሜታ የሚሰጥ ምርት ወይም ቴክኖሎጂ ማግኘት የግዴታ ከፍተኛ ምርምርን እንደሚጠይቅ ነው።

ከዚህ ስንነሳ ቴክኖሎጂ የተገኘውና ዛሬም የዳበረው በመሰረቱ ቲክኖሎጂን ለማግኘትና የተወሰኑ ሰዎችን ለመቆጣጠሪያ  ሳይሆን የሰውን ልጅ ኑሮ ለማቃለል ብቻ ነው። ደራሲው እንደሚያስተምረን፣ በተለይም በኒዎ-ክላሲካልና በኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚክስ ትምህርት የሰለጠኑ ኢኮኖሚስቶችን አስተሳሰብና ትረካ ፉርሽ በማድረግ የኢኮኖሚ ዕድገት ከቴክኖሎጂ ውጭ በፍጹም ሊታሰብ እንደማይችል ነው። ከዚህ ስንነሳ በአንድ አገር ውስጥ ሰፋ ያለና ርስ በርሱ የተሳሰረ በብዙ መልኮች የሚገለጽ የስራ ክፍፍል መኖር፣ የመንደሮችና የከተማዎች ዕድገት፣ የእነዚህ በተለያዩ የመገናኛ መስመሮችና መመላለሻዎች መያያዝ፣ ህንፃዎች ውብ በሆነ መልክ መሰራትና ህብረተሰብአዊ ባህርይ መያዝ እነዚህ ሁሉ ከቴክኖሎጂ ዕድገትና እንዲያም ሲል ሰፋ ካለ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የሚያያዙ ናቸው። በመቀጠልም አንድ አገር ልታድግ የምትችለው አንድ ህዝብ ራሱን በራሱ ማግኘት ሲችልና ለፈጠራ የሚያመቹ ሁኔታዎች ሲዘጋጁለት ብቻ ነው። ከዚህ ስነነሳ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ህዝባዊ ባህርይ ያለው መንግስታዊ አወቃቀርና እንዲሁም ግለሰብአዊ ነፃነት የግዴታ ለቴክኖሎጂ ዕድገት የሚያመቹ ናቸው። በተጨማሪም ለቴክኖሎጂና በዚህ ላይ ለሚመሰረተው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት  ህብረተሰብአዊ ሰላምና መፈቃቀር የግዴታ አስፈላጊዎች ናቸው። የአገር ወዳድነት ስሜት በሌለበትና አስረሽ ምችው በሰፈነበትና የዘረፋ ኢኮኖሚ በሚካሄድበት አገር፣ አንድ አገር የቴክኖሎጂ ምጥቀትን በማግኘት ራሷን ልታስከብር አትችልም። በመሆኑም አንድ ህዝብና አንድ አገር የሚከበሩት ከውስጥ በሚያሳዩት በማያቋርጥ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዕድገት አማካይነት ከፍተኛ ጥረት ብቻ ነው። ይህ በራሱ ደግሞ በተለይም በተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ  የሞራል ጥንካሬን ይጠይቃል።  የስልጣኔን ምንነት የተረዳ፣ ራሱን ከህዝቡና ከአገሩ ጋር ያገናኘና በጥቅም በመደለል የአገሩን ምስጢር ለውጭ ኃይል አሳልፎ የማይሰጥ ምሁራዊ ኃይል ባለበት አገር ብቻ የቴክኖሎጂ ምጥቀት መታየቱ ብቻ ሳይሆን፣ የህዝቡም ኑሮ ደረጃ በደረጃ እየተሻሻለ ይመጣል። ይህ ሁኔታ በሌለበት አገር ደግሞ ዘለዓለማዊ ድህነትና ውርደት የአንድ ህዝብ መገለጫዎች ይሆናሉ።

ደራሲው የቴክኖሎጂን ለችግር መፍቻ ቁልፍነት በማሳሰብ፣ በተለይም ለብዙ ሺህና መቶዎች ዐመታት አነሰም በዛም ለቴክኖሎጂ ዕድገት የተደረገውን ትግል አለመዘንጋትና የነበሩትንና ያሉትን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ያሳስባል። ከዚህም በመነሳት በሌላ ወገን ደግሞ ካለማወቅ የተነሳ ቴክኖሎጂ አፍላቂዎችን በማንቋሸሽና ቡዳ እስከማለት ድረስ በማግለል በወገኖቻችን ላይ ይደርስ የነበረውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመኮነን፣ ከዚህ ዐይነቱ አላስፈላጊና አላዋቂ ድርጊት በመታገድ ለቴክኖሎጂ አፍላቂዎች ልዩ ቦታና ክብር መስጠት እንደሚያስፈልግ በጥብቅ ያስስባል። በተለይም አዲሱ ትውልድ ቴክኖሎጂ ለአገር ዕድገትና ለችግር መፍቻ ዋናው ቁልፍ መሆኑን በማሳሰብ፣ በአንድ አገር ውስጥ መረጋጋርትና ሰላም ሊፈጠር የሚችለው በቴክኖሎጂ አማካይነት ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊ ሀብት ሲፈጠርና በዐይነት እየተሻሻለ የመጣ እንደሆን ብቻ ነው።

በዚህ ተቺ ዕምነትና አመለካከት በኢትዮጵያ ምድር መሰረታዊ የሆነ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ የመንግስት ጥያቄና ሚና እንዲሁም ፖለቲካ የሚባለው ትልቁ ጽንሰ-ሃሳብ መስመር መያዝ አለባቸው። እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች ከሳይንስ አንፃር መፈታት አለባቸው። የመንግስትን መኪና የሚጨብጡ ሰዎች በከፍተኛ ዕውቀት የተካኑና ሁለ-ገብ ዕውቀት ያላቸውና፣ ዋና ዓላማቸውም ህገ-መንግስትን ማክበርና አገርን ማበልጸግ መሆን አለበት። ፖለቲካ ከዕውቀት ጋር ካልተያያዘና የአንድ ህዝብም ምንነት በሚገባ ግንዛቤ ውስጥ እስካልተገባ ድረስ ስለሳይንስና ስለቴክኖሎጂ ዕድገት፣ እንዲያም ሲል ረሃብንና ድህነትን ስለማሰወገድ ጉዳይ በፍጹም ማውራት አይቻልም። በዚህ ላይ ደግሞ በስልጣን ላይ የሚወጡና፥ ምሁሩ በአጠቃላይ አገርና ስልጣኔ በሚለው ላይ የሚያስማማ በሳይንስ የተፈተነ ሃሳብ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። ምክንያቱም ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ዕድገት የርስ በርስ ሽኩቻንና በሳይንስ ላይ ያለተመሰረተን የሃሳብ መናቆርን አይሹምና። ከዚህ በሻገር በኢትዮጵያ ምድር መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ያፈልጋል። በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ እንደተረጋገጠው ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ዕድገት የመንፈስ ተሃድሶ እንደሚያስፈልግ ነው። እንደኛው ባለው ፣ አሁንም ፊዩዳላዊ አስተሳሰብ በሰፈነበትና ይሉኝታ በበዛበት አገር ስለሳይንስና ስለቴክኖልጂ ዕድገት በፍጹም ማውራት አይቻልም።

የአቶ ታደሰ ንጋቱ መጽሀፍ ከረጅም ጊዜ ምርምር በኋላ በከፍተኛ የአገር ወዳድነት ስሜት የተጻፈ መጽሀፍ ነው። መጽሀፉን መስመር በመስመርና ገጽ በገጽ ላነበበ ውድ ወንድማችን ጠለቅ ያለ የህብረተሰብ ዕድገት ግንዛቤና እንዲሁም የዓለምን የስልጣኔ ታሪክ በደንብ ያነበበና የተረዳ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም ለቴክኖሎጂ ዕድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ-ነገሮችን በጥብቅ የሚያውቅና ከሰላሳ ዐመት በላይ በሙያው የሰራና አሁንም እየሰራ ያለው ታላቅ ሰው ነው። በዚህ ዐይነት ታሪካዊ አስተዋፀዖውም ልናመሰግነው ይገባናል። እኛም በበኩላችን በተማርንበትና በሰለጠንበት የሙያ መስክ ልክ እንደሱ በአማርኛ እየጻፍን መጽሀፍ ብናሳትምና ለወጣቱ ትውልድ መማሪያ ብናቀርብ የታሪክን ኃላፊነት ተወጣን ማለት ነው። መጽሀፉ መነበብ ያለበት ስለሆነ ማንኛው ለአገሩ ዕድገት የሚቆረቆርና አስተዋፅዖ ለማድረግ የሚፈልግ ይህንን መጽሀፍ ገዝቶ ማንበብ ይኖርበታል።

ፈቃዱ በቀለ

fekadubekele@gmx.de

The post ኢትዮጵያና የቴክኖሎጂ ዕድገት ፈለግ ! የተጻፈ ባለ 337 ገጾች መጽሀፍ። በአቶ ታደሰ ንጋቱ – ትችት፣ በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ለዋሉባት እንጅ ለዋሉላት መሆን ያልቻለች ቤተክርስቲያን – በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አራት ኪሎ ከቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አጠገብ የሚገኘው የበዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ‹ልማት ላለማ ነው› ብሎ በዚያ ያረፉ ክርስቲያኖችን ዐጽም አንሡልኝ እያለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የፕሮፌሰር ዐሥራት ወልደየስን፣ ቀጥሎ የመልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬን አሁን ደግሞ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ዐጽም አንሡ ብሏል፡፡ ለመሆኑ በዓለ ወልድ የማን ነው?
ለፕሮፌሰር ዐሥራት የማይሆን በዓለ ወልድ የማን ነው?
ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ያደጉ፣ ቤተ መቅደሱን ያገለገሉ፣ በሕክምና ሞያቸው ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እስከ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያከሙ፣ አያሌ ጳጳሳትንና መነኮሳትን በየጊዜው እቤታቸው ድረስ እየመጡ ሲረዱ የነበሩትን የሕክምና ሰው እንደ ባዕድ ቆጥሮ ‹አንሥቼ ወደዚያ አደርጋቸዋለሁ› አለ፡፡ ገና ለገና ከዘመኑ ጋር አይስማሙም፣ በእርሳቸው ጉዳይ መንግሥት አይቆጣንም ብለው ካልሆነ በቀር የፕሮፌሰሩ ውለታ ጠፍቷቸው አልነበረም፡፡ ቀድሞውንም አቡነ ጳውሎስ ፖለቲካው ተጭኗቸው እንጂ ለጥላሁን ገሠሠ የሰጡትን የሥላሴ ቦታ ለፕሮፌሰር ዐሥራት መንፈግ አልነበረባቸውም፡፡ በርግጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለዋሉባት እንጂ ለዋሉላት መሆን ካቆመች ቆየች፡፡

የፕሮፌሰር ዐሥራትን ጉዳይ ፓርቲዎቹ ጉዳየ ብለው በክብር አስፈጸሙት፡፡ ይመሰገናሉ፡፡ ፓርቲ አልባውን መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬንና ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ግን እንደ ተራ ነገር አንሡልኝ አለ አስተዳደሩ፡፡ ቤተ ክህነቱም አያገባኝም ብሎ ዝም አላቸው፡፡ ለመሆኑ በዓለ ወልድን የሊቀ ሥልጣናቱ ብቻ ያደረገው ማነው? እነዚህ ዛሬ ተነሡ የሚሏቸው ሰዎች እኮ ናቸው በዓለ ወልድን የሠሩት? ምእመኑን በእምነቱ አጽንተው እናንተ የሚከፈላችሁን ደመወዝ እንዳይቋረጥባችሁ ያደረጉት? ለመሆኑ አድማሱ ጀንበሬ የቤተሰቦቻቸው ናቸው? የደብሩ ካህናትና የሊቀ ሥልጣናቱ አይደሉም? ሲያስተምሩና ሲያገለግሉ የኖሩት፣ ሲጽፉና ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጋር ሲታገሉ የኖሩት ለቤተሰቦቻቸው ርስት ጉልት ለማሰጠት ነው? ኮኩሐ ሃይማኖት የተጻፈው ለቤተሰብ ነው? አድማሱ ጀንበሬ የቤተሰቦቻቸው ከሆኑ ነገ ያሬድም፣ አባ ጊዮርጊስም የቤተሰቦቻቸው ናቸው ልትሉን ነው?

እኒህ ሰውኮ የቤተክርስቲያን ከዚያም ሲያልፍ የሀገር ሀብት ናቸው፡፡ መልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬኮ ሙት ያስነሡ ‹ቅዱስ› ናቸው፡፡ በሙት ዘመን ተፈጥረው ቅድስናቸውን የሚያውቅላቸውና የሚያውጅላቸው ጠፋ እንጂ፡፡ ታዋቂነት እንጂ ዐዋቂነት ክብር የማይሰጥበት ጊዜ ሆነ እንጂ ከአትናቴዎስና ከቄርሎስ የሚስተካከሉ ሊቅ ናቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን የሚነሡ አልነበሩም፤ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራላቸው ነበሩ እንጂ፡፡ በምን ሂሳብ ነው ‹ቤተሰቦቻቸው መጥተው አጽሙን ያንሡልን› የሚባለው፡፡ ለመሆኑ ለመልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬ ክብርና ፍቅር የሌለው ሰበካ ጉባኤ ሃይማኖቱ ምንድን ነው? ደብሩስ የማነው ?
የእኒህ አባት ዐጽም የግድ ይፍለስ ከተባለኮ በቤተ ክርስቲያን የፍልሰተ ዐጽም ሥርዓት አለ፡፡ የነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የነ አቡነ ፊልጶስ፣ የነ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፤ ከውጮቹም የነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዐጽም እንዴት እንደ ፈለሰ ከካቴድራሉ ዕቃ ቤት ያሉት መጻሕፍት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ የት ሄዶ ነው የአንድ ደብር አስተዳዳሪ የኒህን ቅዱስ ሰው ዐጽም ‹አንሡ፣ ውሰዱ› የሚለው? ወይስ ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ፈርዖን መጣ?

ቤተ ክህነቱ መጽሐፋቸውን አሳትሞ ከመሸጥ ውጭ አያገባውምን? ዛሬ በመልአከ ብርሃናት አድማሱ ላይ እንዲህ ከተደረገ ነገ የየአንዳንዱ ጳጳስና ካህን ፋንታ ዕጣ ከዚህ የከፋ መሆኑን ረሳው? ዛሬ በበዓለ ወልድ የተጀመረው ነገር ሃይ የሚለው ካጣ ወደ ካቴድራሉ ተዛምቶ የማን ዐጽም እንደሚነሣ መንግሥትስ ጠፋው?
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ የተማሩት በዚህች ቤተ ክርስቲያን፣ የደከሙት ለዚህች ቤተ ክርስቲያን፣ ያገለገሉት ሀገራቸውን ኢትዮጵያን – እንዴት ባለ ሂሳብ ነው አዲስ አበባ ለቴአትሩ ንጉሥ ቦታ የላትም ተብሎ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ዐጽሙ ይሂድ የሚባለው? ደግሞ ብላችሁ ብላችሁ መቀበርም የሚቻለው በክልላችሁ ነው ልትሉን ነው? ዮፍታሔ ንጉሤ የደብረ ኤልያስ ብቻ ናቸው? ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያበረከትሺውን ሰው ጥቀሽ ስትባል ከምትጠቅሳቸው ተርታ አይደሉምን? ይህ ለትውልዱ እየሰጠነው ያለው ትምህርት የት የሚያደርስ ነው?
መሐል ሠፋሪ ጦር ጃንሜዳ እየተሰበሰበ አንዴ እቴጌ ጣይቱ ከቤተ መንግሥት ይውጡ፣ አንዴ ሚኒስትሮቹ ይነሡ ሲል፣ መኳንንቱም እየተቀበሉ ሲያስፈጽሙ፣ እቴጌ ጣይቱ ‹ለዚህ ጦር ክፉ ትምህርት አታስተምሩት፣ ካልሆነ ሁላችሁንም ያወርዳችኋል› ብለው ነበር፡፤ ሰሚ አልተገኘም፡፡ ያው ጦር ግን በ66 ዓም ንጉሡንም መኳንንቱንም አወረደ፡፡ ያውም እንደ እቴጌ ጣይቱ ወደ እንጦጦ አልላካቸውም ፣ ወደ እንጦሮጦስ እንጂ፡፡ ዛሬም ለዚህ ትውልድ ክፉ ትምህርት ባታስተምሩት መልካም ነው፡፡ ዐጽም እያሽቀነጠሩ ሱቅና አዳራሽ መሥራት ነገ በዐጽመ ቅዱሳን መወጋትን ያመጣል፡፡ ሲሠራና ሲታደስ ገንዘብ ካላመጣችሁ የምትሉን ቤተ ክርስቲያን፣ እንዲህ ደስ ሲላችሁ ዐጽማችንን የምትወረውሩበት ከሆነ በዓለ ወልድ የማነው? ብለን እንጠይቃለን፡፡

በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅጽር ውስጥ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕንጻ እየሠራ ነው፡፡ ከሕንጻው አጠገብ አንድ አምስት መቃብሮች አሉ፡፡ አንዱ የጣልያን ወታደር፣ ሌሎቹ የኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት እነዚህን ዐጽሞች እግር ከሚጠቀጥቃቸው በክብርና በሥርዓት አንሥተን በተገቢው ቦታ እናድርጋቸው፣ ብለው ጠየቁ፡፡ ቤተ ክህነቱ የሰጠው መልስ ግን አስገራሚ ነበር፡፡ ‹ከመቃብሮቹ መካከል የኢትዮጵያውያንን እንደፈለጋችሁ ማንሣት ትችላላችሁ፤ የጣልያኑን መቃብር ግን እኔ መፍቀድ አልችልም› አላቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለጣልያን ወታደር የምትሰጠውን ቦታ ያህል ለአድማሱ ጀንበሬና ለዮፍታሔ ንጉሤ የላትም?
ዛሬ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ
ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ
ይሉ ነበር
©መ/ር ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

The post ለዋሉባት እንጅ ለዋሉላት መሆን ያልቻለች ቤተክርስቲያን – በዲያቆን ዳንኤል ክብረት appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


ድንቅ ኢትዮጵያውያን – እነማንን ያስታውሱ ይሆን ? – አሰፋ ገብረማሪያም

$
0
0
በፎቶግራፉ መደብዘዝ ጥቂቶቹን ላውቃቸው አልቻልኩም።ያወኩዋቸው ቀጥሎ ያሉትን ነው፦
ከላይ በ1ኛው ረድፍ ከግራ ወደቀኝ፤መንግስቱ ለማ ፣መንግስቱ ወርቁ፣ አቤ ጎበኛ፣ ሀዲስ አለማየሁ
በ2ኛው ረድፍ፤ በአሉ ግርማ፣ ደበበ ሰይፉ፣ ወጋየሁ ንጋቱ፣?
በ3ኛው ረድፍ፤?፣ፀጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፣  ጥላሁን ገሰሰ፣?
በ4ኛው ረድፍ፤ Richard Pankhurst፣ አፈወርቅ ተክሌ፣  ገብረክርስቶስ ደስታ፣?
በ5ኛው ረድፍ፤ አሳምነው ገብረወልድ፣   ሙላቱ አስታጥቄ፣   ጌታቸው ካሳ፣   ስብሃት ገ/እ/ብሄር፣  አበበ ቢቂላ፣ ይድነቃቸው ተሰማ።
ውድ አለማየሁ፤መንግስቱ   ለማ፣አፈወርቅተክሌና  ገብረክርስቶስ ደስታ  ከቅርብ ወዳጆቼ መካከል ነበሩ በአበው መልካም ዘይቤ አፈር ይቅለላቸውና!ሙላቱ አስታጥቄ በህይወት አለ አይደለም ወይ አለማየሁ?በተረፈ አብሮ አደጌ ፍቅሩ ኪዳኔ በጥያቄ ምልክት ?የዘለልኳቸውን እንዲያሟላልኝና ድንገት የተሳሳትኩትም ስም ካለ እንዲያርምልኝ በዚህ አጋጣሚ በትህትና እጠይቀዋለሁ።በቸር ይግጠመን፨አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ

By Assefa Gebremariam

The post ድንቅ ኢትዮጵያውያን – እነማንን ያስታውሱ ይሆን ? – አሰፋ ገብረማሪያም appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሰበር መረጃ…….. የወያኔ ሶሻል ሚዲያ ሰራዊት ተሸነፈ – ልኡል አለሜ

