Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

“የኔታ መስፍን ምን አጠፉ?” (በመስከረም አበራ)

$
0
0
ፕ/ሮ መስፍን ወ/ልደማርያም

ፕ/ሮ መስፍን ወ/ልደማርያም

ሃገራችን ኢትዮጵያ መማር ብቻውን “ንወር ክበር!” የሚያስብልባት ምድር ነች፡፡ ተምሮ ለወገኑ ምን ሰራ? ለሃገሩ ምን አበረከተ? የሚሉት ወሳኝ ነገሮች ከክብሩ በፊት ጥያቄ ውስጥ የሚገቡ ነገሮች አይደሉም፡፡ ብዙሃኑ ምሁራን በበኩላቸው ትምህርታቸው ደሃ አደግነታቸውን የሚበቀሉበት ብርቱ በትር፣ የቅንጦት ህይወት የይለፍ የሚወስዱበት ሰልፍ ብቻ ይመስላቸዋልና ዲግሪ በደራረቡ ቁጥር ከትናንት በተሻለ ራሳቸውን ለማገልገል፣ ከሰው በልጦ ለመታየት ይታጠቃሉ፡፡ ትምህርታቸው ያልሰራውን ቁስ ከየፈረንጁ ሃገር ይሰበስባሉ፡፡ ቁሱን ይበልጥ ለማጋበስ ከግፈኛ መንግስት ጋር ማህበር ይጠጣሉ፡፡ ከደም አፍሳሽ ጋር ግንባር ይገጥማሉ፤ ከእናት ሃገር ሆድ ወጥተው የሷኑ ደካማ ጎን ይመታሉ፡፡

ከትናንት በስቲያ እግረኛ ወታደር የነበረ ኩሽሹን በከረባት ቀይሮ ባላዋቂ እጁ ሲያቦካው የኖረው ፖለቲካ እንደ ቂጣ ምጣዱ ላይ እንክትክት ሲልበት ‘ኑና ስራየ ልክ እንደ ነበረ ዱክትርናችሁን እየጠቀሳችሁ ከሙያ አንፃር አስረዱ ሲላቸው’ ሊያስረዱ ይሽቀዳደማሉ፡፡ በኢቢሲ አንድ ሁለት ቀን ካናዘዛቸው በኋላ አያያዛቸውን አይቶ፣ ፍልስፍናቸው እንደ ቅማል “እራስ ደህና” ማለት እንደሆነ አጥንቶ ለሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ያጫቸዋል፡፡ “የዶክተሮች ካቢኔ አቋቋምኩ” ብሎ ከመጠላቱ በላይ እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም ለነሱ ክብር መስሎ ይታያቸዋልና ሹመቱ ሃሴታቸው፣ የሹመቱ ቱርፋት እርካታቸው ይሆናል፡፡

የመማር ዋና አላማው በስብ መጥገብ ከሆነ ዳርቻው ይህ ቢሆን አይስገርምም፡፡ በስብ ለመጥገብ ግን መማር ግድ አልነበረም፡፡ እንደውም ለቁስ ሰቀቀን ፍቱን መድሃኒቱ፣ የቀጥታ መንገዱ ተደራራቢ ዲግሪ የግድ የማይለው የመነገድ ማትረፉ ጎዳና ነው፡፡ መማር ግን ቁስ ከማንጋጋት፣ ሆድ ከመቀብተት ያለፈ ተልዕኮ ያለው ነገር ነው፡፡ መማር መንጋው ያላየውን ቀድሞ አይቶ ማሳየትን፣ ባልደላው ማህበረሰብ ውስጥ እውነተኛ ድሎት እንደማይኖር የመገንዘብ ራስ ወዳድነትን የመሰናበት ልዕልና፤ ለእውነት እና ለሃቅ ብቻ የመወገን እና ይሄው የሚያመጣውን ቱርፋትም ሆነ ችግር የመቀበል ልቅና ነው፡፡ ይህ ልቅና በተለይ በድሃ ሃገር እንደልብ የሚገኝ አዘቦታዊ ገጠመኝ ሳይሆን እንደ ማዕድን በመከራ ተፈልጎ የሚገኝ ብርቅ ነገር ነው፡፡

ፕ/ሮ መስፍን ወ/ልደማርያም በግብር መማራቸውን ከሚመስሉ፣ ሁሉን ከሚመረምሩ፣ ሳይደክሙ ከሚጠይቁ፤ የቁስ ምኞት የራስ ድሎት እምብዛም ከማያስጨንቃቸው ብርቆች ወገን ናቸው፡፡ ሰውየው ከጉብዝና እስከ ሽምግልናቸው ወራት ሲፅፉ ሲሞግቱ የኖሩ የሃገር አድባር ናቸው፡፡ እውቀት ልምዳቸውን በወረቀት አስፍረው፣ በቃል ተናግረው አይጠግቡም፡፡ የተናገሩ የፃፉት ለብዙ የፖለቲካችን ህማማት መልስ አለው፡፡ ሆኖም የሚታያቸውን ለማየት፣ የሚሰማቸውን ለመረዳት አቅሙም ልምዱም የሚያጥረን ሰዎች ልንወርፋቸው እንጣደፋለን፤ የምናስበውን እንዲናገሩልን እንሻለንና ብዙ ጊዜ ባልሆኑት እንከሳቸዋለን፡፡ በበኩሌ ሰው ፍፁም ነው ብየ አላምንም፤ ይህን መጠበቅም ደግ አይመስለኝም፡፡ ሰው ናቸውና ፕ/ሮ መስፍንም ሊስቱ፣ ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡ ወይም በእኛ ግንዛቤ ያጠፉ ሊመስለን ይችላል- ሁላችንም የግንዛቤያችን ነፀብራቅ ነንና! ይሄ ጤናማ ነው፡፡

ዋናው ጉዳይ ግን ጥፋትን እና ልማትን የመመዘን እርጋታ፣ ቅሬታችንን የምንገልፅበት ሁኔታ፣በተለይ የተቃውሟችን ሁለመና ሌት ተቀን ከምናወራለትን ኢትዮጵያዊ ማንነት አንዱ የሆነውን ታላቅን የማክበር ጨዋነት ጋር አብሮ ይሄዳል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ይሄን ያስባለኝ በተደጋጋሚ ከፕ/ሮ መስፍን ጋር በማይጥም ሁኔታ የሚሟገተው የርዕዮት ሚዲያ ባልደረባ አቶ ታምራት ነገራ ከሰሞኑ ፕ/ር መስፍን የተናገሩትን አንስቶ ከሰውየው ጋር ያለውን ልዩነት የገለፀበት ድንፋታ ነው፡፡ ራሴም በአንድ ወቅት ከፕ/ሮ መስፍን ሃሳብ ጋር ባለመስማማት ተሟግቼ ነበርና ታምራት ነገራ ለምን የፕ/ሮ መስፍንን ሃሳብ ሞገተ የሚል አቋም የለኝም፡፡ ጥያቄየ እሳቸውን ሲሞግት እንደዚህ ጣራ አድርሶ በሚያፈርጥ ንዴት የሚበግነው ለምንድን ነው የሚል ነው፡፡በእውነት እና በእውቀት፣በደንብ በገባው ነገር ላይ ለሚሞግት ሰው ጥርስ በሚያፋጭ ብግነት ውስጥ መሆን ምን ይረዳዋል? በንዴት ፈረስ ላይ ሆኖ አያት የሚሆንን ትልቅ ሰው መዘርጠጥስ አስተዳደግን ከማስገመት፤ የራስን ኪሎ ከማቅለል ያለፈ ምን ረብ አለው? ንዴት እውቀት፣ስድብ ሙግት ሆኖ አያውቅም! ማወቅ ያረጋጋል እንጅ አያንተገትግም፤ስድብ እና ዝርጠጣ ያዋቂነት ምልክት አይደለም፡፡ ስድብ የመከነ አእምሮ ውላጅ እንጅ እንደ ታምራት ነገራ ሃሳብ አለኝ ብሎ ሚዲያ ላይ ከተሰየመ ሰው የሚጠበቅ “አበጀህ” የሚያስብል ነገር አይደለም፡፡ በተለይ ፕ/ሮ መስፍንን ከመሰለ ባለ ከባድ ሚዛን ምሁር ጋር ሲሟገቱ ሰውየው የተናገሩትን በደንብ መረዳት፣መረጋጋት፣ የሚናገሩትን ማወቅ፣ራስን መግዛት ተሻይ ነው፡፡ ካልሆነ ንግግር የሚያስገምተው ራስን ነው! ስለተደጋጋመ ዝም ብየ ማለፍ ስለከበደኝ የታምራትን ጉዳይ አነሳሁ እንጅ የፅሁፌ አላማ ስላልሆነ በዚህ ትቼ ፕ/ሮ መስፍን ሰሞኑን በሲያትል ተገኝተው በተናገሩት ጠቃሚ ንግግር ዙሪያ ወዳለኝ ሃሳብ ልለፍ፡፡

ስለ ጎሳ አጥራችን ገበና፤ የልዩነት አንድነት እንዴትነት

ፕ/ሮ መስፍን ያደረጉት ንግግር የሚጀምረው በሃገራችን ወቅታዊ ፖለቲካ ዋነኛ መዘውር የሆነው አግላይ የጎሳ ፖለቲካ የሃገራችንን የማህበረ-ፖለቲካዊ ታሪክ የማይወክል ልብ ወለድ ነው በማለት ነው፡፡ይህው ስሁት እሳቤ ስህተቱን የሚያባብሰው በጎሳ መሃል አንድነት እንጅ ልዩነት የለም ብሎ ሲደመድም፤የዚህ ተቃራኒ የአንድነት አቀንቃኖች ደግሞ በሚዘምሩለት አንድነት ውስጥ ልዩነትነትን የሚያስተናግዱበት ቦታ የሌለ ወይ የጠበበ መሆኑ ነው በሚል ግራ ቀኙን የሚገስፅ እና ልብ ላለው በዚህ መሃል ያለውን አዋጭ መንገድ የሚያሳይ ነው -የፕ/ሮ መስፍን ተግሳፅ አዘል ንግግር፡፡ የጎሳ ፖለቲካ ማቆሚያ የሌለው የሽንሸና እና የማነስ ጉዞ እንደሆነም ጠቆም አድርገዋል፡፡መስማት የምንችል ብልሆች ከሆንን ይህ የፕ/ሮ መስፍን ንግግር ለፖለቲካችን ፍቱን ፈውስ የሚሆን መድሃኒት ያለው ነገር ነው፡፡

ነገሩን ከነባራዊው የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር ለማመሳከር ያህል ቆየት ካለው የኦሮሞ ጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞች እሳቤ አንፃር ብናየው ሰፊው የኦሮሚያ ክልል ያቀፋቸውን ኦሮምኛ ተናጋሪ ሰፊ ህዝቦችን እንደመንታ ልጆች ተመሳሳይ መልክ፣እሳቤ፣ፍላጎት ያቸው አድርጎ “ኦሮሙማ” የሚል የጅምላ ማንነት ሊያላብስ ይለፋል፤ከኦሮሞ በቀር ለኦሮሞ የሚያስብ እንደሌለ እርግጠኛ ሆኖ ‘ኦሮሞዎች ብቻ ተሰብሰቡና ምከሩ’ ሲል በር አዘግቶ ሲያስዶልት አይተናል፡፡ በዚህ እሳቤ መሰረት ኦሮሞዎች እንደነዶ ለብቻቸው ታስረው የተቀመጡ ህዝቦች ስለሆኑ እነሱ ለብቻቸው የሚወስኑት ውሳኔ በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ተፅዕኖ የለውም፤ወይም ሌላው ኢትዮጵያዊ የነሱን የብቻ ውሳኔ አሜን የማለት እዳ አለበት፡፡ኦሮሞ በተባለው ሰው ውስጥ በሚናገረው ቋንቋ ምክንያት ካገኘው አንዱ ማንነቱ (ኦሮሞነት) በቀር ሌላ ማንነት ስለሌለው ፍላጎቶቹ፣ጥያቄዎቹ፣ምኞቶቹ ሁሉ የሚመነጩት ከሚናገረው ቋንቋ ብቻ ስለሆነ መነጋገር ያለበት ከቋንቋ መሰሎቹ ጋር ብቻ ነው-እንደ እሳቤው፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡

የሚናገሩት ቋንቋ (ጎሳቸው) በፍፁም የማይገናኝ ሁለት በገጠር የሚኖሩ አማራ እና ኦሮሞ አርሶ አደሮችን በአንድ በኩል ሁለት ከተሜ አማራ እና ኦሮሞዎችን በሌላ በኩል አስቀምጠን ምኞት ፍላጎታቸውን ችግር ጥያቄቸውን ብንጠይቅ ከሚናገሩት ቋንቋ ይልቅ በተሰማሩበት የኑሮ ፈርጅ የተነሳ ተመሳሳይ እምነት፣ ፍላጎት፣ ጥያቄ፣ ዝንባሌ እንደሚኖራቸው አያጠራጥርም፡፡ ይሄን በጾታ፣ በእድሜ፣ በትምህርት ደረጃ ወዘተ እየተካን ብናሰላው ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ በተጨማሪም አካባቢ እየሰፋ በሄደ ቁጥር ሰዎች ተመሳሳይ ቋንቋ እየተናገሩም ቢሆን እምነት፣ ዝንባሌ፣ ጥያቄ፣ ፍላጎታቸው በአጠቃላይ ባህላቸው ከመመሳሰል ይልቅ እየተለያየ መሄዱ ሳይንሳዊ ነው፡፡ ፕ/ሮ መስፍን ‘በጎሳ ውስጥ ልዩነት የሌለ አይምሰላችሁ’ የሚሉት እንዲህ ያለውን ጉራማይሌነት ነው፡፡ ሌላ ማሳያ ለማከል ያህል አንድ አይነት ቋንቋ መናገር አንድ ወጥ ማንነት የሚያመጣ ቢሆን ኖሮ ኦሮሞው አቶ አባዱላ የተሰለፉበት የፖለቲካ እምነት ኦሮሞውን አቶ በቀለ ገርባን እስርቤት የሚያመላልስ አይሆንም ነበር፡፡

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ከምክንያታዊነት እና ነባራዊነት ጋር ጥብቅ ጠብ የተጣላው የጎሳ ፖለቲካችን ለምክንያት የዝሆን ጆሮ ሰጥቶ ይነጉዳል፡፡ በየጎሳ ፖለቲካ “ቄሰ-ገበዙ” አቶ ጃዋር መሃመድ በአንድ ወቅት አቶ አባዱላ ገመዳ ዛሬ ኦ.ኤም.ኤን ካባረረው ጋዜጠኛ አብዲ ፊጤ እና ሌሎች ጋር የነበራቸውን እራት ግብዣ አስመልክቶ ‘እንዴት የኦሮሞ ወጣቶችን ከሚያስረው ሰው ጋር ማዕድ ትቀርባላችሁ?’ በሚል ትችት ሲቀርብበት ‘ኦሮሞ ሁሉ ወገናችን ነው አበሾች በልዩነታችን ማትረፍ ስለምትወዱ እኛ ስንሰባሰብ አትወዱም’ ሲል መልስ በሰጠ አንድ አመት ሳይሞላው ነው ኦህዴድ በሚመራው የኦሮሚያ ክልል የዚያ ሁሉ የኦሮሞ ደም የፈሰሰው፡፡ ጃዋር ባለው መሰረት ኦሮሞ ሁሉ የኦሮሞ ወገን፤ ኦሮሞ ያልሆነ ሁሉ ለኦሮሞ የማይተኛ ከሆነ ለምን ኦህዴድ በሚመራው ክልል፤ወገኔ ብሎ እራት ያቋደሳቸው አቶ አባዱላ ዋና በሆኑበት ስርዓት ያሁሉ ኦሮሞ ሞተ፣ ጃዋርስ እንዴት የሞት ነጋሪት ጎሳሚ ተደርጎ በስሙ ፋይል ተከፈተ? ‘ይህን መዛባት አጢኑና ወደ መስመር ግቡ’ ነው የፕ/ሮ መስፍን ምክርና ተግሳፅ፡፡

የአማራ ብሄርተኝነት ለማስፈን የሚለፉ የአማራ የጎሳ ፖለቲከኞች እንደ ኦሮሞ ጓዶቻቸው አንድ አማራዊ ማንነት አለን እንጅ ጎጃሜ፣ጎንደሬ፣ወሎየ፣መንዜ አትበሉ ይላሉ፡፡እኔን ጨምሮ አብዛኛው ኢትጵያዊ ደግሞ ይበልጥ የሚያውቀው ጎጃሜ፣ጎንደሬ፣ተጉለቴ የሚለውን እንጅ አማራ የሚለውን ማንነት አይደለምና ይህም ትልቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሆኖ ያነታርካል፡፡እንዲህ ብሎ ለያይቶ መጥራት የአማራን ህዝብ ማንነት የማጥፋት ሂትለራዊ ተንኮል ተደርጎ ይወገዛል፡፡ የአማራ ህዝብ ራሱ ግን ይህ ውድቅ የሚያደርግ በልጅነቴ እየሰማሁት ያደግኩት አንድ አባባል አለው -“የጎንደሬን አማርኛ እንኳን መንዜ ጎጃሜም አይሰማው” ይላል፡፡አባባሉ የሚያስረዳው በአሁኑ የሃገራችን የጎሳ ፖለቲካ ፈሊጥ የፍፁም መመሳሰል ዳርቻ እየተደረገ ባለው በአንድ አይነት ቋንቋ በመግባባት ውስጥ እንኳን ልዩነት መኖሩን ነው፡፡ እንደሚባለው አማራነት፣ከአማራ ምድር መወለድ እንደ ፋብሪካ ምርት አንድ የሚያደርግ፣ ሁሉን ፍጡር አንድ አይነት ነገር የሚያሳስብ ከሆነ በትቂቱ ቤተ-አማራ ከሞረሽ ወገኔ ተለይቶ አናየውም ነበር፡፡ እውነታው እና የሚያስኬደው መንገድ ፕ/ሮ እንዳሉት ሰው ባለበት ሁሉ ልዩነትም አንድነትም መኖሩን ተቀብሎ የማያልቀውን የጎሳ አጥር እያጠበቡ ሲያጥሩ ከመኖር እልፍ ማለቱ ነው፡፡

የጎሳ ፖለቲካ አጥር ማለቂያ የለውም የሚለው አባባል አሁንም ሰከን ብሎ ለሰማ፣ሰምቶም ለመማር ለተዘጋጀ ጥሩ ጥቁምታ ነው፡፡ ይህን ነገር ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በአንድ ወቅት “በዘር ፖለቲካ ሄደህ ሄደህ የምትገባው ቤትህ ነው” ካለው ግሩም እይታ ጋር መሳ ነው፡፡ ነገሩን ወደ ነባራዊው የሃገራችን የጎሳ ፖለቲካ ሃቅ ስንመልሰው እኔ የምኖርበት የደቡብ ክልል በርካታ ብሄረሰቦችን ያቀፈ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ለስራ ጉዳይ ከክልሉ ብሄር የአንዱ ተወላጅ ከሆነ ሰው ጋር እሱ ተወልዶ ባደገበት የገጠር ቀበሌ የኔ መስሪያቤት የሚሰራው ስራ ኖሮ ከእኛ ጋር ይጓዝ ነበር፡፡እናም የሄድንበትን ስራ ጨርሰን የእርሱን የትውልድ መንደር ለቀን ግን በዛው ዞን ውስጥ ከትውልድ መንደሩ አንድ አስር ኪሎሜትር ርቀን እንደተጓዝን አንዲት ትንሽ ከተማ እንደደረስን ሰውየው “እኔኮ እዚች ከተማ ልጄን ማስቀጠር አልችልም” ብሎ ዝምታችንን የሚሰብር ንግግር አመጣ፡፡ “ለምን አንድ ዞን አይደል እንዴ?” አልኩኝ በጣም ስለገረመኝ ተሸቀዳድሜ፡፡ “አንድ ዞን ቢሆን፣ ቋንቋው አንድ ቢሆን ጎሳችን ግን የተለያየ ነው፤ እነሱ ጎሳቸው ያልሆነን ሰው አበጥረው ያውቃሉና የኔ ልጅ ይወዳደር ይሆናል እንጅ መቀጠር የማይታሰብ ነው” ሲል የደረስንበትን አዘቅት ቁልጭ አድርጎ አሳየኝ፡፡ ቀጥየ ጥያቄ አላነሳሁም፤ዝም ዝም ሆነ! የሚያፅናናው ነገር ግን ፕ/ሮ እንዳሉት የጎሳ ፖለቲካ ቀሳውስት ለስልጣን እና ለጥቅም ዘር እያቋጠሩ ሃረግ ሊያማዝዙት ቢሞክሩም የኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ ግን እየተጋባ እየተዋለደ ኢትዮጵያዊነቱን በሰውነቱላይ፤ዜግነቱን በኢትዮጵያዊነቱ ላይ እያፀና “ሃዘንህ ሃዘኔ፤ደምህ ደሜ” እየተባባለ በሩቅ እየተነጋገረ ይኖራል፡፡ ይህ ሁሉ ዘመን አመጣሽ እትብት የመማዘዝ ፖለቲካ የመጣውም በትቂቶች ነውና ፅናት አይኖረውም፤እነዚህ ትቂቶች የመሰረቱት ክፉ አግላይ ስርዓት በስብሶ ሲወድቅ ሁሉም ይስተካከላል፡፡

ቂም፣ ልግም፣ የክፋት አዙሪት – ቆሞ መቅረት!

ፕ/ሮ መስፍን እንደህዝብ ያለብንን ችግር በደንብ ተረድተው፣ የተረዱትን እውነት በሚገባን፣ መሬት በወረደ ቋንቋ ተርጉመው ጉድፋችንን በማስረጃ አበልፅገው በማንክደው ሁኔታ በማሳየት ተወዳዳሪ የሌላቸው ምሁር ይመስሉኛል፡፡ “የኔታ” የሚለው የኢ-መደባዊ ማዕረጋቸው ትርጉምም ይሄው ይመስለኛል፡፡ የኔታ የሚለው ማዕረግ ፊደል ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን የመገሰፅ የመኮርኮም ሞራላዊ ስልጣንንም ይይዛል፡፡ ፕ/ሮ መስፍን በማህበረ-ፖለቲካዊ ችግሮቻችን እና በመፍትሄዎቻቸው ዙሪያ በአማርኛም በእንግሊዝኛም በደንብ ፅፈዋል፡፡ፅፌያለሁ ብለው መናገራቸውንም አይተውም፡፡ የፃፉ የተናገሩትን ወጣቱ ትውልድ እንዲያነብ፤በትኩረት እንዲያደምጥ ይፈልጋሉ፡፡ አብዛኛው የዘመናችን ጋዜጠኛ፣ፖለቲከኛና ተንታኝ ደግሞ ማንበብ ላይ ወገቤን ባይ ስለሆነ የተናገሩ የፃፉት የሚመልሰውን ጥያቄ ይዞ ወደ እሳቸው ሲመጣ ይቆጣሉ፤ይገስፃሉ፡፡ “ቁጣው የፃፍኩትን ሁሉ አሜን ብላችኑ እመኑ” ከማለት አይመስለኝም፡፡ አንብቦ “እርስዎ በመፅሃፍዎ እንዲህ ብለዋል ግን እኔ እንዲህ ይመስለኛል” ለሚላቸው ቦታ የሌላቸው ሰው አይደሉም፡፡ ሳያነቡ፣በውል ሳያዳምጡ ከበሬ ፊት ሊበሉ ለሚመጡ ጥጆች ግን ትዕግስት የላቸውም፡፡ ቁጣቸው ይነዳል፡፡ በበኩሌ ቁጣው አያስቀይመኝም፤ይልቅስ ከመናገር ከመፃፋችሁ በፊት አንብቡ የማለት የታላቅ ምክር አድርጌ እወስደዋለሁ፡፡

ፕ/ሮ ረዥም የህወት ልምዳቸው እና ምጡቅ ታዛቢነታቸው እንዳቀበላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ግፈኛን የሚያሸንፍባቸውን ዘዴዎች አሳይተውናል፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ግፍ ሲበዛበት ያቄማል፣አቂሞ ይለግማል፣ ለግሞም አይቀርም ጊዜ ጠብቆ ቂሙን ክፉን በክፉ በመመለስ ተንፈስ ያደርጋል፡፡ ክፉን በክፉ ሲመልስ የሚጠላውን፣የተቃወመውን ክፋት ራሱ መልሶ ያደርገዋል፡፡ ይህ አካሄድ ውጊያው ከክፋተኛው ግለሰብ እንጅ ከክፉ አስተሳሰቡ ስላልሆነ ክፋተኛ ነቅሎ ሌላ ክፋተኛ ይነተክላል፡፡ ስለዚህ የሃገራችን ፖለቲካ ከክፋት አዙሪት ሊወጣ አልቻለም ይላሉ፡፡ መፍትሄውን ሲያስቀምጡ መዋጋት ያለብን ክፋትን ራሱን አስተሳሰቡን መሆን አለበት፡፡ ይህ መንገድ በደንብ ገብቶን ከጀመርነው ክፋትን ለማጥፋት ሌላ ክፋትን እንደመሳሪያ አድርገን መጠቀም እናቆማለን ይላሉ፡፡ ክፉ አስተሳሰብን ለመዋጋት ደግሞ ከራስ ጋር ብቻ የማውራት አድፋጭነትን አስወግደን መነጋገርና መግባባት መጀመር አለብን፡፡ እስከዛሬ ሳንነጋገር ስንግባባ የኖርነው ክፋትን በክፋት በመመለሱ ማድፈጥ ውስጥ ባለ ክፉ ቋንቋ ነው፡፡ አሁን ግን እርስበርስ ተነጋግረን ከሃሳባችን ፍጭት ክፉን በክፉ ከመቃወም የተለየ፣የተሻለ፣የዘመነ መንገድ ማውጣት አለብን ባይ ናቸው-የኔታ መስፍን!

 

ሌላ ሳንካ…..!

ጨቋኝ መንግስታትን ለመንቀል ስንታገል የግፍ አስተዳደርን እሳቤ፣ክፋትን ራሱን በፅንሰሃሳብ ደረጃ ተቃውመን፤ክፉን ካስወገድን በኋላ በጎ የመትከሉ ነገር ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ አልተቻለንም፡፡ ለምን ቢባል ክፉን ለመንቀል የሚያስችለን የቂም፣የልግመኝነት እና ክፉን በክፉ የመመለስ ሃይል በሙላት ስላለን ክፉን መንቀል ችለናል፡፡ እነዚህ ክፉን ለማስወገድ ሃይል የሆኑን ነገርግን ቂም፣ልግመኝነት፣ማድፈጥና፣ክፉን በክፉ መመለስ በጎ ስርዓትን ለመትከል የሚያስችል ልዕልና የሌላቸው፤ለዘመነ ፖለቲካ ስፍነት፣የተሻለ አኗኗር እውንነት የማይመጥኑ ኋላ ቀር እና ተራ ልምዶች ስለሆኑ ፖለቲካችንን ቆሞ-ቀር አድርገውታል፡፡ እስከዚህ ድረስ ከፕ/ሮ መስፍን ጋር እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን ለፖለቲካችን ቆሞ መቅረት ሃላፊነቱን መውሰድ ያለበት አካል በየፈርጁ መታየት ያለበት ይመስለኛል፡፡

እንደሚታወቀው አብዛኞቹ በኢትዮጵያ የተካሄዱ ጨቋኝ አስተዳደርን የማስወገድ እንቅስቃሴዎች ወጣኔያቸውን እና ፍፃሜያቸውን የሚያገኙት ከፖለቲካ ልሂቃን ሆኖ ህዝቡ የሚፈለገው መሃል ላይ ለለውጡ ጉልበት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን የመጣበትን ሁኔታ ብናይ ፕ/ሮ መስፍን እንዳሉት በማራቶን ሩጫ ሃገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፈት የህዝቡን እርዳታ ማግኘት ምትክ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ ነበር፡፡ወደ አፈሙዝ ላንቃ የሚማገድ እግረኛ ወታደር ወልዶ መስጠቱ፣ ለወታደሩ እህል ውሃ ማቅረቡ፣ቁስለኛ ማስታመሙ፣ የጠላትን ሁኔታ ሰልሎ መረጃ ማቀበሉ፣ ጠላት ገፍቶ ሲመጣ መደበቅ መሸሸጉ ሁሉ ኢህአዴግ በመጨረሻዎቹ አመታት ወደ አዲስ አበባ ለመገስገስ ያስቻሉት ቀደም ብሎ ያገኛቸው የህዝብ ድጋፎች ነበሩ፡፡ ‘ህዝቡ ይህን ድጋፍ ለምን ሊያደርግ ቻለ?’ ለሚለው ጥያቄ አንዱ መልስ ፕሮፌሰር መስፍን ያነሱት በግፈኛ ላይ የማቄም፣የመለገም፣ክፉን የመበቀል ዝንሌ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ህዝቡ ይህን ሲያደርግ ‘በወታደር ጫማ እየረገተህ ያለውን ክፉ ጥለን ዲሞክራሲን እናመጣልሃለን’ ያሉትን ሸማቂዎች አምኖ የተሻለ ያደርጉልኛል ብሎ ተማምኖ ይመስለኛልና ክፉን ነቅሎ ደግ ባለመትከል እጅግም መወቀስ ያለበት አይመስለኝም፡፡ ክፉ ነቅሎ በጎ ባለመትከል መወቀስ ያለበት ዲሞክራሲ ላመጣልህ እታገልኩ ነው ብሎ የህዝብን አጥንት እየጋጠ፣በህዝብ ጫንቃ ላይ እየተረማመደ ለስልጣን የበቃው የትናንት ነፃ አውጭ ነኝ ባይ ሸማቂ የዛሬ ተረኛ ግፈኛ አስተዳደር ይመስለኛል፡፡

ይህ አካል በቃል አባይነት፣በመሰሪነት እና በአታላይነት መወቀስ፤ለፖለቲካችን ቆሞመቅረት የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ አለበት፡፡ህዝባችን በየዋህ ልቦናው አምኗቸው የመሶብ የቡኾእቃውን ገልብጦ እንዲያበላቸው፣ ልጆቹን ለሞት መርቆ እንዲሰጥ ያደረገው የሸማቂዎቹ አስመሳይነት ነበር፡፡ ሸማቂዎቹ የልባቸውን እሲኪያደርሱ፤እንጦጦ አፋፍ እስኪደርሱ ዲሞክራትነታቸውን ለየዋሁ ህዝብ የሚያስረዱት “ቅጫማም” እየተባሉ ሲሰደቡ ዝም በማለት፣ “የተሰማችሁን ተናገሩ መብታችሁ ነው” በሚል ሽንገላ፣ሌባ የተባለን ሁሉ ያለፍርድ በየመንገዱ በጥይት በመቁላት ወዘተ እንደ ነበር ያየ የሰማ የሚናገረው ነው፡፡ያለፍርድ ሌባ የተባለን ሁሉ አስፋልት ላይ ሲያጋድሙ የነበሩት የፍትህ አለቃ ነን ባዮች በወንበራቸው ሲደላደሉ መንግስታቸው የሌባ መርመስመሻ እንደሆነ ራሳቸው ‘የመንግስት ሌባ ከቦናል’ ሲሉ በፓርላማ መስክረዋል፡፡ተራ ስድብ ሲሰደቡ ዝም ሲሉ እንደ ባህታዊ ይቃጣቸው የነበሩ ሸማቂዎች ዛሬ ጋዜጠኞች ስራቸውን ስለሰሩ ብቻ የሚያስሩ ፈርኦኖች ወጥቷቸዋል፡፡ ‘ደርግ የሰማኒያ አመት ሽማግሌ አሰረ ብለን ደደቢት ነጎድን’ ያሉ የነፃነት ነብያት ነን ባዮች ዛሬ የሰማኒያ አመት ሽማግሌ አስረው ቦክስ የሚያቀምሱ “ጎበዞች” ፤እናትን በልጇ አስከሬን ላይ አስቀምጠው የሚደበድቡ ጉዶች ሆነዋል፡፡

ከላይ በተንደረደርንበት ነባራዊ ሃቅ ላይ ቆመን ለፖለቲካችን ቆሞ-መቅረት፣አልለቅ ላለን የክፉ አስተዳደር አዙሪት ስፋኔ ዋነኞቹ ተጠያቂዎች የትናንቶቹ የነፃነት ታጋይ፣የእኩልነት አደላዳይ፣የዲሞክራሲ ነብይ ነን ባዮቹ ሃገራችን የፖለቲካ ልሂቃን መሆን አለባቸው ብየአስባለሁ፡፡ የእነዚህ አካላት አታላይነት፣አስመሳይነት፣ግብዝነት እና መሰሪነት ፕ/ሮ መስፍን ለፖለቲካችን ክፉ አዙሪት በምክንያትነት ካነሷቸው ቂመኝነት፣ልግም፣ማድፈጥ፣እና ክፋት እኩል ፖለቲካችንን የክፋት አዙሪት ውስጥ የከተቱ መሆናቸው ታውቆ ለፈውሳችን መላ መባል አለበት፡፡

ያልተስማማኝ….

ከላይ እንደተቀስኩት ፕ/ሮ መስፍን እግራቸው ስር ቁጭ ብለን የፃፉ የተናገሩትን ልናስተውል የሚገባን ድንቅ መካር ናቸው፡፡ ብዙ የሚያመርት ፈጣን ጭንቅላት ያላቸው፣ፍርሃት የማያውቃቸው፣ብዙ ምሁራንን የሚያንገላታው የቁስሰቀቀን ሲያልፍም የማይነካካቸው፣ ሃገር ወዳድ አድባር እንደሆኑ አያነጋግርም፡፡ሆኖም ከሃሳባቸው ጋር አለመስማማትም ሆነ በከፊል መስማማት ተፈጥሯዊም ጤናማም ነው፡፡ግን አለመስማማታችንን ስንገልፅ ሽምግልናቸውን ብቻ ሳይሆን አዋቂነታቸውን የሚመጥን ክብር ልንነፍጋቸው አይገባም፡፡ ለትልቅነታቸው ያለኝ ክብር እንዳለ ሆኖ፤በንግግራቸው ብዙ በመማሬ እያመሰገንኩ ከንግግራቸው ያልተስማሙንን አንድ ሁለት ነጥቦች ላንሳ፡፡ አንደኛው ከላይ የጠቀስኩት ህዝቡን እና አታላዩን ልሂቅ በአንድ ላይ አይተው ለፖለቲካችን ክፉ አዙሪት በእኩል ተጠያቂ ያደረጉበት መንገድ ቢነጣጠል እና ልሂቁ እንደጥፋቱ መጠን ትልቁን ሃላፊነት ቢወስድ የሚል ነገር አለኝ፡፡ ፕ/ሮ መስፍን የሚሉት በጎ ስርዓትን ለመትከል ሚገፋውን በጎ ሃይል ያጣው አስመሳይ መልቲነትን ተከናንቦ ስልጣን ላይ ቂጢጥ ያለው ልሂቅ ነው፡፡ ‘ህዝቡስ በዚህ አዙሪት ውስጥ ድርሻ የለውም ወይ?’ የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም ህዝቡ ከተወቀሰ የሚወቀሰው በደርሶ አማኝነቱ ምክንያት ለልሂቁን ብልጣብልጥነት መረዳት ባለመቻሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የግንዛቤ ነገርም ስላለበት በብዛት ላልተማረው ህዝባችን ይቅርታ ለማድረግ በቂ ምክንያት ነው ብየ አስባለሁ፡፡ ህዝቡ ሸማቂዎች ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ቃልአባይነታቸውን ተረድቶ ለምን በጊዜ አይሸኛቸውም የሚል ሌላ ጥያቄ ከመጣ ህዝቡ ይህን የሚያደርግበት የህግ የበላይነት፣ለይስሙላ ህግ በወረቀት ከመቸከቸክ ባለፈ ህግን የሚያስፈፅም ተቋማዊነት እንዳይኖር የልሂቃኑ አታላይ የፖለቲካ ማንነት ስላልፈቀደ፤ህዝቡ ገፍቶ ሲመጣም ልሂቁ በጥይት ቋንቋ ስለሚያናግረው አሁንም ወደ ማድጥፈጡ ከመመለስ ያለፈ አማራጭ የለውም፡፡ ስለዚህ ትልቁ ስራ የቀረው ስልጣን ላይ ካለው የፖለቲካ ልሂቅ ይመስለኛል፡፡

ሁለተኛው ጥቅሙን ያጣሁት የፕ/ሮ መስፍን ንግግር ስለ በላይ ዘለቀ እና አፄ ኃ/ስላሴ፤ ኦሮሞነት ስለ ኃ/ማርያም የወላይታ የመጀመሪያው ባለስልጣን ያለመሆን ጉዳይ ያነሱት ነገር ነው፡፡ ይሄ በተለይ እንደ እርሳቸው ለሰብአዊ ፍጡር ሁሉ መብት ለሚሟገት፤ይህንንም በሃገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቋም መስርቶ በማስኬድ ለሚወደስ የሰብዐዊነት ምልክት ሰው አይመጥንም፡፡ ለፖለቲካችን ፈውስም አስፈላጊነቱ አይታየኝም፡፡

 

የምንጣፉ ውበት!!!!

ፕ/ሮ መስፍን በንግግራቸው መጨረሻ ላይ በሃገራችን የፖለቲካ ወለል ላይ መነጠፍ ስላለበት በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በህግ ስርዓት የተማገረ ውብ ምንጣፍ የተናገሩት ውብ ንግግር በጣም ድንቅ ነው፡ ፡ምንጣፉ ዜጋን ሁሉ በእኩልነት የሚያንከባልል መሆን እንዳለበት፤ ሆኖም የሚንከባለሉ ሰዎች ወደ ምንጣፉ ሲመጡ ምንጣፉን እንዳያቆሽሹና ወደ ተለመደው አዙሪታችን እንዳይጨምሩን አእምሯቸውን፣ ከቂም በቀል ማፅዳት፣ ከክፋት መፈወስ አለባቸው ይላሉ፡፡ ነገሩ ድንቅ ነው፡፡ ሆኖም ጉዳዩን ከምኞት ባለፈ ገቢራዊ ለማድረግ ደግሞ የፖለቲካ ንቃትን በህዝቡ አእምሮ ውስጥ ማስረፅ አስፈላጊ እንደሆነ በደንብ ሊጤን ይገባል፡፡ አእምሮን የሚያቆሽሽ፣ ክፋት የሚሞላ፣ጨለምተኝነት፣ ጠጠራጣሪነት፣ ቂም በቀልን የሚያሸክም፣ በምኞት ፈረስ የሚያስጋልብ፣ በልቼ ልሙት የሚያስብል ራስ ወደድነት፣ የህግ ማህበረሰብ ያለመሆን፣አምባገነንን ለመሸከም የማጎንበስ አድርባይነት ሁሉ ምንጩ አለማወቅ ነው፡፡ ስለዚህ በሃገራችን የሲቪክ ማህበራት እንደልብ ተንቀሳቅሰው ህዝቡን ስለመብቱ፣ ግዴታው፣ ከመንግስት ጋር ሊኖረው ስለሚገባ ተገቢ ግንኙነት እንዲያስተምሩ መሆን አለበት፡፡ ይሄኔ የነቃው ህዝብ ዲሞክራሲ መብቱን ለማስከበር ተቋማትን ገንብቶ ለመብቱ ተቋማዊ ጠበቃ ያቆማልና አምባገነን እየተፈራረቀ ሊያስጨንቀው አይችልም፡፡

The post “የኔታ መስፍን ምን አጠፉ?” (በመስከረም አበራ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


እስቲ ጠይቁልኝ! – አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0

ወያኔ ደብረ ብርሀን ላይ በከፈተው የአእምሮ ማጫጫ የፖለቲካ ማዕከል [ዩኒቨርሲቲ ላለማለት ነው] «ዳግማዊ ምኒልክ ካምፓስ» በሚል ስም የመሰረት ድንጋይ ለወደቀለት ትውልድ ማምከኛ ካምፕ የትግራይ ካድሬዎች እነ ዳንኤል ብርሀነ «ንጉሱ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋልና በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር አልፈልግም ቢል እንዴት ይታያል?» ሲሉ ዘመቻ ከፍተዋል።

አቻምየለህ ታምሩ

የወያኔ ካድሬዎች ሰው ሁሉ እንደነሱ ደንቆሮና ማገናዘብ የተሳነው ይመስላቸዋል። ይሄ እነሱ «ንጉሱ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል» የሚሉት ነገር ሁሉኮ የተፈጸመው ወያኔ ሀውልትና ትምህት ቤት ያቆመላቸው ዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሰ ነገሥት በነበሩበት [ያኔ ምኒልክ ንጉስ ነበሩ] ዘመንኮ ነው። ፖለቲካቸው ጸረ እውቀት፣ የዘርና የዐማራ ጥላቻ ስለሆነ ዓፄ ዮሐንስ አራተኛ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጸመ ለሚሉን «የሰብዓዊ መብት ረገጣ» የአንዱን ጠቅላይ ግዛት[ የሸዋን] ገዢ ንጉስ ምኒልክን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ይገርማልኮ! ወያኔ ሐውልት ያቆመላቸው የጨለንቆም ሆነ የአኖሌ እየተባሉ የሚነገሩት ጦርነቶችኮ የተካሄዱት በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ሳይሆን ዓፄ ዮሐንስ አራተኛ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት በነበሩበት ዘመንኮ ነው። እና በምን መስፈርት ነው በዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሰ ነገሥት ዘመን በሆነው ንጉስ ምኒልክ ተወቃሽ ተደርገው «ንጉሱ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል» ሊባሉ የሚችሉት?

ምን ይሄ ብቻ! እነዚህ ካድሬዎች ምኒልክን «በየሰብዓዊ መብት ረገጣ» እየከሰሱ እነሱ ተጨማሪ ሀውልት እንዲቆምላቸው፤ ግዛት እንዲሰየምላቸው ዘመቻና ቅስቀሳ የሚያካሄዱላቸውና «የኛ ናቸው» የሚሏቸው እነ ዓፄ ዮሐንስኮ «ጎጃም ተቃጠለ ከአባይ እስከ አባይ፣ ትግሬ ቅጠል ይዞ ሊያጠፋው ነው ወይ?» የተባለላቸው፤ በነ ዳንኤል ብርሀነ አገላለጽ «ከሰብዓዊ መብት ረገጣ» አልፎ ጎጃምን በሙሉ ያጠፉ፤ ወሎን የጨፈጨፉና የዋጉን ተክለ ጊዮርጊስን አይን በእጃቸው አፍርጠው በዱልዱም በማረድ ዘግናኝ ጭካኔ የፈጸሙ ናቸው።

ምን ይሄ ብቻ! የተከዘ ማዶ ካድሬዎች በየቦታው ሀውልት እንዲቆምላቸውና ትምህርት ቤት እንዲሰየምላቸው የሚቀሰቅሱላቸውና «የኛ ናቸው» የሚሏቸው እነ ራስ አሉላ አባነጋኮ «ሰብዓዊ መብት ረገጣ» ብቻ ሳይሆን ጦርነት በሌለበት ሁናቴ ሰላማዊ ሕዝብ በመውረር ፌቫሊና ሮይ ፓተማን «Blood, Land, and Sex፡ Legal and Political Pluralism in Eritrea» በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሀፍ ገጽ 36 ላይ እንደገለጽው እ.ኤ.አ. በ1886 ዓ.ም. በባህረ ነጋሽ ባርካን ክልል ባካሄዱት ወረራ ሁለት ሶስተኛውን የኩናማና የናራ ህዝብ እንደጨፈጨፉ አስከፊውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የተካሄደውን ጥናት ጠቅሰው አቅርበዋል።

እና እንግዲህ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋልና በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር አልፈልግም ቢል እንዴት ይታያል?» ከተባለ መታየት ያለበት የምኒልክ ብቻ ሳይሆን በዓፄ ዮሐንስ አራተኛና ራስ አሉላ አባ ነጋ ስም የተሰየመውና የሚሰየመው ሁሉ ነው መሆን ያለበት። በዚህ በማይዋሽበት ዘመን ሲያቃጥል በማንኪያ፤ ሲቀዘቅዝ በእጄ አይሰራም! ኢትዮጵያስ ዳግማዊ ምኒልክ በግፍ የመሰረቷት አገር ከሆነች ለምን ሁላችን ወደነበርንበት ከግራኝ በፊት ወደነበረው ይዞታችን አንመለስም?

በምኒልክ ከተማ በአዲስ አበባና በመላው በአገሪቱ ተንፈላሰው ደልቷቸው ተዘባነው እየኖሩ «ንጉሱ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋልና በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር አልፈልግም ቢል እንዴት ይታያል?» የሚሉትን የትግራይ ካድሬዎች እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁልኝ፤

1. «ዳግማዊ ምኒልክ » በሚል በተሰየመ ካምፓስ ውስጥ «ንጉሱ ሰብአዊ መብት ረገጣ ስለፈጸሙ» ተማሪ መማር ላይፈልግ ይችላል ካላችሁ የናንተው ድርጅት ወያኔ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን ይሰራል? ሁሉ ነገር ከራስ ይጀምራል እንደሚባለው «ሰብአዊ መብት በፈጸሙት» በምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ፋሽስት ወያኔ ለምን ይኖራል? እስቲ መጀመሪያ እናንተ «ሰብአዊ መብት ረገጡ» ካላችኋቸው ከምኒልክ ቤተ መንግሥት ውጡና ለመርሃችሁ መገዛታችሁን አሳዩን?

2. እናንተ የትግራይ ካድሬዎች «ምኒልክ የሰብአዊ መብት ረገጣ ስለፈጸሙ በሳቸው ስም በየተሰየመ ካምፓስ ውስጥ አዲስ ገቢ ተማሪ መማር የለበትም» ስትሉ ያነሳችሁት «ተጠይቅ» የመርህ ጉዳይ ከሆነ፤ ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በገነቡት አገር ውስጥ፤ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በቆረቆሩት ከተማ ውስጥ እናንተ ምን ትሰራላችሁ? ለምንስ እናንተ የትግራይ ሰዎች ተከዘን ተሻግራችሁ፤ ወሎና ሸዋን አልፋችሁ ምኒልክ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው በገነቡት አገር፤ በቆረቆሩት ከተማ በአዲስ አበባ ውስጥ ትኖራላችሁ?

3. «ዳግማዊ ምኒልክ ካምፓስ» በሚል ስም የመሰረት ድንጋይ በወደቀለት ትውልድ ማምከኛ ካምፕ ውስጥ ንጉሱ ሰብአዊ መብት ስለፈጸሙ ተማሪ መማር ላይፈልግ ይችላል ካላችሁ ለምን ይህ ጉዳይ ከናንተ አይጀምርና ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» በገነቡት አገር፤ በቆረቆሩት ከተማ መኖር አንፈልግም ብላችሁ ወደ ትግራይ አትገቡም? እናንተ የሰብአዊ መብት መምህሮች ሰብአዊ መብት ተረግጦ በተገነባ አገር ውስጥ ለምን ትኖራላችሁ?

4. የናንተ ድርጅት ፋሽስት ወያኔስ ለምን ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» አንድ ያደረጉትን አገር ይገዛል? እንዴትስ ብሎ ምኒልክ «የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመው» አንድ ካደረጓቸው «ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች» ግብር ይሰበስባል? እስቲ ጠይቁልኝ!

The post እስቲ ጠይቁልኝ! – አቻምየለህ ታምሩ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የአዜብ ጎላ ዋነኛ ገንዘብ ደባቂዋ ተጋለጠች! – አስናቀው አበበ

$
0
0

የአዜብ የእክስት ልጅ የአዜብ ጎላ ብር አስቀማጭና አንቀሳቃሾች ውስጥ አንዷ መሆኗን Forbes አስነቃባት። ሃፍታም “ኢትዮጵያዊያን” ተብለው አንድ አምስት ሰወች ስማቸው ቢደረደርም “አኪኮ ስዩም አምባዬ” የተባለችው ቁጥር አንድ ላይ ተሰድራለች። ከአሁን በፊትም አዜብ ጎላ የናጠጡ ሃብታም ተርታ በይፋ መዘገቧ ይታወቃል። እነዚህ የእፉኝት ልጆች ምን ያክል እንደቦጠቦጡን ተመልከቱ። እነዚህን የገቡበት ገብተን ጨርሰው ሳያጠፉን ካላስወገድናቸው አጥንታችንም አይተርፍ።

እናም የመለስ ዜናዊ ሚስት የአዜብ ጎላ የአክስት ልጅ የሆነችው አኪኮ ስዩም የኦርካይድ ቢዝነስ ግሩፕ ( Orchid Business Group , OBG ) መስራችና ባለቤት እንደሆነች ተጠቅሷል። ሸፍጡ አዜብ ጎላን ለመከለል እንደሆነ የማይታበል ነው። ይህ ኩባንያ በመንገድ ስራ ተቋራጭነት ፣ በኮንሰትራክሸን ዕቃዎች አቅራቢነት እና ኪራይ ላይ የተሰማራ ነው ተብሏል።
ይህች ስሟንም ሰውነቷንም ድልት እንዲለው ያደረገች ምስጥ ፎቶዋን እዩትና ለሃገራችን መራቆት አንዷ ባለወፍራም ባለእዳ መሆኗን አስምሩበት።

The post የአዜብ ጎላ ዋነኛ ገንዘብ ደባቂዋ ተጋለጠች! – አስናቀው አበበ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ለሶስተኛ ጊዜ ተቀጥሮ የነበረው የባሕር ዳር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የዋስትና መብት ጥያቄ ዳግም ውድቅ ተደረገ

$
0
0

ለዛሬ ሰኔ 7/2009 ዓ.ም ፡፡
(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
****************************************
«በከፍተኛ የአገር ሃብትና የሰው ህይወት ውድመት » ተጠርጥራችኃል በሚል አስር ወራቶች በእስር የቆዩት የሰማያዊ ፓርቲ የባህር ዳር አመራሮች ዳግም ያነሱት የዋስትና መብት ተነፍገው በባህር ዳር ማረሚየ ቤት እንዲቆዩ ሲል ፍርድ ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በዋለው ችሎት ወሰነባቸው። በማረሚያ ቤት ሁናችሁ ጉዳያችሁን ተከታተሉ የተባሉት ታሳሪዎቹ “የትኛውን ጉዳይ” ብለው ቢጠይቁ ዳኛው መልስ እንደሌለው የተናገረው የታሳሪዎቹ ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ

« የአንድ ምርመራ መዝገብ ማለቅ ያለበት በ15 ቀን ውስጥ ነው። ይህ ቀን በቂ አይደለም ከተባለ በፍርድ ቤት ተቀርቦ ተጨማሪ ቀናት ይጠየቃል እንጂ ምንም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ባልተጠየቀበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ባለታወቀበት ምክንያት በማረሚያ ቤት ሁናችሁ ጉዳያችሁን ተከተተሉ ማለቱ አገሪቱ ያለችበትን ስር የሰደደ ህገ ወጥ የሆነና የህግ መሰረት የሌለው በተጨማሪም በአገሪቷ ላይ ፍትህ አልባነትና ምን ያህል እንደነገሰ አመላካች ድርጊት ነው ብሏል።» ፓርቲውን ለማዳከም ሲባል ብቻ ክስ ሳይመሰረትባቸው ከአስር ወራቶች በላይ ታስረው መራራ መስዋትነት ካለ ምንም ጥፋታቸው እየከፈሉ ያሉት አመራሮች አቶ ማሩ ዳኘው፣ አቶ መልካሙ ታደለ፣ አቶ ሲሳይ ታከለ፣ አቶ እጅጉ አስማረ እና አቶ ወርቁ ጥላሁን ናቸው።