$
0
0

በ2008 የህወሃት ፖለቲካ ዘርፍ ሐላፊዎች እና ብሄራዊ መረጃዎች ባጠኑት ጥናት መሰረት የወያኔ መንግስት የመጨረሻዉ ገደል አፋፍ ላይ መዉደቁን የሚያመላክት ነበር ለዚያም የስርአቱ መንኮታኮት ዋነኛዉ የጦር ስምሪት ማሕበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ማለትም ፌስ ቡክ፣ ትዊተር፣ ዋትሳፕና የመሳሰሉት እነደ አንድ ጠላት ተፈረጁ። በጦርነቱም ላይ ለመሳተፍ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዉስጥ ሰርጎ ገብቶ የሚያጠቃ 50.000 የሚጠጉ የመሐበራዊ መገናኛ አጥቂና ተከላካይ ሰራዊት ( Social Media warriors ) በመገንባት ወደ ጦርነቱ በይፋ ገባ በዚያም ወቅት ጦርነቱ መጀመሩን አዲስ እራይ የሚባለዉ የህወሃት ልሳን አወጀ።

ይሁን እንጂ ከፍተኛ በጀትና ወጪ ተመድቦለት የተዋቀረዉ የህወሃት ሶሻል ሚዲያ ሰራዊት ስርአቱን ከዉድቀት ለመታደግ ወይም ጥቃቶችን ለመከላከልም ሆነ በቂ ምላሽ ለመስጠት አልቻለም ሲሉ የሰሞኑ የሚዲያ ግንባታ ክፍል ሰራተኞች ሪፖርት ማቅረባቸዉን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል በዚህ ሪፖርት ዉስጥ። ችግር ተብለዉ የተጠቀሱት 

1. በሰራዊት ደረጃ ተመልምለዉ በሚዲያዉ ላይ የተሰማሩት አባላት ከወዲያኛዉ አካል በሚሰነዘሩ የጥቃት ይዘቶች በመማለላቸዉ
2. በብሔር ተኮር የማጋጨት ስራ ላይ በቂ የሆነ ስልት መጠቀም ባለመቻላቸዉ
3. ከወዲያኛዉ አካል በብሎክ በመጠራረጋቸዉ
4. በትዊተር ዘመቻ ላይ እንደምሳሌ ሆኖ የቴድሮስ አድሐኖም አይመረጥም ዘመቻ ላይ በታየ ጥቃት ፈጽመዉ መከላከል አለመቻላቸው
5. በቂ የሆነ የጽሁፍ ስልጠና ስለሌላቸዉ አርእስት ይዘዉ የመጻፍና የምላሽ ብቃት ላይ ዜሮ በመሆናቸዉ
6. በተቃራኒ አካል ቆመዉ የሚተኩሱ ጸሀፍት ሚዲያ ሰራዊቶች እጅግ አደገኛ በመሆናቸዉ 

እና የመሳሰሉት ሲሆኑ ሶሻል ሚዲያ ሰራዊቱ ፈጽሞ አገልግሎት እየሰጠ ባለመሆኑ ስረአቱን ለመከላከል በሚደረገዉ እርብርብ ላይ አይነተኛ ተሳትፎ ለመስጠት የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚዲያ ግንባታ ዘርፉ ሐላፊዎች አበክረዉ አስታዉቀዋል።

ህወሃት ወያኔ አሁን ከገባበት ከፍተኛ አጣብቂኝ የተነሳ የተለያዩ ስልቶችን ቢጠቀምም እየፈጠነ ከመጣዉ ዉድቀት ለማገገም ፈጽሞ የማይቻልበት ሁኔታዎች ዉስጥ መግባቱን ያመላከቱት ምንጮች አያይዘዉ እንደጠቆሙት በተለያዩ ግንባሮች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጦርነቶችን በህወሃት ልሳነ ሚዲያ ይፋ እንዲደረግ የሚጠይቅ ትእዛዝ በመምጣቱ የሚዲያ ዘርፉ በዚህ ጉዳይ ላይ ባለመስማማት ለሁለት ተከፍሎ እየተነታረከም እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

The post ሰበር መረጃ…….. የወያኔ ሶሻል ሚዲያ ሰራዊት ተሸነፈ – ልኡል አለሜ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ዶ/ር መረራ የቀረበባቸው ክስ የፖለቲካ፣ እርሳቸውም የፖለቲካ እስረኛ መሆናቸውን ገለፁ – መለስካቸው አምሃ(VOA)

$
0
0

ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸው ክስ የፖለቲካ እንደሆነ እርሳቸውም የፖለቲካ እስረኛ እንደሆኑ ለፍርድ ቤቱ አስታወቁ፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸው ክስ የፖለቲካ እንደሆነ እሳቸውም የፖለቲካ እስረኛ እንደሆኑ ለፍርድ ቤቱ አስታወቁ፡፡ ዳኞች ውሳኔ ሲሰጡ ታሪክን እንዲያስታውሱም አደራ አሉ፡፡ፍ/ቤቱ ዶ/ር መረራ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያቀረቡዋቸውን የክስ መቃወሚያዎች በአብዛኛው ውድቅ አድርጓል፡፡

ከቀረቡት የክስ መቃዎሚያዎች አንዱ ወደ ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል እንዲመራ አዘዘ፤ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“file”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/07/ab4f91fa-01ed-41a6-8568-28c5f1f40890_32k.mp3″});

The post ዶ/ር መረራ የቀረበባቸው ክስ የፖለቲካ፣ እርሳቸውም የፖለቲካ እስረኛ መሆናቸውን ገለፁ – መለስካቸው አምሃ(VOA) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አማርኛን እየጠሉ በግዳጅ ሳይሆን በፍቅር ነው አፋን ኦሮሞ የሚያድገው – ናኦሚን በጋሻው

$
0
0

መግቢያ

ሰሞኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም በሚል አንድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው አቅርቧል። ይህ አዋጅ እንደ ልዩ ጥቅም ካስቀመጣቸው በርካታ ነጥቦች መካከል አንዱ “በአዲስ አበባ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ቤት መቋቋም አለበት” የሚል ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመቀሌ፣ በጎንደርም፣ በአፋን ኦሮሞ መማር የሚፈልጉ ካሉ፣ ቁጥራቸው በርከት ካለና የክልሉም ሆነ የዞኑ መንግስት አቅም ካለው፣ በአፋን ኦሮሞ የመማር ሙሉ መብት ሊኖራቸው ይገባል። ይሄ ልዩ ጥቅም ሳይሆን መሰረታዊ መብት ነው። ይህ መብት ደግሞ ለአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መከበር ያለበት መብት ነው። ሁሉም ዜጎች በእኩልነት መታየት አለባቸው። ለአንዱ ተሰጦ ሌላው የሚከለክልበት ምክንያት አይኖርም።

እዚህ ጋር የክልሉ መንግስታት ሆነ የአዲስ አበባ አስተዳደር አንደኛ ቋንቋቸው የተለያዩ የሆኑ፣ የተለያዩ ማህበረሰባት ካሉ ለሁሉም ትምህርት ቤቶችን ቢያዘጋጁ ጥሩና ተገቢ ቢሆንም፣ የአቅም ችግር ሊኖርባቸው እንደሚችል መዘንጋት አያስፈለግም። እንደዚያም ሆኖ ግን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ዜጎች በግል ተነሳሽነት የግል ትምህርት ቤቶች ማቋቋም ከፈለጉ ሊበረታቱና አስፈላጊው መንግስታዊ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል።

እንግዲህ በዴሞክራሲያዊና የሰብአዊ መብት መርህ አንጻር በአፋን ኦሮሞ ትምህርት መሰጠቱ በምንም መስፈርት ችግር ሆኖ ሊታይ እንደማይችል ከተግባባን በዚህ ዙሪያ ብዙ መከራከር የሚኖርብን አይመስለኝም።

  1. የኦሮሞ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው የሚማር አልተገኘም

ሌላው ብዙዎች የምንዘነጋው ነገር ቢኖር በሚኒስትሮች ምክር ቤት በረቀቀው አዋጅ እንደ ልዩ መብት ከተቀመጡት መካከል አንዱ በአዲስ አበባ፣ በአፋን ኦሮሞ ትምህርት ቤቶችን የመክፈት ጉዳይ፣ እንደ ልዩ ጥቅም ቢቀርብም፣ ከዚህ በፊት በአቶ መለስ ዜናዊ የተፈቀደና ተግባራዊ ሆኖ የነበረ መሆኑን ነው። ከባድመ ጦርነት በኋላ በነ አቶ ግርማ ብሩና አባ ዱላ ገመዳ የሚመራው ኦህዴድ፣ አቶ መለስ ዜናዊን አስፈቅዶ፣ በአዲስ አበባ ሁሉም ወረዳዎች የአፋን ኦሮሞ ት/ቤቶች ለመክፈት ሞክሮ ነበር። የቀድሞ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር የነበረው ኤርሚያ ለገሰ እንዲህ ሲል የነበረውን ሁኔታ በግልጽ ይተነትናል፡

“እነዚህ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እስኪያልቁ አምስቱም ዞኖች በአጣዳፊነት ነባር ትምህርት ቤቶችን በመለየት ለጐልማሶች የማታ፣ ለህጻናት እና ታዳጊዎች የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በክረምት ኢ_መደበኛ ትምህርት እንዲጀመር ጥብቅ ኦህዴዳዊ ትእዛዝ ተላለፈ። በድርጅት ቋንቋ መደብ ወረደ። መደቡን ለማስፈፀም ደግሞ የአዲሳአባ ካቢኔ የነበሩት ሊቀመንበር አሊ አብዶ ፣ ሀይሉ ደቻሳ ፣ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ( የአፈ ጉባኤ ደግፌ ቡላ ባለቤት እና በኋላ ላይ በአዜብ መስፍን ከም/ል ሚኒስትርነት የተባረረች የምንወዳት እህታችን) እና አምባሳደር ሰለሞን ተመደቡ። ተግባሩ በቁልፍ ደረጃ በመቀመጡ ስራውን ያንጠባጠበ ካድሬ በኦህዴድነት መቀጠል እንደማይችል ተገለፀ። በየቀበሌው የሚገኝ ካድሬ ቤት ለቤት እያሰሰ የኦሮሞ ዘር አለው የሚለውን አዲስአበቤ እንዲመዘግብ አደረገ። እንደ መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ፍቃደኛ ያልሆነውን ማስገደድ ተጀመረ። በደርግ ጊዜ ዝነኛው ቆምጬ አምባው ” አስኳላ የማይሄድ ቡዳ ነው!” ያለውን በተሞክሮ በመውሰድ የአዲሳአባ ኦህዴድ ካድሬዎች ” አፋን ኦሮሞ የማይማር የነፍጠኛ ተላላኪ ነው!” የሚል ማዕከላዊ መልእክት ቀርፀው በጥቅም ላይ አዋሉ።ስራው በተጀመረ የመጀመሪያው ወር የተመረጡት አምስት ትምህርት ቤቶች በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ከጠቅላላው አዲሳአባ በአማካይ 500 ተማሪ ተገኘ። ቅዳሜ እና እሁድ በተዘጋጀው የህጻናት፣ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ክፍለጊዜ በአማካይ አንድ ሺህ የሚጠጋ ተገኙ። የኦህዴድ አብዮታዊ ካድሬዎች አጀማመሩ ጥሩ እንደሆነ ገመገሙ። ስራው በተጀመረ ሶስተኛው ወር የምሽቱ 60 ፣ የሰንበቱ ወደ 90 ተማሪ ብቻ ቀረ። አምስቱ ትምህርት ቤት ታጥፈው በዞን ሁለት ውስጥ ወደ ሚገኘው ተግባረ እድ ትምህርት ቤት እንዲጠቃለል ተደረገ። በአራተኛው ወር እንደ ኮንደሚኒየም ወደ 40/60 ተቀየረ። አካሄዱ አስደንጋጭ የሆነበት ኦህዴድ ” ሁሉም ዜሮ ዜሮ” መመዝገቡ በፊት ትምህርቱ ባልተገለፀ መመሪያ እንዲቀር ተወሰነ”

እንግዲህ እዚህ ላይ የምናየው የኦሮሞው ማህበረሰብ ለአፋን ኦሮሞ ክብር ቢኖረዉም፣ በዋናነት ግን ልጆቹ በአማርኛና በእንግሊዘኛ እንዲማሩለት እንደሚፈለግ ነው። ልጆቹን ወደ ኦፋን ኦሮሞ ትምህርት ቤት ለመላክ ፍቃደኛ አልነበረም።

ከሁሉም የሚገርመው ኤርሚያስ እንደ ገለጸው አዲስ አበባ የሚኖር አንድም የኦህዴድ ባለሥልጣን ልጆቹን አፋን ኦሮሞ እንዲማሩለት አልሰደደም። በክረምቱ ክፍለ ጊዜም ሆነ በሰንበት ባለሥልጣናት ልጆቻቸውን የሚልኩት የእንግሊዘኛ እውቀታቸውን የሚያሳድጉበት ከ3ሺህ ብር በላይ የሚከፈልባቸው ውድ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች ነበር። ለምሳሌ ግርማ ብሩ ልጆቹን ሳንፈርድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤት፣ አባ ዱላ ደግሞ በቅድስ ዩሴፍ የግል ትምህርት ቤት ነው ያስተማሩት። የእነዚህ የኦህዴድ አመራሮች ልጆች አማርኛና እንግሊዘኛ በደንብ የሚጽፉና የሚናገሩ ናችው። ይሄ ቁቤ የሚባለው ላቲን እንኳን ሊጽፉ አፋን ኦሮሞን መናገራቸዉንም እግዜር ይወቀው።

እንግዲህ አስቡት፣ በኦሮሞ ስም እየነገዱ ያሉ የኦህዴድ ሆነ ሌሎች ለኦሮሞ ቆመናል የሚሉ ግለሰቦች የሚሰብኩትንና የሚለፍፉትን በራሳቸው ሕይወት፣ በልጆቻቸው ተግባራዊ ሳያደርጉ ነው በሌላው ድሃ የኦሮሞ ልጅ እየቀለዱ ያሉት። አማርኛን እና እንግሊዘኛን የማወቅ ጥቅሙን ያውቃሉ። ለዚህም ነው ልጆቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረጉ ያሉት። ሆኖም ግን የስንቱን ድሃ ሕይወት ግን አጨለሙ።

  1. የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥያቄ

በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥያቄ የስራ፣ የመብት፣ የፍትህ ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ወጣት የሚያስፈልገው አማርኛን ማወቅና መማር ነው። በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደሮች፣ በአማራው፣ በደቡብና በቤኔሻንጉል ክልሎች ፣ በተለያያዩ የግል መስሪያ ቤቶች የመቀጠር እድላቸው እንዲሰፋ፣ በኦሮሚያ ልማት እንዲስፋፋ ነው የሚፈልጉት። በርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ወድቀዋል። ያ እንዲለወጥ ይፈልጋሉ።

ሕወሃቶች ቆመንለታል የሚሉትን የትግራይ ሕዝብ በሁሉም መስክ ቀዳሚ እንዲሆን፣ የትግራይም ክልል ከሁሉ ቀድማ እንድታድግ እያደረጉ ነው። የትግራይ ልጆች ከአራተኛ ክፍል ጀመሮ አማርኛ ማንበብና መጻፍ ይችላሉ። (ከትግሪኛ በተጨማሪ)። ከዚህም የተነሳ በፌዴራል መንግስት ይሁን አማርኛ የሥራ ቋንቋ በሆነባቸው አብዛኛው ክልሎች የመስራት እድላቸው የሰፋ ነው። ሆኖም ግን ለኦሮሞው ቆመናል የሚሉት የሕዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ ላይ አይደለም ትኩረታቸው። የሕዝቡን ኑሮ የሚያሻሽለው ላይ ከማተኮር፣ ጠባብ ሆነው፣ ኦሮሞው ከአማራው፣ ከጉራጌው፣ ከሶማሌው፣ ከጉሙዙ ..ጋር እንዲቃቃር እያደረጉት ነው። ሌላውን ማህበረሰብ የሚያስቀየሙ፣ ኦሮሞው በሌሎች እንዲፈራና እንደ ጠላት እንዲታይ የሚያደረጉ ጊጂና የኋላ ቀር ፖለቲካን ነው የሚያራመዱት። ሕወሃቶች የመኪና መገጣጠሚያ በትግራይ ሲገነቡ፣ ኦህዴዶችና የኦሮሞ ፖለቲከኞች የጥላቻ ሃዉልት ነው የሚገነቡት።

  1. አፋን ኦሮሞ እንዲያድግና እንዲስፋፋ የሚያስፈለገው

አሁን የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ቤት ቢቋቋም የሚለውጠው ነገር አይኖርም። ከዚህ በፊት ተሞክሮ ከሽፏል። አፋን ኦሮሞ የሥራ ቋንቋ ቢሆን አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ አፋን ኦሮሞ የማይናገር በመሆኑ አብዛኛው ሰው መናገር እስኪጀመር ድረስ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ሌላው አፋን ኦሮሞ እንዲያውቅና እንዲማር ከተፈለገ ደግሞ፣ አፋን ኦሮሞ ከኦሮሞው አልፎ በሌላው ማህበረሰ ተቀባይነቱ ፣ ተወዳጅነቱ መጨመር አለበት። ለዚህም የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከሕወሃት ጋር ታንጎ እየደነሱ በሃይልና በግርግር በግዳጅ ሕዝቡ ላይ ለመጫን መሞከር ሳይሆን ሌላውን ማሳመንና ማግባባት ይጠበቅባቸዋል። በፍቅር ነው ሁሉም ነገር ሊሆን የሚችለው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅን ተከትሎ አንዳንድ በፓርላማ የኦህዴድ ተወካዮች፣ በአዲስ አበባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በግዳጅ አፋን ኦሮሞ ትምህርት መሰጠት አለበት የሚልም አስቂኝ አስተያየት አቅርበዋል። እነዚህ ሰዎች ያልተረዱት ነገር ቢኖር አንደኛ ሕዝብን በማስገደድ የሚሆን ነገር አይኖርም። ሁለተኛ አዲስ አበባ ራሷን በራሷ የማስተዳደር መብቷ በህግ የተረጋገጠላት መሆኑ ነው።
ለዚህም ነው የፓርላማ የኦህዴድ አባላት፣ በዘረኝነት ሰክረው እንዲህ አይነት አስተያየት ከመስጠታቸው በፊት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ቢገመግሙ ጥሩ ይሆን ነበር የምለው።

ይሄን ስል በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በአፋን ኦሮሞ ትምህርት መሰጠቱትን በመቃወም አይደለም። ከአማርኛና ከእንግሊዘኛ ቀጥሎ ዜጎች መርጠው ሌላ ሶስተኛ ቋንቋ ቢማሩ ጠቃሚ ነው። ሶስተኛው ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ቢሆን ችግር አይኖረዉም። ግን ጥቅሙን በማስረዳት፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር በማስወሰን እንጂ በአዋጅ፣ ከሕዝብ ፍቃድ ውጭ በማድረግ አይደለም። ህዝብን ለማሳመን ደግሞ አሳማኝ ነጥቦች መቀመጥ አለባቸው፡

በዋናነት አፋን ኦሮሞ የሚጻፍበት ፊደል እንደገና መጠናት አለበት። ማንም ላቲኑን በፍቃደኝነት የሚማር አይኖርም። በላቲን የተጻፈ የመማሪያ መጽሀፍ የእሳት ማገዶ ነው የሚሆነው። ላቲኑ ሮምን እንጅ ኦሮሞን አይወክልም። እነ ሃይሌ ፊዳ ናቸው ከአዉሮፓ ያመጡት። መጤ ፊደል ነው። በመሆኑም አፋን ኦሮሞ በሳባ ፊደል እንዲጻፍ ማድረግ ቢቻል አንደኛ በቀላሉ አፋን ኦሮሞ የበለጠ ተቀባይነቱና ተወዳጅነቱን ይጨምራል፤ ሁለተኛ  አማርኛ ተናጋሪዎችም በቀላሉ ሊማሩት ይችላሉ።

“አይ ፊደሉ የኦሮሞዎች ጉዳይ ነው፣ እኛ ኦሮሞዎች ብቻ ነው የምንወስነው” የሚል ፉሊሽና ጠባብ አስተያየት ከተሰጠ ደግሞ “ ታዲያ እዚያው ነጆና ዶዶላ እናንተው ለምን አትማሩት ? ለምን ወደኛ ወደ አዲስ አበባ ታመጡታላችሁ? “  የሚለው ጥያቄያችን ይሆናል። በርግጠኝነት የምነግራቸው ላቲኑ ፊደል የአፋን ኦሮሞ ጠላት ነው የሚሆነው።