The post ለሶስተኛ ጊዜ ተቀጥሮ የነበረው የባሕር ዳር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የዋስትና መብት ጥያቄ ዳግም ውድቅ ተደረገ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከከያኔያን (ከአርቲስቶች) ምን ይጠብቃል? የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለሐሰተኛ ከያኔያን! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

ከያኔ (Artist) ማለት ብዙዎቻችን በስሕተት ኪነጥበብ በምንለው ዘርፍ እና በሥነ ጥበብ (Fine art) ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ወይም ጥበበኛ ማለት ነው፡፡ ቃሉ የአማርኛ ቃል ሲሆን ኪን (ጥበብ) ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ከያኔ የሚለው ቃል በቁሙ የግእዝ ቃል አይደለም፡፡ የዚህ ቃል የግእዝ አቻ ቃል ኬንያ የሚለው ቃል ነው፡፡ ከያኔ የሚለውን ቃል አንዳንዶች በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎች ከያኒ ብለው ሲጽፉትና ሲናገሩት አያለሁ፡፡ ስሕተት ነው መታረም አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ሸማኔ እንላለን እንጅ ሸማኒ አንልም፣ ነጋዴ እንላለን እንጅ ነጋዲ አንልም፣ ገበሬ እንላለን እንጅ ገበሪ አንልም እንዲህ እያልን በርካታ የአማርኛ የሞያ ስሞችን ምሳሌ መጥቀስ እንችላለን፡፡

በስሕተት ኪነ ጥበብ የምንለውም ሆነ ሥነጥበብ የምንለው ሁለቱም ዘርፍ ባጠቃላይ ሥነኪን ይባላል፡፡ በመሆኑም ከያኔ ስንል አቀንቃኙን ወይም ዘፋኙን፣ ተወዛዋዡን ወይም ዳንኪረኛውን፣ መሣሪያ ተጫዋቹን፣ ገጣሚውን፣ አቀናባሪውን፣ የወግ አዋቂውን ወይም ወገኛውን (ኮሜዲያኑን) ፣ ተዋኙን፣ ደራሲውን፣ አዘጋጁን፣ ሠዓሊውን፣ ቀራጺውን ባጠቃላይ በሁሉም የጥበብ ወይም የኪነት ዘርፍ ላይ ያለውን ባለሞያ ማለታችን ነው፡፡

ማንኛውም ሞያ የራሱ ተግባርና ኃላፊነት ወይም የተጣለበት አደራ (Mandate) ዓላማና ግብ አለው፡፡ የሥነኪን ግን ሥነኪን የማትገባበትና የማትዳስሰው፣ የማታበረታው፣ የማታጎለብተው፣ የማትደግፈው የሞያ ዓይነት የለምና የአንድን ማኅበረሰብ ወይም ሕዝብ ሁለንተናዊ ጤና፣ ሰላም፣ እድገት፣ ብልጽግና፣ ደኅንነትና ህልውናን ለማሳደግ፣ ለመጠበቅና ለመንከባከብ የተጣለባት ኃላፊነት ዓላማና ግብ ከሌላው ሞያ ሁሉ የከበደ ነው፡፡

ምንጊዜም የትም ቢሆን ሥነኪን የሕዝብ ከሕዝብ ለሕዝብ ነች፡፡ ይህም ማለት ሥነኪን ሁልጊዜ የሕዝብ መብትና ጥቅም፣ የእውነት ወይም የሐቅ ተሟጋችና ጠበቃ ነች ማለት ነው፡፡ የተፈጠረችበት ዓላማና ግብ ሕዝብን ማገልገል ለእውነት መሟገት ብቻ ነው፡፡ ይሄ ሲባል ግን የሕዝብ ጠላት የሆኑት አንባገነንና አረመኔ ገዥዎች እጇን እየጠመዘዙ አስገድደው አይጠቀሙባትም ማለት አይደለም፡፡ አንባገነን ገዥዎች ከሀድያንና በሥነኪን ላይ የመነፈቁ ከያኔያንን ይዘው ለራሳቸው ፀረ ሕዝብ የጥፋት ዓላማና ተግባር እጇን ጠምዝዘው ሲጠቀሙባት ቆይተዋል እየተጠቀሙባትም ይገኛሉ፡፡ የዛኑ ያህል ደግሞ ዓለማችን በርካታ ብርቅየ ከያኔያን ለዚህ ሕዝባዊ አገለግሎትና ለእውነት ታምነው በማገልገል የሕዝብና የእውነት ጠላቶችን በጽናት ሲታገሉ ከባድና የሕይዎት ዋጋ የከፈሉባት ምድርም ነች፡፡ ከያኔያን “ከያኔ ወይም የጥበብ ሰው ነኝ!” ለማለት ለዚህ ሕዝባዊ አገልግሎትና ለእውነት የታመኑና የጸኑም መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

የሕዝብ መበደልና ብሶት የማይሰማው፣ የማይገደው፣ የማያሳስበውና የሕዝብን ፈተናዎች ለማስወገድ የሚበጅ መፍትሔ ለማመንጨት የማይጥር ሰው በምንም ዓይነት ተአምር ቢሆን የበቃና የነቃ ከያኔ (Artist) ሊባል አይችልም፡፡ ይሄንን ሰብእና (ስብእና አይባልም ስሕተት ነው) ሳይላበስ ከያኔ ነኝ የሚል ካለ አስመሳይ ወይም አታላይ አጭበርባሪ ነጋዴ እንጅ በፍጹም ከያኔ አይደለም፡፡ “ከያኔያን ስስ ቆዳ ነው ያላቸው!” የሚባለውም ለዚሁ ነው፡፡ በሕዝብ ላይ የሚደርስ ጉዳትና በደል ሁሉ ከማንም ቀድሞ ክፉኛ የሚሰማቸውና እረፍት የሚነሳቸው እነሱኑ ስለሆነና የሚከፍሉት ውድ ዋጋ ወይም መሥዋዕትነት ሳያሳስባቸው ሥነኪንን በመጠቀም የሕዝቡን ብሶት ስለሚተነፍሱ፣ ችግሩ ሊቀረፍ የሚችልበትን መላና ምክርም ለሕዝብ ስለሚጠቁሙ ነው፡፡

እርግጥ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት ወይም እኩል የብስለት ደረጃ፣ የማሰብ አቅም፣ የማገናዘብ ችሎታ፣ የሀገር ፍቅርና የተቆርቋሪነት ስሜት አለው ማለት አይቻልም ሊሆንም አይችልም፡፡ እነኝህ እሴቶች ቢጠበሱ የማይሸቷቸው ያለሆዳቸው ምንም ሌላ የማይታያቸው ግለሰቦች ጥቂት ቢሆኑም በሥነኪናችን ዘርፍም አሉ፡፡

እነ ሰሎሞን ተካልኝ፣ እነ ነዋይ ደበበ፣ እነ ፍቅረአዲስ ነቅዓጥበብ፣ እነ አስቴር አወቀ (ለወያኔ ያላትን ቅርበት በሚያሳዩ ተግባሮቿ በተጨማሪ ወያኔ እንዳይነካ ካላት የቅጥረኝነት ፍላጎቷ የተነሣ ከዓመታት በፊት ከሸገር የነጋሪተወግ ጣቢያ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ላይ ዘፋኝ በፖለቲካ ጉዳይ ላይ መግባት የለበትም! ብላ መናገሯ ይታወሳል) ፣ እነ ኩኩ ሰብስቤ፣ እነ ሠራዊት ፍቅሬ፣ እነ ሙሉዓለም ታደሰ፣ እነ ሸዋአፈራው ደሳለኝ እና ሌሎች አሁን ያልታወሱኝ ግለሰቦች “መስሚያችን ጥጥ ነው!” ብለው ጆሯቸውን ደፍነው ለሕዝብ ጀርባቸውን ሰጥተው ከሕዝብና ከሀገር ጥቅም በተፃራሪ በ21ኛው መቶ ክ/ዘ የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ወንጀልን የዚህች ሀገር የጀርባ አጥንት በሆነ ሕዝብ ላይ (በአማራ ሕዝብ) በሰፊው እየፈጸመ ካለ ከወያኔ ጎን ቆመው እየሠሩ፣ ለወያኔ ህልውናና ጥቅም የበኩላቸውን እያበረከቱ ያሉ ሐሰተኛ ከያኔያንን ስናይ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት የብስለት፣ የተጠያቂነት፣ ኃላፊነትን የመሸከም አቅም፣ የማገናዘብ ችሎታ፣ የሀገርና የወገን ፍቅር ስሜት፣ የሕሊና ወቀሳና ከሰሳ ስሜት፣ የሞራል (የቅስም) ስሜት የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡

ለእነኝህ ግለሰቦች ከያኔ ማለት ማንም እንደ ሱቅ ዕቃ እያነሣ እንደፈለገ የሚጠቀምበት፣ እስከተከፈለው ጊዜ ድረስ ለማን? ለምንና ምን? ብሎ ሳይጠይቅና ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ሳይለካ ማንም ቢያሠራው ታዛዥ ሆኖ መሥራት ያለበት ተናጋሪ ዕቃ ወይም ለሆዱ ብቻ ያደረ እንስሳ ማለት ነው፡፡ እንደ ዜጋና እንደ ከያኔ (Artist) ከሀገርና ከሕዝብ የተጣለበት ግዴታና ኃላፊነት እንዳለ ከዚህም የተነሣ በሀገርና በሕዝብ ጥቅም ላይ ለድርድር የማይቀርብ አቋም ሊይዝ እንደሚገባው ጨርሶ አይረዱም መረዳትም አይፈልጉም፡፡ የሚኖሩትና የሚለፉት የማይሞላ ሆዳቸውን ለመሙላት ብቻና ብቻ ነው፡፡

በጣም የሚገርመኝ ነገር እነኝህ ግለሰቦች በዚህ የወረደ የብስለትና የሰብእና ደረጃ ላይ ያሉ ሆነው ሳለ ከርሳቸውን ለመሙላት ለሚያደርጉት ጥረት የሚረዳቸውን የብልጣብልጥነት ችሎታን እንዴት ለመላበስ እንደቻሉ ነው፡፡ ለነገሩ ብልጥ ማለት ብልህ ማለት አይደለምና የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ሕዝቡ በእንደነዚህ ዓይነት ግለሰቦች የተነሣ ዘፋኝነትን ምንም ዓይነት ኃላፊነትና ተጠያቂነት የማይሰማው አጭሉግ፣ የሞራል ዋጋው የወረደ ስድ፣ ትምህርት የማይገባው ደደብ ሁሉ ሔዶ የሚታጎርበት ክፍት የሥራ ቦታ አድርጎ ለማሰብ የተገደደውም ለዚህ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ግለሰቦች በመስኩ ገነውና ከብረው ስለሚመለከት፡፡

ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ የሕዝብ ገዳይ የወያኔ መጠቀሚያ ሆነው፣ ከሕዝብና ከሀገር ገዳዮች ጎን ተሰልፈው እያሉ “እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን! ሕዝብን ማስደሰት ነው ሥራችን!” የሚሉ መሆናቸው ነው፡፡ ለመሆኑ የሕዝብ አገልጋዮች ነን ማለት ምን ማለት ነው? የትኛውንስ ሕዝብ ነው እያገለገሉ ያሉት በሞቴ?

ነብሰበላውና ነጋዴው ወያኔ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻ ወንጀል የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሕዝባችን ላይ በመፈጸም እጁን በወገናችን ደም ደጋግሞ በመታጠቡ፣ የበርካታ ንጹሐን ወገኖቻችንን ደም በግፍ በማፍሰሱ ሕዝቡ “ዳሸን ቢራ የተባለው የንግድ ድርጅቱን ቢራ መጠጣት ማለት በግፍ የፈጃቸውን የወገኖቻችንን ደም መጠጣት ማለት ነው!” የሚል የጸና አቋም ይዞ አድማ በማድረጉ ምክንያት ዳሸን ቢራ ለከፍተኛ ኪሳራ በመዳረጉ ስሙን ቀይሮ ለመምጣት ተገዶ አዲሱን “ባላገሩ ቢራ” ሲል የሠየመውን ምርቱን ለማስተዋወቅ በቅርቡ ባሕር ዳር ከተማ ላይ በፍንዳታ የታጀበን የሙዚቃ ኮንሰርት (የዘፈን ትዕይንት) አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ የዘፈን ትዕይንት ዝግጅት ላይ ከተፈጸመው የፈንጅ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ዝግጅቱን ለማድመቅ በቦታው የነበረችው ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ከአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ላይ “እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን! ሕዝብን ማስደሰት ነው ሥራችን!” በማለት በሕዝብ ላይ ተሳልቃለች፡፡

እርግጥ እውነት ነው ከያኔያን የሕዝብ አገልጋዮች ናቸው፡፡ የሚሠሩትም ሕዝብን ለማስደሰት ብቻ ሳይሆን ለማንቃት፣ ለማስተማር፣ ለማሳወቅ፣ ለማጀገን፣ ለማጽናናት፣ ለማነፅ ወዘተረፈም ነው፡፡

የሀገርና የሕዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን እያገለገሉ ግን ያውም አሁን በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን መብታቸውን ጠያቂ ወገኖቻችንን በእሩምታ ቶክስ በፈጀባት ባሕር ዳር ከተማ አደባባይ ላይ ገና በግፍ የፈሰሰው ደማቸው ከመሬቱ ላይ ሳይለቅ ሳይጠፋ እንደቀለመ ባለበት የወያኔን የንግድ ድርጅትን ምርት ለማስተዋወቅ ከወያኔዎችና ደጋፊዎቹ ጋር እየጨፈሩ “እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን!” ብሎ ማለት ግን በሕዝባችን ደም ላይ ማፌዝ መቀለድ ብቻ ሳይሆን ይቅር የማይባል ዘለፋና ስድብም ነው፡፡ ይህችው ደንቆሮ የሥነኪን መናፍቅ በዚሁ ቃለምልልስ ላይ ጨምራም “…ከዳሸን ቢራ ጋር ችግር ያለባቸው ካሉ ጉዳያቸውን መጨረስ ያለባቸው ከዳሸን ቢራ ድርጅት ጋራ ነው እንጅ ከእኛ ጋር አይደለም!” በማለት በሕዝብ ላይ ምን ያህል ከባድ በደል እንደፈጸመች እንኳ መረዳት ተስኗት የባንዳነት ተግባሯን ለመከላከል ሞክራለች፡፡

ይህች ሰው የወያኔ መሣሪያ ከሆነች በጣም የቆየች ናት፡፡ ቴዎድሮስ ካሳሁንን አዛኝና አሳቢ መስለው አሳች ምክር በመምከር ለማወየን፣ ከሕዝብ አገልጋይነቱ ለማንጠብ፣ ሕዝብን ለማስካድ ከተላኩት ሥውር ተኩላዎች አንዷ ይህችው ኩኩ ሰብስቤ ነች፡፡ ቴዲን እግዚአብሔር ታደገውና ተጠልፎ ከመውደቅ ተረፈልን እንጅ በተላኩት በነኩኩ ሰብስቤ ውስወሳ ተንሸራቶ ለመውደቅ ተቃርቦ ነበር፡፡ ከእስር እንደተፈታ ገቢው ከትግራይ ለመጡ ለማኞች ብቻ የሚሆን ኮንሰርት (የዘፈን ትዕይንት) እንዳደረገ፣ በዚያው ሰሞንም ወያኔ ለዓባይ ግድብ መቀስቀሻ የተጠቀመበትን አዲስ ቴዲ ስለ ዓባይ ያቀነቀነውን ዘፈን በኢቴቪ እስከመስማት ደርሰን እንደነበረ ወዘተ ወዘተረፈ. በእነዚህ ነገሮችም ቴዲ ወደቀብን ብለን ደንግጠን እንደነበረ የሚታወስ ጉዳይ ነው፡፡

ከያኔያን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእነሱ ምን እንደሚጠብቅ የማያውቁ ሆነው ማወቅ ካሻቸው ምንም ማብራሪያና ትንታኔ መስጠት ሳያስፈልገኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን ምን ስለሠራ ሕዝቡ ለእሱ እንዲህ ዓይነት የሞቀ ምላሽ እንደሰጠውና እንደሚንሰፈሰፍለት በማየት ብቻ ከበቂ በላይ ትምህርት ይሰጣቸዋልና ከዚህ ይማሩ፡፡

እናም ከያኔያን ሆይ! ብትችሉ እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሁኑ፡፡ ባትችሉ ግን እባካቹህ ፈጽሞ በምንም ዓይነት ሁኔታ ቢሆን የወያኔ መጠቀሚያ ሆናቹህ የገዛ ሀገራቹህንና ሕዝባቹህን አትጉዱ አታጥቁ? ወያኔ እኮ ነገ ጠዋት ጠፊ ነው፡፡ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው “ያኔ የት እንገባለን? ምን ይውጠናል?” ብላቹህ አስቡ እንጅ ጃል!

እርግጥ ነው ወያኔ እናንተን ለማሳሳት ለማርከስ እንደ ዳሸን ቢራ ባሉ ድርጅቶቹ አማላይ ክፍያ በማቅረብና ለተለያዩ የሥነኪን ሥራዎች ስፖንሰር (ደጋፊ) በመሆን፣ ማስታወቂያ በማሠራት እናንተን በጥቅም ደልሎ መጠቀሚያ ሊያደርጋቹህ ይጥራል ሲያደርግም ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ እንደ የማለዳ ኮከቦች ዓይነት የትወና ውድድር ዝግጅት፣ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን (የዘፈን ትዕይንቶችን) እና ከያኔያን የሚሠሯቸውን የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በእርግጠኝነት የሥነኪን ዓላማ ምንነትና ግብ የገባው ከያኔ ወይም የሥነኪን ሰው ምንም ዓይነት መደለያ ቢቀርብለት በምንም አይደለልም፡፡ እሱን የሚያረካው ለሕዝብ በሚያቀርበው የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር በሚሞክሩና ለሕዝብና ለእውነት ጥብቅና በቆሙ ሥራዎቹ ነው እንጅ ሥነኪንን አርክሶ ከሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ ተጉዞና ወስልቶ በሚያገኘው የረከሰ የግፍ ገንዘብ አይደለም፡፡ ሥነኪንን መጠቀሚያ አድርጎ በአቋራጭ ለመክበር የሚቋምጥ የሥነኪንን ምንነት ዓላማና ግብ የማያውቅ የማይረዳና መረዳትም የማይፈልግ አስመሳይ ከያኔ ነኝ ባይ ነጋዴ ግን ዓላማው በየትኛውም አማራጭ ቢሆን አወናብዶ ገንዘብ ማግኘት ብቻ በመሆኑ እንኳንና አማላይ መደለያ ቀርቦለት ይቅርና በአምስት ሳንቲምም ቢሆን የሚደለል ነው፡፡ የማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር ዝግጅት፣ የወያኔ የንግድ ድርጅቶችን በስፖንሰርነት (በደጋፊነት) የሚጠቀሙ የሙዚቃ ኮንሰርቶች (የዘፈን ትዕይንቶች)፣ የቴሌቪዥን ድራማዎች (የምርዓየ ኩነት ትውንተ ኩነቶች)፣ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያዎችን የያዙ ጥቂት የማይባሉ የቪዲዮ ፊልሞች (የትዕይንተ ኩነት ምትርኢቶች) እነዚህ ሁሉ ሆዳቸው አምላካቸው በሆኑ ጥበብን በርቀት እንኳ በማያውቋትና ለሀገርና ሕዝብ ቅንጣት ታክል ደንታ የሌላቸው ከያኔ ነኝ ባይ ሆዳም ነጋዴዎች የሚዘጋጁና የወያኔ መጠቀሚያዎች ናቸው፡፡

ይህች ሀገር በወያኔ አገዛዝ ምን ዓይነት ምስቅልቅል ውስጥ እንደገባች፣ በዘር መጥፋት የወንጀል ተግባሩ ወገን ደብዛው እየጠፋ መሆኑ ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡ ሀገራችን ከዚህ ምስቅልቅል እንድናወጣት፣ ራሳችንን እንድናድን ደጋግማ ላሰማችው የድረሱልኝና የንቁ ጩኸት ምላሽ የሰጡና መብታቸውን የጠየቁ ንጹሐን ውድ ልጆቿ ትናንት በየአደባባዩና በየጎሬው በሩምታ ቶክስ ተፈጅተዋል፣ አሁንም ድረስ በየወኅኒ ቤቱ ታጉረው በአረመኔው አገዛዝ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ፣ ለብዙ ዓይነት ተነግሮ ለማያልቅ ሰቆቃ ተዳርገዋል፡፡

ሀገራችን ከገጠማት ከዚህ እጅግ አሳሳቢ ችግር ለመውጣት የሁሉንም ዜጋ ርብርብ የግድ ይጠይቃል፡፡ በዚህ ርብርብ የዳር ተመልካች ወይም ገለልተኛ የሚባል ዜጋ ሊኖር አይችልም፡፡ አንድ ዜጋ ወይ ከጠላቷ ከወያኔና ግብረ አበሮቹ ጋር ነው ወይ ደግሞ ከሕዝብ ወገን ነው፡፡ ማንም ሰው ከሁለቱ ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ የዜግነት ግዴታውን ወርውሮ ጥሎ ስንቶቹ ዋጋ እየከፈሉ ባሉበት ጊዜ “በእኔ ካልደረሰብኝ ምን ቸገረኝ!” በሚል በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ኢሰብአዊ ግፍ በዝምታ የሚመለከት ዜጋ ካለ ይሄ ከወያኔ ተለይቶ አይታይም ወያኔ ነው፡፡ ሕዝብን ፍዳና ሰቆቃ እያሳየ እያበላ ያለው የወያኔ መጠቀሚያ ሆኖ በግልጽ እያገለገለ እየታየም “እኔ ገለልተኛ ነኝ!” ማለት ሕዝብን እንደማያስብ መቁጠርና መናቅም ነው፡፡ ይሄ ነውረኛነት የተሞላበት ንቀት ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሁሉም ሊያውቅ ይገባል፡፡

ይህ አቋም የዜጎችን በነጻ የማሰብ ነጻነትንና የመሰላቸውን የመደገፍ ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) እና ሰብአዊ መብትን መጻረር መገደብ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን በፍጹም አይደለም፡፡ የየትኛውም ሀገር ሕግ ቢታይ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻው የወንጀል ጥቃትን ማለትም የዘር ማጥፋትን በግልጽና በስውር በሚፈጽመው አረመኔያዊ ጥቃት ሕዝብን እያጠፋ ያለን እጅግ አደገኛን የጥፋት ኃይል መደገፍ “የሚያስጠይቅ የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው!” ይላል እንጅ “ለዜጎች የተፈቀደ መብት ነው!” የሚል አንድም ሕግ በዓለማችን የለም፡፡

የሀገርንና የሕዝቧን አንድነት አጥፍቶ ለመበታተን ሌት ተቀን የሚያሴርን ከዚህም በላይ ለርካሽ ቡድናዊ ጥቅሙ ሲል ሕዝብን ከሕዝብ ጋራ በማጋጨት እስከወዲያኛው እንዳይስማሙ አድርጎ በሚፈጥረው ሐሰተኛ ታሪክ ተቂያቂመው እየተባሉ እንዲኖሩ የሚጥርንና ወደፊት እሱ የማይገዛበት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ ልትፈራርስ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ያስቀመጠ በሽተኛ የወንበዴ ቡድን መደገፍ፣ ለሕልውናዋ ተነግሮ የማያልቅ መራር መሥዋዕትነት የተከፈለባትን ሀገር ገንጥሎ የሚያስረክብና ለርካሽ ቡድናዊ ጥቅሙ እየቆረሰ ለባዕድ የሚሸቃቅጥን እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ የአህዮችን የጥፋት ኃይል መደገፍ፣ ዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መብታቸውን ስለጠየቁ ብቻ በዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ግፍ የሚፈጽምን አረመኔ የግፍ አገዛዝን ፣ “የአማራንና ኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርገን ሰብረናል!” በማለት በሕዝብ ላይ ከሚፈጽመው የዘርማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ ለዚህች ሀገር ሁለንተና የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከተችውን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መጫወቻ መቀለጃ አድርጎ ያዋረደ የሰበረና እያጠፋት ያለን የአጋንንት ውላጆች የጥፋት ኃይልን መደገፍ “የሚያስጠይቅ የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው!” ይላል እንጅ “ለዜጎች የተፈቀደ መብት ነው!” የሚል አንድም ሕግ በዓለማችን የለም፡፡ ከዚህም በላይ በነፍስም የሚያስኮንን፣ የገሃነም ፍርድ የሚያሰጥ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡

ስለሆነም የዜጎችን ነጻነትና መብት መገደብ ወይም መጻረር አይደለም፡፡ በመሆኑም እነኝህን አስከፊ ወንጀሎችን የፈጸመውንና እየፈጸመ ያለውን ወያኔን መደገፍ የሚያስጠይቅ ወንጀል እንጅ መብት አይደለም፡፡ ይሄንን ሀቅ ሁሉም ሊያውቅ ይገባል፡፡ ወያኔ እነኝህን በገሀድ እየፈጸማቸው ያሉትን ወንጀሎች ስለመፈጸሙ የማያውቅ አንድም ዜጋ የለም! ይሄ ሆኖ እያለ የዚህ ግፈኛ የጥፋት ኃይል ደጋፊ በመሆኑ እርምጃ የሚወሰድበት ግለሰብ ቢኖር ኃላፊነቱን እራሱ የሚወስድ ይሆናል፡፡ ወያኔ እንዲህ ዓይነት የጥፋት ኃይል መሆኑን እያወቀ እንደዜጋ ይሄንን የጥፋት ኃይል በተለያየ መንገድ መታገልና መቅበር ሲኖርበት የወያኔን አገዛዝ የደገፈ ሁሉ የሀገርና የሕዝቧ ጠላት ነውና ወያኔ ዕድሜ እንዲያገን ተጨማሪ አቅም ሆኖለታልና ፈጽሞ ምሕረት አይደረግለትም!!!