ሌላው የኦሮሞ ፖለቲከኞች ይሄ ፊንፊኔ፣ ሸዋ፣ ያ መሬት፣ ይሄ መሬት የኦሮሞ ነው የሚሉትን አጉል ፈሊጥ ማቆም አለባቸው። ኦሮሞዎች የሚኖሩባቸው አብዛኛው ቦታዎች በወረራ የተያዙ ናቸው። ኦሮሞዎች ራሳቸው ወራሪዎችና መጤዎች ሆነው ሌላው መጤ የማለት መብት የላቸውም። ከዚህ አጉል ቅዠታቸው ቢነቁና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት ለኦሮሞ የሚጠቅም አቅጣጫ ቢይዙ ጥሩ ነው። ያኔ ከሌላው ጋር የሚያስተሳስራቸው ገመድ ያጠብቃሉ። ያኔ የኦሮሞ ጥያቄ የሌላው የሌላውም ጥያቄ የኦሮሞ ጥያቄ ይሆናል። ያኔ አፋን ኦሮሞ የኦሮሞዎች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ቋንቋ ይሆናል። ያኔ ከፍቅርና ከአንድነት የተነሳ የተለያዩ ባህሎቻችን፣ ቅርሶቻችን፣ ቋንቋዎቻችን የሁሉም ሃብቶች ይሆናሉ።

(ከዚህ በታች ያለው፣ የነቀምቴን፣ የአሰላን የመቀሌን ከተሞች የሚያሳይ ምስል ነው። መቀሌ የትግራይ ክፍል ሃገር ነበረች። ነቀምቴ የሃብታሟ የወለጋ ክፍለ ሃገር፣ አሰላ ደግሞ የአርሲ ክፍለ ሃገር ዋና ከተሞች ነበሩ። ከ25 አመታት የሕወሃት/ኦሃዴድ ዘመን በኋላ ከተሞቹ ይሄን ይመስላሉ። ያለፉትን ቁርሾ በማንሳት ፣ አላስፈላጊ፣ ጥቃቅን፣ የኦሮሞ ማህበረሰብ የሚጎዱ አጀንዳዎችን የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከሕወሃት ጋር እያራገቡ፣ የዘር ፖለቲካን እያራመዱ፣ በሌላ በኩል ግን የኦሮሞ ከተሞች በዚህ መልክ የወዳደቁ ሆነዋል። የኦሮሞ አካራሪዎች ኦሮሞ በብዛት የሚኖርባቸውን  ከተሞች ለማሳደግ ከመስራት፣ ሌሎች ማህበረሰቦች በብዛት የሚኖሩባቸውን እንደ አዳማ፣ አዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ ያሉትን ኦሮሞያዝድ ለማድረግ ነው እየደከሙ ያሉት።ከንቱ ድካም።)

The post አማርኛን እየጠሉ በግዳጅ ሳይሆን በፍቅር ነው አፋን ኦሮሞ የሚያድገው – ናኦሚን በጋሻው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

(ሪፖርተር) ቴዲ አፍሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ለሚያዘጋጀው ኮንሰርት የመንግሥትን ይሁንታ እየጠበቀ ነው

$
0
0

ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኘውን አልበም ካወጣ በኋላ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ የመጀመርያውን ኮንሰርት ለማቅረብ የመንግሥትን ይሁንታ እየጠበቀ ነው፡፡

ድምፃዊው ጳጉሜን 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ መዘጋጀቱን፣ ማኔጀሩ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ኮንሰርቱን አልበሙን ያከፋፈለው ኩባንያ ጆይ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ኩባንያ ከኤፕላስ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ኩባንያ ጋር በጥምረት የሚያዘጋጁት መሆኑን፣ ጆይ ኤቨንት የሚሊኒየም አዳራሽን ከሚያስተዳድረው አዲስ ፓርክ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጆይ ኤቨንት ኮንሰርቱን ለማዘጋጀት የሚያስችል ዕውቅና ለማግኘት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ለሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ፈቃድ ማሳወቂያ ክፍል ጥያቄ ማቅረቡም ታውቋል፡፡

የአዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንትና ማኔጅመንት ኩባንያ የማርኬቲንግና የሰው ኃይል መምርያ ኃላፊ አቶ ስለሺ ለማ፣ ሰኔ 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት በጻፉት ደብዳቤ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ኮንሰርት በሚሊኒየም አዳራሽ ለማካሄድ ፕሮግራም መያዙን ገልጿል፡፡ ‹‹ለፕሮግራሙ ተገቢው ትብብር ይደረግለት ዘንድ እንጠይቃለን፤›› በማለት አቶ ስለሺ በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የኮንሰርት ጥያቄ መቅረቡን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ነገር ግን ከሚመለከተው አካል ጋር ንግግር ከተደረገ በኋላ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡

ለዚህ ኮንሰርት ቴዲ አፍሮ 1.8 ሚሊዮን ብር እንደሚከፈለው፣ ለሚሊኒየም አዳራሽ የዕለቱ ዝግጅት ኪራይ 1.2 ሚሊዮን ብር ክፍያ ለመፈጸም ስምምነት ላይ መደረሱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ቴዲ አፍሮ የአዲስ አበባውን ኮንሰርት ካካሄደ በኋላ በሐዋሳ፣ በጎንደርና በመቀሌ ተጨማሪ ኮንሰርቶችን እንደሚያካሂድ ከስምምነት ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኘውን አልበም ጨምሮ አራት አልበሞቹን ለአድማጮች አቅርቧል፡፡ ከአልበም በተጨማሪ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን በተለያዩ ጊዜያት ያቀረበ ሲሆን፣ ሥራዎቹ በአድናቂዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንደነበራቸው ይታወቃል፡፡

The post (ሪፖርተር) ቴዲ አፍሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ለሚያዘጋጀው ኮንሰርት የመንግሥትን ይሁንታ እየጠበቀ ነው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ለአዲስ ዓመት ቅድመ ዝግጅት- በራሳችን ላይ እንዝመት፣ – ይገረም አለሙ

$
0
0

የዘመን መለወጫ ግዜ እንደ የሀገራቱ ቢለያይም በሁሉም የሰው ልጆች ዘንድ አንድ ተመሳሳይ ስሜት ይኖራል፣ በሁሉም ረገድ ካለፈው ዓመት የተሻለ መመኘት፡፡ ለዚህ ይመስለኛል አንኳን አደረሳችሁ፣እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ መጪው ዘመን የደስታ የፍቅር፣ የሰላም የብልጽግና ወዘተ ይሁንላችሁ የሚባለው፡፡ በሀገራችን ባህልም በዋዜማው ምሽት ችቦ ከቤት ተለኩሶ ሲወጣ ከበሩ ግራና ቀኝ እየተተረኮሰ የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ የሚባለው የአዲስ አመት ተስፋ   ተስፋ መገለጫ ነው፡፡ (ይህን እንኳን የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጆች በተለይ ከሀገር ውጪ ያሉቱ እምብዝም የሚያውቁት አይመስለኝም፤) ነገር ግን አንዲህ እያልን እየተመኘን እየተናገርን ግና የተመኘነው ላይ ሳንደርስ የናፈቅነውን ሳናገኝ አመታት ተቆጠሩ፡፡ ዘመኑ የቁጥር ለውጥ ማድረጉን እኛም ምንም አዲስ ነገር የሌለውን አዲስ አመት ማለቱን ቀጥለንበታል፡፡

የናፈቀ ሰው ወይ እርሱ የናፈቀው ሰው ወዳለበት ጨክኖ የሚቻለውን ሁሉ አድርጎ መሄድ ካልቻለ፣ ወይንም ያኛው ተናፋቂው እርሱ ካልመጣ መናፈቅ/መነፋፈቅ  ብቻውን ሊያገናኝ አይችልም፡፡ምኞትም ቢሆን የተመኙትን ነገር ለማግኘት መደረግ ያለበትን ካላደረጉ እደው ዝም ብሎ በመመኘት የሚገኝ ነገር የለም ሊኖርም አይችልም፡፡

አመቱ የቁጥር ለውት ባደረገ ቁጥር ሰላምና  ፍቅር እንመኛለን፣  ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንናፍቃለን፤ መጪው አመት የሰላም የፍቅር የብልጽግና ወዘተ ይንላችሁ እንባባላለን፡፡ ነገር ግን የናፈቅነው ጋ ለመድረስም ሆነ የተመኘውን ለማግኘት የሚያስፈልገውን መፈጸም ባለመቻላችን ከወያኔ አገዛዝ መገላገል ተስኖን ሰላም እንዳጣን አርስ በእርስ መቀራረበብ ተስኖነወ ፈወቅር እንደራቀን አለን እንዳለን፡፡ ዛሬም ባዶ ምኞትና ተስፋ የምንገልጽበት ተግባር አልባ ምኞት የምንለዋወጥበት የአመት ለውጥ ሁለት ወራቶች ቀርተውታል፡፡

ወያኔ ሥልጣነ ወንበሩን ለማደላደል ዙሪያ ገባውን በሚያጠናበትና የኢትዮጵያውያንን ምኞት፣የፖለቲካ ቅዝቃዜ ሙቀት   በሚለካበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ለዚሁ ተግባ  ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት መፍቀድ ነበር፡፡ ይህ ቢያንስ በሁለት መንገድ ጠቅሞታል፤አንድም ሰውን ለማስተንፈስ፣ብሎም ለማናካስ፣ ሁለትም ብንለቀቅ ምን ያህል እንደምንሄድ፣የቱን ያህል ለሥልጣኑ ሥጋት እንደምንሆን  ለማወቅና ልጓም ለማዘጋጀት አስችሎታል፡፡ እናማ በዛን አጭር የቆይታ ግዜ ወር እየጠበቅን በጉጉት እናነባቸው ከነበሩ መጽሄቶች አንዷ በነበረችው ሙዳይ ላይ ይጽፉ የነበሩ አንድ ሰው ምን የሚል አለ ብለነው ብለነው፣ ሲያልቅብን ግዜና እየደገምነው ያሉት ሁሌ ይታወሰኛል፡፡ ዛሬ ከአስር አመት በኋላ እኚህ ሰው በህይወት ካሉ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት ይከብዳል፡፡ ያኔ ሁሉ ተነግሮ ተጽፎ መደገም ተጀምሮ ከሆነ ከዛን ወዲህ የተባለው የተጻፈው ሁሉ ድግግሞሽ ነው ማለት ነው፡፡ ግን እኮ ምን ያልተነገረ ምን ያልተጻፈ ነገር አለ? ያልተተገበረ እንጂ የሞላው፡፡

ይህን ያልኩት ያንን ማስታወስ  ፈልጌ ሳይሆን ብዬ ነበር ማለት የማልወደው ሰውዬ  በሁኔታዎች አስገዳጅነት ምን አልባትም ጸሀፊው እንዳሉት የሚባል አዲስ ነገር ባለመኖሩ መለስ ብዬ ዛሬ ባነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ ላይ በየአዲስ አመቱ ዋዜማ እንደ አቅሚቲ አንስቼአቸው የነበሩ ሰሚ ያላገኙ ሀሳቦችን በማስታወስ ለማጣቀሻነት ማቅረብ አስፈልጎኝ ነው፡፡

ልክ እንደ አሁኑ ከሶስት ዓመት በፊት በ2006 ዓም መግቢያ ዋዜማ ላይ በአዲስ አመት ብንለውጥ የሚል ከእኛ ከኢትዮጵያውያኑ በተለይም በፖለቲካው ምህዳር ላይ ከሚስተዋሉት ሰዎች ባህርይ አንጻር ሊፈጸም የማይችል ቅዠት  ውስጥ ገብቼ በጻፍኩት ጽሁፍ ውስጥ፣ መጪው ዓመት 2006 ሙሉ ቁጥር ነው፡፡ ለሙሉ ቁጥር ያለው አመለካከት ደግሞ በአብዛኛው አወንታዊ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ የሙሉ ቁጥር የዘመን መለወጫ እለት የጥል ምንቸት ውጣ የፍቅር ምንቸት ግባ፣ የበቀል ምንቸት ውጣ የይቅርታ ምንቸት ግባ፣ የጥርጣሬ የሸፍጥና የሴራ ምንቸት ውጣ፣ የመተማመን የቀናነትና የግልጽነት ምንቸት ግባ ወዘተ ማለት ብንችል በማለት ይህችን መልእክት ጻፍሁ፡፡

ለሀገር ይበጃሉ የተባሉ ያልተነገሩ ያልተጻፉ ነሮች የሉም ተግባራዊነት የለም እንጂ፡፡ ሌላው ቀርቶ ፖለቲከኞቻችን እነርሱው ከተናገሩትና ከጻፉት ከፊሉን እንኳን ገቢራዊ ማድርግ ቢችሉ ሀገራችን ዛሬ ካለችበት በብዙ መልኩ የተለወጠች ለመሆን በቻለች ነበር፡፡ እናም ከላይ የገለጽኩትን ለማለት መድፈሩ የመጀመሪያ ርምጃ ሆኖ ያሉትን ለመፈጸም መቻል ደግሞ ዋናውና ወሳኙ ጉዳይ ይሆናል፡፡ የምንለውን ተፈጻሚ ለማድረግ ለቃል የመታምን፣ ለህሊና የመገዛትና ከራስ በላይ የማሳብ ቁርጠኝነቱ ካለ 2006ን ለአስተማማኝ ለውጥ የሚያበቃንን ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት አመት ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን ማድረግ ቻልን ማለት ደግሞ ለምርጫ 2007 ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ትውልድ ተሻጋሪ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የሚያበቃንን ጥርጊያ ጎዳና ተያያዝነው ማለት ነበር፡፡ ከራስ በላይ ለሀገር፣ ከሥልጣን ይልቅ ለትውልድ ማሰብ ካለ ይህ የማይቻልም የሚገድም አይደለም፡፡ ይቻላል! የሚል ሀሳብ ነበረበት፡፡

ግን አንዱም አልሆነምና 2006 እንደቀደሞቹ ሁሉ ግዜውን ጠብቆ ቀናቱን ቆጥሮ አለፈ፤2007ም በዚሁ መልኩ እንደውም እርሱ በተለየ ሁኔታ ወያኔን ለመቶ በመቶ የፓርላማ ወንበር አሸናፊነት አብቅቶ ሊጠናቀቅ ሲል በዋዜማው ያው ቅዠቴ አለቅ ብሎኝ በዲስ ዓመት ፍቅር ብንመሰርት በሚል ርዕስ በጻፍኩት ጽሁፍ እንዲህ የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ሞከርሁ፡፡

የቱንም ያህል ስንቆፍር ውለን ስንቆፍር ብናድር የሚያለያዩን ጉዳዮች አንድ ከሚያደርጉን በዝተውም ልቀውም ሊገኙ አይችሉም፡፡ እንደውም በሀቅና በንጹህ ህሊና በንጽጽር ከተፈተሸ የሚያለያዩን ሚዛን የማይደፉ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ገነውና ጎልተው ማዶና ማዶ እንድንቆም ለማድረግ የሚያስችል አቅም ያገኙት ከእኔ በላይ የሚል አጋንንት ሰፍሮብን  የመነጋገር ፈቃደኝነት፣ የመወያየት ባህል፤ የመደማመጥ ትእግሰት ያሳጣን በመሆናችን ነው፡፡ እናም በዚህ አዲስ አመት ዋዜማ ይህን አጋንንት እናስወጣና  የፍቅርን አምላክ ወደ ውስጣችን እናስገባ፡፡

ነገር ግን ከጋኔኑ ተላቀን ወደ ፍቅር መቅረብ ሳንችል 2008 አለቀ 2009ኝም ሊሰናበትን ይሄው ዋዜማው ላይ እንገኛለን፡፡ ወደ ፍቅር ቀረብን ማለት አግዚአብሄር ፍቅር ነውና ወደ እግዚአብሄር ቀረብን ማለት ነበር፡፡ ወደ እግዚብሄር ስንቅርብ ደግሞ ሁሉን አንደ ፍቃዱ የሚያደርግ የማይሳነው አምላክ ነጻነት ካሳጣን ወያኔም ፍቅር ከነሳን ሰይጣንም ይገላግለን ነበር፡፡እኛ ግን መች …..!

ዛሬም እነሆ ምንም ለውጥ ማምጣት አይደለም ለመለወጥ ሀሳቡ እንኳን ሳይኖረን 2009 ባለንበት እንደተገተርን ጥሎን ሊለወጥ ነው፡፡ የማይቆጨን መስቃ የማይመረን ምን ጎዶች ነን፡፡ሌላውን ለመውቀስ፣ ለመክሰስ፣ ለማኮሰስ የምንደፍር ራሳችንን ለማየት ግን ቅንጣት ወኔ የሌለን፣በራሳችን አይን ውስጥ ግንድ ተጋድሞ በሌላው አይን ውስጥ ሰንጥር ፍለጋ የምንማስን ፣ የሚገዙንን የምንንቅ የምንሳደብ የምናናቅ ግን በእነርሱ መገዛታችን ውርደት ሆኖ የማይታየን፣  አረ ስንቱ የእኛ ጉድ ተዘርዝሮ ይዘለቃል፡፡

ሀይሉ ገብረ ዮሀንስ ገሞራው ለሽልማትም ለእስራትም ባበቀው በረከተ መርገም የሚል ርእስ በሰጠው ግጥሙ ውስጥ “ያሰብከው ምኞትህ አልሆን ብሎ ሲከሽፍ ሁኔታው ሲጠጥር፣ ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር፤” የሚል ዘመን አይሽሬ መለልእት አስፍሮ ነበር፡፡የተማረበት ቀርቶ በቅጡ የተረዳው መኖሩ ያጠራጥራል እንጂ፡፡

ሀያ ስድስት ዓመት ሙሉ ከወያኔ ጋር ያለውን ገመድ ጉተታ ትተን እርስ በእርት እየተጓተትን ወጥረን ተወጣጥረን ወያኔ እየተንገዳገደም ወድቆ እየተነሳም እንዲገዛ አበቃነው፡፡ ይህ ሊቆጨን ሲገባ ፈጽሞ ስሜት አልሰጠንምና፡አሁንም  እዛው የዛሬ ምናምን አመት በቆምንብት ነን፡፡ እንደው እስቲ በእኛ በቀጥታ ባይደርስብንም በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ላይ የሚፈጸመው ሞት እስራት ስደት እንግልት ይታሰበንና የሀገሪቱ በጥቂቶች መቦጥቦጥ ይቁጨንና አዲሱ አመት ከመድረሱ አስቀድሞ ባሉት ሶስት ወራቶች የጠጠረውን ትተን የላላውን የምንወጥርበት፣ የትም ሊደርሰን ካልቻለው መንገድ ወጥተን አዲስ መንገድ ምንመርጥበት፣ የሰአስተሳሰብ ለውጥ አድርገን ከራስ በላይ ሀገር ለማለት የምንበቃበት፣ዙፋኑ አንድ ብቻ መሆኑንና እርሱም በህዝብ ፈቃድ መያዝ የሚገባው መሆኑን በማመን በየኪሳችን ያለውን ዘውድ ለመጣል ቢያሳሳንም በየቁም ሳጥናችን ውስጥ የምንቆልፍበት  ደረጃ ላይ ለመድረስ የሚያስችለን ዘመቻ በየራሳችን  ላይ ላይ እናውጅ፡፡

ብእረኛው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድን በትያትሩም በሥነ- ግጥሙም ለመምከርም ለማነሳሳትም ብሎ ብሎ ሲያቅተው  ይመስለኛል በስተመጨረሻው ግድም ይድረስ ለእኛ ከእኛ የሚል ተከታታይ ግጥም በጦቢያ መጽሄት አስነብቦን ነበር፤ ያም አንባቢ እንጂ የሚገነዘብ፣ የሚመለከት እንጂ የሚያስተውል ለማግኘት አልበቃም  እንጂ፤ እሱ እንኳን ይህችን ዓለም ከተሰናበተ አስራ አምስት አመታት ተቆጠሩ፡ በህይወት ያለነው ግን ወደፊት የለ ወደ ኋላ የለ እንደ ተርኪስ ባቡር ተገትረሽ ቅሪ እንደተባለው አንድ ቦታ እንደተቸከልን አለን፡፡ እስቲ ታዲያ ዛሬ እንኳን ትንሽ በምንላቸው መገዛታችን፣ በምንንቃቸው መዘረፋችን ይቁጨንና፣ ምንም ማደርግ ባለማቻላችን ህሊናችን ይወቀሰንና፣ ለልጆቻችን ምን እያቆየን እንደሆነ ለአፍታ ይታሰበንና ወዘተ የሶስት ወር ዘመቻ በራሳችን ላ አውጀን እኛ በእኛ ብለን እንነሳ፡፡ ያጣነው ፍቅር ነው እንጂ፤የራቀን ከራስ በላይ ማሰብ ነው እንጂ፣ችግራችን የሥልጣን ጥም ሆኖ ነው እንጂ  ወያኔን አስገድድም ሆነ አንበርክኮ ኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ካባ ማለበስ ለ90 ሚሊዮን ሕዝብ የሚገድም የሚከብድም አልነበረም፡፡( ቀሪው ወያኔ ቢሆን ማለቴ ነው)

ታዲያ እንግዲህ አንቺ ኢትዮጵያ እኛስ ልጆችሽ ምንድን ነን?

አመንኩሸ ማለት የማንችል ፍቅራችን የሚያስነውረን፣

ዕድላችን የሚያስፎክረን

ቅንነት የሚያሳፍረን ቂማችን የሚያስደስተን

አረ ምንድን ነን? ምንድን ነን?

አሜኬላ የሚያብብብን

ፍግ የሚለመልምብን

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን

The post ለአዲስ ዓመት ቅድመ ዝግጅት- በራሳችን ላይ እንዝመት፣ – ይገረም አለሙ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የፍፃሜው ጦርነት ነው፤ ሁሉም ዐማራ ዘብ ይቁም ለኅልውናው!!

$
0
0

ቅጽ 1 ቁጥር 4
ሀምሌ 2 ቀን 2009 ዓ.ም

         “የምኖርበትን ቤት ለምን ያቃጥሉብኛል?”  ህፃን ዩሓን ዮሐንስ

ረቡዕ ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ.ም የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው በለንደን ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 1 ሰዓት ላይ በለንደኑ ግሬንፌል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ (Grenfell Towers) ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በለንደን ታሪክ እጅግ አስቃቂ የተባለ አደጋ አደረሰ። በዚህ የእሣት አደጋ በጣም የደነገጠችውና ግራ የገባት ጨቅላ ህፃን ዩሓን ዮሐንስ “የምኖርበትን ቤት ለምን ያቃጥሉብኛል?” በማለት የእምባ ሳግ እየተናነቃት ፊት ለፊት የከበቧትን የለንደን ነዋሪዎችና ጋዜጠኞች ጠየቀች። ዩሓን ዮሐንስ አከታትላም ከምትኖርበት ሕንፃ መቃጠል ጋር በተየያዘ የደረሰባት ከፍተኛ የአዕምሮ መረበሽና ጭንቀት ሳያግዳት፣ የምትወደውን እርሳስና ወረቀት አንስታ ሁሉንም ባስደመመ መልኩ አሰቃቂውን ቃጠሎ በሥዕላዊ መግልጫ መልክ ለጋዜጠኞች አቀረበችላቸው። ጋዜጠኞችም የጨቅላዋን የአዕምሮ መረበሽና ተሰጥዖ ጭምር የሚያሳየውን ሥዕሏንና ጥያቄዋን በመገረም ተቀብለው የጋዜጣቸው የግርጌ ማሳታዎሻ አደረጉት::

በዚህ አጋጣሚ ለዩሓን ዮሐንስ የአዕምሮ መረጋጋቱንና እንዲሁም በእሳት ቃጠሎው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች ደግሞ መጽናናቱን እግዚአብሔር እንዲሰጥልን እየተመኘን፣ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ግን በድንገተኛ አደጋ ምክንያት ስለተቃጠለው የግሬንፌል ሕንፃና እርሱን ተከትሎ ስለታየው የጨቅላ ዩሓን አስደማሚ ሁኔታ ለመዘገብ ሳይሆን ከዚህ እጅግ ስለከፋና ሆን ተብሎ ስለተፈፀመ አሰቃቂ እልቂት ለማውሳት ነው። አዎ! ግሬንፌል ሕንፃ ላይ የደረሰው አደጋ የሚያሳዝን ቢሆንም ዘርና ቀለም ሳይለይ በማንም ላይ የደረሰና ሆን ተብሎ ያልተፈፀመ ድንገተኛ አደጋ ነው።

በተቃራኒው ሕፃን ዩሓን ያላወቀችዉ ጉድ በኢትዮጵያ ተፈፅሟል፤ እስከ አሁኗ ሰዓትና ደቂቃም በመፈፀምም ላይ ነው። በኅዳር ወር 1993 ዓ.ም. ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ የዩሓን የዕድሜ እኩያ ወይም ከእርሷ ያነሱ ሕፃናት ከዐማራ ቤተሰብ በመወለዳቸው ብቻ በወያኔ ትዕዛዝ በኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ካድሬዎችና ወታደሮች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቤት ተዘግቶባቸው መቃጠላቸውን ብንነግራት ዩሓን ምን ያህል ታምነን ይሆን? ይህ ብቻ አይደልም፤ ከዚህም የበለጠ ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊት ተፈፅሟል እንጅ። ተዝግቶ ከሚቃጠለው ቤት ያመለጡ የዩሓን የዕድሜ እኩዮች ወይም የበታቾች፣ በተአምር ከሚቃጠለው ቤት አምልጠው ሲሮጡ፣ ዙሪያውን ከብበው የነበሩት ካድሬዎች እያነቁ ከሚነደው እሣት መልሰው በመጨመር አንድደዋቸዋል። ይህ ልብወልድ ሳይሆን በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በዐማራው ቤተሰብና ሕጻናት ላይ ዐማራ ሆነው በመወለዳቸው ብቻ የተፈፀመና እየተፈፀመ ያለ እጅግ ዝግናኝ ዕውነታ ነው። የምሥራቅ ወለጋውን እንደምሳሌ አነሳነው እንጅ ይህ በዐማራው ላይ በወያኔዎችና በጀሌዎቻቸው እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብአዊና እጅግ ሰቅጣጭ ድርጊት በየትኛውም ቦታ እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈፀመብት ነው። በንፁህ ኅሊናው ለሚፈርድ ሰው ይህ በዩሓን እና በመሰሎቿ በግሬንፊል ሕንፃ ላይ የደረሰው ድንገተኛ የእሣት ቃጠሎ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐማራ በመሆናቸው ብቻ እየተዘጋባቸው ከሚቃጠሉት ጋር በማንኛውም መሥፈርት ፍፁም ሊወዳደር አይችልም።

ይህን መሰሉ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ድርጊት ወያኔዎች መፈፀም የጀመሩት ገና በ1972 ተከዜን ተሻግረው ወልቃይትና አካባቢው እግራቸው ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ ነው። ጉዳዩ የመከረኛውና የወዳጅ – አልባው የዐማራ ሕዝብ ጉዳይ በመሆኑ አስታዋሽ አጣ እንጅ፣ ወያኔዎች በዐማራውና በተልይም በወልቃይት ሕዝብ የፈፀሙት የዘር ፍጅት ሂትለር አውሮፓ ውስጥ ይኖሩ በነበሩ የአይሁድ ተዋሎጆች ላይ እ.አ.አ. ከ1933-1945 ድረስ ከፈፀመው የዘር ፍጅት የማይተናነስ ነው። ሂትለር አይሁዶቸን በመርዝ ጭስ ፈጅቶ ሳሙና እንደሠራባቸው ሁሉ ወያኔዎችም የወልቃይትን ዐማራዎች ጉድጓድ ውስጥ ቀብረው እየተሉ እንዲሞቱ፣ አለበለዚያም እዚያው ጉድጓድ ውስጥ በጭስ አፍነው ከገደሏቸው ብኋላ አቃጥለዋቸዋል። የተከመረውንም አጥንትና አመድ “የትግራይን መሬት የምናለማበት ማደባሪያ ነው” እያሉ ግፍን ሳይፈሩ ተመፃድቀዋል። ሂትለር ከአይሁዶች ሰውነት ሣሙና ሲሠራ፣ ወያኔ ደግሞ ዐማራን አቃጥሎ ለትግራይ ምድር ማደበሪያ አደርገዋልሁ አለ። ታዲያ በዚህ ዓይነት ሂትለርና ውያኔ ልዩነት አላቸው? በፍፁም የላቸውም። ይሁንና በጨካኝ ዘረኞች የዘር ፍጅት የተፈፀመባቸው አይሁድና ዐማራ ግን ልዩነት አላቸው። በዘራቸው ላይ ሂትለር የዘር ፍጅት በመፈፀሙ ውስጣቸው የተነካው በዐልም ዙሪያ ያሉ አይሁዶች ሁሉ እንደ አንድ ሰው በአንድነት በመነሳትና በመተባበር እንዲህ ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ ዘራቸውን ያጠፋውን የናዚ አባል የሆነውን ሁሉ እየተከታተሉ ለፍርድ አቅርበው ተበቅለውታል።  የእኛ ዐማራ ግን እንደ አይሁዶቹ አንድ ሆኖ በመቆም ጠላቱን ሊበቀልና ለፍርድ ሊያቀርብ ቀርቶ፣ ችግሩ ቀድሞ ገብቷቸው በዐማራነት ለመደራጀት የሚሞክሩትን “ዐማራ መደራጀት የለበትም” በማለት ከማንም ቀድሞ እንቅፋት ይሆንበቸዋል።

የዐማራው እልቂት የጀመረው ወያኔ ደርግን ጥሎ ምኒልክ ቤተመንግሥት ከገባ ከ1983 ጀምሮ ሳይሆን ከላይ እንደተጠቀሰው ወልቃይትን ከረገጠበት ከ1972 ዓ.ም. ጅምሮ ሲሆን በአሶሣ በኩል ደግሞ ከ1982 ጀምሮ ነው። በኦነግ መሪነት፣ በወያኔና ሻቢያ ተባባሪነት (ሱዳንን ባሳተፈ መልኩ) አሶሣ ወስጥ በጥር ወር 1982 ዓ.ም. ከ300 በላይ የሚሆኑ ዐማራዎች ተልይተው ሕፃናት፣ ሴቶች፣ እመጫቶች፣ ወጣቶች፣ ወንዶችና አረጋውያን በአንድ ላይ ተረሽነዋል፤ ትምህርት ቤት ወስጥ ተቆልፎባቸው በእሣት ጋይተዋል። ይህ ዐማራን የማጥፋቱ ሥራ ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላም በመላ ሀገሪቱ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በስፋትና በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል። በወገኖቻችን ላይ ይህ አሰቃቂ የግፍ ጨፍጨፋ የተደረገባቸውና እየተደርገባቸው ያለው ምንም ወንጀል ሠርተው ሳይሆን ዐማራ ሆነው በመወለዳቸው ብቻ ነው። በለየላቸው ዘረኞች ዐማራን ነጥሎ የሚደረገው የዚህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ጭፍጨፋና የእሣት ቃጠሎ እኛን የግፉ ሰለባ የሆነውን የዐማራ ተወላጆች ዛሬም ድረስ እሣቱ ትኩስ ሆኖ እየፈጀን መሆኑን ዓለም እንዲያውቅልን እንሻለን!  ይህንን አረመኒያዊ የዘር ፍጅት የፈፀሙት ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ለፍርድ ቀርበው ተገቢ ቅጣታቸውን እስኪያገኙ ድረስም ፈፅሞ እርፈት አይኖረንም።

ወደ ተነሳንበት ርዕስ እንምጣና እንሆ ባለፈው ዓመት፣ ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ከወሰደው የኅልውናና ሕጋዊ ራስን የመከላከል እርምጃ ጋር በተየያዘ በጎንደርና በጎጃም በሚገኙ የዐማራ ነገድ ተወላጅ ወገኖቻችን ላይ የማያባራ እሣት እየነደደ ነው። በዚህ ኢሰብአዊ  ጭፍጨፋ ያልረካው ናዚው የትግሬ የወያኔ ቡድን አሁን ደግሞ የኅልውናና የማንነት ጥያቄን ላነሳው ሕዝብ እየሰጠ ያለው ምላሽ ፍትሃዊ ምላሽ ሳይሆን፣ ልክ ጠላት የሆነ ሌላ ሀገርን እንደሚወር ሁሉ በከባድ መሣሪያ ሳይቀር ሙሉ የሀገር መከላከያ ኃይሉን እስከአፍንጫው አስታጥቆ መላ ጎንደርን በማንደድ ነው። አዎ፣ ለጊዜው የጎንደርን ያክል አይሁን እንጅ የጎጃም ወገናችንም የዚሁ እልቂት ገፈት ቀማሽ ነው። መሠሪው ወያኔ የጎንደርን ዐማራ ለዘር እንዳይተርፍ ካደረገ በኋላ የቋጠረውን ቂም እንደያዘ ወደ ጎጃም ሕዝብ በሙሉ ኃይሉ እንደሚመለሰ ሳይታለም የተፈታ ነው። ከዚያ ወሎና ሸዋ ተራ በተራ የናዚውን የዕልቂት ፅዋ ይጎነጫሉ። በአራቱ ከፈለ ሀገራትም ሆነ በየትም ያለው ዐማራ ሁሉ የወያኔውን እኩይ ዓላማ በመረዳት ሁሉም በያለበት መነሳትና ራሱን ከጥፋት መከላከል ለነገ የማይለው የኅልውና ግዴታው ነው። ወያኔ ገና ከጥዋቱ ዓልሞ የተንሳው የዐማራን ዘር ለማጥፋት እንጅ ጎንድርን ወይም ጎጃምን ብቻ ለይቶ ለማጥፋት አይደለም።  አሁን ጎንደር ተነጥሎ ሲመታ ሌላው ዐማራ “እኔ ልተርፍ እችል ይሆናል” ብሎ እጁን አጣጥፎና አፉን ለጉሞ ከተቀመጠ ልክ “የገናው በሬ ሲታረድ፣ የፋሲካው በሬ ሣር ይግጣል” እንደሚሉት መሆኑን በእርግጠኝነት ልንነግረው እንወዳለን። ልክ እንደገናውና የፋሲካው በሬዎች የጊዜ ቅደም – ተከተል ጉዳይ እንጅ ሁሉም አይቀርለትም። ስለዚህ ናዚው ወያኔ አንድ በአንድ ነጣጥሎ ሳያጠፋን በፊት ዛሬውኑ በያለንበት ሆ ብለን እንነሳ።

ሌላው ደግሞ ይህን በወገን ላይ የሚፈፀምን የዘር እልቂት እያዩ ያሉ የአገር ውስጥ ታማኝ ተቃዋሚ ተብዬዎችም ሆኑ በውጭ ሀገር ያለው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በጎንደር ወገኖቻችን ላይ የናዚው ትግሬ ወያኔ ጦር የገበሬውን ቤት በከባድ መሣሪያ እያቃጠለና ሕዝቡንም ሕፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ወንድ ሳይል በመደዳ ሲጨፈጭፍ እንደወገን ተቃውሟቸውን በማሰማት ፋንታ ዝምታን መርጠዋል። አንዳንዶቹማ እንዲያውም “ላም ባልዋለበት፣ ኩበት ለቀማ” እንደሚባለው አንድ እንኳን ወታደር ባላሰለፉት የጦር አውድማ ላይ ጥይት በጮኸ ቁጥር “የእኛ ጦር ነው” እያሉ በዐማራው ገበሬ ደም እየነገዱበት ነው። እንዲህ ያለውን ለከት የለሽ ድርጊት የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) ከምር ያወግዘዋል! ምክንያቱም ባልዋሉበት የጦር ሜዳ የዐማራውን ድል መቀማት አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ዐማራውን ሆን ብሎ ለማስጨረስ የተሸረበ ሤራ እንደሆነ አድርጎም ስለሚቆጥረው ነው።

ግንቦት 7 በጎንደርና በጎጃም ወታደር ሳይሆን ያለው፣ ከሕዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ ተከፋይ የሆኑ ወሬ አቀባዮች ብቻ ነው። እነዚህ የኢሣት የመሥመር ወሬ አቀባዮች የሚያቀበሉትን ዜና ደግሞ ናዚው የትግሬ ወያኔ ቡድን በሁለት ዐበይት ምክንያቶች እጅግ በጣም ይፈልገዋል:: የመጀመሪያውና ዋናው ምክንያት በጎንደርና በጎጃም እየተካሄደ ያለውን የዐማራ ኅልውናን የማዳን ሕዝባዊ ትግል ወያኔ “የሻዕቢያ ተላላኪ” ብሎ በፈረጀው ግንቦት 7 እየተካሄደ ያለ የሽብር ድርጊት እንጅ የዐማራን ኅልውና ለመታደግ እየተደረገ ያለ ሕዝባዊ ትግል መሆኑን ለማዳፈን ይጠቅምበታል። ይህም የጥያቄውን አቅጣጫ በማስቀየሩና ጭራሹንም ግንቦት 7 በሚያቀርበው “የኔ ትግል ነው” ጥያቄ ምክንያት ሁሉም የዐማራው ነገድ ተወላጆች “የእኛ ትግል ነው” በማለት በአንድ ጊዜ ሆ! ብለው እንዳይነሱበት  ረድቶታል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወያኔ የዐማራ ነገድ ተወላጆችን እንደፈለገ ለመግደልና ለማስር በአሸባሪነት የፈረጀውን የግንቦት 7ን “ትግሉ የኔ ነው” ጥያቄ በደንብ ተጠቅሞበታል። ለዚህም ነው ግንቦት 7 “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እየሄደ ለወያኔ ጥይት እያቀበለ “ለኅልውና” እየተደረገ ያለውን ትግልና ወገናችንን በጅምላ ደርቦ እያስመታ ነው ብሎ ዐኅኢአድ በጽኑ የሚያወግዘው!! ግንቦት 7 ይህን መሰሉን ደባ በዐማራው ሕዝብ ላይ ከመፈፀሙም በላይ በአባላቱ አማክኝነት በግልፅም ሆነ በሥውር “ዐማራው መደራጀት የለበትም” እያለ ደጋግሞ መዝመቱንም አኅኢአድ ያወግዛል።

በመሠረቱ በመርህ ደረጃ የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ከግንቦት 7 ጋር ምንም ዓይነት ጠብ የለውም። ግንቦት 7 ዕውን ተዋጊ ሠራዊት “አለኝ” በሚላቸው ቦታዎች ሁሉ ሠራዊት ኖሮት ቢዋጋና ሕዝባችን ላይ የሚወርደውን ፍላፃ ለመመከት ሙከራ ቢያደርግ “እሰየው” ብለን ከጎኑ በቆምን ነበር። ባለመታደል ግን ባልተገኘበት የጦር አውድማ ሁሉ በአፈጮሌነት የዐማራውን ድል እየነጠቀ በእርሱ ስም የዐማራው ገበሬ በፋሺስቱ ወያኔ ያለምንም ርህራሄ እንዲጨፈጨፍ ማድረጉ በጣም እያሳዘነን ነው። ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ ወያኔ ወገናችንን መጨፍጨፉ ብቻ ሳይሆን ነገ ከነገ ወዲያ እንኳን ለፍርድ እንዳይቀርብ ግንቦት 7 የሕግ ከለላ እየሰጠው መሆኑ ነው። ምክንያቱም ምንም እንኳን የወያኔን አሻንጉሊት ፓርላማ እኛ ተቃዋሚዎች ባንቀበለውም፣ ግንቦት 7ን “አሸባሪ ድርጅት” ብሎ ፈርጆታል። ይህ “አሸባሪ” የተባለ ድርጅት ደግሞ ባልዋለበት የጦር ሜዳ ዋልኩ እያለ ወያኔ “አሸባሪውን ድርጅት መታሁ” እያለ ምስኪኑን የዐማራ ገበሬ ያለምንም ረህራሄ እንዲጨፈጭፍ መንገድ ከፍቶለታል። ይህ ደርጊት ደግሞ ባለማወቅ ተደርጓል ብለን አናምንም። ስለዚህ ግንቦት 7 ከእንዲህ ዓይነቱ እኩይ ድርጊት እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

ግንቦት 7 እንደሚለው ዕውን ከልቡ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመ ቢሆን ኖሮ በአንድነቱ የማያወላውለውን የዐማራ ነገድ አግልሎ “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዣችን ናት” ከሚሉት ጋር ጥምረት እየፈጠረ ሽር-ጉድ ባላለ ነበር። ነገሩ “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ” እንደሚባለው ሁሉ እኛም ግንቦት 7 ጥምረት ከነማን ጋር እየፈጠረ እንደሆነ አየንና ማንነቱን አወቅን። በመሆኑም ለግንቦት 7 ተገንጣይ ጓደኞችህን ጠበቅ፣ ዐማራውን ለቀቅ አድርግ ልንለው ተገደድን።

ይህንን ካልን በኋላ በዐማራ ስም ለተደራጁ ድርጅቶችና ለመላው የዐማራ ሕዝብ ጥሪ ማስተላለፍ ፈለግን።

1/ በዐማራ ስምም ሆነ በክፍላተ – ሀገራት ለተደራጃችሁ በሙሉ!