በአሁኑ ሰዓት ማንም ሊገነዘበው እንደሚችለው የሀገርንና የሕዝብን ህልውናና ደኅንነት ከወያኔና መሰሎቹ የጥፋት ኃይሎች እጅ ታድጎ የሀገርንና የሕዝብን አንድነት ህልውናና ደኅንነት ለማስጠበቅና ለማስቀጠል የሚደረገው ሕዝባዊ ትግል በአንድ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡ ከወያኔ ጋር እየረከሱና አረመኔ የጥፋት ኃይሉን ወያኔን እያገለገሉ እንደትናንትናው ሁሉ ዛሬም በሰላም ከርሳችንን እየሞላን እንኖራለን ብለው የሚያስቡ ባንዳና ከሀዲ ሐሰተኛ ከያኔያን ወይም የሥነኪን መናፍቃን ካሉ እጅግ መሳሳታቸውን ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡

ባለኝ ግንዛቤ በአሁኑ ጊዜ ሐሰተኛ ከያኔያኑ በየትኛውም ቦታ ይሁኑ፣ በማንኛውም ሰዓት ቢሆን ለዚህ ክህደታቸውና እርኩሰታቸው የሚገባቸውን ቅጣት ሊወስድባቸው የሚችል ሕዝባዊ የነጻነት ኃይል ከአጠገባቸው እንዳለ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ባላሰቡት ሰዓት፣ ባልጠበቁት ቦታና ባልገመቱት ሰው እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል ጠንቅቀው ይወቁት፡፡ የመጸጸቻ ዕድልም አያገኙምና ከዚህ በኋላ ባለው እርምጃቸው ካልታረሙ በሚወሰድባቸው ነጻ እርምጃ በሌላ በማንም ሳይሆን በራሳቸው ይዘኑ፡፡ ጨዋታ ወይም ቀልድ አይደለም የተያዘው፡፡ ብዙ ሀገር ወዳድ ወገን ውድ ዋጋ እየከፈለበት ያለ መራራ የነጻነት ትግል ነው የተያዘው፡፡

አሁንም በድጋሜ በርካታ ወገኖችን መራራ ዋጋ እያስከፈለ ያለውን ይሄንን የነጻነት ትግል ቀልድ አድርጎ የሚመለከትና እንደትናንትናው ሁሉ ዛሬም ለከርሱ ሲል የወያኔ መሣሪያ መጠቀሚያ ሆኘ ከሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ እቆማለሁ የሚል የሐሰት ከያኔ ካለ ለሚወሰድበት እርምጃ ኃላፊነቱን እራሱ የሚወስድ ይሆናል፡፡

ባንዳ ከያኔያን በአንድ በሁለቱ ላይ እርምጃ ተወስዶ ካላዩ በስተቀር የነጻነት ኃይሉን ማስጠንቀቂያ የምር አድርገው መውሰዳቸው የሚያጠራጥር ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም በባንዳነት ተግባራቹህ ቀጥሉና እርምጃው በማንኛቹህ ላይ ሊወሰድና ማንኛቹህ መማሪያ ልትሆኑ እንደምትችሉ ጠብቃቹህ የምታዩት ይሆናል ከማለት ውጭ ምንም ማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ አንድ ነገር ግን አስቡ እንደ ወያኔ ባለሥልጣናት በወታደር ተከባቹህ እየተጠበቃቹህ የምትኖሩ ባለመሆናቹህ እናንተን ማጥቃት ባስፈለገ ሰዓት በቀላሉ እርምጃው ሊወሰድባቹህ የሚቻል መሆኑን አስባቹህ ብትሰበሰቡ ወይም ብትታረሙ ጥሩ አይመስላቹህም? በነገራችን ላይ ይህ የነጻነት ኃይሉ ማስጠንቂያ በዋናነት በከያኔያን ላይ ያተኩር እንጅ ሁሉንም ዜጋ ይመለከታል፡፡ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ (የእምነተ አሥተዳደር ቡድን) ስም ተቋቁመው ወያኔን እያገለገሉ ያሉ ቆሻሾችን ጨምሮ፡፡

በዚህ አጋጣሚ “በሕዝብ መጠላት አልፈልግም!” በሚል ምክንያት ከወያኔ ጋር ከመነካካት ራሱን የጠበቀውን ወይም ያራቀውንና በዚህም ምክንያት ዋጋ ለመክፈል ተገዶ ዋጋ ለከፈለውና እየከፈለ ላለው ለሰፊው የሥነኪን ማኅበረሰብ ከዚህም በላይ ደግሞ የዜግነት ግዴታቸውንና የሥነኪን ሐዋርያነታቸውን ተረድተው በሥነኪን ሥራዎቻቸው ሕዝባዊ የነጻነት ትግሉን እያገዙ ላሉ ብርቅዬ ከያኔያን እንደዜጋ በግል ላቅ ያለ ምስጋናየን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጨረሻውን ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ከያዘው የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ምርት የሆኑ ሸቀጦችን ያለመጠቀምና ያለመገብየት አድማ በተጨማሪ የወያኔ መጠቀሚያ የሆኑ ሐሰተኛ ከያኔያንን ሥራዎችንም ባለመጠቀም፣ ባለመመልከት፣ በአነዚህ ባንዳ ሆድ አደር ሐሰተኛ ከያኔያን የሚተዋወቁ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ባለመጠቀም ትግሉን አጠናክሮ ይገፋል!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

The post የኢትዮጵያ ሕዝብ ከከያኔያን (ከአርቲስቶች) ምን ይጠብቃል? የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለሐሰተኛ ከያኔያን! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ኢትዮጵያነት የሰውነት ከፍታ ነው። አማራነትም የብሄራዊ ስሜት ዋልታና ማገር ነው፤ አትውረድ !!! – መስቀሉ አየለ

$
0
0

ሰው ሆኖ መፈጠር የድንቅ አእምሮ ባለቤት መሆን ነው። ሰማየ ሰማያትን ቀዶ ማሰብ መቻል ነው። ይህችን አለም ድንበር አልቦ ማድረግ ነው። እንደ መላእክት በመንፈስ መነጠቅ ነው። እኛ ደግሞ በአባቶቻችን የደም ዋጋ የተገዛን የሰማእታት ልጆች ነን። መጫሚያ የሌላቸው የቀደሙት አባቶቻችን ከአራቱም ማእዘን እየፈሰሱ በከፈሉት ዋጋ ነው እዚህ ያደረሱን ስንል ዛሬ የቆምንበት አፈር በነሱ አጥንትና ደም ጭምር ተለውሶ የተሰራ ነው ለማለትም ጭምር ነው። እኛ ደግሞ ከዚህ አፈር ጋር በእትብታችን ጭምር የተገመድን እንደመሆናችን ከዚህች መሬት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ማንነት ወደየትም አንሄድም ወደየትም አንወርድም። ይኽ ውበታችን ብቻ ሳሆን እንደ አንድ ሉአላዊ ህዝብ የሚያኖረን ዋስትናችንም ነው። ሰንኮፋው ወያኔና ኩባንያው ነው። መፍትሄው እሱን ነቅሎ መሄድ ነው። ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን ብለን የተስፋ ስንቅ የምንሰንቅና ተስፋችንም ስጋና ደም ገዝቶ እውን እንዲሆን እስከ ሲዖል ዳርቻም ቢሆን ለመጓዝ ቁርጠኛ መሆን እንጅ ከዚህ ራእይ መጉደል ጉዞውን የኋሊት ያደገዋል።

በአባቶቹ የወገብ ልክ መሙላት ያቃተውና ወያኔ ሰፍሮ በሰጠው ማንነት እንዲያስብ የተሰራ ብቻ ሳይሆን በዚህም የሚኮራ ትውልድ ከዚህ አካሄድ ጀርባ የተጠመደለትን አደጋ ማየት የተሳነው ብቻ ነው። ሰው ከአመክንዮ ወርዶ ሁሉን ነገር በስጋና በደም ብቻ መመንዘር ሲጀምር ምን ያህል ከእውነት ጋር እንደሚጣላና ሜዳና ገደሉን መለየት እንደሚሳነው ዳር ቆሞ ለሚያየው ሁሉ ፍንትው ያለ እውነት ነው። ችግሩ እርሱ በጎሳ ተስቦ መለከፉ ብቻ አይደለም። መለከፉን አለማወቁ ነው፤ ሌላውም እንደሱ እንዲሆንለት እንቅልፍ ማጣቱ ነው። በሌላ አነጋገር ታምሜያለሁና እናንተም፣ ታመሙ ማለቱ ነው። ሁሉም ታሞ ታሞ አስተማሚ በሚጠፋበት ቤት ማን ጥርኝ ውሃ እንደሚያቀብል እግዚአብሔር ይወቅ።በጎረቤታሞች መካከል በተነሳ ግጭት ግለሰቦች በደረሰባቸው ልብ ሰባሪ ሀዘን ተግፍተው የፈጸሙትን የሃይል እርምጃ እንደ ሰው ሆኖ ከተቻለም እንደራስ ሆኖ መፍረድ ሲገባ ዝም ብሎ እርምጃ የተወሰደበት ሰው ምንም ይስራ ምንም ነገር ግን አማራ ብቻ ስለሆነ የሌላውን ጉዳት ባለማየት ብቻ ሳይሆን የተፈጸመውን ወንጀል ወደ ጎሳ ፖለቲካ በማውረድ እነሱ ለሚፈልጉት አላማ ማዋልና ህብረተሰቡንም በዚያው በኩል እንዲፈስ ማራገብ ወይ የጤና ጉዳይ ካልሆነ ከወያኔ አለማነስ ነው።

አማራነት እኮ ፍትሃዊነት ነበር:: አማራነት እኮ ሰውን በአርአያ ስላሴ መፈጠሩን እንጅ በጎሳ መንዝሮ ያለማየት አቅም ነበር። አማራነት እኮ የካህኑ የመልከጸዴክ ልጅነት ነበር። አማራነት እኮ በሄንኖክ ተወክሎ በብሄረ ሔዋን ማእጠንት የሚሰዋ ህዝብ መሆን ነበር። ዛሬ እንደ ኤሳው ብኩርናቸውን ያቃለሉና በመለስ ዜናዊ ጫማ ልክ ጨንግፈው የተሰፉ ሁሉ ሁለት ልጅ በሆዷ ተሸክማ ስለተገደለችው እናት ጸጸትት የሚገልጥ አንዲት ጥርኝ ቃል ከ አፋቸው ሳይወጣ ስለተቃጠለ ንብረት ግን ብዙ ብለዋል። እኔ በእንዲህ አይነት ተፈጥሮ የማውቀው ቦኮሃራምን እና አጋዚን ነበር። የኔታ እንዳሉት ይኽ ነገር ለኔ ክሽፈት ነው።

ከምእራባዉያን የዜና ማሰራጫ ቋቶች በሚወጣ ፕሮፓጋንዳ የተፈለገውን ያህል ተጽእኖ ማሳደር አልተቻለም ተብሎ ቢቢሲና ሲኤን ኤን የአረብኛ ጭምብል ለብሰው በኩዋታር ከተሙና አልጀዚራ ሆነው መጡ። ከሱኒዎች እምብርት ኩዋታር በሚፈልገው የራሱ ቋንቋ የሚረጨውን ሁሉ ገና ለገና አረብኛ ነው በሚል ጆሮውን የሰጠው አረብ ሁሉ አልጀዚራን ተከትሎ ወደ ሰናኦር ዘመን ማዝገም ከጀመረ ሁለት አስርተ አመታት ሊሞላው ነው። ኢራቅ፣ ሊቢያ ሶሪያ የመን አፍጋኒስታን ካርታ ላይ አሉ ማለት አይቻልም። ቱርክ ግብጽ ባህሬን ኩዋታርና ሳውዲ አረቢያ ደግሞ ከፊት መስመር ተሰልፈው ቀናቸውን እየጠበቁ መሆኑን ለማየት አራት አይን አያስፈልግም።ከዚህ ሳይማር ጥቂት ወደ ጽንፍ የተገፉ ሰዎች የሚጽፉትን ብቻ እየተከተለ የሚሄድ ማንም ቢኖር ጤናውን ይፈትሽ።

The post ኢትዮጵያነት የሰውነት ከፍታ ነው። አማራነትም የብሄራዊ ስሜት ዋልታና ማገር ነው፤ አትውረድ !!! – መስቀሉ አየለ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የዘር መቧደንን ትግል፣ ፍርድ በመገምደል አንታገል! (ልያ ፋንታ)

$
0
0

ትግራይ፣ ትግራይ ( የህዋህት ደጋፊ)
ኦሮሞ፣ ኦሮሞ ( ኦሮሞ ፈርስት፣ ኦቦ ጁሀር)
አማራ፣ አማራ ( ቤተ አማራ ፣ ሞረሽ )
የአነዚህን አንድ ኢትዮጵያን ፈታኝ የሆነ መንገድ ላይ የጣለ የዘር የገመድ ጉተታ ለመፍታት ኢትዮጵያን ከእነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት የሚሹ ብዙ ሀገር ወዳዶች ተው! የዘር ጥምጥም ገመድ ለአንድ ሀገር ውድቀት ፣ ለውጭ ወራሪ በር የሚከፍት ነው እያሉ ስሚ እንኳ ባያገኙ ስለ ኢትዮጵያ ሲቃትቱ አመታት ተቆጥረዋል።
አንዳንዴ ደግሞ የአንድነት ሀይሉደጋፊ አቅጣጫውን ስቶ ወደ ፍርደ ገምድልነት ሲሄድ የእነ እከሌ አጃቢ የነገር ጁራፍ ይገርፈኛል ብሎ ማለፍ ህልናዮ አይቀበለውም። ጎንደር የሚገኙ የነጻነት ተፋላሚዎች የገዳይ ወያኔ አፈሙዝ እያጓራባቼው ለነጻነት ሲዋደቁ እኔ የማንንም ደጋፊ ተቃውሞ ፈርቼ ዝም ልል አይቻለኝም።
ወደ ዋናው ሀሳቤ ልግባ ፣ ትናንት በስፋት በሁለት ወገን ተቧድኖ ሲወዛገብ ያየሁት ጉዳይ አንድ አማራ በ በጉራጌ ዞን ውልቂጤ አንዲት ሴት ተገድላለች በሚል ሰበብ ወንጄሉን ፈጻሚው እርሱ መሆኑ በህግ ፊት ቀርቦ ሳይጣራ በቀቤና ጉራጌዎች ከፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት ወጥቶ ልክ እንደ ሳውዝ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን በግፍ በገጄራ ተከትክቶ ያለ ገላጋይ የመገደሉ ዜና ነው። እዚህ ላይ ሟቹ ተጋሩ፣ ኦሮሞ ቢሆን ይህ የግፍ ዜና እንዴት በጦዘ የእዮዮው እንቢልታ አለምን ባዳረሰ። ደግነቱ በዚህ ዘመን ለሞት የተፈጠረ በሚመስለው በአማራ መሆኑ ለሟች በግፍ መገደል ምንም ሳይታዘን የገዳይ ዘር የ ቀቤና ጉራጌ ለምን ተወሳ በማለት ልብሳቼውን አውልቀው ያበዱ የሚመስሉ ፀሀፊ እና ደጋፊዎችን አስተዋልኩ ። ዜናውን የዘገበውን ጋዜጠኛ ሙሉቀንንም ይባዝቱት ጄመር። ዳኛ አልባዋ፣ ሁሉም ሊቅ እና ዜና ዘጋቢ ጋዜጠኛ የሆነባት ፌስ ቡክ ቀውጢ ሆነች። ጉራጌ እኮ እነ እከሌ የወጡበት ማህበረ ሰብ ነው ተብሎም ተደሰኮረ።
አቤት ጉድ! ማስተዋላችንን ማን ወሰደው እረ? እኛ እያነስን ሄድን እንጂ ከየትኛውም ብሔረሰብ በተለያዩ ዘመን ጄግና ያልወጣበት ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ እኮ የለም። ክብር የነፈግካት አንተ ፣ ኡትዮጵያ ሁሌም የጄግና መብቀያ መሬት ነች።
አንተም አማራ፣ አማራ የምትለው ወገን ፣ግድያውን አስፈጻሚው መግደያ ገጄራ አቀባዪ ወያኔ እንጂ ጉራጌ እማ እንደ አማራ በድህነት እንዲማቅቅ የተፈረደበት ማህበረሰብ መሆኑን ለምን አታስተውልም?
የእብድ ገላጋይ በመሆን ፍርድን በመገምደልሳይሆን ይልቁን የነጻነት ትግሉን ተባብረን ዳር ማድረስ እንድንችል ሁል ጊዜ በደል ለሚደርስበት ብቻ ለመጮህ እንንቀሳቀስ። የዘር ፖለቲካ ወያነያዊ ጥርጊያ መንገድ ነው ፣ ግቡም መፈራረስ እና መለያየት ነው።
በመጨረሻም እጁ በካቴና እያለ ከስር ቤት በግፍ ወጥቶ በገጄራ የተከተከተውን መስፍን አዳነ ኢሰብአዊ ግደያ አምርሬ አወግዛለሁ።
ፍትህ ለሟች ቤተሰብ እንዲሰጥ እጮሀለሁ።
ጨረስኩ!
ልያ ፋንታ

The post የዘር መቧደንን ትግል፣ ፍርድ በመገምደል አንታገል! (ልያ ፋንታ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ወደድንም ጠላንም ከፖለቲካው ዉጭ ልንሆን አንችልም #ግርማ_ካሳ

$
0
0
“ፖለቲከኛ” አይደለሁም። በሞያዬ ኢንጂነር/ፊዚሲስት ነኝ። ግን አንድ ነገር እረዳለሁ። ፖለቲከኞች ባንሆንም ፖለቲካው በአዎንታዊ ሆነ በአሉታዊ መልኩ ይነካናል። ፖለቲካው ከተበላሸ አገር ትጠፋለች። ሊቢያ፣ ሲሪያ፣ ሶማሊያ፣ የመን ዉስጥ እያየን ያለነው እልቂት የፖለቲካው ብልሹነት ውጤት ነው። በአገራችን “አማራ ናችሁ” ተብለው ወይንም የሚኖሩባት ቦታ ለልማት ይፈለጋል በሚል ምንም ከፖለቲካው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ብዙዎች ተፈናቅለዋል። በባድመ ጦርነት ከ120 ሺህ ወጣቶች የሞቱት አስመራና አዲስ አበባ በነበረው የፖለቲካ ብልሹነት ምክንያት ነው። የኑሮ ዉድነቱ፣ የብር የመግዛት አቅም ማሽቆልቆሉ፣ ለሁሉም ነገር ጉቦ መጠየቁ፣ ግፍ ሲሰራ አቤት የሚባልበት አካል አለመኖሩ፣ ዳኞች አመዛዝነው ፍርድ ከመስጠት ይልቅ ከሌላ አካል የተሰጣቸውን መመሪያ የሚያነቡ መሆናቸው፣ አቃቤ ሕጎች ምስክሮችን እያስጠኑ ዜጎችን በዉሸት እየከሰሱ ማሰራቸው…… ሁሉም ምንጫቸው የፖለቲካው መበላሸት ነው። ፖለቲካው ከተበላሻ ፍትህ አይኖርም። ፍትህ ከሌለ መረጋጋትና ሰላም አይኖርም። ሰላምና መረጋጋት ከሌለ እድገትና ልማት አይኖርም። ሁሉም ነገር የተያያዘ ነው።

ለዚህ ነው ፖለቲካ ሱሳችን ሆኖ ሳይሆን፣ የፖለቲካው መበላሸት የችግራችን ዋና ምንጭ በመሆኑ፣ ፖለቲካው እንዲስተካከል ለማድረግ የምንጽፈዉና የምንጦምረው።
የአገራችን ፖለቲካ በገዢው ፓርቲ ዘንድ ይሁን በተቃዋሚዎች ዘንድ የተመሰረተው ጤናማ በሆነ መሰረት ላይ አይደለም። ኢሕአዴግ ከስህተቶቹ መማር ያልቻለ፣ ግትርና ዘረኛ ፖለቲካን የሚያራምድ ነው። አገሪቷን በዘር ሽንሽኖ በሰላም ሲኖሩ በነበሩ ማህበረሰቦች ዘንድ ቁርሾና ጠብ እንዲያድግ እያደረገ ነው። ሁለት ምሳሌ ልጥቀስ። በሸዋ፣ ኦሮሞ፣ አማራው፣ ጉራጌው…በሰላም ነበር የሚኖረው። ተዋልዶ፣ ተዛምዶ። አሁን ግን ሸዋ በአክራሪ ኦሮሞዎች ስር ወድቆ፣ አብዛኛው ሸዋ ኦሮሚያ የሚባል በታሪክ ያልነበረ ክልል ዉስጥ ተጠቃሎ፣ ኦሮሚያ ደግሞ የኦሮሞዎች ብቻ ነው ተብሎ፣ የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ ሆኖ፣ ሌሎች እንደ ዉጭ አገር ዜጋ እየታዩ ከፍተኛ የዘር መድሎ፣ በአገራቸው እየተፈጸመባቸው ነው። ሁሉም እኩል የሆኑበትን አሰራርና ክልል ከማስቀመጥ አንዱን የመሬት ባለቤት ሌላውን መጤ ኦድርጎ በመውሰድ አላስፈላጊና ኋላ ቀር የዘር ንትርቅ ዉስጥ እንድነገባ ተደርገናል።

በወልቃይት ጠገዴ ለዘመናት ሰዉ ትግሬ፣ አማራ ሳይባባል፣ በፍቅር፣ በሰላም ተዋልዶ ነበር የሚኖረው። እንደ ትግሬ ወይንም እንደ አማራ ሳይሆን እንደ ወልቃይቴ። ትግሪኛም ፣ አማርኛም እየተናገሩ፣ ሲያሻቸው ሽሬ፣ ሲያሻቸው ጎንደር ሄደው እየነገዱ። አሁን ግን በሕወሃት ዘመን፣ ነዋሪዉን በዘር መነጽር መመልከት ተጀመረ። ወልቃይቶች “ትግሬ ናችሁ” ሲባሉ፣ “ትግሬ አይደለንም፣ አማራ ነን” የሚል መልስ ሰጡ። የትግሬነት ማንነትን በግድ ካልተቀበላችሁ ተብለው ብዙዎች ታሰሩ፣ ተሰደዱ። ፖለቲካው አላስፈላጊ የትግሬነት ማንነትን ለመጫን በመሞከሩም የአማራ ማንነት አቀነቀነ። ነገሮች ከዘር ጋር በተገናኘ ከረሩ።እንግዲህ ይሄ ፖለቲካው ያመጣው ጣጣ ነው።

በአብዛኛው ተቃዋሚ ወገኖች ዘንድም ፖለቲካው የተመሰረተው በጥላቻ ነው። አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ተቃዋሚ የሆኑት ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ብለው አይደለም። ወይም ለስልጣን አሊያም ዘረኛ ከመሆናቸው የተነሳ እንዴት “ትግሬዎች” ይገዙናል ከሚል ነው።

ለምሳሌ ግንቦት ሰባት የተባለውን ቡድን እንመልከት። ይህ ቡድን በአንድ በኩል ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆምኩኝ ነኝ ይላል። ለፍትህ የቆመ ሰው ወይንም ድርጅት ኢፍትሃዊነትን የሚቃወመው እየለየ አይደለም። በማንም ፣ በየትም ቦታ ይፈጸም፣ ኢፍትሃዊነትን መታገልና ማውገዝ አለበት። በአንድ በኩል ኢሕአዴግን እያወገዙ፣ በሌላ በኩል የለየለት በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የተወገዘ፣ ለብዙ ሺህ ኤርትራዉያን ወገኖቻችን እልቂት ምክንያት የሆነ አረመኔ አገዛዝ ስር ሄዶ መለጠፍና ይሄን አገዛዝ ማመስገን ግን ግብዝነት ነው። “ወያኔን እስከጠለልን ድረስ ሰይጣን ልለምን አይሆንም፣ አብረን እንሰራለን” ነው የሚሉት የድርጅቱ አመራሮች። ደርግም እስከጣለለን ትተብ፤ኦ ወያኔ ተደግፎ እንደነበረው ማለት ነው። ይህም ግንቦት ሰባቶችና ጽንፈኛ ተቃዋሚዎች ለፍትህ ቆመናል የሚሉት በፋቸው እንጂ በልባቸው እንዳልሆነ የሚያሣየው። የሚታገሉትም በአገራችን ፍትህ እንዲሰፍን ሳይሆን ወያኔን ለመጣል ብቻ ነው። ጸባቸው ከኢፍትሃዊነት፣ ከግፍ ጋር ሳይሆን ከግለሰቦችና ከድርጅቶች ጋር ነው። ይህ አይነቱም በመርህ ላይ ሳይሆን በጥላቻ ላይ፣ በፍቅር ላይ ሳይሆን በንዴት ላይ፣ በእዉነት ሳይሆን በዉሸትና በማጭበርበር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የተበላሸ ፖለቲካ ነው።

ብዙ ድርጅቶች አሉ በአንድ በኩል ሕወሃትን በዘረኝነት እየከሰሱ እነርሱም በዘር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ። እንደ ሕወሃት እነርሱም መርዛማ የዘር ፕሮፖጋንዳ የሚረጩ። ህወሃቶች “ተጋሩ፣ ተጋሩ” እንደሚሉት እነርሱም “ኦሮሞ፣ ኦሮሞ” ፣ “አማራ ፣ አማር” እያሉ መልኩን ቀየረ እንጂ፣ የሕወሃቶች ጠባብ አስተሣሰብ እየበከላቸው ነው። በዉስጣዊ አሰራራቸው ከኢሕአዴግ ባልተናነሰ እነርሱም አምባገነናዊ አስራራ ነው ያላቸው። አንዳንዶቹማ መሪዎቻቸውን ቀይረውም አያውቁም። መሪዎቻቸው፣ከአገርና ከጥቅም ይልቅ ስልጣናቸወንና የግል ጥቅማቸው የሚያስቀድሙ በመሆናቸው አብረው መስራት እንኳን የተሳናቸው ናቸው። (በተለይም በዉጭ አገር ያሉ)

ወገኖች መሰረታዊ ችግር ነው ያለብን። ዉጫዊ ሳይሆን ዉስጣዊ። እመኑኝ ትልቅ የአስተሳሰብ ተሃድሶ ካላደረግን፣ ከዘር ፖለቲካ ካልወጣን፣ ዜጎችን በዘራቸው ሳይሆን በስራቸውና በምግባራቸው ብቻ መመዘን ካልጀመርን፣ አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆን ሁላችንም እኩል የሆንበት አሰራር ካልፈጠርን፣ ሕግ የበላይ ካልሆነ፣ የሚመሩንን በነጻነት መሾምና መሻር ካልቻልን፣ አሁን ካለንበት የበለጠ ዉድቀት ዉስጥ መውደቃችን አይቀርም። ትግሬ አማራ መባባል ካልቆመ የወልቃይት ችግር አይፈታም። አማራ፣ ኦሮሞ መባባል ካልቆመ የሸዋ/አዲስ አበባ ችግር አይፈታም። ሶምሌ ኦሮሞ መባባል ካልቆመ የሞያሌ፣ የጭናቅሰን..ችግር አይፈታም።

ከዘረኝነት ፣ ከጥላቻ፣ ከቂም በቀል፣ ከቁርሾ፣ ከእልህና ከኋላቀርነት ፖለቲካ ወጥተን፣ ወደ ሰለጠነ የፍቅር፣ የአንድነትና የኢትዮጳዊነት፣ የይቅር መባባልና የመቻቻል ፖለቲካ እንሽጋገር ዘንድ እግዚአብሄር ይርዳን። ልባችንን ለፍቅር፣ አይምሯችንን ለማስተዋል የተከፈተ ያድርግልን !!!!