ፋሺስቱ ወያኔ የዛሬ 42 ዓመት ሲቋቋም ምንም ያላደረገውን የዐማራ ሕዝብ “ዐማራ ጠላቴ ነውና ማጥፋት አለብኝ” ብሎ ነው የትግል ፕሮግራም ነድፎ ጫካ የገባው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ልክ የዛሬ ዓመት እነኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለኅልውናቸው ሲሉ ባልሞት ባያ ተጋዳይነት እስከተኮሷት ራስን የመከላከል ጥይት ድረስ ዐማራው ዝም ብሎ ሲታረድ ነበር የኖረው። ከሃምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግን ዐማራው በሙሉ ኃይሉም ባይሆን በአንዳንድ ቦታዎች (በተለይ በጎንደርና በጎጃም) ራሱን መከላከል በመጀመሩ ወያኔው ዐማራው ተደራጅቶ ቢነሳ ምን ዓይነት ኃይል ሊሆን እንደሚችል ትምህርት አግኝቶበታል። በመሆኑም ይህንን መሰሉን ኃይል “ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ሳይደራጅ ነጣጥሎ እያጠፋው ነው። እያንዳንዱ በዐማራና በክፍለሀገር ደረጃ የተደራጀ የዐማራ ስብስብ ከተደራጀንበት ርዕዮተ ዓልም በፊት ኅልውና ይቀድማልና ኅልውናው ፍፁም አደጋ ላይ ያለው ወገናችን በፋሺስቱ ወያኔ ጨርሶ ከመጥፋቱ በፊት በማንኛውም መልኩ ተባብረን እንድንታደግው (ዐኅኢአድ) ክልብ ጥሪ ያቀርባል። ይህንን ጊዜ የማይሰጠው የኅልውና ትግል ለማስተባበር አንድ የጋራ ግበር – ኃይል በአስቸኳይ አቋቁመን የወገናችንን ኅልውና እንድንታደግ በፋሺስቱ ወያኔ በግፍ በሚጨፈጨፈው የዐማራ ወገናችን ስም እንጠይቃለን።  ኅልውናችን በአስተማማኝ ሁኔታ ካስጠብቅን በኋላ ብንስማማ የጋራ ግብረ – ኃይሉን ይበልጥ አጠናክረን አብረን እንቀጥላለን፤ ካልተስማማን ደግሞ የየራሳችን የትግል መሥመር ተከትለንና ከጎንዮሽ ትግል ታቅበን በየመረጥነው መሥመር መጓዝ እንችላለን።

2/ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ እንዲሁም በተለያዩ ክፍላተሀገራትና በውጭ ሀገራት ላለው መላው የዐማራ ሕዝብ!

ፋሺስቱ ወያኔ አንተን አጥፍቶ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ምን ያህል እየሠራ እንደሆነ ከትናንት ዛሬ ይበልጥ ግልፅ የሆነልህ ይመስለናል። እኛም አምርረን የምንነግርህ ናዚው ወያኔ የዐማራን ዘር ከምድረ-ገጽ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይተኛ ነው። ይህንን ደግሞ እኛ ሳንሆን የምንነግርህ ፋሺስቱ ወያኔ ራሱ በ1968 ዓ.ም. ባወጣው የድርጅት መመሪያ (ማኒፌስቶ) “ዐማራ ካልጠፋ ትግራይ ማኅበራዊ እረፍት አታገኝም” ብሎ አውጇል። በዚህ መመሪያው መሠረትም እስከአሁን በጥቂቱ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዐማራ ከምድረ ገጽ አጥፍቷል። ዐማራ ሴቶች ዘራቸውን እንዳይተኩ እንዲመክኑ ሲደረጉ፣ ወንዶች ደግሞ በሰበብ አስባቡ በታሠሩ ቁጥር ብልታቸው እየተቀጠቀጠ እንዲመክኑ ተደርገዋል። ቤት እየተዘጋባቸው ተቃጥለዋል፤ ከነሕይዎታቸውም ገደል ተጥለዋል። መናኝ መነኮሣት ሳይቀሩ በዐማራነታቸው እየተመረጡ በአፀያፊ ሁኔታ በትግሬ ኮርማዎች ተደፍረዋል፤ ከገዳምም ተባረዋል። በአጠቃልይ ባለፉት 40 ዓመታት ተዘርዝሮ የማያልቅ እጅግ ብዙ አስቃቂ ግፍ በዐማራው ነገድ ላይ ተፈፅሟል። አሁንም እጅገ በተጠናከረ ሁኔታ በጎንደር ሕዝብ ላይ ሠራዊቱን አዝምቶ ንፁሐን ገበሬዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ያለምንም ረህራሔ እየጨፈጨፈ ነው። የጎንደርን ዐማራ ከጨረሰ በኋላ አንድ በአንድ ወደ ሌሎቹ የዐማራ ክፍላተ ሀገራት ሣንጃውን እንደሚያዞር ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለዚህ ጀግናው የጎንደር ዐማራ በፋሺስት ከበባ ከመጥፋቱ በፊት ቀኝ ክንዱ የሆነው የጎጃም ሕዝብ ልክ አምና እንዳደረገው አሁንም በየቦታው ተነስቶ ወያኔን መውጫ መግቢያ ሊያሳጣው ይገባል። ወሎም ሆነ ሸዋ እንዲሁ። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ያለው ዐማራ ደግሞ በሥውር በመደራጀት በስንቅ ወገኑን ማገዝ ይጠበቅበታል። በውጭ ሀገር የሚኖረው የዐማራ ልጅ ደግሞ ያለ የሌለ አቅሙን በማስተባበር በመዋደቅ ላይ ላለው ዐማራ ወገኑ እንዲደርስለት ዐኅኢአድ ጥሪ ያቀርባል። አንገት ደፍቶና እጅን አጣምሮ በመቀመጥ ከወያኔ ጭፍጨፋ ሊያመልጥ የሚችል ዐማራ የለም። ምክንያቱም በወያኔ መዝገበ ቃላት ዐማራነት ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል ነውና! በመሆኑም የትም ያለ ዐማራ እንደ አንድ ሰው ተባብሮ ይህንን በፋሺስቱ ወያኔ የተከፈተብትን የእልቂት ጦርነት ካልመከተ በቀር፣ የዐማራ ዘር ታሪክ ሆኖ እንደሚቀር መናገር ገሀድ ዕውነታውን ከመመሥከር ውጭ ነቢይነትን አያመለክትም። ሕዝባችን ቃላት ሊገልፀው ከሚችለው በላይ ፍፁም የመጥፋት አደጋ ላይ ነው። ስለሆነም ዐማራው በአንድ ላይ ተባብሮ ራሱን ካላዳነ በስተቀር ማንም እርሱን ለማዳን ከየትም አይመጣም። ዐማራን የሚያድነው ዐማራ ብቻ ነው። ስለሆነም የዐማራ ልጆች ሆይ! የፍፃሜው ጦርነት ነው፤ ሁሉም ዐማራ ዘብ ይቁም ለኅልውናው!!

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና ነው!!

 

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ)

 

The post የፍፃሜው ጦርነት ነው፤ ሁሉም ዐማራ ዘብ ይቁም ለኅልውናው!! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


‹‹ኢትዮጵያ የባህር ኃይሏን መልሳ ለመመሥረት ማጤን አለባት››አቶ አብዱል መሐመድ፣ የኢንተርአፍሪካ ግሩፕ መሥራች

$
0
0

ሳዑዲዎቹ በድጋሚ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ማቅረባቸው እንደማይቀር ይሰማኛል፡፡

አቶ አብዱል መሐመድ፣ የኢንተርአፍሪካ ግሩፕ መሥራች

አቶ አብዱል መሐመድ የኢንተርአፍሪካ ግሩፕ መሥራች አባል ናቸው፡፡ በኢንተርአፍሪካ ግሩፕ የሰብዓዊ፣ የሰላምና የልማት ጉዳዮች የምክክር ማዕከል የአፍሪካ ቀንድ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥም ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ተቋሙ በኢትዮጵያ የ1997 ጠቅላላ ምርጫ ወቅት ፖለቲካዊ ውይይቶችና ክርክሮች እንዲደረጉ በማገዝ መንቀሳቀሱ ይታወሳል፡፡ አቶ አብዱል የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ለዓመታት አገልግለዋል፡፡ በሙያው ዓለምም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) እንዲሁም በአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው በማገልገልም የካበተ ልምድና ተሞክሮ አላቸው፡፡ ከሚጠቀሱት ዋና ዋናዎቹ ኃላፊነቶቻቸው መካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዳርፉር ወታደራዊ ተልዕኮ (ዩናሚድ) የፖለቲካ ክፍል ተጣባባቂ ዳይሬክተር፣ እንዲሁም የዳርፉር- ዳርፉር የምክክር መድረክ ሊቀመንበር በመሆን መሥራታቸው ይገኙበታል፡፡ በተመድ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የአፍሪካ ኅብረት ተወካይ በመሆን ከመሥራታቸውም በተጨማሪ፣ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የዓለም ቤተ ክርስቲያን አግልግሎት ውስጥ በተለያየ ደረጃ ከማገልገላቸውም በላይ፣ ለሱዳን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የዕርዳታና የፈጥኖ ደራሽ ክፍል ዳይሬክተር በመሆን ሠርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የዕርቅ ጉዳዮች አማካሪ በመሆን ያለገሉበትም ከሚጠቀሱ ተሞክሮዎቻቸው መካከል ይመደባል፡፡ ግጭት በማያጣው በመካከለኛው ምሥራቅና በባህረ ሰላጤው አገሮች ጉዳይ፣ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ስላለው ተፅዕኖ የጠለቀ ዕውቀት ያላቸው አቶ አብዱል፣ ባለፈው ሳምንት ከሪፖርተር ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ የዓረብ ባህረ ሰላጤ አገሮች ቀውስ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ በግላቸው ያላቸውን ዕይታና ትንታኔ አሥራት ሥዩም እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡ 

ሪፖርተር፡- እንደሚታወቀው የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በተለይም ደግሞ በዓረብ ባህረ ሰላጤ ምክር ቤት (GCC) አገሮች በቅርብ ጊዜ እየተስተዋለ ያለ ከፍተኛ የጦር ኃይል ማጠናከር እንቅስቃሴ አለ፡፡ በተለይ እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ አገሮች በመከላከያ ዘርፍ የሚያፈሱት መዋዕለ ንዋይ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ለምን እየተዘጋጁ ይመስልዎታል?

አቶ አብዱል፡- በትክክል እንደተረዳኸው በገልፍ አገሮች አካባቢ ከፍተኛ የሚሊተሪ ዝግጅት መስተዋል ከጀመረ ቆይቷል፡፡ ዋናው ነገር እነዚህ አገሮች ምን ዓይነት የፀጥታ ችግር ቢኖርባቸው ነው፣ በዚህ ደረጃ የጦር ኃይላቸውን ማደራጀት ያስፈለጋቸው የሚለው ጉዳይ  ነው፡፡ በታሪክ ስንመለከት ቀደም ብሎ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር የነበረበትና ግጭት የማይጠፋው የመካከለኛው ምሥራቅ ክልል ወደ ሰሜን ያለው ማለትም ኢራቅን፣ ኢራንን፣ ሶሪያን፣ ሊባኖስንና ፍልስጤምን የሚያጠቃልለው ክፍል ነበር፡፡ ይህ አካባቢ በጣም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የበዛበትና ግጭቶችም በተደጋጋሚ የሚደርስበት ክልል ነበር፡፡ ነገር ግን በኢራንና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው ዘላቂ ጠላትነት እየከረረ በመሄዱ፣ አሁን የገልፍ አካባቢም እንዲሁ በወታደራዊ ውጥረት ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህ ዘላቂ ጠላትነት እንደሚታወቀው በየመን ወደ የእጅ አዙር የለየለት ጦርነት ተቀይሯል፡፡ በጂሲሲ ሥር ያሉት አገሮችን ጨምሮ ሳዑዲ ዓረቢያ መራሹ ቡድን በየመንና በኢራን ይደገፋል ተብሎ ከሚታሰበው የሁቲ የአማፅያን ቡድን ጋር እየተዋጋ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል በተለይ ሳዑዲ ዓረቢያ በምዕራቡ ዓለም በአሜሪካና በኢራን መካከል እየተፈጠረ የመጣው መለሳለስ እያሠጋት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዋናነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዘመን ከኢራን ጋር የፈረሙት የኑክሌር ስምምነት፣ ለሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የፀጥታ ሥጋት የፈጠረባት ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ የወታደራዊ አቅሟን ማጠናከር መርጣለች፡፡ ለነገሩ ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በኋላ ሳዑዲ ዓረቢያ አሜሪካ የገባችላትን ድጋፍ ለመስጠት ቃል ለማደስ በሩ ክፍት ቢሆንም፣ በኦባማ ጊዜ ግን ይህ ሥጋት ያየለበት ነበር፡፡ በእኔ አመለካከት ሳዑዲ ዓረቢያ ከኢራን በኩል ሊሰነዘርብኝ ይችላል የምትለው ጥቃት ሥጋት ያለልክ የተጋነነ ነው፡፡ አሁን ይህ መጋነን ቅጥ ያጣ እየሆነም ይመስለኛል፡፡ በሌላ በኩል ኢራን ከፀጥታው ምክር ቤትና ከጀርመን ጋር የፈረመችው የኑክሌር ስምምነት ለሳዑዲ ዓረቢያና ለአካባቢው የሳዑዲ ተቀፅላ አገሮች ተጨማሪ የፀጥታ ማረጋገጫ ሲሆን፣ አገሮቹ ግን እንደ ሥጋት እያዩት ነው፡፡ ይህ ስምምነት እነዚህ የምዕራብ አገሮችና የፀጥታው ምክር ቤት የነሳዑዲን የፀጥታ ጉዳይ ለኢራን አሳልፎ የሸጠም አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሳዑዲ ዓረቢያዎቹ የሚፈልጉት ማረጋገጫ በጣም የተጋነነና መቶ በመቶ የሆነ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ የተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተው የሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ሥጋት፣ አገሪቱን ወደ ተጋነነ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድትሄድ አድርጓታል፡፡

በዚህ አላበቃም፡፡ አሁን ደግሞ እነዚህ የገልፍ አገሮች ከራሳቸው ክልል አልፈው በአጠቃላይ የቀይ ባህር ክልልን እያስታጠቁ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ቀይ ባህር አካባቢ ያሉ ወደቦችን ብናይ ከታች ከኪስማዩ (ሶማሊያ) ጀምሮ ላይ ፖርት ሱዳን ድረስ ያለው ክልል በከፍተኛ የወታደራዊ ድርጅትና ትጥቅ እየተጥለቀለቀለ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ይህ የቀይ ባህር ክልል ባብ ኤል መንደብን ጨምሮ ለዓለማችን የንግድ እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በእስያና በአውሮፓ መካከል ያለው ንግድ 40 በመቶ የሚሆነው በዚህ በባብ ኤል መንደብ እንደሚያልፍ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም አብዛኛው የኃይል አቅርቦት ለእስያ አገሮች የሚላከው በዚሁ የባህር መተላለፊያ ነው፡፡ በመሆኑም ብዙዎቹ በዚህ ክልል ላይ ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው አገሮች አሁን የባህር ኃይላቸውን በቀይ ባህር ወደቦች ላይ እያከማቹ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ብትወስድ አሁን ጂቡቲ ላይ ወታደራዊ ጦር ሠፈር የሌለው አገር ጥቂት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሳዑዲዎቹ የጦር መሣሪያ እየታጠቁ ያሉት ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ነው፡፡ አሁን የመን ውስጥ ያለውን ሁኔታ ብታይ በጣም አሥጊ ነው፡፡ እንዲሁም ነባራዊ ሁኔታውን ስንቃኝ የመን አሁን የጨነገፈ አገር ሆኗል፡፡ ታዲያ መንግሥት አልባነት ከከባድ ወታደራዊ እንቅስቃሴና የጦር መሣሪያ ጋር ሲደመር ለእነ አልሸባብና አልቃይዳ ልዩ ዕድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ በመሆኑም የእነዚህ አገሮች በከፍተኛ ደረጃ መታጠቅ ክልሉን ለማተራመስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከላይ እንደጠቀሱት ለዚህ ክልል ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴና ትጥቅ ምክንያቱ በኢራንና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው ዕድሜ ጠገብ የጠላትነት ስሜት ነው፡፡ የዚህ ስሜት ታሪካዊ ዳራው ምንድነው?

አቶ አብዱል፡- እኔ እንደሚመስለኝ ነገሩ ከመንግሥታቱ ተፈጥሯዊ ባህሪ የሚወረስ ነው፡፡ ኢራንን የወሰድን እንደሆነ በተለይ እ.ኤ.አ. ከ1979 የእስልምና አብዮት በኋላ በአገሪቱ በሥልጣን ላይ ያለው ኃይል በከፍተኛ ደረጃ በሃይማኖት የተቃኘ መሆኑ ሲታወቅ፣ በአጠቃላይ ለሺዓ እስልምና ተቋማት እንደ ማዕከል ሲያገለግልም ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም የኢራን መንግሥት ለአብዛኛው በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ የሺዓ አናሳ ማኅበረሰቦች እንደ መጠለያ ይታያል፡፡ በሌላ በኩል ኢራን ከሺዓ ማዕከልነት ባለፈ በታሪክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አንድነቱን የጠበቀ ጠንካራ አገር መሆኑም ይታወቃል፡፡ እንዲያውም የኢራን ታሪክ ከአውሮፓም የቀደመ ጥንታዊ መንግሥትነት ልምድ ያለው ነው፡፡ በአጠቃላይ ኢራን መሠረት ያለው በቅጡ የተደራጀ መንግሥት ያለው አገርም ነው፡፡ ይህ መንግሥት በቅጡ ስትራቴጂካዊ ጥቅሙን ማስከበር የሚችልና ከራሱ አልፎ በአካባቢው ኃይሉን ማሳየት የሚችልም ነው፡፡ በመሆኑም በአካባቢው ካሉት እነ ሳዑዲ ዓረቢያ ባለፈ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ምልከታ ኢራንን ብጥብጥ ፈጣሪ አገር አድርጎ ፈርጆታል፡፡ በሳዑዲና በአሜሪካ እንዲሁም በእስራኤል መካከል ፀረ ኢራን ትብብርም ተፈጥሯል፡፡ በመሆኑም ለዘመናት እነዚህ ሱኒ የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮችና አሜሪካ ኢራንን የመገደብ ስትራቴጂ ሲያራምዱ ኖረዋል፡፡

ነገር ግን በዚህ መሀል የአሜሪካን የኢራቅ ወረራ ይህንን የቆየ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ አወሳሰበው፡፡ ወረራው በሚገርም ሁኔታ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጥቅም የሰጠው ለኢራን ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቱ አሜሪካ በወረራው የተጠናከረውንና በሳዳም ሁሴን የሚመራውን የሱኒ ኃይል (የኢራቅ መንግሥትና ባዝ ፓርቲን) ሲያፈራርስ ለኢራን መልካም አጋጣሚ ፈጠረለት፡፡ ከወረራው በኋላ በኢራቅ ወደ ሥልጣን የመጣው ኃይል የሺዓ ኃይል በመሆኑ ለኢራን ተፈጥሮአዊ ቅርበት ነበረው፡፡ በጥቅሉ ይህ ወረራ በቀጣናው የነበረውን የኃይል ሚዛን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አፋለሰው፡፡ ሌላው በአካባቢው አሻራውን እያሳረፈ ያለው ጉዳይ በሶሪያ የተቀሰቀሰው ግጭት ነው፡፡ የዚህ ግጭት ውጤት ባልተጠበቀ መንገድ የሱኒና የሺዓ ግጭት መሆኑ እየታየ ነው፡፡ በዚህ መሀል እንደ አልቃይዳ ያሉ ኃይሎች በሳዳም ሁሴን የሱኒ መንግሥት መውደቅ ምክንያት የተፈጠረውን የሱኒ ተሟጋችነት ሚናን ብልኃት በተሞላበት ሁኔታ የተጠቀሙበት ሲሆን፣ ይህም የሽብር እንቅስቃሴያቸውን ለማስፋፋት በእጅጉ ጠቅሟቸዋል፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ ቡድኖች በተለይ በኢራቅ ከሳዳም ውድቀት በኋላ የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅመው የእምነት የጎራ ግጭት የቀሰቀሱ ሲሆን፣ በኋላ ወደ ሥልጣን የመጣው የሺዓ መንግሥትም በዚሁ መንገድ መሄዱ ግጭቱ እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል በአሜሪካ ወረራ የተሠራው ሌላው ስህተት ደግሞ በዓረቡ ዓለም ሁለተኛው ጠንካራ ሠራዊት የነበረውን የኢራቅ ጦር [አንደኛ ግብፅ ነው] ሜዳ ላይ መበተን ነበር፡፡ ይህ ጦር የሠለጠነ ሲሆን፣ ያለ ምንም ዓላማ ከተበተነ በኋላ የነአልቃይዳ ፍጆታ  ሆኗል፡፡ በተለይ የአልቃይዳ ግንጣይ የሆነው ኢስላሚክ ስቴት ወይም አይኤስ እንዲቀላቀል በር ከፍቶለታል፡፡ ለዚህም ነው አይኤስ አልቃይዳ እንኳን አስቦት የማያውቀውን ያህል ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የቻለው፡፡ ከዚህ በላይ በኢራቅ የተፈጠረው ክፍተትና በሶሪያ ግጭት የተገኘውን ቀዳዳ በመጠቀም አይኤስ በጣም ሰፊ ቦታን መቆጣጠር የቻለ በመሆኑ፣ ይህም ስኬት አበረታቶት ካሊፌት እስከ ማወጅ ደርሷል፡፡ በኢራቅ ለምሳሌ ሁለተኛዋን ትልቅ ከተማ (ሞሱል) እስካሁን ይዘው በመዋጋት ላይ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- በሌላ በኩል ኢራን ጠንካራ የቀጣናው አገርና የሳዑዲ ዓረቢያ ጠላት ከመሆኗ ባለፈ፣ በአሸባሪነት ዙሪያ ብዙም የታወቀ ሚና ኖሯት አያውቅም፡፡ ነገር ግን አሜሪካም ሆነች እስራኤል የኢራንን መንግሥት ለአሸባሪዎች ድጋፍ በመስጠት ይከሱታል፡፡ እንዲያውም የብዙ የአሸባሪ ግለሰቦች መፍለቂያ ናት የምትባለው ሳዑዲ ዓረቢያ በሽብር ስትወቀስ አይሰማም፡፡ ታዲያ ኢራን በምዕራባዊያን እንድትጠላ ያደረጋት ዋናው ምክንያት ምንድነው?

አቶ አብዱል፡- ዞሮ ዞሮ በኢራን ላይ ያለህ የፖለቲካ አቋም ምንም ይሁን ምን ኢራን አሁንም ቢሆን አንድነቱን የጠበቀ፣ ኃይሉን ከራሱ አልፎ በቀጣናው ላይ ማሳየት የሚችልና ረጅም ታሪክ ያለው አገር ነው፡፡ ይህ አገር ትልልቅ ስትራቴጂካዊ ፈተናዎችን ለማለፍ የሚያስችል አቅም ያለው አገርም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ኢራን ወዳጆቹን መደገፍና ከጠላቶች መከላከል የሚችል አገር መሆኑም ይታያል፡፡ ኢራን በሌላ በኩል የኑክሌር ቴክኖሎጂ ማበልፀግ አቅም ያለው አገር መሆኑም ታይቷል፡፡ በመሆኑም በቅድሚያ ለሱኒ የቀጣናው አገሮች ሲቀጥል ደግሞ ለእስራኤል የማይጋፉት ባላጋራ እየሆነ የመጣ አገር ነው፡፡ በመሆኑም የቀጣናው አገሮች ካለአሜሪካ ዕገዛ የዚህን አገር ግፊት መቋቋም ይከብዳቸዋል፡፡ በቅርቡ የተፈረመውን የኑክሌር ማዕቀፍ ስምምነት ብትመለከት ከስድስት አገሮች ጋር ተደራድሮ የራሱን አገራዊ ጥቅም አስጠብቆ ስምምነት መፈረም፣ በተለይ በዓረቡ ዓለም በቀላሉ የሚገኝ ጥንካሬ አይደለም፡፡ ከዚያ በላይ ኢራን የፈረመችውን ስምምነት በከፍተኛ አፈጻጸም ተግባር ላይ እያዋለች ለመሆኑ የፀጥታው ምክር ቤትም ሆነ ራሷ አሜሪካ መስክረውላታል፡፡ አሁን የትራምፕ መንግሥትና እስራኤል ስምምነቱ በመጀመሪያም የተሳሳተ ነበር ብለው መከራከር ጀምረዋል፡፡ የፀጥታ ምክር ቤት ግን በስምምነቱ ላይ ምንም ችግር የለበትም፣ ሳዑዲ ዓረቢያም ብትሆን የእስራኤልንና የአሜሪካንን አቋም ነው የምታንፀባርቀው፣ ማለትም ስምምነት መኖር አልነበረበትም የሚለውን፡፡

በሌላ በኩል ሳዑዲና እስራኤል በአሜሪካ ላይ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ሲወተውቱ የኖሩት በኦባማ ጊዜ አሜሪካ በቀጣናው ላይ ያላት ግንዛቤ የተለየ ነበር፡፡ እሱም እንደ ኢራን ዓይነት አገሮች ላይ ወታደራዊ ዕርምጃ መውሰድ በቀጣናው ለማቆም የሚከብድ ግጭት መቀስቀስ ሊሆን ይችላል የሚል ነበር፡፡ የኢራን ምላሽ የመስጠት አቅም መናቅ የለበትም የሚለው የኦባማ መንግሥት ዕይታ፣ በተለይ የሆርሙስን መተላለፊያ የመዝጋት አቅም ያላት ኢራን የዓለም አቀፉን የነዳጅ ንግድ ችግር ውስጥ ልትከተው ትችላለች የሚል ሥጋት ነበረው፡፡ በሌላ በኩል አብዛኛውን የመካከለኛው ምሥራቅ የዓረብ አገሮችን የሕዝብ አሠፋፈር ካስተዋልን አብዛኛው የሺዓ ማኅበረሰቦች የሚኖሩት የእነዚህ አገሮች የነዳጅ ሀብት ባለበት አካባቢ ነው፡፡ በመሆኑም በሺዓ ማዕከልነቷ ኢራን ለእነዚህ አገሮች በጣም አደጋ መሆን ትችላለች ማለት ነው፡፡ በቀላሉ ኢራን ቀጣናውን ለአገዛዝ አስቸጋሪ ማድረግ ይቻላታል፡፡ አሜሪካኖቹም ይህንን እውነታ ያውቁታል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካኖች የአብዛኛው የዓረብ አገሮች አቅም ከኢራን ጋር ሲነፃፀር የት እንደሆነ ያውቁታል፡፡ ያለ እነሱ ድጋፍ ራሳቸውን መከላከል እንደማይችሉም ይገምታሉ፡፡ በቀላሉ ሳዑዲ ዓረቢያን ማየቱ በቂ ነው፡፡ አሁን በየመን ሳዑዲ ዓረቢያ በሙሉ ኃይሏ ነው የገባችው፡፡ ለጦር መሣሪያና ትጥቅ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በየዓመቱ እያጠፋች ነው፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ትንሽዬ አመፀኛ ጦር ለማሸነፍና ለመቆጣጠር  ነው፡፡ እንደ አንዳንድ መረጃዎች ከሆነ ሁቲዎች ከኢራን ያገኙታል የሚባለው ድጋፍ በጣም የተጋነነ ነው፡፡ ነገር ግን ሳዑዲ ዓረቢያ የገልፍ አገሮችን ከጎኗ አድርጋ በአሜሪካ የሎጂስቲክስ ድጋፍ ነው ውጊያ ውስጥ የገባችው፡፡ ከዚህ መወሰድ ያለበት ትምህርት ትንሽ ጦር ማሸነፍ ካልቻሉ እንዴት እንደ ኢራን ዓይነት ኃይል ለማሸነፍ ይቻላል? ስለዚህ የቀጣናው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ኢራንን በማግለልና በመጨረሻም ኢራን በቀጣናው የማተራመስ ሚና እንድትጫወት በመግፋት ሳይሆን፣ ከእሷ ጋር በመወያየት ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም እነዚህ አገሮች ኢራንን በአካባቢው እንዳለ አንድ ኃይል መቀበል አለባቸው፡፡ ኢራንም ብትሆን ሌሎችን የቀጣናውን አገሮች መቀበል አለባት፡፡ ከተቻለ እነዚህ አገሮች የሁሉንም ጥቅም የሚያንፀባርቅ የስምምነት ማዕቀፍ ቢኖራቸው ለቀጣናው የወደፊት ሰላም በጣም ወሳኝ ነው፡፡

የዚህ የገልፍ ቀጣና ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ በሁለቱ ቀጣናዎች መካከል በጣም ቅርቡ የሚባለው ቦታን ብንወስድ ባብ ኤል መንደብ ነው፡፡ ባብ ኤል መንደብ ግፋ ቢል ከ25 ኪሎ ሜትር አይበልጥም ከዓረቡ ቀጣና የሚርቀው፡፡ በመሆኑም በዚያ ቀጣና የሚፈጠረው ነገር ለአፍሪካ ቀንድም፣ ከዚያ ባሻገርም ለዓለም በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ በቀይ ባሕርና በኤደን ባህረ ሰላጤ መረጋጋት መኖሩ የተለየ ጥቅም አለው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ 100 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር ናት፡፡ ነገር ግን አጠቃላይ የወጪና የገቢ ንግድ እንቅስቃሴዎችዋ የተመሠረቱት በዚህ የኤደን ገልፍ ላይ ነው፡፡ ይህ አካባቢ ደግሞ በጣም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚበዛበት መሆኑን ቀደም ብለን ገልጸናል፡፡ በነገራችን ላይ የገልፍ አገሮች በወታደራዊ ትጥቅ እየተደራጁ ነው ሲባል፣ ለምሳሌ የሳዑዲ ዓረቢያን ዓመታዊ የመከላከያ በጀት ብናይ ከ87 ቢሊዮን ዶላር የማያንስ ነው፡፡ ይቺ አገር ብቻዋን የምታወጣው ወጪ አጠቃላይ የአፍሪካ አገሮች ተጣምረው በመከላከያቸው ላይ ከሚያወጡት የበለጠ ነው፡፡ ከዓለም አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለችው፡፡ አንዳንዴ ከሩሲያ በላይ ነው የምታወጣው፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ለ30 ሚሊዮን ሕዝብ ነው፡፡ የነፍስ ወከፍ የመከላከያ ወጪ ሲታይ ሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ወታደራዊ ትኩረት የምታደርግ አገር መሆኗን መረዳት አይከብድም፡፡ ነገር ግን የሳዑዲ ዓረቢያ ጦር በሰው ኃይል ደረጃ ሲታይ ያን ያህል ትልቅ አይደለም፡፡ ስለዚህ ትልቁ ጥያቄ በዚህ ሁሉ የጦር መሣሪያ ምን ሊሠሩበት አቅደው ነው የሚለው ነው፡፡ በእኔ አስተያየት ለቀጣናው ሰላም የዚያን ያህል ቢያወጡ የፀጥታ ሥጋታቸውን በተሻለ ሊቀንሱት ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ በየመን ያለው ግጭት ከቀጠለና የጦርነቱ ግፊት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ካዘነበለ ከጊዜ በኋላ ጦርነቱ ከየመን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ መዛወሩ አይቀሬ ነው፡፡ አሁን ችግሩ ይህ ሁሉ የጦር መሣሪያ በማይሆኑ ቡድኖች እጅ እንዲወድቅ በር መክፈቱ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ለመነሻ ያህል ከታሪካዊው የሳዑዲ ዓረቢያና የኳታር ግንኙነት እንጀምር፡፡ ሳዑዲ በኳታር ላይ የበላይነቱን በመያዝ ለረጅም ጊዜ በተፅዕኖዋ ሥር አቆይታታለች፡፡ ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኳታር ከሳዑዲ ጋር የነበራትን ቁርኝት በመተው ይልቁንም የራሷን የወደፊት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ቀይሳለች፡፡ ይህ አፋጣኝ የለውጥ ሒደት እንዲፈጠር ሰበብ የሆነው ምንድነው ብለው ያስባሉ?

አቶ አብዱል፡- ሲጀመር ሳዑዲም ሆነች ኳታር የሚከተሉት ዋሃቢ የሚባለውን የእስልምና ክንፍ ነው፡፡ በዚህ አኳኋን ሲታይ ሁለቱም አገሮች በሃይማኖትም ሆነ በዓለም እሳቤዎች ተመሳሳይ አቋም ይጋራሉ፡፡ ሐሳቡን ይበልጥ ለማስጨበጥ ያህል ሳዑዲና ኳታር በንጉሣዊውያን ቤተሰቦች የሚመሩ፣ በሳዑዲ ወገን አል ሳዑድ፣ በኳታር ወገን ደግሞ አል ታኒ የተባሉት ንጉሣውያን ቤተሰቦች አገሮቹን ያስተዳድራሉ፡፡ እርግጥ ኩዌትና ባህሬንን ጨምሮ ሁሉም በሼኮች አማካይነት በንጉሣውያን ቤተሰቦች የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ አንዱ ልዩነት ግን ኳታሮቹ ንጉሣውያን  የተማሩ ወይም በሙስሊም ወንድማማቾች አስተምህሮ የተቀረፁ በመሆናቸው፣ ስለወደፊቱ የአገራቸው መፃኢ ዕድልና ስለዓለም ያላቸው ዘመናዊ ዕይታ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ እንደምታውቀው የሙስሊም ወንድማማቾች አስተምህሮ መነሻው ከግብፅ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ የነበሩ የግብፅ ምሁራን በኳታር ይሠሩ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የኳታር ንጉሣውያን ቤተሰቦችን የማስተማር ዕድል ነበራቸው፡፡ እንደ አልቱራቢ ያሉት የሱዳን ሙስሊም ወንድማማቾችም በዚህ ወቅት ነበር ወደ ኳታር ያቀኑት፡፡ የአሁኑ የኳታር አሚር አባት የሙስሊም ወንድማማቾች ያስተማሯቸው ሲሆኑ፣ እ.ኤ.አ. በ1990 ሽማግሌውን አሚር ከዙፋናቸው አውርደው ነበር፡፡ እኚህ አሚር ኳታርን ወደ ሌላ የተለየ አቅጣጫ እንድታቀና ማድረግ ጀመሩ፡፡ ለአገራቸው የነበራቸው ራዕይ ሳዑዲዎቹ ለራሳቸው ካላቸው ዕይታ የተለየ ነበር፡፡ ይህ ልዩነት የተንፀባረቀውም የራሳቸውን ገለልተኛ የውጭ ፖሊሲ በቀረፁ ጊዜ ነበር፡፡

ለውጡ ሥር እንዲሰድ ምክንያት የሆነው ደግሞ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ካላቸው አገሮች አንዷ ኳታር መሆኗ ከተረጋገጠበት ወቅት ጋር በመገጣጠሙ ነበር፡፡ ይህ በመሆኑም ከገልፍ አገሮች የትብብር ምክር ቤት የተለየ የፖሊሲ ምልከታ እንዲኖራቸውና የተለዩ ተቋማትን እንዲመሠርቱ ረድቷቸዋል፡፡ የዘመናዊነታቸው አንደኛው አካል የሆነው እንደ ቢቢሲ ካሉ ዓለም አቀፍ ሞዴል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር የሚመሳሰለውን አልጄዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈታቸው ቢሆንም፣ ይህ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግን የራሱን የአቀራረብ ሥልት የሚከተል ሆኖ ብቅ ያለ ነው፡፡ የዓረብ ወጣቶች አማራጭ የመረጃ ምንጭ በማፈላለግ ላይ በነበሩበት ምቹ ወቅት ነበር አልጄዚራን የመሠረቱት፡፡ ስለዚህም ጣቢያው ዘመናዊና ምዕራባዊ ይዘት የሌለው የዜና ምንጭና በአቀራረብ ረገድ ክፍተቱን በፍጥነት ለመሙላት የቻለ ጣቢያ በመሆን ብቅ አለ፡፡ ምርጥ ዶክመንተሪዎችን በማዘጋጀት በኩል ብልጫውን ወስዶ ተገኘ፡፡ የኳታር አሚሮችን መንካት ባይፈቀድለትም፣ ከዚያ ባሻገር ባለው ክልል እንዳሻው የመዘገብ ነፃነትና ገደብ የለሽ ወሰን ተሰጥቶታል፡፡ ተዓማኒነት ማግኘት በጀመረ ማግሥት ግን የአረብ የፀደይ አብዮት ፈነዳ፡፡ ይህም ጣቢያውን ወደ ላይኛው ማማ እንዲወጣ ረድቶታል ማለት ይቻላል፡፡ የዓረብ አብዮትን ሲዘግቡ የነበረው ልክ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ በሚመስል አኳኋን ነበር፡፡ በርካታ ሀብት የፈሰሰበት ዝግጅት በማድረጋቸው ኩነቱን በቀጥታ ሥርጭት ለማስተላለፍ ጭምር ችለዋል፡፡ የዓረቡ ዓለም ወጣቶች የየአገራቸው መንግሥታት የሚያስተጋቡትን ፕሮፓጋንዳ በመተው፣ ከቀን ወደ ቀን አልጄዚራን መከታተል በመጀመራቸው የአመራር ክፍሎቹን ማስከፋቱ አልቀረም፡፡ በመሆኑም በጣቢያው ላይ ተባብረው በመነሳት ለህልውናችን አደገኛ ነው እስከ ማለት ደረሱ፡፡ ለረጅም ጊዜ የገዙ መሪዎች ከወደቁ በኋላም ቢሆን በጣቢያው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ይበልጥ እየተካረረ ሄዷል፡፡ ሳዑዲዎች አል አራቢያ የተሰኘ ጣቢያ በመክፈት አልጄዚራን ለመቀናቀን ቢሞክሩም፣ ነገሩን ከማባባስ በቀር የፈየዱት ነገር አልነበረም፡፡ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ለመሳሰለው መብት ሁሉ መከታ ነን የሚሉት አሜሪካውያንም ቢሆኑ፣ አልጄዚራ አሜሪካ በዓረቡ ዓለም ጦርነት እያቀጣጠለች ስለመሆኗ መዘገብ ሲጀምር ትችታቸውን ይሰነዝሩበት ገቡ፡፡ ስለዚህም የዓረብኛ ማሠራጫ ጣቢያው በተለይ የሙስሊም ወንድማማቾች ወይም የእስልምና ፖለቲካ ቡድን እየተባለ የሚጠራው አካል መሣሪያ ተደርጎ ይታይ ጀመር፡፡

ሪፖርተር፡- የእስልምና ወንድማማቾች ወይም የእስልምና ፖለቲካ ቡድን አስተምህሮ ለገልፍ አገሮች የትብብር ምክር ቤት፣ እንዲሁም ለሳዑዲ ሥጋት ሆኖ የሚታየው በምን ምክንያት ነው?