The post ወደድንም ጠላንም ከፖለቲካው ዉጭ ልንሆን አንችልም #ግርማ_ካሳ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


ህዝባዊዉ ጽንስ እስኪወለድ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋዉ ስራህን ዝም ብለህ ከዉን – ሸንቁጥ አየለ

$
0
0
ሙሉቀን ተስፋው

ሙሉቀን ተስፋው

ሙሉቀን ተስፋዉ የህዝብ ልጅ ነዉ::ጎበዝ ወጣት ነዉ::ወደፊት ደግሞ እየበሰለ ሲመጣ በርካታ ስራን ለኢትዮጵያ ህዝብ የመስራት አቅም ያለዉ ወጣት ነዉ::
አሁን ባለዉ የወጣትነት ዘመኑ ሶስት መጽሃፍን ማበርከት የቻለ እና ብዙ ግፎችን ያጋለጠ ትንታግ ጋዜጠኛ ነዉ::በተለይም የተደበቀዉን የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ስራ ቁልጭ አድርጎ በመረጃ እና በድፍረት ተንትኖ በመጽሀፍ አዘጋጅቶ ለህዝብ ያቀረብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነዉ::

ኢትዮጵያ ዉስጥ ጋዜጠኛ በነበረበት ወቅት ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ አንገብጋቢ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ የሚዘግብ ብቻ ሳይሆን እቦታዉ ድረስ እየሄደ: ልዩ ልዩ ፖለቲከኞችን እየጋበዘ እና እያከራከረ በትጋት ያለወገንተኝነት ሲሰራ የነበረ ደፋር ጋዜጠኛ ነዉ:: ቀለም ቀንድ ላይ በሀላፊነት በሚሰራበትም ጊዜ በግሉ መንግስታዊ ድርጅት ዉስጥ ይሰራ ነበርር:: ሆኖም ከዚህ ዋና ስራዉ በተጨማሪ ግን የቀለም ቀንድ ጋዜጣ አንድም ደሞዝ ሳይከፍለዉ ጋዜጣዉን በታላቅ ሀላፊነት ሲያገለግል የነበረዉ ለህዝብ ካለዉ ፍቅር እንጅ ጥቅም ፈልጎ አይደለም::

በሂደትም ጠቅልሎ ወደ ጋዘጠኝነት ከገባ ብኋላ ማንም ጋዜጠኛ ደፍሮ ሊያከናዉነዉ የማይችለዉን ስራ በታልቅ ወኔ ሰርቷል:: ይሄን ጋዜጠኛ ወያኔ ብዙ ቢያንገላታዉም በመጨረሻ እንደ ሌሎች ጋዜጠኞች ወደ ግዞት ሳይወረዉረዉ እግዚአብሄር አድኖት ወደ ዉጭ አገር መዉጣት ችሏል:: ሆኖም ሙሉቀን አሁንም ህዝባዊ ስራዉን ቀጥሏል::

እናም ሙሉቀን ሊበረታታ እና ሊመሰገን ይገባዋል :: ሃያ አምስት አመታት ሙሉ አንድ መጽሃፍ እንኳን ሳይጻፍበት የከረመዉን የአማራ ህዝብ ላይ የተከናወነዉን የዘር ማጥፋት ስራ እጅግ በታላቅ ድፍረት : በቁርጠኝነት እና በትጋት ማጋለጥ የቻለ አንድም ጋዜጠኛ : ወይም አክቲቪስት ወይም ፖለቲከኛ እስካሁን አላዬንም::

ይሄን ወጣት የሚጠሉት ሶስት ሀይሎች ናቸዉ::የኢትዮጵያን ህዝብ መበደል የሚዘግብ በተለይም አማራዉ በደሉን የሚዘግብለት ጋዜጠኛ እና ድምጽ ሊሆነዉ የሚችል ታዋቂ ሰዉ ወጣለት ብለዉ ስጋት የያዛቸዉ የጸረ አማራ ስነ ልቦና የታጠቁ ሰዎች ግንባር ቀደሞቹ የሙሉቀን ተስፋዉ ስም አጠልሺዎች ናቸዉ:: የወያኔ ቡችሎችም ህዝብ ማወናበድ ስራቸዉ ስለሆነ መልካሙን ሰዉ ሀሰተኛ: ሀሰተኛዉን መልካም እያደረጉ ያቀርባሉ:: ሌሎች ደግሞ በተወናበደ መረጃ ሙሉቀን ላይ የግል ጥላቻ ያላቸዉ ሀይሎች በሀሰት ሙሉቀንን ይከሳሉ::ያብጠለጥላሉ:: ወይም ሙሉቀን የሰራዉን ታላላቅ ስራ ከማዬት የተሳሳተዉን ጥቃቅን ነገር እየመዘዙ የሙሉቀንን ሰብዕና ለመግደል ይተጋሉ::

መሉቀን ተስፋዉ የሰራዉን አንድ መቶኛ እንኳን ስራ ያልሰሩ ተቃዋሚ ነን ባይ ከሳሾቹን ሳይ አፍርላቸዋለሁ::ግን የእያንዳንዱን ድብቅ እና ግልጽ አላማ በደንብ በመከታተል ለህዝብ ማጋለጥ ይገባል:: ወያኔን ለማስወገድ በዚህ ወይም በዚያ መልክ የሚሰሩ ህዝባዊ ጀግኖችን የምታጠቁ እቡያን የማታዉቁት ስዉር ህዝባዊ ጣት እንዳይወጋችሁ ጥንቃቄ አድርጉ::

ይሄ ልጅ ማንንም ሲያንቋሽሽ: ወይም በማንም ላይ ድንጋይ ሲወረዉር አልታዬም::እርግጥ ነዉ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ስለ አማራ ህዝብ መገፋት: መገደል: መሰደድ እና ዘር መጥፋት ተግቶ እየጮህ እና እየዘገበ ያለ ጋዜጠኛ ነዉ::

ሙሉቀን በርታ::ሁሉም ነገር በሂደት ግልጽ መሆኑ አይቀርም:: ወሽ ከሆነ ይጠፋል: ሽል ከሆነ ይጋፍል ነዉና ህዝባዊዉ ጽንስ እስኪወለድ ስራህን ጠንክረህ ስራ::

ኢትዮጵያ እጅግ ዉስብስብ ሀገር ነዉ::ጠላቶቹም ዉስብስብ: ፖለቲካዉም ዉስብስብ: ህዝቡ ጠላትና ወዳጁን ለመለዬት በብዙ ሀሰተኛ ቡድኖች በየቀኑ ይወናበዳል::በፖለቲካ መድረኩ ላይ ከነሱ በቀር ሌላ ሰዉ ጭፈራ እንዲያቀርብ የማይፈልጉ እኩያንን እና እቡያን ብዙ ናቸዉ::ስለሚታረደዉ እና ስለሚገፋዉ ህዝብ ግድ አይላቸዉም::በያዙት ጋዜጠኝነት ወይም በተቆጣጠሩት ሚዲያ ስለሚታረደዉ ህዝብ እና የዘር ማጥፋት ስለሚደረግበት ህዝብ መዘገብ አይፈልጉም::በተቃዋሚ ፖለቲከኝነት ተሰልፈዉ ለህዝብ ነጻት እና ፍትህ እንታገላለን ቢሉም ሆዳቸዉ ዉስጥ ግን ጥቁር ጥላቻ እና ሙት የጸረ ህዝብ ተልዕኮ አለ::እናም ህዝባዊ የመሰላቸዉን ሁሉ አንቀዉ ለመግደል ይተጋሉ::

የፍትህ ታጋይ ነን ይላሉ::ግን ሀሰተኛ ናቸዉ:: ፍትህ ምን እንደሆነ አያዉቁም::እዉነትን በመደበቅ ፍትህ ያደረጉ ይመስላቸዋል::ህዝብ ሲታረድ እና ሲገፋ ስለታረደዉ ህዝብ እና ስለተገፋዉ ህዝብ ከመዘገብ እና ከመጮህ ይልቅ ቅራንቅንቦ ምክንያት እየደረደሩ እዉነቱ እንዳይወጣ ይተጋሉ::እዉነትን በእግራቸዉ ይረግጣሉ::ግን ህዝባዊ ነን ይላሉ::

ወያኔ አማራ ህዝብ ላይ ሀያ ስድስት አመታት የዘር ማጥፋት ስራዉን አንዴ በሰሜን አንዴ በደቡብ አንዴ በምስራቅ አንዴም በምዕራብ እያደረገ የአማራን ህዝብ ከሁሉ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ጋር እያቃረነ አሁንም ቀጥሏል::ይሄን የሚያከናዉነዉ ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነዉ:: የአማራ ህዝብ ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነዉ:: የአማራ ህዝብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የሚወድ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ጋር የተዋሃደም ነዉ:: የኢትዮጵያ ህዝብም ሁሉ ሰዉ ወዳድ እና ደግ ህዝብ እንጅ የማንም ጥላቻ የለዉም::የህዝባችን አንድ እና አንድ ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነዉ::

ሆኖም ተቃዋሚ ነን : ጋዜጠኛ ነን : አክቲቪስት ነን የሚሉት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያከናዉንበት የዘር ማጥፋት ስራ አይዘገብ እያሉ በሚታረደዉ ህዝብ ላይ ሌላ እርድ ያከናዉናሉ:: እናም አሁን የሙሉቀን ወንጀል ስለ አማራ ህዝብ መዘገቡ ብቻ ነዉ::የሙሉቀን ወንጀል እዉነትን ማጋለጡ ብቻ ነዉ::

ሙሉቀን አይዞህ በርታ ! ወሽ ከሆነ ይጠፋል: ሽል ከሆነ ይጋፍል ነዉና ህዝባዊዉ ጽንስ እስኪወለድ ስራህን ጠንክረህ ስራ::

The post ህዝባዊዉ ጽንስ እስኪወለድ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋዉ ስራህን ዝም ብለህ ከዉን – ሸንቁጥ አየለ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አገሬ ኢትዮጵያ ለምትሉ ኢትዮጵያውያን ጠቃሚ መረጃ – ሰርጸ ደስታ

$
0
0

ቴክኖሎጂ ያመጣው የመረጃ ልውውጥ በጎነቱ እንዳለ ሆኖ በዛው ልክ ግን በተዛባ መረጃ ብዙ ሰው ከትክክለኛ አካሄድ እየወጣ ነው፡፡ በተለይ ልዩ ሴራን የሚያራምዱ ሰዎችም ሆኑ ቡድኖች ይህ የዘመኑ ቴክኖሎጂ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል፡፡ በእኛ በኢትዮጵያውያን ላይ እየሆነ ያለውን ሴራ ብዙ ወሬ በማዛመት ልከልሉን እየሞከሩ ያሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለሚያስተውል ግን ይህ እነሱ ለውዥንብር የተጠቀሙበትን መረጃ በመተንተን የእነዚህን ግለሰቦችና ቡድኖች ማንነት መመንዘር ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያውያን በብዙ ነገር እየተሸወዱ ነው፡፡ በተለይ ትንሽ ቀለም ቆጠርኩ የሚለው ወጣት እንደ ቦይ ውሃ የሚነዳ ሆኗል፡፡ በመሆኑም ሴረኞቹ ይህን የሕዝብ ክፍል እንደመሳሪያ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ በእርግጥ ይህ የሕብረተሰብ ክፍል የሰጡትን የሚቀበል ስሜታዊነት የሚንጸባረቅበት መሆኑ ነው፡፡ ከ60ዎቹ አብዮት ጀምሮ ኢትዮጵያ በውዥንብር የኖረቸው ቀስ በቀስም አሁን ለደረሰችበት ውድቀት የተጋለጠቸው በዚህ የሕብረተሰብ ክፍል መሰረጣዊ መረጃ አለማግኘት ነው፡፡ ብዙ ምሁር ተብለው ለዘመናት በሕዝብ ዘንድ እንደ ትልቅ ሲታዩ የነበሩ ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ጥፋት ጀርባ እንደነበሩና ትውልዱንም ለማምከን ወሳኝ ሚና እንደተጫወቱ አሁንም እየተጫወቱ እንደሆነ እናያለን፡፡ አሁን አሁን ከቀድሞዎቹ ወጣቶች በተሻለ ነገሮችን በጥርጣሬ ማየት የሚችሉ ወጣቶች እየወጡ ይመስላል፡፡ ግን እነሱም ቢሆኑ በሌላ ውዥንበር ግራ ይጋባሉ፡፡ የ60ዎቹ ትውልድ የዛሬዎቹ ጎልማሶችና አዛውንቶች እድሜ ለንስሀ ማለት ፈጽሞ እንዳይችሉ በሴራ ተጠምቀዋል፡፡

ሁሉም ሰው ያስተውል አገርና ሕዝብ እየጠፋ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እየተመሩ ነው፡፡ በዘርና በሀይማኖት፡፡ ኢትዮጵያ የብዙ ሕዝቦች መኖሪያ መሆኗ ጠቀማት እንጂ እንደ ሩዋንዳ የሁለት ወይም የሶስት ብትሆን እስካሁንም ብዙ አደጋ በሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም ሰላም መኖር የቻሉት በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር እንጂ ከኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር ለአንድ ሳምንት ቢለዩ  እጅግ የከፋ አደጋ አለባቸው፡፡ ትንንሾቹ አሁን ባለው በሕዝቦች መካከል እርስ በእርስ መጠላላት ከኢትዮጵያ ውጭ የዘር መጥፋት አደጋ ሁሉ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ትልልቆቹም ቢሆኑ መጠፋፋቱ ከውስጣቸው የሚጀምር ነው፡፡ ለምሳሌ ትልቅ የሚባለውን የኦሮሞን ሕዝብ እንውሰድ፡፡ ኦሮሞ በሚል በአንድ የታጨቀው ይህ ትልቅ ማህበረሰብ ለብቻ ወጥቶ እንደ አገር ልኑር ቢል ከምናውቃት ሱማሌ የከፋ መጠፋፋት ይገጥመዋል፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ ኢትዮጵያን የማዳን ኃላፊነት ለራሴ ሊሉት የሚገባ እንጂ በልምምጥ እትዮጵያዊ እንዲሆን በማባበል አደለም፡፡ ሁሉም ራሱን ለማዳን ከፈለገ ኢትዮጵያን ማኖር ግድ ይለዋል፡፡ ለእኔ ጡሩ ምሳሌዬ ስለሆነ ነው ደጋግሜ የማነሳው፡፡ ኦሮሚያ የሚባል አገር ተመስርቶ ዛሬ የኦሮሞን ነጻነት እንመራለን የሚሉ ብዙ ቡድኖች ወደ ስልጣን ቢመጡ የመጀመሪያ ሥራቸው በጉልበት የቻሉትን ሁሉ ሌላውን ሕዝብ ማጥፋት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ግን አጸፋዊው ሌሎች ራስን ለመከላከል በሚገደዱበት ሁኔታ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አንድ ሆነው መዝመታቸው አይቀርም፡፡ ያኔ እንኳንስ ትልልቆቹ የሱማሌ ወይም የሲዳማ ሕዝብ ይቅርና ትንንሾቹ ሌሎች የደቡብ ክልል ሕዝቦች በአንድነት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ይነሳሉ፡፡ ይህ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነውና፡፡ ከውስጥ ደግሞ አንኳንስ ወለጋና ባሌ የአንድ አባት ልጆች ነን ብለው ዘራቸውን 20ና 30 ትውልድ ጠርተው ዋናቸውን የሚናገሩት ጉጂና ቦረናም አሁን አሁን እንደጠላት መተያያት የተለመደ ነው፡፡ ጦርነትም ተዋግተዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በዘር ፖለቲካ ነው፡፡

ከዘር ውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕቡዕ እየተካሄደ ያለው ሀይማኖታዊ ሴራ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሶስት ትልልቅ ሀይማኖቶች መሠረት በሚባል ሁኔታ ታሪክ ያላት አገር ናት፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ከአገሪቱ ታሪክ ጋር የጠበቀ ትስስር አለው ብቻም ሳይሆን ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተጣመረ በመሆኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያሴሩ ብዙ ሴረኞች ይህን የእምነት መሠረት ኢላማ ማድረግን እን ዋና ስልት እየመሩት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ እምነት አላቀቁ ማለት እውነታው ግልጽ ነው፡፡ ስለኢትሐዮጵያ የማያስብ ሰውኛ ፍጡርን ማብዛት ነው፡፡ እውነታውን እንጋፈጠውና ኢትዮጵያዊነት በአብዛኞቹ የተቀሩት እምነቶች ብዙም ቦታ የለወም፡፡ የእምነት መሪዎቻቸውም ከኢትዮጵያ ይልቅ የእነሱ እምነት መሠረት ነው የሚሉትን አለም በማወደስ ተከታዮቻቸውን የሌሎች አገር ናፋቂ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ የታሪክ እውነታው ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የእምነቱ ተከታዮች ቦታ ያገኙባትና እምነታቸውን ያስፋፉባት አገር እንደሆነች ቢነግረንም ብዙ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የአረብ አገራት ከራሱ አገር ይበልጡበታል፡፡ አረብኛም ከተወለደበት የራሱ ቋንቋ ሳይቀር ይናፍቀዋል፡፡  አረቦች አገር ግን ቢሄድ ባሪያ እንደሚሆን አያስተውልም፡፡ ይህ አይነት አስተሳሰብ ደግሞ በሙስሊም ኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የከፋ ነው፡፡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችም የምዕራባውያን አለም ናፋቂዎች ናቸው፡፡ ምዐራባወያን እንደ ባሪያ እንሚያስቧቸው አያስተውሉም፡፡  የኦሪት እምነት ተከታዮች በአሁኑ ወቅት ምን ያህል እንዳሉ አላውቅም፡፡ እንዚህ ግን ከሁሉም በፊት አገራቸው እንደሆነች ያውቁታል፡፡ እርግጥም እንሱ የመጀመሪያዎቹ ናቸውና፡፡ ለሙሰሊም ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊ መሠረት ያለው የእምነት ፍልስፍና በማሳደግ አለምን እያመሰ ያለውን ሰይጣናዊውን አክራሪነትን ለማክሸፍና አረቦችንም በበላይነት በእምነቱ ለመምራት እድሉ ነበራቸው፡፡ ይህን ለዘመናት አላደረጉትም፣ ሁሌም የአረብ ጥገኛ በመሆን ዛሬም የእነሱን ሰይጣናዊ ፍልስፍና ለማስተናገድ የተጋለጡ ሆነዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹን የእምነቱን መሪዎች በእንግድነት ያስተናገደው ኢትዮጵያዊ ንጉስ ፍልስፍና ነበር ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ሊከተሉ የሚገባው፡፡ ይህ ነበር የሰው ልጆች ፍቂርና ፍትሀዊ ደግንነት መሠረት፡፡ ቀጥሎም ቢላል በሙስሊሙ ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ ያለው ሌላው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ዛሬ ቢላልን ሥሙን እንጂ የማንነት መሠረቱን ኢትዮጵያዊነቱን ለማንጸባረቅ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምን ያህል አንደሚያጎሉት አላውቅም፡፡

በክርስትናውም ለእኛ ኢትዮጵያውያን የሚያኮራ ፍልስፍናዎች ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤትከርስቲያን እንደዛሬው ሳትሆን በርካታ ቅዱሳንና ፋላስፋ አባቶችና እናቶች ተነስተውባት ዛሬ የጠፋውን አለም ምስክር እንዲሆንበት ታላላቅ ከእምነቱና ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር የተገኙ መረጃዎችን አከማችተውባት አልፈዋል፡፡ ዛሬ ትልልቅ የእምነት ፍልስፍና ምሁራንን ውይይት ቢታይ ከክርስትናው በተያያዘ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በልዩ መልኩ ነው የምትታየው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የክርስትናውም ብቻ ሳይሆን የኦሪቱንም ታሪክ በሰነድም በተግባሪም እስካሁን ያቆየች መሆኗ አፍሪካዊ መሆኗና እንዴት የጥልቅ ሚስጢራት መረጃዎችን ልታቆይ ቻለች የሚለው ለብዙዎቹ ምሁራን ግራ ቢያጋባቸውም እውነታውን ግን ሳይወዱ በግዳቸው እንዲያምኑትና ክርስትናንም ኦሪትንም ወደኋላ ሄደው ከመነሻው እንዴት እንደነበር ለማመሳከር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መረጃዎች ዋና ዋቢዎች ሆነዋል፡፡  ከነዚህ አንዱ በዘመኑ የክርስትናው አለም እያነጋገረ ያለው የሄኖክ መጻፍ፣ ኩፋሌ የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=zBCYD_eQjjs ምሁራኑን እያነጋገረ ያለው 66 መጻፍ ብቻ ያዘ የተባለው መጻፈ ቅዱስ ብዙ ወሳኝ መረጃዎችን በማስቀረት የተጠናቀረ ነው የሚል ነው፡፡ ከ66ቱ ውጭ በኢትዮጵትዮጵያ(ኤርትራንም ማለቴ መሆኑን ይታወቅ) ኦርቶዶክስ መጻፈቅዱስ የተካተቱት ሌሎች መጻኅፍት የበለጠ ስለክርስትናው መረጃ የሚሰጡ መሆናቸውም ብቻ ሳይሆን ክርስትናንም እንደፈለጉ ለመዘወር በማያመች ሁኔታ አመክንዮዋዊ የሚያደርጉት ፍልስፍናዎች ጭምር ያሉበት ነው፡፡ ለምሳሌ ያለ መጻፈ ኩፋሌ አምስቱ የኦሪት መጻህፍት ሙሉ አደሉም፡፡ ያለ መጻፈ ሄኖክ ስለክርስቶስ ማንነት መረዳት ግልጽ አይሆንም፡፡ ከዛም በላይ ለዘመናዊው የኢቮሉሽን ፍልስፍና መሰረተቢስነትን መጻፈሄኖክ ወሳኝ መረጃ ነው፡፡ መጻፉን ከኢትዮጵያ መገኘቱ ለማመን ብዙዎችን ቢያስቸግራቸውም፣ የዚሁ መጻፍ የተወሰነው ክፍል በኩምራን ዋሻዎች በ1959 መገኘቱና በግልጽ በይሁዳ መልዕክትም ከዚህ መጻፍ ምዕራፍ 9 ቃል በቃል መፃፉ ብዙ የተጠራጠሩትን ሳይወዱ እንዲያምኑ ሆነዋል፡፡

አሁን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ትውልድ በተለይ ተማርኩ የሚለው በዚህች ቤተክርስቲያን ላይ ጦርነት የከፈተ ይመስላል፡፡ እውነታው ኦርቶዶክስ መሆንና አለመሆን አልሆንም፡፡ ኦርቶዶክስም ነኝ የሚለው ለሆዱ ሌላም ነኝ የሚለው ለተሰማራበት ሴራ የቤተክርስቲያኗ መሠረታዊ ፍልስፍናዎች መውደምን ይፈልጉታል፡፡ ዛሬ ላይ ስለእምነት እዋቂ ነን እያሉ በየከተማው ሕዝብን የሚያምሱ ብዙዎችን ለታዘበ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ሲጀምር አብዛኞቹ ከእምነት ጋር የተገናኘ መስመርን የመረጡበት እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን በሌላ ቦታ ስለማይሳካላቸውና ችሎታ ስለሌላቸው እምነትን እንደ መኖሪያ ለመጠቀም ነው፡፡ ይህ አሳዛኙ የዘመናችን ክስተት ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ እየሆነ ያለውን ላስተዋለ ግብግቡ የጥቅም ፍጥጫ ነው፡፡ እምነቱን ካልን መናፍቃን ከተባሉትም በተባሉትም ሆነ እኔ ነኝ የቤተክርስቲያኒቱ አሌኝታ የሚሉት ምንም ልዩነት የላቸውም ባይ ነኝ፡፡ ሁለቱም አያምኑምና፡፡ የሚያምኑት የሚያወሩት አደሉም፡፡