አቶ አብዱል፡- ቀድሞ ነገር ስለሽብርና አሸባሪነት ሳዑዲና የገልፍ አገሮች ምክር ቤት ያስቀመጡትን አስቸጋሪ ትርጓሜ መረዳት ይኖርብሃል፡፡ ከግብፅ በመነሳት በመካከለኛው ምሥራቅ የተስፋፋውን የሙስሊም ወንድማማቾች ወይም የእስልምና ፖለቲካ ቡድን፣ ሳዑዲዎቹ ለየትኛውም ዓላማቸው ሲሉ ከአልቃይዳ ብሎም ከአይኤስ እኩል የሚታይ አሸባሪ ቡድን አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ስለዚህ ሳዑዲና የገልፍ አገሮች ምክር ቤት ኳታርን አሸባሪዎችን በገንዘብ ትደግፋለች ብለው ሲወነጅሉ፣ የሙስሊም ወንድማማቾችን ማለታቸው እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ሳዑዲዎች ይብሱን የሙስሊም ወንድማማቾች ኅብረትን ከእነ አልቃይዳ፣ ከእነ አይኤስ እንዲሁም ከሒዝቦላ እኩል በሽብርተኝነት እንድትፈርጀው አሜሪካን ሲወተውቱ ነበር፡፡ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወቅት ግን ይህ ውትወታቸው ተቀባይነት ያገኘ ይመስላል፡፡ ከሒዝቦላ ጋር በተገናኘ የሚነሳው ነገር አስገራሚነት አለው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሺዓ እስልምና አካል በሆነችው ኢራን የሚደገፈውና ራሱም የሺዓ ቁርኝት ያለው የሊባኖስ መንግሥት ከሒዝቦላ ጋር ትስስር ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ቡድን ከእስራኤል ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ አሜሪካ በአሸባሪነት ብትፈርጀውም፣ ኢራን ግን ሕጋዊና ገለልተኛ ንቅናቄ እንደሆነ ትናገራለች፡፡

በመሆኑም የአሸባሪነት ጉዳይ ከተነሳ ምንም እንኳ ለቃሉ የተሰጠ ጥቅል ትርጓሜ ቢኖርም፣ እያንዳንዱ አገር ማንን አሸባሪ በማለት እንደሚፈርጅና ማንን እንደሚተው የየራሱ ድምዳሜ አለው፡፡ ይህ ክስተት ሁልጊዜም ጥገኛ የሚሆነው አገሮች በቡድኑ አማካይነት በሚፈጠርባቸው ሥጋት ላይ ነው፡፡ የገልፍ ምክር ቤት አባላትን ስታይ አብዛኞቹ ከአይኤስ ጋር ከመዋጋት ይልቅ፣ ብዙውን ጊዜ የሚያጠፉት የሙስሊም ወንድማማቾችን በመዋጋት ላይ  ነው፡፡ ለአብነት ያህል ካየህ ከአይኤስ ጋር ያለውን ፍልሚያ ለአሜሪካኖች የተውላቸው ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ዮርዳኖስ፣ ቱኒዚያና ሞሮኮ በመሳሰሉት አገሮች ውስጥ ግን የሙስሊም ወንድማማቾች ኅብረት የፖለቲካቸው አንድ አካል ሆኖ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በቱኒዚያ ዋናዎቹ የፖለቲካ ኃይሎች ቢሆኑም በግብፅ ግን በአሸባሪነት ተፈርጀዋል፡፡ በፍልስጤም ያለውን የሐማስ ንቅናቄ ካየህ በአብዛኛው በሙስሊም ወንድማማቾች ኅብረት አስተምህሮ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ እስራኤል፣ ግብፅና ሳዑዲ ዓረቢያ ግን አሸባሪ እያሉ ይጠሩታል፡፡ ኳታሮች ደግሞ የተቃውሞ ንቅናቄ ቡድን እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ሪፖርተር፡- በሳዑዲና በኳታር መካከል ላለው አለመግባባት መነሻው ይህ ከሆነ፣ በቅርቡ ስለተከሰተው ሳዑዲና የገልፍ ምክር ቤት አባላት በኳታር ላይ ስለወሰዱት የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ጫና ቢያራሩልን?

አቶ አብዱል፡- ይህ ክስተት በቀጣናው ውስጥ ውስጡን እየተብላላ የቆየው ውጥረት ውጤት ነው፡፡ ኳታሮች ሳራቸውን እንደ ገለልተኛ አገር፣ እንዲሁም ገለልተኛ የውጭ ፖሊሲ ግቦች እንደሚከተል አገር ነው የሚቆጥሩት፡፡ በበርካታ የዲፕሎማሲ ሽምግልና ሥራዎች ውስጥ በመሳተፍ በሊባኖስ፣ በፍልስጤም፣ በሱዳን፣ በአፍጋኒስታንና በሌሎች በርካታ አገሮች ውስጥ ሚናቸውን ተጫውተዋል፡፡ ታሊባን በኳታር ጽሕፈት ቤት በመክፈቱ በታሊባንና በአሜሪካ መካከል ውጤታማ የፖለቲካ ግንኙነት እንዲፈጠር በማገዝ በተለይ እስረኞችን ለማስለቀቅ ጠቅሟል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ኳታሮች በየመን ጉዳይ ላይ ምክክር እንዲደረግ ለማድረግ ቢጥሩም ሳዑዲ ውድቅ አድርጋዋለች፡፡ በመሆኑም ኳታሮች ማንም ሊያነጋግራቸው ከማይፈልጋቸው ቡድኖች ጋር ፖለቲካዊ ውይይቶችና ድርድሮች እንዲደረጉ የማመቻቸት ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡ ይህንን ሲያደርጉ ታሳቢ ያደረጉት ካላቸው የፋይናንስ አቅም፣ እንዲሁም ካላቸው የዲፕሎማሲ ኃይል አኳያ ከተነጠሉ ቡድኖድ ጋር ግንኙነት የመሠረቱ ናቸው ብሎ የሚከሳቸው አካል እንደማይኖር ነበር፡፡ ከኢራንም ጋር ይህንኑ ነበር ያደረጉት፡፡ ምንም እንኳ ኳታሮች ከኢራን ጋር የማይግባቡበት ጉዳይ ቢኖራቸውም፣ የተመጠነ ግንኙነት መፍጠሩ ተገቢ እንደሆነ ግን ተገንዝበው ነበር፡፡ ከዚህ ባሻገር ኢራንና ኳታር የሚጋሯቸው የነዳጅ ማውጫዎች ስላሉ፣ ኳታሮቹ ይህንንም ማበላሸት አልፈለጉም፡፡ ኢራኖቹ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶችና ከኦማን ጋር የሥራ ግንኙነት አላቸው፡፡ እንዲውም በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደርና በኢራን መካከል ለተደረሰው የኑክሌር ማዕቀፍ ስምምነት፣ ኦማኖች በድብቅ ድርድሮቹን በማመቻቸት እንደተሳተፉ ይነገራል፡፡ በኢራን ጉዳይ ኩዌቶችም ከኢራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው፡፡ ሆኖም በቀጣናው ኢራንን እንደ ጭራቅ የምትቆጥራትና የዲያቢሎስ አምሳያ በማድረግ የምትፈርጃት ብቸኛዋ አገር ሳዑዲ አረቢያ ነች፡፡ በመሆኑም ሳዑዲዎች ኳታርን ሲወነጅሉና የገልፍ አገሮች ምክር አባላትም ተመሳሳይ አቋም እንዲያራምዱ ሲያነሳሱ መነሻ ያደረጓቸው ሰበቦች ከኢራን ጋር ግንኙነት አላት፣ የሙስሊም ወንድማማቾችን ትደግፋለች፣ እንዲሁም የእስላማዊ ፖለቲካ ቡድንን የሚያበረታታ የዜና ማሠራጫ ጣቢያ በመክፈቷ አሸባሪዎችን ትረዳለች በማለት ወንጅለዋታል፡፡

ሪፖርተር፡- በኳታር ላይ ለተጣለው ዕገዳ ድንገተኛ ምክንያት የሆነው ምንድን ነበር?

አቶ አብዱል፡- እንደሚመስለኝ በአሜሪካኖች የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ነው ለሳዑዲዎቹ የልብ ልብ የሰጣቸው፡፡ ምንም እንኳ ፕሬዚዳንት ኦባማ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ተመሳሳዩን ለማድረግ ቢፈልጉም፣ የአሜሪካ መንግሥት ግን የገልፍ አገሮች ልካቸውን እንዲያውቁ ሲያስጠነቅቃቸው ቆይቷል፡፡ የ80 ሚሊዮን ሕዝብ አገር የሆነችው ኢራን በቀጣናው የወደፊት ህልውና ውስጥ ወሳኝ አካል እንደሆነች መቀበል፣ አሜሪካኖች ለገልፍ ምክር ቤት አባላት ካቀረቧቸው መካከል የሚጠቀሰው ነው፡፡ የኦባማ አስተዳደር በግልባጩ ኢራን በቀጣናው ገንቢ ሚናዋን እንድትጫወት ጫና ለመፍጠር ዝግጁ ነበር፡፡ ይህ አቋም ይበልጥ የተንፀባረቀው ደግሞ በአሜሪካና በኢራን መካከል የኑክሌር ስምምነት ሲፈረም ነበር፡፡ በኦማን አማካይነት በድብቅ የተሸመገለውና በይፋ የተፈረመው ስምምነት ግን እስራኤልና ሳዑዲን በጣም አስቆጥቷቸው ነበር፡፡ በመርህ ደረጃ ሲታይ የማይታሰብ ቢመስልም፣ ስምምነቱ ሁለቱ አገሮች የጋራ ትብብር እንዲፈጥሩና በኢራን ላይ እንዲነሱ ግን ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እጅግ ተለዋዋጭ አቋም ያላቸው፣ አንዳንዴ ያለምንም አጥጋቢ ምክንያት ፕሬዚዳንት ኦባማ የሠሩትን እያንዳንዱን ነገር ሁሉ ለመናድ የተነሱ የሚመስሉ ፕሬዚዳንት መከሰታቸው ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ከሳዑዲዎች ዕይታ አኳያ ነገሩን የምታይላቸውና የምትቀበላቸው አሜሪካ ለማግኘት ችለዋል፡፡ ቀጥሎ ምን እንደሚከሰት ያሳየው የዚህ ጉዳይ መገለጫ ደግሞ በቅርቡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሳዑዲ ሥርወ መንግሥትን መጎብኘታቸው ነው፡፡ ሳዑዲዎቹ የሱኒ እስልምናን የሚከተሉ የቀጣናውን አገሮች አሠልፈዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሳዑዲዎች ያቀነባበሩት ድራማ የሚመስል ሲሆን፣ ሱኒ ወይም ሺዓ የሚባል ክፍፍል የሌለ አስመስሎታል፡፡ የዚህ ዓይነቱ መርዘኛ የሃይማኖት ፍረጃ ወደ አፍሪካ አገሮችም እየተዛመተ ነው፡፡ አዎ ጥቂት የሱኒ እስልምናን የሚከተሉ የአፍሪካ አገሮች አሉ፡፡ አብዛኞቹ የሱፊ እስልምና ተከታዮች ናቸው፡፡ አንዳቸውም ግን ዋሃቢዎች አይደሉም፡፡ ሳዑዲዎች ግን ዋሃቢ ናቸው፡፡ የዋሃቢ አተረጓጎም በአብዛኛው ለሰለፊ ንቅናቄዎች መፈልፈያ በመሆኑ፣ ከዚህ የመነጩ በርካታ ጽንፈኛ ቡድኖች ሊፈጠሩ ችለዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያው በተለመደው ማንነታቸው ሳዑዲ ያቀረበቻቸውን ነጥቦች በመቀበላቸው፣ እንደ ኳታር ባሉ አገሮች ላይ ለመነሳት ጊዜ አልፈጀባትም፡፡

ሪፖርተር፡- ትራምፕ የሳዑዲ አረቢያ እንቅስቃሴዎችን እንደተቀበሉ ካሳወቁባቸው ነገሮች መካከል በንግግራቸው ኳታርን በይፋ አሸባሪዎችን ትረዳለች ብለው መወንጀላቸው ነው፡፡ ይሁንና አሜሪካ በኳታር የጦር ሠፈር በመመሥረት በኢራቅና በአፍጋኒስታን የምታካሂደውን ጦርነት የምትመራው ከኳታር ነው፡፡ እንዲህ ያለው አሻሚ ነገር እንዴት ሊገለጽ ይችላል?

አቶ አብዱል፡- ይህ ሁኔታ የሚሳይህ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በአሁኑ ወቅት የማይሠራ እንደሆነ ነው፡፡ የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት የሆነው ፔንታጎንና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኳታር ጉዳይ ላይ የተለየ አመለካከት ቢኖራቸውም፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግን ኳታር አሸባሪዎችን ትደግፋለች የሚል አቋም ያራምዳሉ፡፡ እሳቸው ስለወሰኑ ብቻ ነው ይህ የሆነው፡፡ አሜሪካኖች ለሳዑዲዎች በቢሊዮኖች የሚቆጠር የጦር መሣሪያ ሽያጭ እንደሚያከናውኑ ባስታወቁበት ወቅት፣ ፔንታጎን ለኳታር 12 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው የጦር መሣሪዎችን ሲሸጥ ግን ታይቷል፡፡ በቀጣናው ካላቸው ወታደራዊ የአየር ቤዝ ትልቁ የሚገኘው በኳታር  ነው፡፡ ስለዚህ አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ የምትከተለው ፖሊሲ ችግር ያለበት ነው፡፡ ለሳዑዲዎቹና ለሌሎቹም የተሰጣቸው ዕድል ወደፊት በቀጣናው የአሜሪካ የረጅም ጊዜ ፍላጎት ላይ ችግር የሚያስከትል አዝማሚያ እንደሚያመጣ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ አካሂዳቸውን ካልቀየሩ በቀር አሜሪካኖች በቀጣናው ለተከሰተው ችግር አንድ አካል ሆነዋል፡፡ ሌላው በሳዑዲ በኩል የተፈጠረው በተሳሳተ አስተሳሰብ ኢራንን ዳር ማውጣታቸው ነው፡፡ አየህ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ያላትን ኢራንን ገሸሽ ማድረግ መላ ቀጣናውን ግጭት ውስጥ ሊያስገባ ወደሚችል አዝማሚያ እንዲገፋፋ ሊያደርግ የሚችል ሥጋት ይፈጥራል፡፡ ራሳቸውን ብቻም ሳይሆን ቀጣናውንም አብረው ሊያጠፉ ወደሚችሉበት አዝማሚያ ማንደርደርም ሊሆን ይችላል፡፡ በገልፍ አገሮች ትብብር ውስጥ የሚኖረው አብዛኛው የሺዓ ሙስሊም ሕዝብ ምንም እንኳ ቁጥሩ አነስተኛም ቢሆን፣ በአብዛኛው በነዳጅ በበለፀጉ አገሮች ውስጥ የሚኖር ነው፡፡ ስለዚህ ነገሮችን ሳታጤን እንዲሁ በነሲብ በሃይማኖት ከፋፍለህ ለመጓዝ የምታስብ ከሆነ ምንም አታተርፍም፡፡ አሜሪካ ለሳዑዲ የምትሰጠው ከለላም ከሁሉም ግጭቶች አያስጥላትም፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ አካባቢው ጉዳይ ስንመጣ ከአዲሱ ክስተት ቀድሞ ኳታር በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ውስጥ ፍላጎት እንዳላትና በአንዳንድ አገሮች ውስጥም እንቅስቃሴ እንደ ጀመረች እንገነዘባለን፡፡ ከየመን ዘመቻ ጋር በተያያዘም ሳዑዲና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ፍላጎት አላቸው፡፡ በመሆኑም በአፍሪካ ቀንድና ከዚያም ባሻገር ባለው ቀጣና ውስጥ የኳታር ፍላጎት ላይ ወደፊት ምን ሊከሰት ይችላል?

አቶ አብዱል፡- እንደምታውቀው ኳታር ትንሽ አገር ስትሆን ሙሉ በሙሉ በገልፍ አገሮች የተከበበች ነች፡፡ ፈጠነም ዘገየም ሁሉ ቦታ መገኘት እንደማይችሉ መገንዘባቸው አይቀርም፡፡ የቱ ጋ እንደሚቀራቸው ይገነዘባሉ፡፡  እንደ ሊቢያ፣ ሶማሊያና ሌሎች አገሮች ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡ ሊያቆያቸው የሚችል በቂ ሀብት ስላላቸው የሚደርስባቸው ነገር አይኖርም፡፡ ፈጠነም ዘገየም አሜሪካኖች ለሳዑዲ ያላቸው ከልክ ያለፈ ፖሊሲም መቀየሩ አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በሳዑዲዎቹ የማግለል ዕርምጃ ምክንያት በኳታር ያላቸው የጦር ሠፈር እንዲዘጋ በገልፍ ምክር ቤት የቀረበው ጥያቄ ታክሎበት ቱርኮች ደስተኞች አይደሉም፡፡ እርግጥ ቱርኮች ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋል፡፡ የገልፍ ምክር ቤት የኳታርና የኢራን ግንኙነትም እንዲቋረጥ ጠይቋል፡፡ እርግጥ ነው ኳታሮች ይህንን ጥያቄ ተግባራዊ አያደርጉትም፡፡ ሌላው ትልቁ ጥያቄ ኳታር ለአሸባሪዎች የምትሰጠውን ድጋፍ ታቁም የሚለው ሲሆን፣ በሳዑዲዎች ትርጓሜ መሠረት የሙስሊም ወንድማማቾችን አለመደገፍ ማለት ነው፡፡ ኳታሮች ከአሜሪካ በሚመጣባቸው ተጨማሪ ግፊት የተነሳ ለሙስሊም ወንድማማቾች የሚሰጡትን ድጋፍ ለመቀነስ የሚገደዱ ይመስለኛል፡፡ አልጄዚራን እንድትዘጋ ለቀረበው ጥያቄ ኳታር የምዕራቡን ዓለም ድጋፍ የምታገኝ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ከሚዲያ አኳያ የሕዝቡን ሐሳብ መጋፋት ስለማይቻሉ ነው፡፡ ይሁንና ውጥረቱ ወደፊትም ሊቀጥል ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- በአፍሪካ ቀንድ ስላላቸው ፍላጎትስ ምን ሊባል ይችላል?

አቶ አብዱል፡- ሳዑዲዎቹ በአፍሪካ ቀንድ እያደረጉ ያሉት ነገር ቢኖር ለአቋማቸው ድጋፍ ማሰባሰብ ነው፡፡ ይህ ማለት ፖሊሲያቸውን የሚደግፍላቸው ሲያገኙ በምላሹ ድጋፍ መስጠት ማለት ነው፡፡ እንደ ኤርትራ ያሉ አገሮች እስካሁን ከሳዑዲ ጎን ለመሠለፍ ተነስተዋል፡፡ ጂቡቲዎች እያቅማሙ ነው፡፡ ለየትኛው ጎራ አቋማቸውን እንደሚያሳዩ እስካሁንም ግልጽ አልሆነም፡፡ ከዚህ ባሻገር ሶማሊያ በሚደንቅ ግፊት ውስጥ ሆናም ቢሆን አሁንም እየተከላከለች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያንም አነጋግረዋታል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ አለመግባባቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደምትፈልግና የኩዌትን የአደራዳሪነት ሚና እንደምትደግፍ አስታውቃለች፡፡ የኢትዮጵያ አቋም ትክክለኛ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ሳዑዲዎቹ በድጋሚ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ማቅረባቸው እንደማይቀር ይሰማኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በየመን የሚካሂደው ጦርነት በቀጠለበት ወቅት የቀጣናው የሚሊታሪ እንቅስቃሴም እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ወደፊት ምን ዓይነት ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል እርግጠኛ መሆን አንችልም፡፡ ምናልባትም በቀጣናው የምንገኘውን ሁላችንንም ሊያካትተን ይችላል፡፡ እንደምታውቀው አካባቢው የዓለምን 40 በመቶ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስተናግደው ስትራቴጂካዊው የባብ ኤል መንደብ መተላለፊያ የሚገኝበት ሥፍራ ነው፡፡ በመሆኑም አካባቢው የምዕራብ ኃይሎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚታይበት፣ የቻይናና የሌሎችም አገሮች ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይሎች የሚገኙበት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ሥፍራ ዓለም አቀፍ የማሪታይም መስመር ከመሆኑም ባሻገር፣ እንደ ቻይና ያሉ የእስያ አገሮችም ዋነኛ የኃይል ፍጆታቸው የሚተላለፍበት መስመር በመሆኑ ዓለምአቀፍ አካባቢው ይዘት ተላብሷል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያለ 100 ሚሊዮን ሕዝቦች የሚኖሩበት፣ የባህር በር ለማግኘት በሌሎች አገሮች በኩል ለማለፍ የሚገደድ፣ የተለየ ፈተና የሚገጥመው አገርም በዚሁ ቀጣና ውስጥ አለ፡፡ ይህ አገር በኢኮኖሚ እያደገ ነው፡፡ ይህ ዕድገት ሳይገታ ለመጓዝ እንዲቻል ንግድ ያስፈልጋል፡፡ ንግዱን ለማቀላጠፍ የሚረዳ መሠረተ ልማት ለመገንባት ትልቅ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል፡፡ በዚያም ላይ በአፍሪካ ከትልልቆቹ አንዱ የሆነ የመርከብ ድርጅት ያለው አገር  ነው፡፡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ መጠነ ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴዎችን እያስተናገደ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ኢንቨስትመንት በጂቡቲ በኩል በሚገኘው የባህር በር ላይ ጥገኛ በመሆን የሚካሂድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያና ጂቡቲ በተግባርም ሊታይ በሚችል ምክንያታዊነት፣ በአንድ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኙ አገሮች ሆነዋል፡፡ በፖለቲካ ሊተሳሰሩ ባይችሉም በኢኮኖሚ ረገድ ግን ከፍተኛ ትስስር ፈጥረዋል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ሒደት የኢትዮጵያና የጂቡቲ ተሞክሮን በጥሩ ምሳሌነት ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ካላት የጥቅም ፍላጎት አኳያም ከሌሎች አገሮች የበለጠ የቀጣናውን ሰላም መሆን አጥብቃ ትሻለች፡፡ ስለዚህም ኢትዮጵያን ይህንን መረጋጋት እንዴት ልታረጋግጥ ትችላለች? ከተባለ እንደሚመስለኝ የኢትዮጵያ ስትራቴጂ አውጪዎች ሁሉንም ነገር በመመልከት አማራጫቸውን ማየት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ አስገዳጅ የሆኑ የትብብር ስምምነቶችን መሠረት ያደረገና በባህር በር የመጠቀም መብቷን የሚያረጋግጥ አካሄድ ማለት ነው፡፡ ይህ ስምምነት በምንም ሁኔታ የማይነካ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከተቻለን እንዲህ ያለውን ተመሳሳይ ስምምነት ከሌሎች ጎረቤት አገሮችም ጋር ማድረግ ይገባናል፡፡ እስካሁን የታየው የሥጋት ስብስብ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ዝግጁ ሆና መጠበቅ አለባት፡፡ ኢትዮጵያ የማትቋቋመው ቀጣና ውስጥ የምትገኝ ብትሆንም፣ ስትራቴጂካዊ ሥልት ሊኖራት ይገባል፡፡ ሌላው ሊታይ የሚችለው ጉዳይ አስፈላጊ ከሆነ ኢትዮጵያ የባህር ኃይሏን መልሳ መመሥረት እንዳለባት ማጤን ነው፡፡ የኢትዮጵያ የባህር ባህር ኃይል የፈራረሰ አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም እንዲህ ላለ እንቅስቃሴ እንዲቀመጥ የተደረገ ይመስለኛል፡፡ ይህ የፀጥታ ሥጋት እንደ ቻይና ያሉ ሌሎች አገሮችም የሚጋሩት በመሆኑ፣ ዕቃዎችንና አገልግለቶችን ያለ ፀጥታ ሥጋት በቀይ ባህር በኩል የማስተላለፍ ዋስትና የማግኘት ጥረቷ የዓለም አቀፍ ማዕቀፍ አካል እንዲሆን ግፊት ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡

ሪፖርተር፡- በሳዑዲና በኳታር መካከል የተከሰተው አለመግባባት የገልፍ አገሮች ምክር ቤትንም የሚያዳክም እንደ መሆኑ ለኢትዮጵያ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ?

አቶ አብዱል፡- አይደለም፡፡ በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ትክክለኛ ሊሆን የሚችለው አካሄድ በገልፍ አገሮች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ማበረታታት፣ እንዲሁም ሰላማዊ የማሪታይም ንግድ መተላለፊያ እንዲኖር መጣር ነው፡፡ ኢትዮጵያ የባለብዙ ወገን መፍትሔ የማፈላለግ፣ ሁሉንም ያሳተፈና ግልጽነት የተላበሰ የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲመጣ መደገፍ አለባት፡፡ ሰላም የሰፈነበት ቀይ ባህር እንዲኖር ማድረግና ያሉት ግጭቶችም ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው መተላለፊያ እንዳያሳጧት ማድረግ ይኖርባታል፡፡ እንደማስበው ኢትዮጵያ ይህንን ሐሳብ በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ)፣ በአፍሪካ ኅብረት፣ በዓረብ ሊግ፣ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኩል በማስተጋባት ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ ይኖርባታል፡፡ የመሪነት ሚናዋን መጫወት ይኖርባታል፡፡ ይህንን የምለው በቀጣናው ከሚገኙ አገሮች ይልቅ ኢትዮጵያ ባለብዙ ወገን የግጭት አፈታት ሥልትን የመከተል ባህል ስላዳበረች ነው፡፡ ይህ አካሄድ የዲፕሎማሲ ባህላችን አካል ነው፡፡ በጋራ ደኅንነት እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ከመሠረቱ ሁለቱ የአፍሪካ አገሮች አንዷ ነች፡፡ የአፍሪካ ኅብረትም መሥራች ነች፡፡ በኢጋድ ውስጥ ኢትዮጵያ ንቁ አባልና የመሪነት ሚና የምትጫወት በመሆኗ፣ ይህ ብቃቷ ከሌላውም ጊዜ የበለጠ እንዲዳብር ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡

The post ‹‹ኢትዮጵያ የባህር ኃይሏን መልሳ ለመመሥረት ማጤን አለባት››አቶ አብዱል መሐመድ፣ የኢንተርአፍሪካ ግሩፕ መሥራች appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ቮላድሚር ፑቲን እና ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው ቀን ግንኙነታቸው ስምምነት ፈጸሙ

$
0
0

በወንድወሰን ተክሉ

በአሜሪካው ፕሬዚዳንት እና በሩሲያ አቻቸው ቮላድሚር ፑቲን መከካል በተካሄደ የመጀመሪያ የገጽ-ለገጽ ግንኙነት ሁለቱ መሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማተቸው ተገለጸ።

በሀምቡርግ የጀርመን ከተማ ይፈጅብናል ብለው ከመደቡት የ40ደቂቃ ቆይታ ወደ 2ሰዓት በላይ በፈጀው የሁለቱ ሀገር መሪዎች ውይይት ውጤታማና ተስፋ ሰጪ ነው የተባለ ሲሆን በሶሪያ ጉዳይ ላይ የተኩስ አቁም ስምምነትና ብሎም በኢንተርነት ደህንነትም በጋራ ለመሰራት መስማማታቸው ከሀምቡርግ ተዘግባል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዲሞክራቶች በሩሲያ ጣልቃ ገብነት የፕሬዚዳንታዊውን ምርጫ እንዳሸነፉ በመግለጽ መንግስት በጉዳዩ ላይ በገለልተኛ ወገን የማጣራት እርምጃ እንዲወስድ በማድረግ ምርመራ እያካሄዱ እንዳለ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ደግሞ አሜሪካና ሩሲያ በሶሪያ፣በሰሜን ኮሪያና በዩክሬይን ጉዳይ ላይ የሚያወዛግብ እንጂ የሚያቀራርብ የጋራ መንገድ አጥተው የተቸገሩ ሀገሮች እንደሆኑም ይታወቃል።

ሆኖም በትናትናው በሁለቱ መሪዎች መካከል በተካሄደው የመጀመሪያው ውይይታቸው አመርቂ ስምምነቶች በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በማድረጋቸው ብዙዎቹን አስገርማል።

“ከፑቲን ጋር ያደረኩት ውይይት እጅግ የተዋጣለትና ውጤታማ ውይይት ነው” ያሉት ዶናልድ ትራምፕ “በሶሪያ ላይ ከሀምሌ 9ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርመናል” ሲሉም የውጤታማ ውይይታቸውን ፍሬ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት በበኩላቸው “በቲቪ የምናውቀው ዶናልድ ትራምፕ እና በአካል ገጽታ ያየነው ዶናልድ ትራምፕ ሰፊ ልዩነት አለ” ካሉ በሃላ ያዩትንም ልዩነት ሲያስረዱ “በጣም ተግባቢና እርሰበርስ መናበብ የቻልን ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይህ ግንኙነታችን እና ሁኔታችን ሳይለወጥ በዚሁ መልክ ከቀጠለ በሩሲያና አሜሪካን መካከል የፈረሰውን ግንኙነት መልሰን እንገባለን ብዪ አምናለሁ” ሲሉ ፕሬዚዳንት ፑቲን ተናግረዋል።

የጀርመና ቻንስለር አንጄላ መርከር የሁለቱን መሪዎች ግንኙነት በበጎ እይታ ከተመለከቱት መሪዎች ውስጥ አንዳ ሲሆኑ እንደሳቸው አባባል በአሜሪካና ሩሲያ መልካም ግንኙነት አውሮፓን ጨምሮ ብዙዎች ሀገራት ተጠቃሚ ይሆናሉ ባይ ናቸው።

ሆኖም የመሪዎቹን ውጤታማ ውይይት በጥርጣሬ የሚያዩ አልጠፉም። በተለይም በተፈራረሙት የሶሪያ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ጥርጣሬያቸውን አጉልተው ያሰሙ ዲፕሎማቶች ቁጥር በርካታ ሆኖ ተገኝታል።

አሜሪካና ሩሲያ ከዚህ ቀደም በሶሪያ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ስምምነቶችን እየተፈራረሙ ማክበር እያቃታቸው ያፈረሳቸውን እንደ አብነት በመጥቀስ ይህ የአሁኑም ስምምነትም ስለመተግበሩ ዋስትና የለውም ሲሉ ይደመጣሉ።

The post ቮላድሚር ፑቲን እና ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው ቀን ግንኙነታቸው ስምምነት ፈጸሙ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ጥቂት ዕውነቶች ስለጣና ሐይቅ፤ – ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0
  1. ከ10% እስከ 15% ወይም ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የዐማራ ሕዝብ ኑሮው የተመሠረተው በጣና ሐይቅ ላይ ነው፡፡ የባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በምዕራብ ጎጃም፣ በደቡብና በሰሜን ጎንደር ዞኖች የሚገኙ 54 ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ኢኮኖሚያዊ መሠረታቸው ከጣና ሐይቅ በሚገኝ የአሣ ምርትና መስኖ ነው፡፡
  2. የኢትዮጵያን 50% የንጹህ ውኃ ክምችት የያዘ ጣና ነው፡፡
  3. ከ40 በላይ ወንዞችና ጅረቶች ወደ ጣና ሐይቅ ይፈሳሉ፤ የዓለማችን በርዝመቱ ትልቁ ወንዝ ዓባይ ከጣና ሐይቅ ይነሳል፡፡ ወደ ሐይቁ ከሚገቡ ወንዞችና ጅረቶች መካከል ግልገል ዓባይ፣ ርብ፣ ጉማራ፣ እንፍራንዝና መገጭ ይገኙበታል፡፡
  4. በጣና ሐይቅ ውስጥ ከ31 በላይ ደሴቶች አሉ፡፡ ትልቁ ደሴት የደቅ ደሴት ሲሆን 16 ካሬ ኪሎ ሜትር አለው፤ 4,816 ሰዎች በደሴቱ ላይ ይኖራሉ፡፡ ደሴቶቹ በጥንታዊ ገዳማትና ታሪክ የታጨቁ ናቸው፡፡ ረዥም እድሜ ያለው ገዳም የጣና ቂርቆስ ሲሆን በብሉይ ዘመን የኦሪት መስዋት ሲሰዋባቸው ከነበሩት ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ እንደ አንቀጸ ብርሃን፣ ዚቅና የዜማ ድርሰቶች የደረሰው በዚሁ ደሴት ገድሞ ነው፡፡ 
  5. የጣና ሐይቅ በትንሹ 19 ዓይነት ገበሎ አስተኔዎች፣ 35 ዓይነት ተሳቢዎች፣ 28 ዓይነት አጥቢዎችንና 437 ዓይነት የተለያዩ አእዋፋትን የያዘ ነው፡፡ 
  6. የጣና ሐይቅ ምድቡ በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኝ ሲሆን ከባሕር ወለል በላይ 1800 ሜትር ከፍ ያለ ነው፡፡ 
  7. ሐይቁ 90 ኪሎ ሜትር የዲያሜትር ርዝመትና የ385 ኪሎ ሜትር የጠርዝ ርዝመት አለው፡፡ የሐይቁ ጥልቀት ከ4 እስከ 14 ሜትር ጥልቀት ሲኖረው አማካይ ጥልቀቱ 8 ሜትር አካባቢ ነው፡፡ ቀደም ሲል 9.8 ሜትር አማካይ ጥልቀት እንደነበረው ይገመታል፡፡ 
  8. የሐይቁ ስፋት 3672 ካሬ ኪሎ ሜትር የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ 3000 ብቻ ቀርቷል፡፡ 672 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሆነው ውኃ ደርቋል ወይም ወደ የብስነት ተቀይሯል፡፡ 
  9. የጣና ሐይቅን አደጋ ላይ የጣሉ አራት ምክንያቶች እስካሁን በውል ተለይተው ታውቀዋል፡፡ እንደጥፋት መጠናቸው ቅደም ተከተል የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ፣ የእንቦጭ አረም፣ የከተሞች ፍሳሽና በደለል መሞላት ናቸው፡፡ የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የሐይቁ ጥልቀት ከ50 ሣ.ሜ በላይ ጥልቀት ቀንሷል፡፡ ከጎንደርና ከባሕር ዳር ከተማዎች የሚወጣ ወደ ሐይቁ የሚለቀቅ ቆሻሻ ሐይቁን እየበከሉት ነው፡፡ 
  10. ከእምቦጭ አረም ውጭ ሌሎች ሁለት የተለያዩ መጥፎ አረሞች ጣናን እንደወረሩት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንቦጭ በጣና ላይ የተከሠተው በፈረንጆች አቆጣጠር በ2011 ሲሆን እንቦጭ ቆቃን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ሐይቆች ውስጥ እንደነበረ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ 
  11. በ2014 እና 15 በጣና ሐይቅ ላይ በእንቦጭ ተሸፍኖ የነበረው የጣና ክፍል 20 ሺህ ሔክታር ቢሆንም በ2017 ወደ 24 ሺህ ሔክታር ከፍ ብሏል፡፡ 
  12. እምቦጭ 50 በመቶ የሚሆነውን የሐይቁን ጠርዝ ወሮታል፡፡ እምቦጭ ወደ ጣና የገባው በመገጭ ወንዝ ጫፍ አካባቢ እንደሆነ ሲገመት በፎገራ በኩል ከሩዝ ምርት ጋር ሌሎች ሁለት መጥፎ አረሞች እንደገቡ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ሁለቱ ሌሎች መጤ አረሞች Azolla እና water lettuce በመባል ይታወቃሉ፡፡

The post ጥቂት ዕውነቶች ስለጣና ሐይቅ፤ – ሙሉቀን ተስፋው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አስደናቂው ከመቐለ የህዝብ ተወካዮች ጥያቄ

$
0
0

የመቐለህዝብ  ተወካዮቹ ለጠ/ሚኒስትሩ ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን የትግራይ ህዝብ በጦርነትና ድርቅ የተጎዳ ስለሆነ ትልልቅ የመስኖ ግድቦች ያስፈልገሉ ፣የውሃ ጥያቄም አሁንም ጥያቄችን ነው ያሉት ተወካዮቹ ፡፡

በተጨማሪም የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይና ትግራይ ልዩ ተጠቃሚ ተደርጋ የምትታየው የፌደራል መንግስት ምን እየሰራ ነው የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ሃ/ማርያም ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን ግድብ እንደሀገር የሚገነባና በትንሽ ክፍያ ውሃ እያከፋፈለ በክፍያው ደግሞ ሌላ ግድብ የሚሰራ ሀገራዊ ድርጅት መቋቋሙ የገለፁ ሲሆን በተከዘ ዙሪያ 8 ግድቦች መጠናታቸው ተናግረዋል፡፡

ከ3 አመት በፊት የንጹህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ ይዤ ሂጄ ነበር ያሉት ጠ/ሚኒሰትሩ አሁን አስተማማኝ ምላሽ ሰለተገኘ ከ4 ቀናት በፊት ጥናት የሚያጠኑ መቐለ እንደገቡ ገልፀው ወደ ተግባር መግባት ብቻ ቀርቷል ብለዋል፡፡

የትግራይ የበላይነትን አለ የሚሉት ያሸነፍናቸው ሃይሎች ናቸው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ ሰለ አልጠፎ አሁንም ትግል ይጠይቃል ያሉ ሲሆን ይሰራበታልም ብለዋል፡፡

የኤርትራ ጉዳይ በተመለከተ ጦርነት ምርጫችን አይደለም ያሉት ጠ/ሚኒስትር ሃ/ማርያም ከዓሊተና እስከ ሑመራ ያለው ህዝብ እንዳይጎዳ የተያዘ እቅድ መኖሩ ጠቅሰው ምክክሩ ሲጠናቀቅ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በሰፓርት እየታየ ያለው ትምክህትና ጠባብነት ጠቃሚ መስለው የራሳቸው አጀንዳ እየቆሰቆሱ ያሉትን ህዝቡ አደብ ሊያስገዛቸው ይገባል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ በዋናነት ከላይ ያለ ችግር ሰለሆነ ሊሰተካከል ይገባዋል ብለዋል ፡፡

ይህ ችግር ከስረ መስረቱ ለማስተካከል ለሰላም ፣ ፍቅር ፣ አንድነት እና ወዳጁነት የሚሰብኩና የሚሰሩ ተማሪዎች በመገንባት ረገድ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ሚና እንዳለቸው ጠ/ሚኒሰተር ሃ/ማርያም ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡

The post አስደናቂው ከመቐለ የህዝብ ተወካዮች ጥያቄ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አርከበ እና አደይ አልጋነሽ – ናትናኤል አስመላሽ

$
0
0

አቶ አርከበ በዛሬው ምርቃት እንዲህ አለ “በዚህ ኣጋጣሚ በቂ ካሳ ሳይጠይቁ ለተነሱ ኣርሶ ኣደሮች ማመስገን እፈልጋለው” የትግራይ አርሶ አደሮች መሬታችን አንሰጥም ስላሉ ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው እንደታሰሩ አቶ አርከበ አውቀው እንዳላወቁ ሰምተው እንዳልሰሙ አልፈዉታል። አፓርታይድ መንደርን ስትመሰርቱ ስንቱን ገበሬ አስለቅሳቹ ከቦታው እንዲፈናቀል አድርጋቹታል።

አደይ አልጋነሽ መሬቴን በነጻ አልሰጥም ስላሉ ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው ለሁለት አመታት ያክል ታስረዋል፣ ከአደይ አልጋነሽ ጋር የታሰሩ ስድት የእግሪ ሓሪባ አርሶ አደሮችም አሉ፣ ታድያ አቶ አርከበ የትኛው የትግራይ አርሶ አደር ነው በቂ ካሳ ሳይሰጠይው መሬቱን የፈቀደላቹ? ከአርሶ አደሩ የተነጠቀ መሬት እኮ በሁለት መቶ እጥፍ ለጨረታ አቅርባቹ ሸጣቹ; ለአርሶ አደሩ መሰረታዊ የውሃ እና የመብራት ችግሮቹን መፍታት አልቻላቹም። እናንተ ከገበሬው መሬት ነጥቃቹ ፋብሪካው ለማስመረቅ ዊስኪ እና ጮማ ስትበሉ፣ የአደይ አጋነሽ ልጆች ደግሞ በርሃብ አለንጋ ይገረፋሉ።https://www.gofundme.com/hk3df-medical…

ኢፈርት ባቋቋማቸው ፋብሪካዎች ውስጥ ለስራ የሚቀጠር በሙሉ የባለስልጣን ዘመድ እንጂ መሬቱን የተነጠቀ ድሃው አርሶ አደር አይደለም። አሁንም በተገነባው ፋብሪካ ውስጥ ስራ የሚሰጣቸው ምንም ካሳ ሳይጠይቃቹ የተፈናቀለ አርሶ አደር ሳይሆን የናንተው ዘመዶች እና ተላላኪዎች ናቸው። መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎች ሳትመልሱ በባዶ መሬት ላይ ለስልጣናቹ ብላቹ ፋብሪካ ብትገነቡ ዋጋው የለውም። ነገ ፋብሪካው በኤሌትሪክ እና ውሃ እጥረት ቢቆም ተጠያቂው ማን ነው? ትንናት ከናንተ ጋር እኩል ቂጣ ተካፍሎ ሲበላ የነበረው የትግራይ ገበሬ አሁን ስልጣን ስትይዙ መቀለጃ አደረጋቹት፣ የትግራይ ህዝብ ዝምታ ሞልቶ ሲፈስ ግን ዋጋውን አትችሉትም።

The post አርከበ እና አደይ አልጋነሽ – ናትናኤል አስመላሽ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live