ሌላው ለዘመናት ምሁር ናቸው እየተባለ ሲካቡ የኖሩ ግለሰቦች ጉዳይ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸው ድብቅ ተልዕኮ ነው፡፡ በቅርቡ ደቂቀ እስጢፋኖስ የተባለ የኦርቶዶክስ እምነትን የሚቃወም የካቶሊኮችን በመቃወም የተነሳውን ማርቲን ሉተርን ቀድሞ የተነሳ ኢትዮጵያዊ የእምነት ቡድን እንደነበር እንደ ትልቅ ችሎታ ምሁር ተብዬውና በኢትዮጵያዊ እሴቶች ውስጥ ተደብቀው ለዘመናት ሲያሴሩ የኖሩትን ፕሮፌሰር መስፍንን በአንድ ሰሞኑን ይለቀቃል ተብሎ እየተዋወቀ ያለ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ እምነትን የሚኮንን ፊልም ማስተወቂያ ላይ አይቼ ስለሰውዬው ቀድሞውንም የነበረኝን ጥርጣሬ የበለጠ አጉልቶታል፡፡ ለእኔ መስፍን ማለት በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ጥሮ ያልሆነ ብዬ ባልፈው ይሻለኛል እንጂ ዘለቅ ብዬ ከተነተንኩት የእሳቸውን ሀጥያት እኔ መሸከም ይሆንብኛል፡፡ እውነታው ከብዙ ሰው በተሻለ ማረቲን ሉተር እንዴት እንደተቃወመ በሂደትም ምን እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖም ማርቲን ሉተር ከካቶሊኮች ሸሽቶ የተደበቀበትንና መጻፈቅዱስን ወደ ጀርመንኛ የተረጎመበትን ቦታ በቱቢንገን የምትገኘውን አይዘናህንም ማየት ችያለሁ፡፡ እሱ የጻፈውንም የመጀመሪያውን መጻፈ ቅዱስ፡፡ ሰውዬው መሠረታዊ መነሻው እስነትነት ያለው ቢሆንም በኋላ በተከተለው ፍልስፍና ሳቢያ በሰው ሳይን በመንፈስ እጅግ ተጠቅቷል፡፡ እና የተከተለው ፍልስፍና ለብዙዎች የካቶሊኮችን አገዛዝ ለመሸሽ በሚል ቢከተሉትም ወድ ትክክለኛ ፍልስፍና አልነበረም፡፡ ዛሬ ላለው የመላ አውሮፓ ሀይማኖት ማጣት መሠረት ሆነ እንጂ፡፡ ሌላው እንደ መስፍን  ለእኔ የማይገቡኝ ብዙዎች እንደ ታላቅ ምሁርና ኢትዮጵያዊ የሚያስቧቸው ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ናቸው፡፡ እንደ እውነቱ እነዚህ ምሁራን ኢትዮጵያዊነትን ሲነግዱበትና ሲያሴሩበት የኖሩ ሆኖ ነው የተሰማኝ፡፡ የኦርቶዶክስ እምነትንም እንዲሁ፡፡ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን ጌታቸው ኃይሌን ሲያደንቁ እሰማለሁ፡፡ እኔን ግን አልዋጥልህ ከሚሉኝ አንዱ ቢሆኑም፡፡

ሌሎችም ለቤተክርስቲያኗ ቅርብ ናቸው እየተባሉ ሲነግዱ የኖሩ አሉ፡፡ አንዳንዶቹም ጊዜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል፡፡ ከእነዚህ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነትም፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነትም ፍልስፍና ትልቅ ቦታ ሰጥተው የማያቸው ኦሪታዊው ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ናቸው፡፡ ኤፍሬም ኢትዮጵያዊነትን የሚመሰክሩለት ምሁር ብቻም እየኖሩት የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ለብዙዎች ኤፍሬም ከሌሎች ይልቅ አይታመኑም፡፡ እንዲህ ነው የሆነው፡፡ ኤፍሬምን ለብዙዎች እንዳይታመኑ ያደረጋቸው ደግሞ በኢትዮጵያዊ ቅን እሳቤ በኢትዮጵያዊነት ሥርዓትና ወግ የአገሬን ልጆች እሸመግላለሁ ብለው ተሰልፈውበት የነበረው ጥረታቸው ነው፡፡ በእርግጥም ጀምረውት ስኬትም አስመዝግበው ነበር፡፡ ከሟቹ ጠ/ሚኒስቴር መለስ ጋር ያላቸው ወዳጅነትም በሌሎች እንደ ጠላት እንዲታዩ ነው ያደረጋቸው፡፡ እውነታው ኤፍሬም ከመለስ ጋር የነበራቸውን ወዳጅነት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተጠቀሙበት እንጂ ከዚህ ለግላቸው አንዳች አልተጠቀሙም፡፡ መለስን ወዳጅ ማድረጋቸውም ስህተት አልነበረም፡፡

መለስ በብዙ ነገሮች ክፉ ቢባልም አሁን ከቀሩት የቡድናቸው አባላት በብዙ እጥፍ የተሻሉ እንደሆነ አናውቃለን፡፡ የመለስ ልቃቂት የሚል መጻፋቸውን ልዩ ሚስጢር እንዳዘለ በየቀኑ የሚወተውቱን የሚያደነቁሩን የኢሳቱ ኤርምያስ መለስን አውቃቸዋለሁ ያሉትን ያህል ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ከዚያም በላይ፡፡ የመለስ ሞት ለአንዳንዶች ጮቤ ቢያስረግጥ በእርግጥም የኢትዮጵያን ሕዝብ አሳዝኗል፡፡ በእርግጥም ለኢትዮጵያ ጥሩ አደጋ እንደነበረው እናውቅ ነበር፡፡ መለስ ጥሩ ናቸው እያልኩ ሳይሆን በብዙ እጥፍ ግን የተሻሉ ኢትዮጵያዊነትም ቡድናቸው ውስጥ ከነበሩ ሁሉ የነበራቸው እንደነበሩ እናስተውል ነበር፡፡ በመለስ ቦታ አንጃ ተብለው የተገለሉት እነ ሲዬና ዛሬ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ የሚያላዝኑብን እነ ጻድቃን ሆነው ቢሆን የፌደራል ሥራ ቋንቋም ትግርኛ ይሆን ነበር፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን በፕትርክና የመሩት አቡነ ጳውሎስ ቅን ሰው እንደነበሩ እናስተውላለን፡፡ በጊዜያቸውም በብዙ ወሬዎችና ድርጊቶች ተፈትነዋል፡፡  ከመለስ ሞት በኋላ የነበረውን ውንብድና ላስተዋለ የመለስን ችሎታና ሥራ ያደንቃልነ፡፡ ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ ወደለየለት ውንብድና እንደገባች እናውቃለን፡፡ በእኛ መረጃ 85 በመቶ የመሬት ዝርፊያዎች የተፈጸሙት ከመለስ ሞት በኋላ በአለው በዚህች አጭር ጊዜ ነው፡፡ መለስ ብዙ ስህተት ከሰሩ መሪዎች እንደሆነ አልጠፋኝም ግን መለስ እንደሰው በስሜትም በጫናም የሰሯቸውን ስህተቶች ብናነሳው ሰውዬው ምን ይህል የተሻሉ ሰው እንደነበሩ እናውቃለን፡፡ ሌላው ቀርቶ ትልልቅ አመራር ላይ ያሉ ጠንካራ ኢትዮጵያውያን እየተነሱ ለዝርፊያ የሚያመቹ ሰዎች በይፋ ሲተኩ በአይናችን አይተናል፡፡ ለዚህ የመላኩ ፋንታው ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ወደ ወህኒ መጣል አንዱ ማሳያ ነው፡፡ መላኩ መለስ እንደሞቱ ትግሬ ወያኔዎች ትልቅ ፈተና ሆነውባቸው ነበር፡፡ ይህንንም ሰው ያለ መስሏቸው ለባዕዴን አመራሮች ቢያነሱላቸው ጭራሽ መላኩን አሳልፈው ለወያኔዎች ሰጥተዋቸዋል፡፡ መላኩ በእርግጥም በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ትልቅ እምርታ ያመጡ መሪ ነበሩ፡፡ መለስ በሕይወት ቢኖሩ መላኩ ለሌላ ለተሻለ ስልጣን የሚታጩ ነበሩ፡፡ በእርግጥም በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ መለስ ሰው ፈልገው ነበር፡፡ የሚሰራላቸው ግን የማይጋፋቸው፡፡ መለስ በሕዝብም ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እያተረፉ የመጡበትን በተግባር የተገለጠ ስኬትን እያመጡ ነበር፡፡ በቆይታም የአጠፉትን ኢትዮጵያዊነት እያንሰራሩት ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ነው መለስ ሞተው ዛሬ እየሆነ ላለው ውንብድና አገር የተጋለጠቸው፡፡ አስተውሉ ከመለስ በኋላ ከፍተኛ የሆነ የዘርኝነት ሴራዎችም ተስፋፍተዋል፡፡ የአኖሌ ሀውልት የተሰራው ከመለስ ሞት በኋላ ነበር፡፡ ከመለስ ሞት በኋላ እያጎረሷቸው አልጠግብ ያሉ ትግሬ ወያኔዎች ሜዳ ወጡ አለ የተባለ ነገር ሁሉ ማጋበስ ጀመሩ፡፡

ከመለስ ጋር ብዙ ወደ ኢትዮጵያዊ ፍለስፍና የሚያመራና ለሕዝብ የሚጠቅም ሀሳብ ሊያጋሩ የነበሩትም ኢትዮጵያዊው የመለስ ወዳጅ ኤፍሬም በእነ ፓስተር ዳንኤል ከአሁን በኋላ ጊዜው የእኛ ነውና አታስፈልገንም ተባሉ፡፡ ኤፍሬምን በማውገዝ የተደናበረው ዲያስፖራ ረዳቸው፡፡ ዳንኤል ጴንጤውን ጠ/ሚኒስቴር ከእኔ በቀር ሊያናግረው የሚችል የለም እሱን ማናገር ከተፈለገ እኔን ክፈሉኝና ሁሉንም አስፈጽማለኁ አሉ፡፡ ጴንጤው ጠ/ሚኒስቴር ጥላቻ፣ የበታችነት ስሜት፣ ተፈጥሯዊና አስተዳደጋዊ ግድፈቶቻቸው በአንድ ላይ ተደምረው አገር የተዋረደችበት ሰው ሆኖ፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ሊያጠፏት በሚደነፉ ወንበዴዎች ይሁንታ እየተመራች ነው፡፡ የወየኔ የፌስቡክ አስተያየት ሰጭዎች በሚሰጡት አመራር ነው ነገሮች እየተመሩ ያሉት፡፡ የሙስሊም ጽንፈኞች በሚመሩት የፌስቡክና ሌሎች መገናኛዎች የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ተመርቷል፡፡ ከመለስ ሞት በኋላ ኦሮሚያ የሚባለውን ክልል የመራው የእነሙክታር ቡድን ትዕዛዝ የሚሰጠው በፌስቡከኞቹ ነበር፡፡ አኖሌም የተገነባው በዘህ መልኩ ነው፡፡ ይህ ሂደት በመጠኑም ቢሆን ዛሬ ላይ የተቋረጠባቸው የኦሮሞን ሕዝብ የሚዘውሩት የሙስሊም ጽንፈኞች ሴራ ትልቅ ተጽኖ ለመፍጠር ብዙ እየሰራ ነው፡፡ መረጃዎች እንዲዛቡ፣የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው ጋር አንድነት እንዳይፈጥር(ከሌላው ጋር ከአበር ከእነሱ ባርነት ይወጣባቸዋልና)፡፡

ሌላው ቢመከር ቢዘከር ማንነቱን አልገልጥም ብሎ ለሕዝብ መደናገር የሆነው የግንቦት 7 ጉዳይ አሁንም አስቂኝነቱ ቀጥሏል፡፡ ሰሞኑን አንደ ከሱዳን ሲመጣ የነበረ የፈሳሽ ጭነት መኪና ሹፌር ገደልኩ የሚል ዜና አስደምጦናል፡፡ዜናው በእርግጥም የግንቦት 7 ከሆነ፡፡ ከአልሆነ ደግሞ ማስተባበል ይኖርበት ነበር፡፡ ለመሆኑ አንድ ለፍቶ ራሱንና ምን አልባትም ብዙ ሌሎች ቤተሰቡን እያኖረ ያለን ሚስኪን ሹፌር ገደልኩ ብሎ ማውራት ዓላማው ምንድነው፡፡ የግንቦት 7 ትግል ተውት የዚህ አይነት ዜና አላማ ምንድነው; እስካሁን ገደልኩ የሚለን ምንም የማያውቁ ሚስኪኖችን ነው፡፡  ዓላማው ምንድነው ከተባለ በጎንደርና አካባቢው እየሰፋ የመጣውን የሕዝብ ትግል ወደ ግንቦት 7 እንዲህ ያለ አረመኔያዊ ድርጊት በማስደመጥ ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ ግብዓት እንዲሆን አስተዋፅኦ በማድረግ ለነጻነት እየተጋደሉ ያሉ ወገኖችን በሌሎች በመጥፎ እንዲታዩ ማድረግ ነው፡፡ ልብ በሉ እንዲህ ያለ ወሬ በስህተት እንኳን ቢፈጸም የሚወራ አደለም፡፡ ከወንጀልም አረመኔነት ነውና፡፡ ግንቦት 7 የሚባል በቦታው የሌለ ቢሆንም በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ታጋዮችን በሕዝብ ዘንድ ለማስጠላት ግንቦት 7 ምን ያህል ከወያኔ ጋር እየሰራ እንደሆን ልዩ ማሳያ ነው፡፡ ዲያስፖራ በግንቦት 7 መወናበድ ብቻ ሳይሆን መታለብ መብቱ ነው፡፡

ሌላው የአማራ ብሄረተኛ ዋነኞቹ ነን የሚሉ እንደነ ሙሉቀን ተስፋው ያሉ አደገኞች የሚነዟቸው ወሬዎች ናቸው፡፡ ሰሞኑን በጉራጌ ሲልጤ ዞን የአማራ ተወላጆች 5ሚሊይን ንብረት ወደመ፣ በሕግ ቁጥጥር ሥር የነበረ የአማራ ተወላጅ ተገደለ በሚል ለሕዝብ ይሄው ሙሉቀን ተስፋው የተባለው አስነበቧል፡፡ ይህን ሁሉ መረጃ ሲያገኝ ሂደቱ እንዴት እንደነበረ ሳያውቅ ቀርቶ አይመስልም፡፡ እኔ ይህን ሳነብ እንዴት ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ ነበረኝ፡፡ በሌላ መረጃ አቀባይ እውነታው ሲወጣ ነው ሊሆን እንሚችል የገባኝ፡፡ ሕዝብ እነ ሙሉቀን አስፋው እንደሚከፋፍሉት፡፡ ሕዝብ ከምንም በላይ ሰላማዊ ኑሮ ይፈልጋል፡፡  እውነቱን ያስነበበን ሌላው ጸሀፊ የነገርን ክስተት ግን ማንንም ለበቀል ሊያነሳሳና አማራ ሆነ ቀቤና ሊሞት የሚችልበት ነበር፡፡ ሟቹ በአማራነቱ ሳይሆን በድርጊቴ ነው የበቀል እርምጃ የተወሰደበት፡፡ ሌላው ጸሀፊ ያስነበበን ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ነው፡፡ ሙሉቀን አስፋው ይህን ደብቆ አማራ ያለውን ሰው ጻድቅ ሟች ነበር እርጎ ያስነበበን፡፡ 5ሚሊየን የተባለውም ንብረት 50ሺም ለመኆኑ እንጃ፡፡ እንዲህ ያለ ወሬ ግን አማራን ለማዳን ሳይሆን አማራን ለማጥፋት ሆን ተብሎ የሚዘራ ነው፡፡ የቤተ ዓማራዎች ዋነኛ ሴራ ይሄው እንደሆነ በተደጋጋሚ ብንናገርም የሚሰማ የለም፡፡ ቤተ አማራ ዋናኛ አላማ የአማራውን ሕዝብ እንደ ኦሮሞው ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነቱ አምክኖ ለጠላቶቹ ተገዥ እንዲሆን ለማድረግ ለረጅም ጊዜ ታስቦበት እየሰራ ያለ ቡድን ነው፡፡ አማራ ዛሬም ወያኔን እያስፈራ ያለው ኢትዮጵያዊነቱ እንጂ አማራነቱ አደለም፡፡ ቢገደልም ብዙም መከራ ቢደርስበት፡፡  ነፍጠኛ ሲባል በኩራት አው ነፍጠኛ ነኝ አገር የገነባሁ እያለ ወኔ የሆነው ኢትዮጵያዊነቱ ነው፡፡ አማራነቱ ውስጥ ታሪክ የለውም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ የሆነው እንዲህ ነው፡፡ የራሱ ታሪክና ክብር የሆነውን የኢትዮጵያን ታሪክ ሲክድ፣ በተለይም የኦሮሞ ልጆች በበላይነት አሸብርቀው የወጡበትን የታላቁን መሪ የሚኒሊክን ታሪክ እንጠላት አድርጎ ሲቆጥር ነበር አሮሞ የተዋረደው፡፡ ወያኔና ሙስሊሞች ኦሮሞን ሁሉ ለአርሲ ሰጥተው የአርሲን የጦርነት ታሪክ ከኦሮሞ ጋር በማጣመር መላ ኦሮሞን የሚኒሊክ ጠላት እንዲሆን አደረጉ፡፡ በአርሲ ጦርነት የተሳተፉ ወናዎቹ አርሲዎች ቢጠየቁ ሚኒሊክን የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ቢዋጓቸውም እንደጠላት እንደማስቧቸው እንገምታለን፡፡ ያም ሆኖ አርሲ ማለት አርሲ እንጂ ቦረና አደለም፣ ወለጋ፣ ሸዋ አደለም፡፡ ሚኒሊክ አርሲን የወጉት በአርሲነቱ ነው፡፡ የአርሲ የሚኒሊክ ጦርነት ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር የተደረገ ጦርነት የሆነው ኦሮሞን ሁሉ ነጻነቱን ቀምተው በበላይነት የሚመሩት የአክራሪ ሙስሊም ኦነጋውያን ናቸው፡፡ ኦሮሞ በዚህ ሁኔታ ከራሱ ታሪክ ተጣልቶ ዛሬ የመከነ ምልክት የለሌው ማንም የሚዘውረው ቁጥር ብቻ ሆነ፡፡ የአማራን ብሄርተኝነት የሚያቀነቅኑት አላማቸው የአማራን ሕዝብ እንዲሁ እንደኦሮሞው ማምከን ነው፡፡ አማራን ሁሉ ወክለዋል አክራሪ ሙስሊሞቹ ኦሮሞን ሁሉ እንደወከሉት፡፡ ለመሆኑ ቦረናን የሚኒሊክ ጠላት ያረገው ማን ነው; ቦረናዎችን ጠይቋቸው አማራ ብቻ አይምሰላችሁ እምዬ ሚኒሊክ የሚለው የቦረና አባቶችም እንጂ፡፡

የኦሮሞን ገዳ ሥርዓት እኮ እስከዛሬ እንዲኖር ያደረጉ ሚኒሊክ ናቸው፡፡ በተለይ ለቦረናዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፡፡ ገዳ እኮ  በአንደም የሙስሊም ኦሮሞ አካባቢዎች አይታወቅም፡፡ ገዳ የሚታወቀው በዋናነት የሚኒሊክ ወዳጆች በሆኑት ቦረናዎች በመጠኑ በጉጂዎችና ሸዋዎች እኮ ነው፡፡ ሚኒሊክ ባይነሱ ገዳ የሚባል ሥርዓት ተረት ሆኖ ለመስማት እንኳን አንችልም ነበር፡፡ አባ ባህሬ የጻፉትንም ለማንበብ እድሉ አይኖረንም፡፡ ዛሬ ገዳን የማያውቁት የአክራሪ ሙስሊሞች እንደነተስፋዬ ገብረአብን ያሉ ዘረኞች የኦሮሞ ሕዝብ ጠላቶች የገዳ ሹመት ሲሰጡ ስንሰማ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው እውነታው ሕዝብ ጠንቅቆ ስላላስተዋለው ነው፡፡ ገዳ በአንደም የሚስሊም ኦሮሞዎች አይታወቅም፡፡ በኦሮሞ ሙሰሊሞች የአረብ ሸሪያ ነው የሚውጠነጠነው፡፡ ልብ በሉ ቦረናና ጉጂ የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ አሁን አሁን ወደ ፕሮቴስታንትነት እየተቀየሩ ያሉ ናቸው፡፡ ኢሬቻ በዋናነት፣ ገዳንም በመጠኑ የሚከተሉት ሸዋዎች ደግሞ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሚኒሊክ ልጆች ናቸው፡፡

 

አመሰግናለሁ!

 

እግዚአብሔር ኢትዮጰያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!

አሜን!

ሰርጸ ደስታ

The post አገሬ ኢትዮጵያ ለምትሉ ኢትዮጵያውያን ጠቃሚ መረጃ – ሰርጸ ደስታ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

“ከሽብርተኞች ጋር በመገናኘት፣ አሸባሪ ለሆነው የኢሳት ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠየቅ በመስጠት

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

በሚል ክስ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙት ተከሳሾች መካካል ዛሬ ሰኔ 9/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ በሰባቱ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ የሚከተሉት ስድስቱን በነፃ ለቋቸዋል።
(በሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
1ኛ. 1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን
2ኛ. 4ኛ ተከሳሽ አቶ አወቀ ሞኙ ሁዴ
3ኛ. 8ኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ
4ኛ. 10ኛ ተከሳሽ አቶ ታፈረ ካሳሁን
5ኛ. 13ኛ ተከሳሽ አቶ እንግዳው ባዩና
6ኛ. 15ኛ ተከሳሽ አቶ አግባው ሰጠኝ ናቸው። ፍርድ ቤቱ በዚሁ የክስ መዝገብ ተከሳሽ የነበሩትን
5ኛ፣ 6ኛ ና 7ኛ ተካሽሽን አቶ ዘሪሁን በሬ ፣ አቶ ወርቅየ ምስጋናው እና አቶ አማረ መስፍን
ከዚህ በፊት ነፃ መልቀቁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አስራ አምስተኛ ተከሳሽ የሆነው የሰሜን ጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው አግባው ሰጠኝ በነሐሴ 28/2008. ዓ.ም በቂሊንጦ እስር ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ “የሴራው አቀናባሪ ናችሁ” በሚል ከተከሰሱትና በመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ ክሳቸውን ከሚከታተሉት አንደኛው ስለሆነ ዛሬ ከክሱ ነፃ ቢሆንም ከእስር ግን አይለቀቅም። በዚሁ የክስ መዝገብ ውስጥ በገቡበት ክስ ነፃ ተብለው ከቂሊንጦው እሳት ጋር በማያያዝ ዳግም እንዲታስሩ ከተደረጉት ውስጥ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ይገኙበታል። ዛሬ በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈባቸው ሰባት ተከሳሾች አቶ በላይ ሲሳይ፣አቶ አንጋው ተገኝ ፣ አቶ ቢሆነኝ ፣ አቶ አትርሳው ፣ አቶ አለባቸውና አቶ አባይ ዘውዱ ናቸው።የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ/ም ተቀጥሯል::

The post “ከሽብርተኞች ጋር በመገናኘት፣ አሸባሪ ለሆነው የኢሳት ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠየቅ በመስጠት appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ፍትሕ ለወ/ሮ እማዋይሽ እና በእስር ላይ ለሚገኙ የፖለቲካ እስረኛ ሴቶች! (ይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0

3291ቀናትን ያለ ምንም ወንጀል በእስር ላይ 🙁 እማዋይሽ አለሙ አንቺ የሁላችንም እናት ነሽ!!!

የሴቶች እኩልነት እና የላቀ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ተግቼ እሰራለው የሚለው የህወሃት/የኢህአዴግ መንግስት ላለፉት 26 ዓመታት የገባውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን አድርጎ፤ ለሰብዓዊ መብት መከበረ እንዲሁም ዴሞክራሲ ስርዓት በአገራችን እንዲያብብ የበኩላቸውን አሰተዋአዖኦ ለማድረግ ደፋ ቀና የሚሉ ሴቶችን በተለያየ መንግድ ጫና በመፍጠር፣ በአገራቸው ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን አለኝ የሚለውን አማራጭ ሁሉ እየተከተለ ይገኛል።ገዢው መንግስት ሴቶች በአገራቸው ጉዳይ መንግስትን በመቃወማቸው እና በመተቸታቸው ብቻ የሚደርሳባቸውን
በደል አስመልክቶ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፣ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እና የዴሞክራሲ መብት ተሟጋቾች ፣ እንዲሁም የአለማችን ታላላቅና ለጋሽ ሀገራት ጠንካራ ወቀሳ በገዢው መንግሥት ላይ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የሚቀርበው ወቀሳ በምክንያት እና በእውነት ላይ የተመሰረተ ስለ መሆኑ እጅግ በጣም ብዙ ገላጭ የሆኑ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻላል። እያንዳንዱ ነገር መዘርዝር ለቀባሪው መርዶ እንደማርዳት ስለ-ሚሆን እንደ ማሳያ ይህን ብቻ ማንሳት በቂ ነው ። በአገራችን ከ1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ በኋል ለመጀመርያ ጊዜ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ መሪውን በሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ የመረጠው በ1997 ዓ.ም ነው። የዛሬ 12 ዓመት ሕዝብ ከመረጣቸው መካከል ተዋቂነት ያተረፈችው ወ/ሪ ብርቱ ‘ካን’ ሚደቅሳ አንዷ ናት! ወ/ት ብርቱ ‘ካን’ በሃገሯ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን የበኩላን አሰተዋአዖኦ ለማድረግ ያደረገችው ጥረት በህወሃት/የኢህአዴግ መንግስት በጎ ምላሽ ሊሰጠው አላቻለም። ይባስ ብሎ ለተደጋጋሚ እስር እና እንግልት እንዲሁም ስቃይ ተዳረገች። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የስነ- ልቦና ቶርቸር ተፈጸመባት፣ በመጨረሻ ሰው ናትና አሁን ላይ የሆነው ሆነ። ይህም በመሆኑ ማንም በእሷ ቅር አልተሰኘም! የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታውን የሚያከብር ጥንቁቅ ሕዝብ ነው። ተወዳጁ አንጋፉው አርቲስት ደበበ እሸቱ ብርቱካንን የሚጠራት ብርቱ ‘ካን’ እያለ ነው!ለዚህም ነው እሷን በቅርበት የምናውቃት ብርቱ ‘ካን’ የምንለው ።የስሟ አጠራር እንዴት እና መቼ የእሷ መጠሪያ እንደሆነ ወደፊት እመለስበታለው።

የብርቱ ‘ካን’ ከአገር መሰደድ እና። ፖለቲካውን በቃኝ በማለቷ በህወሃት/የኢህአዴግ ሰፈር ከፍተኛ ፈንጠዝያ ለጊዜው ቢያስገኝም ፣ ብርቱ ‘ካን’ ያሰለፈችው የመከራ ጊዜ እንዲሁ ዝም ብሎ የባከነ አልነበረም !ብዙ ብርቱ ‘ካን’ ያፈራ በሃገራችን ከ1983 በኋል እጅግ በጣም ትንታግ የሆኑ ሴቶች ! የሰብዓዊ እና የዲሞክራሲ መብት ተሟጋቾች እና አራማጆች የተገኙበት ወርቃማ ዘመን ነው። ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባ ገብቶ ስልጣን በያዘ ማግስት የተወለዱ “የኢህአዴግ ዘመን ልጆች” የዚሁ አካል መሆናቸው ነው።እነሱም ቅድሚያ የዜጎች ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲ መብት በማለት በፊት መስመር ተሰልፈው ለሃገራቸዉ እና ለሕዝባቸው የቻሉትን ያህል በጎ አሰተዋአዖኦ ለማበርከት ከመንገድ ላይ ናቸው።ሆኖም ግን እነኚህ የመብት ተሟጋች እና አራማጆች መንገዳቸው ቀና አልነበረም ፣ እንደተለመደው እስሩ፣ስቃዩ እና እንግልቱ ከእነሱ አልተለየም ።በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ እህቶቻችን የዚህ በደል እና ስቃይ አካል ናቸዉ ።

ከእነዚህም መካከል በእስር ላይ የሚገኙት የአራት ልጆች እናት ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ አንዷ ናቸዉ ። ሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤቷ ተይዛ ለእስር የተዳረገቸው ወ/ሮ እማዋይሽ፣ ሕገመንግስቱን በሃይል ለመናድ በህቡዕ ሰርተዋል በሚል በእነ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ መዝገብ የተከሰሱ ብቸኛዋ ሴት ናቸው። 25 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ዛሬም በቃሊቲ እስር ቤት ይገኛሉ።እኚህ እናት ለዘጠኝ ዓመት በእስር ቤት የመከራ ጊዜ እያሳለፉ ናቸዉ ። አዎ ! ፍትህ ለእማዋይሽ ዓለሙ ! እና በእስር ላይ ለሚገኙ የፖለቲካ እስረኛ ሴቶች በሙሉ ! ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ እና በተለያየ እስር ቤት የሚገኙ የሰብዓዊ እና የዴሞክራሲ መብት ተሟጋች እና አራማጆች ፣በአገራችን ኢትዮጵያ ሴቶች የበኩላቸውን አሰተዋአዖኦ ለማድረግ የሚጠሩ ተምሳሌቶች ናቸው ። ይህም በመሆኑ እነዚህ እህቶቻችን እጅግ በጣም ሊወደዱ እና ሊከበር የሚገባቸው ፣ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። የዘመናችን ጣይቱዎች ናቸዉ ! ስለነርሱ አውንም ሁሌም ድምፃችንን ከፍ አድርገን በህብረት ፍትሕ…ፍትሕ… ፍትሕ… ፍትሕ…ፍትሕ በማለት እንጠይቃለን!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

 

The post ፍትሕ ለወ/ሮ እማዋይሽ እና በእስር ላይ ለሚገኙ የፖለቲካ እስረኛ ሴቶች! (ይድነቃቸው ከበደ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የሺህ አመት ባሏን በሃያ አመት ውሽማ የለወጠችው ከተማ – ያሬድ ይልማ

$
0
0

ሳህለስላሴ የተባለው በስራ ዘርፋችንም ለልቤም ቢሆን ቅርብ የነበረ ወደጄ፣ የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ለትምህርት ከሄደበት አውሮፓ ወደ አገር ቤት ሶስት አመት ሳይሞላው ተመለሰና ፣ እንባ ረጭተን የሸኘነውን ጓደኞቹን አስደነገጠን፡፡ “ምን ሆነህ ነው! ከኤርፖርት እቤት ተመልሰን በወጉ እንባ እና ሲቃችንን ሳናባርድ እንዲ ቀልባችንን የምትገፍፈው? ” ፣ ብለን አምባረቅንበት፡፡ ምክንያቱም የአቶ ሳህለስላሴ ልጅ ፍሬፅዮንን ፣ ሁላችን እጅግ በጣም የምንወደው ልዩ ኢትዮጵያዊ ስለነበር፡ የአሸኛኘቱ ነገር አይረሴ ነበርና ነው፡፡

ያላለቀሰ ፣ ያልተነፋረቀ አልነበረም፡፡ ግን ግን ሶስት አመት ሙሉ የማይደርቅ የሚመስለው፣ ኡመር የተባለው ጓደኛችን ልቅሶ ነበር፡፡ ፍሬፅዮንን ከሸኘንና ኤርፖርት ውስጥ ከገባ ከአራት ሰአት በኋላ ቢራ እየጠጣን ተንሰቅስቆ ሲያለቅስ ያየው፣ ሳምሶን የተባለ ጓደኛችን፣ “ኤጭ በቃ አትነፋረቅብን፣ ምን ቀንተህ ነው እንዴ እንደዚህ እምታላዝነው! በል በቃህ አንደዚህ በማያባራ እንባ አሟርተህበት “ፍሬ” በሄደበት አውሮፕላን ተመልሶ መጥቶ አብራችሁ እንዳታነቡ!” ብሎ አሹፎበት ነበር፡፡ ፍሬን ስናየው የደነገጥነውም ለዚሁ ነበር፡፡

ግን የመጣው እጅግ በጎ ለሆነ ፣ ለዚህ ፅሁፍ መነሻ ለሆነኝና እንደ አስረጂነት የምጠቀምበትን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ማህበራዊ ጥናት ለማካሄድ ነበር፡፡  “ፍሬ” (ቅፅል ስሙ ነው) አውሮፓ ሄዶ ሲያጠናው ለነበረው ትምህርት (International peace, conflict and Justice Management) የመመረቂያ ፅሁፉን መስራት ወስኖ የነበረው “በሃረር ከተማ ልዩ ስሙ “አራተኛ” በተከሰተ ሃይማኖታዊ ምክንያት በነበረው ፀብ ከባድ እልቂትን ሊያመጣ ሲችል ፣ እዛው ከስሞ ስለቀረ ፣ አንድ ልዩ ክስተት” !መነሻ ምክንያቱን እና እንዲሁም – ወዴትም ሳይስፋፋ ድንገት እንዴት ከሰመ? ስለሚለው ዋነኛ ሃቅ ጥናታዊ ድምዳሜ ለመስጠት ነበር፡፡

እንደ ፈረንጅ አቆጣጠር በሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት ገደማ፣ ሃረር አራተኛ በሚባል ሰፈር በጥምቀት በአል ወቅት ፣ በተነሳው በዚሁ ሃይማኖታዊ ምክንያት በነበረው ፀብ ፣ ህይወታቸውን ያጡ የዚያው የሃረር ከተማ ነዋሪ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ከነዚያ ከርስቲያኖች ሞት በኋላ በነበሩት ቀናት ውስጥ የሙስሊም “ኢድ” ስለነበር ፣ ከተራ ነዋሪው እስከ መንግስት ድረስ ፣ ተሰራጭቶ የነበረ ፍራቻ ነበር፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ክስተት መነሻነት በከፍተኛ  የቂም በቀል ስሜት ፣ ልክ እንዳለፉት የክርስትያኖች እጣፈንታ ፣ በእስልምና እምነት ተከታዮች የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ደግሞ የማይቀር እልቂት ይከሰታል ተብሎ፣ ለሳምንታት ሃረር ከተማ ቀይ መብራት እንደበራባት ከቆየች በኋላ፣ በዚህ ምንያት ነው፣ ይህ ስለተደረገ ነው፣  ተብሎ ለመናገር በማይቻልበት መልኩ፣ ያ ደም ያቃባል የተባል የቂም ደመና የት እንደገባ ሳይታወቅ፣ ድንገት የሽብር እና ስጋት ስሜት የገባበት ጠፍቶ፣ ህይወት ዳግም እንደበፊቷ ቀጠለች፡፡

ይህ ሃይማኖታዊ ፀብ መነሻ ያለው ክስተት፣ በሰሜን ናይጄሪያ አሊያም በኮንጎ ተከስቶ ፣ የሟቾች ቁጥር ምንም ያክል ይሁን ፣ የአንድ ወገን ሃይማኖተኞች በሌሎቹ ወገን ሀይማኖተኞች ተገድለው ቢሆን ኖሮ ?፣ መጨረሻው ምን ይሆን እንደነበር መተንበይ ከባድ የሚሆን አይመስለኝም፡፡ ይህ ፅሁፍም ሆነ የሃረር ከተማ የቅርብ ጊዜ ታሪክ በሌላ አስቀያሚ ቃላት ይፅፍ ነበር፡፡ ግና አገሩ ኢትዮጵያ ሆነና፣ ከተማዋም ሀረር ሆነችና፣ አገር የማጥፋት አቅም ያለውን የእሳት ብልጭታ በእንጭጩ እዛው አዳፍነው፣ ምንም አይነት ሌላ ድራማ ከተማዋ ሳታስተናግድ የሃረር ነዋሪዎች ህይወትን ቀድሞም እንደነበረችው አስቀጠሉ፡፡

ይህ በምን ምክንያት ሊሆን ቻለ? ምንድነው የቺ በአራተኛ የተነሳጭውን የእሳት ብልጭታ፣ ወደ ሙሉ እሳትነት፣ ብሎም ከተማ ሊያወድም ወደ ሚችል ነበልባልነት ሳይቀየር እዛው እርጥብ ብርድልብስ ጥሎበት ባጭር የቀጨው? ይህ ነበር የፍሬፅዮን ሳህለሰላሴ ጥናት ዋና ትኩረት! ጥናቱን ሲያጠናቅቅ ታድያ ያገኘው መልስ አስገራሚ ነበር፡፡

በእዚሁ በምስራቅ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ያለ እና በተለይ ሃረር ከተማ ውስጥ አንጋፋነቱ ሺህ የደረሰ፣ በትክክል ለማስቀመጥ፣ የፍሬፅዮንን ጥናት አገላለፅ “ከጠንካራ ጅማት ተሰፍቶ የተሰራ እድሜጠገብ ብርድልብስ” ዋነኛ አስተዋፅኦ እንደተዳፈነ፣ በሃረር ከተማ ሺህ አመት በኖረው በዚህ ውበት ምክንያት ሆኖ አገኘው! በቀላል አማርኛ ለማጠቃለል፡ በሃረር ከተማ ባለው “ልዩ ማህበራዊ እሴት” ምክንያት ነበር፣ ህዝብ ያልተጫረሰው፡፡

ስለዚህ ይህ የፍሬፅዮን የመመረቂያ ፅሁፍ ጥናት ብዙ ሰዎችን፣ ብዙ መዛግብቶችን አሳትፎ የተደረገበት ምክንያት፣ በተሰማራበት የትምህርት ዘርፍ (International peace, conflict and Justice Management) ፣ አለም ከአፍሪካ በተለይ ደግሞ ከኢትዮጵያ ፣ በዚህ ረገድ መማር እንዲችል፣ ይህንን እልቂትን ፣ እንደዋዛ ጭጭ አድርጎ ያስቀረን ጥብቅ ማህበራዊ እሴት፣ ከሃረር ከተማ ጋር እንደ ባሏ ተቆራኝቷት፣ ሃረር ውቧም አቅፋው ተጋብታው ሺህ አመት አብራ የኖረችው፣ ይህ ልዩ የማህበራዊ እሴት ጉልቻ ፣ ምን ላይ ነው የተመሰረተው? የፀኑት እና እንደ ጠንካራ ጅማት እርስ በእርስ ተሳፍተው እንዲኖሩ ያገዙት ብልቶቹ ምን ምን ናቸው? በሚሉ ጥያቄዎች ጠቃሚ ቁምነገሩን መርምሮ ለማወቅ እና ከትቦ መረጃ ለማስቀረት የተደረገ ስለነበር፣ እንደ በረከት የሚያዙትም፣ ወደፊት ይህንን የማህበራዊ እሴት ሁለንተናዊ ህልውና ፀንቶ መቀጠል እንዳይችል ሊያደርጉ የሚችሉ እና የሚያሰጉ ግልፅ በአመክንዮ የተደገፉ ድምዳሜዎች ካሉም እንደ አደጋ ተመድበው፣ የሚያሳይ ሰነድ ለማጠናቀቅ፣ በዚህም አለማቀፋዊ መማሪያ የሚሆን ጭብጥ ማስገኘት፣ ሃረርንም ከውቡ የሺህ አመት ባሏ-“መቻል” ጋር ሌላ ሺህ አመት እንድትኖር አቻ ፋይዳ የሚሰጥ ትልም ይዞ የተፈፀመ ልዩ ፅሁፍ ነበረ፡፡

ይህ ጥናት በውል ያስቀመጣቸው እና ሃረር ለነዋሪዎቿ በሃይማኖታዊ እንዲሁም በማህበራዊ መስተጋብራቸው ውስጥ የፈጠረችላቸውን ልዩ የኑሮ ድባብ በዝርዝር ሲመለከት ካገኛቸው እጅግ ብዙ ፣ እንዲህ አይነት ብጣሽ ፅሁፍ ዳስሶ ሲጨርሳቸው ከማይችላቸው ፣ ሃረር ከተማ ነዋሪዎች መካከል በዘመን ብዛት ከጎለበቱት የማህበራዊ እሴቶች አንዱን ብቻ ነጥለን ብንመለከት የምናገኘው፣ በሃረሪ ቋንቋ “አፎቻ” -(የጓዳ እድር አይነት ህብረት) ወይም “መሪኛች” -(ጓደኛሞች) የሚል ተለዋዋጭ መጠሪያ ያለው እጅግ የሚያስገርም ፣ ከዚያም ከዚህም የተውጣጣን የማህበረሰብ ክፍል ፣ በአንድ ጠንካራ ጅማት አስተሳስሮ የሚያቆራኝ “እሴትን!” ነው፡፡

በአንድ “አፎቻ” ውስጥ የሚጠቃለሉ የህብረተሰብ ክፍል አሊያም ሰፈርተኞች  እራሳቸውን ሲጠሩ ወይ ሰው ሲጠይቁ፣ “እገሌ የነማን አፎቻ ውስጥ ያለ ነው ? ፣ የነማን እድርተኛ ነው ብለው ነው፡፡ እንደ ሃረር ያንዱ ሰፈር ነዋሪ የአንዱ አፎቻ አባል ለመሆን ያለው መስፈርት ሁለት ብቻ ነው፣ እድሜና ፆታ!፡፡ ከዚያ ውጪ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የዘፈን ምርጫ እና የሚደግፉትም ሆነ የማይደግፉት የእግርካስ ክለብ አሊያም ሌላ ማህበር ለአፎቻ አባልነት አሉታዊም አዎንታዊም ተፅእኖ የላቸውም፡፡

በነዚህ የአንድ አፎቻ አባሎች መካከል ባለው የእድሜ ልክ ማህበራዊ አብሮነት፣ ማለትም በሃዘንም በደስታም እያንዳንዳቸውን የህይወታቸውን ምእራፎች፣ ከሁሉ በፊት ቀድመው እየተደራረሱ፣ ሌላውንም አስተባብረው ከአፎቻቸው አባል ባንዱ ቤት ስላለው በረከት ሳቃቸውን አብረው ሲያስካኩና ሲያስተጋቡ፣ ባንፃሩ ደግሞ በአፎቻቸው አባል ባንዱ ቤት ለሚደርሰው ሃዘንም ከልብ ፣ ለልብ ቀድመው እየተደራረሱ፣ ነው ፣ “መሪኛች” ፍሬፅዮን በ“ልዩ ማህበራዊ እሴትነት” ደምድሞ የመደበውን ውቡን የሃረርን የሺህ አመት ፀጋ -“መቻቻልን” የገነቡት፡፡

በዚህም ትስስር ምክንያት እነ ናይጀሪያ ፣ ማይናማር እንዲሁም ኮንጎ ላይ አንድ የአራተኛውን የሚመስል ክስተት በተፈፀመ በቀናት ጊዜ ውስጥ ሲፈፀም አለም ከሰማው በተቃራኒ ፣ ህዝብ እርስ በእርሱ እንዳይጫረስ የምታደርገውን ልዩ ሞራላዊ ስብእና አማርኛ ባንድ ቃል ጠቅልሎ “ይሉኝታ!!!” በሚላት መፍቻ ቃል (Keyword) የሃረር ከተማ ነዋሪዎች እርስ ባንድ ጅማት ታስረዋል፣ ማህበራዊ እሴት ባዳበረው ይሉኝታ፡፡ ስለዚህ እንደተፈራው የአራተኛው የጥምቀት ጣጣ ሌላ የኢድ ቀን መአት ሳያመጣ ባጭሩ፣ ተቀጨ፡፡

ታዲያ በዛው ጥናት ላይ ፍሬፅዮን ፣ ወደፊት ይህ አስገራሚ የማህበራዊ እሴት ጅማት ሳይበጠስ እንዳይቀጥል ሊያደርጉ የሚችሉ፣ አሉታዊ እውነታዎችንም ለማየት ሞክሯል፡፡ እነዚህን የሃረር ከተማ ውስጥ በሚገርም ልዩ ቅመማ የዳበሩና የበለፀጉ ማህበራዊ ትስስሮችን ምን ሊያላላ እና ሊበጥስ የሚችል ግብአት አለ ብሎ ካጠናቸው ነገሮች ውስጥም እንዲሁ በጣት የሚቆጠሩ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ተጨባጭ አቅሞችን ጠቅሶ ነው ያለፈው ጥናቱ፡፡ ታዲያ እነዚህ በጣት ከሚቆጠሩቱ የፍሬፅዮን ጥናት ከለያቸውና ፣ ውቡን የሃረርን ማህበራዊ እሴት ሊበጣጥሱ አቅም አላቸው ፣ ብሎ ካረጋገጣቸው ምክንያቶች አንደኛው በተለየ አይን መታየት እንዳለበት መክሮ ያጠቃልላል፡፡ ይህ በተለየ አይን መታየት ያለበት የሃረር ነዋሪ መፃኢ ጠላት፣ “በታሪክ ውስጥ ያለን ቂም በሃረሪ ቋንቋ ውስጥ እንዲካተት የተደረገበት ልማድ እና ለዚህ ልማድ “ከክልልም ሆነ ከፌደራል መንግስት” የተቸረው ፣ “ ታሪካዊ ቂም በቀልን የማበረታታት” ተልእኮ እና ትኩረት ነው!፡፡

ከዘጠኝ አመት በፊት ፣ የሀረር ከተማ ተወላጅ ገጣሚያንና በደራሲያን ማህበር አባሎች አነሳሽነት፣ ከኢትዮጵያ ሚሊኒየም ቀድሞ የጠባውን የሀረር ከተtማን የሺህ አመት በአል በልዩ ሁኔታ ለማክበር ቅን ልቡ እና ፍቅር ሰንቀው ለሄዱ ካዲስ አበባ የተነሱ በጎፈቃደኞች ላይ ከደረሰው አሳፋሪ ከታሪክ የሚነሳ ቂም መርዝ የመጀመሪያ ቡኮ፣ አንደኛ መንገድ፣ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት እስከ ተተከለው የቂም ሃውልት ድረስ ሀረር፣ ሺህ አመት ተቆራኝታ አቅፋ ያኖረችውን ከልዩነት ይልቅ በፍቅር ላይ የተመሰረተውን መገለጫዋን፣ ልዩነትን በሚያበረታታው፣ አዲስ እና መጤ የሃሳብ ውሽማ ለመቀየር የፈጀባት ጊዜ አጭርነት አስገራሚ ነው፡፡

አንድ ወዳጄ የዛሬ አራ አመት ገደማ፣ በተለያየ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎችን የሆኑ ሰዎች መሃል ሆኖ ሃረርን ተዘዋውረው ሲመለከቱ ያጀበ ወዳጄ በዚህ ሃረር ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፣ እንደ ኩታ ተሰፍቶላት የለበሰችውን መጤ ቂመኝነት፣ በምሬት ሰነግረኝ እንዲህ ነበር ያለኝ፡፡ ለፍቅር ሲል ታላቋን ሃገሩን ፈረንሳይን ከድቶ ፣ አልፈልግሺም ብሎ የከተመባትን የባለቅኔውን አርተር (ራምባዱ) ራምቦ  መኖሪያ ቤት በአንድ ጎኑ ቀይ ምንጣፍ ተሰቅሎ የቂም ታሪክ የሚነገርበት ስፍራ እስኪሆን ድረስ የሃረር ተጨባጭ ሁኔታ እንዲቀየር ከተማዋ በማይበጅ እና ጠንቅ በሆነ መንገድ ፣ ሆን ተብሎ እየተመራች ነው ፡፡

ለዚህ ማሳያ እንዲሆን የነገረኝ ነገረ በተለይ ልብ የሚሰብር ነበር፡፡ የአርተር ራምቦ መኖሪያ ቤትን ሊጎበኝ ከነበረው ትልቅ የመንግስት ሰው ጋር ሆነው በአጀብ እየጎበኙ፣ የሚያስጎበኘው ሰው በአደሬ ባህል፣ “ነደባ” የሚባል ቤት ውስጥ ስለሚነጠፍ፣ “ከሊም” (ቀይ ምንጣፍ) እና ከሱ ጋር ስለሚያያዘው ከሚኒሊክ ጦር ጋር ስለተደረገው የጨለንቆው ጦርነት ይናገር ነበር አስጎብኚው፡፡ “ይህ ቀይ ምንጣፍ ምንም ያክል ደሃ ብትሆን የአደሬ ቤት ሰው በዘካ ገንዘብ ሳይቀር እንድትገዛው አዋጥቶ፣ ይሰጥህና ትገዛለህ ምክንያቱም፣ ፋይዳው ለህዝባችን ወሳኝ ስለሆነ” አለ ጋይዱ፣ ቀጠለና ፣ ይህ ምንጣፍ በጨለንቆው የአሚረ አብዱላሂ ጦር እና በምኒሊክ ጦር መካከል በተደረገ ጊዜ፣ ህይወታቸው ያለፈውን ሰባት መቶ ሙሽሮች ፣ ቀዩን ምንጣፍ እያዩ ልጆች እንዲያድጉ የምናስታውስበት ነው”- እነዛ ሙሽሮች በዛ ጦርነት በማለቃቸው ምክንያት- “ነመ ሰበ ቢጩ” (አናሳ ህዝብ ) ያለው ብሄር ሆነናል፡፡ “አሁንማ ለስራ ጉዳይ የመጣ ቻይና እንኳን በቁጥር ከአደሬ ይበልጠናል!- ለዚህ ተጠያቂው ምኒሊክ ስለሆነ ቀዩ ምንጣፍ ወሳኝ ነው” አለ ጋይዱ ሳቅ ተከተለው የጋይዱን ንግግር አለኝ ወዳጄ!

ይህንን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ወደ ሃረር የሚመጣ ጎብኚ ሳይቀር እንዲሰማ የሚነገረውን ታሪክ ሲናገር ጋይዱ ፣ ደጋግሞ “አህ-መራ- አህ-መራ” እያለ ይጠራ ነበር፣ በዚህ ጊዜ ለጉብኝት የመጣው ሰው ምን ማለት ነው “አህ-መራ” ብሎ ሲጠይቅ፣ የሃረሪ ቋንቋ ተናጋሪ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ለመጥራት “አማሮችን” የሚጠራበት ስም አጠራር እንደሆነ፣ እና ትርጓሜ እንዳለው ተነገረው፡፡ “አህ-መራ” የሚለው ቀጥተኛ ትርጉምም፣ “ቁጭት ሳይ” የሚል ትርጉም እንዳለው አስጎብኚው ሲናገር፣ ስፍራው በብዙ ሰው ሳቅ የአርተር ራምባዱ ግቢ ተናጋ፡፡

እውነት ይህ የሚያስለቅስ እንጂ የሚያስቅ እውነት ሆኖ ነው! ወዳጄ እንደዛን ቀን ሃረር ላይ እየተዘራ ያለውን ፣ የቂም እና በቀል አስተምህሮት፣ ለአንድም ደቂቃ አስቦት ስለማያውቅ እንዴት እንዳዘነ ያስዳኝ፣ ልብ በሚነካ መልኩ ነበር፡፡ ጎብኚ ሳይቀር እንዲረዳው በኩራት የሚነገር ሰሞኑን ሃረር የገባው አዲስ የቂም ትምህርት ማለተ ይሄ ነው፡፡ መድሃኒአለም ፊት ለፊት ካለው ሃውልት እኩል በክፉ መረጃ ትውልድን መመረዝ ማለት እንዲህ ነው እንግዲህ፡፡ ዩኔስኮ የመቻቻል መዲና ብሎ እውቅና የሰጣት ሃረር፣ ያቺኛዋ ነበረች፡፡ ያቺ ሺ አመት ከጥላቻ እና ልዩነት ይልቅ የፍቅር ቋንቋ ለመላው ኢትየጵያ በተጨባጭ ስታሳይ የኖረችው፣ ሆደ ሰፊዋ ሀረር ነበረች፣ የሺህ አመት ውቢቷ!

ዛሬ ግን ሃረር ያ እውቅናውን ያገኘችበትን ውቡን ማህበራዊ እሴቶቿ በሚያሳዝን ክፋት በሚመሩ ፊት አውራሪዎች እንድትጥል ተገዳ ፣ ከዛ ተምሳሌትነት ከተገባው፣ የከተማ ባህሪዋ ጎድላለች፣ ለብዙዎች ሳይሆን ለጥቂቶች ብቻ እንድትሆን፣ ልዩነትን ረስታ፣ ፍቅርን እያስቀደመች ትሄድበት ከነበረው ስሪቷ በተቃራኒ፣ ቂም እና ክፉ ታሪክን አነፍንፋ የምታፋፋ ፣ የሺህ አመት ባሏን በሃያ አመት ውሽማ የለወጠች ከተማ ሆናለች!

ልብ ያለው ልብ ይበል-ቂም በቀል ክፉ ነውና ሁላችንም ልናወግዘው ይገባል፣ ለኢትዮጵያ አይበጃትምና!!!

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!

ያሬድ ይልማ

 

 

The post የሺህ አመት ባሏን በሃያ አመት ውሽማ የለወጠችው ከተማ – ያሬድ ይልማ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ክፍል 1, 2, 3 |በየዘመኑ የነበሩ መሪዎቻችን የኤርትራን ጉዳይ ያስተናገዱበት አግባብና ሲከተሉት የነበረዉ ፖሊሲ

$
0
0

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ክፍል 1

 በየዘመኑ የነበሩ መሪዎቻችን የኤርትራን ጉዳይ ያስተናገዱበት አግባብና ሲከተሉት የነበረዉ ፖሊሲ

ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ፃድቅ

ይህ ጽሁፍ የኤርትራን የእብሪት ወረራ ለመመከት በቆራጥነት ሲፋለሙ ለወደቁ የጀግናዉ መከላከያ ሰራዊታችን አባላትና በሻእቢያ የግፍ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ የአይዴር ት/ቤት ህጻናት ማስታወሻ ይሁን፡፡ በተጨማሪም እንደወጣ ሳይመለስ ለቀረዉና የምንግዜም የአየር ኃይላችን ጀግናና የኢትዮጵያ ኩራት ለሆነዉ ለኮ/ል በዛብህ ጰጥሮስ መታሰቢያ ይሁን፡፡  

+ የኢትዮጵያ ህዝብ በነበሩት ስርአቶችም ሆነ በመንግስታቱ ላይ ደስተኛ ሆኖ ባያዉቅም በሃገሩ ሉአላዊነት ላይ ግን ተደራድሮ አያዉቅም፡፡በሶማሊያ ጦርነትም ሆነ ከኤርትራ ጋር በነበረዉ ጦርነት ወቅት የታዬዉ የህዝብና የመንግስት አንድነት መነሳሳት በብዙ መልኩ ተመሳሳይየነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጦርነት ግን ጠንከር የሚል ይመስለኛል፡፡

+ ለኢትዮኤርትራ ጦርነ አነስተኛ ግምት የሠጠነዉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ላይ ያደረግነዉ ተጋድሎ የከፈልነዉ መስዋእትነትና የደረሰብንጉዳት ሁሉ ገና በዚህ አጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲህ በቀላሉ መዘንጋት ነበረበት አላስብም፡፡ ከኤርትራ ጋር ገና ያልተቋጨ ብዙ ጉዳይ እያለንበቀላሉ ሊዘነጋ አይገባዉም፡፡

+ ሰራዊታችን ለሰራዉ አኩሪ ገድልና ለከፈለዉ መስዋእትነት ሃዉልት ባይቆምለት እንኳን ቢያንስ ህዝቡ ስለ ልጆቹ ጀግንነት እንዲያዉቅ፤መጭዉ ትዉልድም እንዲማርበት ተደርጎ የማይዘገበዉስ ለምንድነዉ? የሻዕቢያ መንግስት እንደሆነ በሱ ጠብ ጫሪነት ተጀምሮ በሱ ሽንፈትስለተጠናቀቀዉ ጦርነት ማዉራትና መተረክ ስለማይችል ከዚያ ይልቅ በየጊዜዉ ለህዝቡ የሚያሳየዉ የዉ የድሮዉን ደርግ ጋር ተደርጎየነበረዉን የናቅፋን፤ የአፋበትን ፤የከረንን ፡የምጽዋን ወዘተ ዉጊያ ላይ ሰራሁ ስለሚለዉ ገድል ብቻ ነዉ፡፡

ስለ ባድመ ጦርነት ግን ሻዕቢያ ብዙ ሲያወራ አይደመጥም፡፡ ያን ማድረግም አይጠበቅበትም፡፡ ምክንያቱም  በባድመ ጦርነት ምንም የሚያኮራታሪክ ለሌለዉ ማዉራት አይችልም፡፡ እኛ በኩል ግን ከኤርትራ ጋር የተደረገዉ ጦርነት በአስደናቂ ገድሎች የታጀበና አኩሪ ታሪክየተሰራበት ሆኖ እያለ ብዙ ሊባልበት ሲገባ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም መባሉ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ትላንት በጦርነቱ ወቅት ድንቅ አመራር ሲሰጡየነበሩ ጄኔራሎች፤ የመንግስት አመራሮችም፤ ጋዜጠኞችና ታሪክ ምሁራን  ዛሬ በህይወት እያሉ ያልተነገረ ታሪክ ነገ ይነገራል ብዬ አላስብም፡፡

+ በአንድ ወቅት ከጦርነቱ በኋላ የጦርነቱ ግምገማ መሰል ነገር ተጀምሮ በኋላ አቅጣጫዉን እየሳተ ጣት መጠቋቆም ሲመጣ እንዲቆም መደረጉይታወቃል፡፡ ምስጢራዊነቱን ለመጠበቅ ከተፈለገ ቢያንስ በሚመለከታቸዉ ከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እንኳን ግምገማ ማድረግ እየተቻለጭራሽ ለማድረግ አልተፈለገም፡፡ ለመሆኑ በጦርነቱ አሸናፊዎቹ እኛ ለመሆናችን ማረጋገጫ ለሚጠይቁንስ እንዴት ነዉ የምናስረዳዉ? ስለትላንቱ ጦርነት በሚገባ ሳንገመግም ነገ ከኤርትራ ጋር ለሚኖረን ሌላ ዙር ጦርነትስ እንዴት ነዉ መዋጋት የምንችለዉ?

+ እኛ ብቻ ሳንሆን ኤርትራዉያን ራሳቸዉ ጠንቀቄዉ የሚያዉቁትን ሽንፈታቸዉን እኛ ደጋግመን ስላወራንና ስለፎከርን  ትርጉምአይኖረዉም፡፡ ትልቅ ትርጉም ሊኖረዉ ይችል የነበረዉ ጦርነቱን ከአነሳሱ እስከ ፍጻሜዉ በሚገባ በመገምገም ትምህርት ወስደንበት ቢሆንነበር፡፡ ያለፉ ጦርነቶችን ጠንካራና ደካማ ጎናችንን በጥንቃቄ ሳንገመግም ከኤርትራም ሆነ ከሌላ ባላጋራ ጋር ወደፊት ለሚገጥመን ጦርነትበድሮዉ ያረጀ አሰተሳሰብ ወደ ጦርነቱ ልንገባ ስለምንገደድ ገና ሳንዋጋ ለሽንፈት የሚዳርገን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

+ ለመሆኑመከላከያ ሰራዊታችን አባላት የምርምር ጽሁፎችን የሚያቀርቡበት አዳዲስ የጦርነት ንድፈሃሳቦችና ተሞክሮዎች፤ ወታደራዊቴክኖሎጂዎች ጋር ትዉዉቅ ለመድረግ የሚረዱ፤ የዩንቨርስቲ ምሁራንና የምርምር ተቋማት በመከላከያና በደህንነት ጉዳይ ላይ የጥናትጽሁፎችን የሚያቀርቡበት፤ ሰራዊታችንን ስለሃገሩ ብሄራዊ ደህንነት የዉጭ ግኑኝነት ፖሊሲና ስለ ብሄራዊ ጥቅም እንዲያዉቅ የሚያግዝ  አንድእንኳን የህትመት ዉጤት አለዉ? ዘጠና ሚሊዮን ህዝብን የሚወክልና በቢሊዮኖች የሚገመት ዓመታዊ ባጄት ያለዉ ግዙፍ መከላከያ ተቋምከስምንት ገጽ የማትበልጥወጋገንከምትባል አነስተኛ ጋዜጣ ዉጭ በመከላከያ የሚዘጋጅ ሌላ ወታደራዊ መጽሄት አለዉ እንዴ? ከኢትዮጵያጦር ኃይል ዉጭ በመከላከያ አባላት ብቻ ሳይሆን በሲቪሉ ህብረተሰብም የሚነበብ ወታደራዊ መጽሄት ለዉ ሌላ አገር አለ እንዴ?

+ መንግስትን እየመራ ያለዉ ኢህአዴግ በትግሉ ወቅትደርግን የሚያህል ግዙፍ ሰራዊት ሸነፍኩበት ምስጢር…..” እያለ ሲነግረንየነበረዉ ከአያንዳንዷ ዉጊያ በኋላ ቁጭ ቢለዉ መገማገማቸዉን ነበር፡፡ እኛም በኢህአዴግ ጉብዝና ተደንቀን እንደ ኢህአዴግ ለመሆንስንፍጨረጨር እንዳልነበርን ዛሬ ያን የመሰለ ለግምገማ አመቺ የሆነ ጦርነት ለመገመግም ችላ ማለቱ ግራ ቢያጋባን አይፈረድብንም፡፡

+ በገዥዉ ፓርቲ ዉስጥ በተፈጠረዉ መከፋፈል ፓርቲዉን አደክሞና የህዝብ አመኔታን አሳጥቶት ለነቅንጀትና ኢዴፓ መጫወቻለመሆን የዳረገ ጦርነት ነዉ፡፡ ታዲያ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ሁኔታ የዳረገንን ጦርነት ሳንነጋገርበት ፤ሳንገመግመዉ በሚዲያ ሰፊ ዘገባሳይሰራበት እንደተራ ክስተት ተድበስብሶ ሲቀር እንዴት አያስፋም?

መቅድም

በዚህ ጽሁፍ በቅርብ ግዜ ታሪካችን ዉስጥ ሀገራችን ስላስተናገደችዉ ትልቁ ጦርነት፤ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፤ እናወጋለን፡፡ ጦርነቱ በሻእቢያ ድንገተኛ ወረራ የተጀመረ ነዉ በመባሉ እንዴት ድንገተኛ ሊሆን ቻለ? የሚል አብይ ጥያቄም አንስተን መነጋር የዜግነት መብታችን ይፈቅድልናል፡፡

በዚህ ጽሁፍ የምነካከካዉ አጀማመሩ ብቻ ሳይሆን ፍጻሜዉም “ድንገተኛ“ ስለሆነዉ አስገራሚ ጦርነት ነዉ፡፡  የምንነጋገረዉ “Leaders can lose battles, but only soldiers can win them.” የተሰኘዉን የአሜሪካኖች አባባል ትክክለኛነት በተግባር ያረጋገጥንበት ጦርነት ነዉ፡፡

ይህ ጦርነት በታሪካችን ካጋጠሙን ጦርነቶች ሁሉ በተለየ ከዝግጅቱ ጀምሮ በአካሄዱም ሆነ አፈጻጸሙ ላይ ግልጽነት የጎደለዉና የሀገሪቱ አመራርንም እርስበርስ ያጋጨ ወደፊትም በሚገባ መጥራት በሚገባቸዉ በርካታ አወዛጋቢ ኩኔቶች የተሞላ አስገራሚ ጦርነት ነዉ፡፡  ኤርትራን ወይ አስከመጨረሻዉ አልተዋጋናት አልያም በሚገባ አልተደራደርናት አንዱንም በአግባቡ በስኬት መጨረስ አቅቶን ሁሉም ነገር ዳር ሳይደርስና የህዝብን እርካታ ሳይፈጥር በክሽፈት የተጠናቀቀበት ጦርነት ነዉ፡፡

በዚህ ጽሁፍ ስለጦርነቱ መነሾም ሆነ ስለጦርነቱ አካሄድ ዝርዝር ታሪክ ለመተረክ አልሞክርም፡፡  ከአቅሜ በላይ ነዉና፡፡ ዝርዝር ታሪኩን ለታሪክ አጥኚዎችና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ሃላፊዎች ትቼ በእኔ በኩል አቅሜ በፈቀደልኝ መጠን በጦርነቱ ዙሪያ አንዳንድ ጉዳዮችን ብቻ እያነሳሁ አስተያየት ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡ ጦርነቱ እንዴት ባለ መንገድ ተከናወነ በሚለዉ ጉዳይ ላይ ሌሎች በጦርነቱ ዉስጥ ወሳኝ ሚና የነበራቸዉና ዝርዝር መረጃዉን የማግኘት የተሻለ ዕድልና ብቃቱም ያላቸዉ በሚገባ ይጽፉበታል ብዬ ስለማስብ በእኔ በኩል ዋነኛ ትኩረት የማደርገዉ ከጦርነቱ ወታደራዊና ቴክኒካዊ ጣጣ ዉጭ በሆኑ አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ነዉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ ስነሳም አስካሁን ይህ ጦርነት ተገቢዉ ትኩረት ማጣቱ በፈጠረብኝ ቁጭት አቅሙና የተሟላ መሬጃ ያላቸዉ ታሪክ ጸሃፊዎችና በመከላከያና በደህንነት ጉዳይ ባለሙያ የሆኑ ተመራማሪዎች ትኩረት ሰጥተዉ በጉዳዩ ላይ ግምገማዊ ጥናት እንዲያደርጉ ለማነሳሳት ነዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ መከላከያ ሚኒስቴር ለሰራዊታችን አባላት ለተሞክሮ በሚረዳ መንገድ በድፍረት እንዲገመግመዉ ለማሳሳብም ጭምር ነዉ፡፡

መቼም የኤርትራ ጉዳይ ንቀን ብንተወዉም ሊተወን ያልቻለ የጀርባ ህመም ሆኖብናልና በሱ ላይ መነጋገሩ አይከፋም፡፡  እኔም ይሄን ጉዳይ ይዤ መቅረቤ ወቅታዊ አጀንዳ ነዉ ከሚል መንፈስ ተነሳስቼ ነዉ፡፡  በተረፈ በጽሁፉ ዉስጥ አንዳንድ ጉዳዮችን የተረዳሁበት አግባብ በግል የሚያስከፋቸዉ ቢያንስ የማያስደስታቸዉ ወገኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ በተጨማሪ ጦርነቱ ከተካሃደ ከሃያ ዓመታት በኋላም “ጥብቅ ወታደራዊ ምስጢር!” በሚል ሽፋን ዝምታን ለሚመርጡ ሰዎች ስለ ጦርነቱ የሚያዉቁትን እንዲያካፍሉን እጋብዛለሁ፡፡

በተረፈ ሃሳቤን በአጭሩ መቋጨት ባለመቻለ ምክንያት ጽሁፉ አለቅጥ በመርዘሙ በተለያዩ ክፍሎች ለመክፈል ተገድጀአለሁ፡፡  ሁሉም የጸሁፉ ክፍሎች ለአመቺነቱ ተብሎ በተለያዩ ክፍሎች ከመከፈሉ ዉጭ ዋናዉን ጉዳይ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን መነሻ የሚያደርጉ በመሆናቸዉ እርስበርስ ቁርኝት ያላቸዉ ሲሆን በተጨማሪ የአንባቢን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ እያንዳንዱ ክፍል ራሱን ችሎ ሊነበብ በሚችል መንገድ የተዘጋጀ መሆኑን ለአንባቢ መግለጽ እወዳለሁ፡፡  በተረፈ  የሀገር ሉአላዊነት፤ የመከላከያና የደህንነት ጉዳይ  ላይ ለመነጋገገር ፍላጎት የማጣት ችግር እንዳለ ስለማዉቅ አንባቢ ስለ ስፖርት፤ ስለ ፍቅርና ስለ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች የተጻፉ ጽሁፎች በማንበብና በሀገር ሉአላዊነት ጉዳይ ላይ  የሚያተኩሩ  አሰልቺና አታካች የሚመስሉ ጉዳዮች መካካል ያለዉን ልዩነትና ፋይዳዉን በሚገባ እንዲያጤን በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ፡፡

መግቢያ

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዝም ብሎ ጦርነት ብቻ ሳይሆን ሁሉ ነገሩ ድንገተኛ የሆነ አስገራሚ ጦርነት ነዉ፡፡  ሳናስበዉ በድንገት መወረራችን ሳያንስ ሳናስበዉ በድንገት አቋርጠን የወጣንበት አስገራሚ ጦርነት ነዉ፡፡  ሁልግዜም ከጦርነት አዙሪት ወጥታ ለማታዉቀዉ አገራችን ወደንና ፈቅደን ራሳችን ቆስቋሽ ሆነን የጀመርነዉ አንድም ጦርነት በታሪካችን አለመኖሩና ሁልግዜም ተጠቂና ተጎጂ መሆናችን ያለፉ ጦርነቶችን የሚያመሳስላቸዉ ቢሆንም እንደ ኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ግን አስገራሚ ገድል ተሰርቶበትና የተዋጣለት የጦርነት አመራር ብቃትም ታይቶበት እያለ ነገር ግን ለመወራትና ለመነገር የተነፈገ ብቸኛ ጦርነት ነዉ፡፡

ምናልባትም አስቀድመን እንዳሰብነዉ ጠላትን አስከመጨረሻዉ ያለ መደምሰሳችን ጉዳይ ከሆነ በታሪካችን በተደጋጋሚ የታየ እንጂ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ይሄ ጉዳይ በታሪካችን ቢያንስ ከዚያ በፊት ሁለት ግዜ አጋጥሞናል፡፡  አንዱ በአድዋ ጦርነት ወቅት ጣሊያንን እከመጨረሻዉ አሳደን ሳንደመስስ መረብን አሻግረን ብቻ የተዉንበት፤ ሁለተኛዉ ደግሞ የሶማሊያ ወራሪ ጦርን አስከመጨረሻዉ አሳደን አለመደመስሳችን ናቸዉ፡፡

በሶስቱም ወቅቶች ከአቅማችን በላይ የሆነ በቂና አሳማኝ ምክንያቶች ስለነበሩ በዚህ ጉዳይ የሚወቀስ አመራር ሊኖር የሚገባዉ አይመስለኝም፡፡  ምኒልክም መንግስቱም ሆኑ መለስ በዚህ ጉዳይ ሊወቀሱ አይገባቸዉም፡፡

የኢትዮ -ኤርትራን ጦርነት ልዩ የሚያደርጉት ጥቂት ዓይነተኛ መገለጫዎች  አሉት፡፡

* ድንገት ገብተን ድንገት ጥለን የወጣነዉ አጨራረሱ እንደ አጀማመሩ ድንገተኛ የሆነ ጦርነት፤

* የጋራ ጠላታቸዉን በጋራ ለዓመታት ታግለዉ ካስወገዱ በኋላ ለአንድ አስር ዓመት እንኳን እንደመንግስት በሰላም ሀገር ሳያስተዳድሩ በቀድሞወዳጆች መካካል የተካሄደ ጦርነት መሆኑ፡

* ከሁለት ዓመት ባልበለጠ አጭር ግዜ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ መስዋእት የሆኑበት ጦርነት፤

* በወታደሮቻችን ደምና ላብ ያመጣነዉን ድል በተልካሻ ደፕሎማሲ በደካማ ፖለቲከኞች ምክንያት ድሉን የተነጠቅንበት ጦርነት፤

* ወታደራዊ የጦር ሜዳ ድል ዘላቂ ሰላም ካላመጣ በስተቀር ትርጉም አንደማይኖረዉ በተግባር ያረጋገጥንበት፤

* ለዓመታት ባደረጉዉ ሰፊ ዝግጅት እጅግ ተማምኖ በነበረዉ የሻዕቢያ ላይ በአጭር ግዜ ዝግጅት ድል የተገኘበት እጅግ አስደናቂ የዉጊያጥበብና የጦርነቱ አመራር  ብቃት የታየበት፤

* ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚያኮራ ገድል ተሰርቶበት ነገር ግን በታሪክ ተገቢዉን ስፍራ ያልተሰጠዉ ዕድለቢስ ጦርነት.. መሆኑ ወዘተ ናቸዉ፡፡

Photo - Ethiopian soldiers emerge from a trench on a hilltop overlooking the northern Ethiopian [Credit: AFP, 2005]

Photo – Ethiopian soldiers emerge from a trench on a hilltop overlooking the northern Ethiopian [Credit: AFP, 2005]

1/ የጉዳዩ ወቅታዊነትና በተለይ በአሁኑ ወቅት ስለዚህ ጉዳይ ማዉሳት ያስፈለገበት ምክንያት

ስለ ከ18 ዓመት በፊት ስለተከናወነዉ የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ለመጻፍ ስነሳ ይህን የተረሳና ለዉይይት አጀንዳነት ተነፍጎ የቆየ ጉዳይን “አሁን ላይ ማስታወስ ለምን አስፈለገ?” የሚሉ ወገኖች እንደሚኖሩ ሳልገምት ቀርቼ አይደለም፡፡  በእርግጥም ከተካሄደ ሁለት አስርት ዓመታት ሊሞላዉ ጥቂት ብቻ ስለቀረዉ የኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት  ከስንት ዘመን በኋላ ይሄን ያረጀ ጉዳይ አሁን ላይ ማንሳቱ ፋይዳዉ ላይታየን ይችላል፡፡

ጉዳዩ ግን አንዳንዶቻችን እንደምናስበዉ ያለቀለትና ያረጀ ያፈጀ ጉዳይ ሳይሆን ወደፊትም ብዙ ዋጋ ሊያስከፍለንና እርስ በእርሳችን ሊያጣላን የሚችል ገና ያልተቋጨ ብሄራዊ አጀንዳና የሉአላዊነት ጉዳይ ነዉ፡፡ ለማንኛዉም ይህን ጉዳይ አሁን ላይ እንዳቀርብ ምክንያት የሆኑኝ ጥቂት ምክንያቶች መጥቀስ የሚገባን ይመስለኛልና እነሆ፤

* ኤርትራ እኛ እንደጠበቅነዉ ከጠብ አጫሪነት ተግባሯ ለአፍታም ለመታቀብ አለመፈለጓና ይልቁንም ከቀድምዉ በተጠናከረ ሁኔታመቀጠሏ፤

* ኤርትራ እስትራታጂያዊና ታሪካዊ ጠላታችን ከሆነችዉ ግብጽ ጋር ከቅርብ ግዜ ጀምሮ ጠንከር ያለ መቀራረብ መጀመሯ

* ለኛ መልካም አመለካከት ለሌላቸዉ አረብ አገሮች በአሰብና አካባቢዉ ላይ የጦር ካምፕ  እንዲመሰርቱ መፈቀዷ፤

* ኤርትራ መሬቷን ለባእዳን አገራት በማከራየትና ዉስን ከሆነዉ የማእድን ምርት ሽያጭና ዉጭ አገር ከሚኖሩ ዜጎቿ የምታገኘዉን የዉጭምንዛሪ ተጠቅማ የተጣለባትን ማዕቀብም ሳያግዳት ወታደራዊ አቅሟን እያጠናከረች ነዉ የሚለዉ መረጃ መሰማት፤

* ይልቁንም በሀገራችን ላይ ጦርነት ያወጁ የተለያዩ ተጣቂ አማጺ ቡድኖችን መጠለያ በመስጠት ስልጠናና ሎጂስቲካዊ ድጋፍ በማድረግናወደ ኢትዮጵያ ሰርገዉ እየገቡ አደጋ እንዲያደርሱ በማሰማራት ተደጋጋሚ ያልተሳኩ ሙከራዎች ማድረጓና ወደፊትም ቢሆን ከዚህ ድርጊቷእነደማትቆጠብ ብቻ ሳይሆን አመቺ ግዜ ጠብቃ ወደ አጠቃለይ ጥቃት ልትገባ እንደምትችል ከበፊቱ ይልቅ አሁን ግልጽ እየሆነ መምጣቱ

* አጠቃላይ ሁኔታዉ ያሳሰባቸዉ ወገኖች በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ብዙ መጻፍ መጀመራቸዉ በራሱ የጉዳዩንአሳሳቢነትና ወቅታዊነት አመላካች ነዉ፡፡

መንግስታችንም ቢሆን የኤርትራ ድርጊት የበለጠ ያሳሳበዉ መሆኑን አንዱ በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተናገሩት ንግግር ማሳያ ነዉ፡፡  በክቡር ጠ/ሚኒስትራችን አንደበት ሲነገር እንደሰማነዉም ኤርትራን በሚመለከት አስካሁን የነበረዉ  አካሄዳችን ብዙም ዉጤታማ ባለመሆኑ መንግስት ሌላ ተለዋጭ ፖሊሲ በመቅረጽ ሂደት ላይ መሆኑን ነዉ፡፡  በኤርትራ አዋሳኝ የሆነዉ የትግራይ ህዝብም ቢሆን በኤርትራ ትንኮሳ መማረሩን በመግለጽ አደብ የሚያስገዛ መፍትሄ እንዲወሰድ ክቡር ጠ/ሚኒስትሩን በይፋ አስከመጠየቅ ደርሰዋል፡፡

ኤርትራን የሚመለከተዉ ቀጣዩ ፖሊሲ ይዘቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አሁን ላይ ሆኖ መናገር አይቻልም፡፡  አዲሱ ፖሊሲ ምንም ይሁን ምን ሊቀየር የማይችል እዉነታ ግን አለ፡፡  እሱም የመከላከያ ሰራዊታችንን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ ለማይቀረዉ ጦርነት ከመዘጋጀት ዉጭ ለደህንነታችን የተሻለ ዋስትና አለመኖሩ ነዉ፡፡ ተጨባጭ የሆነ የመከላከያ አቅም ፈጥረን አስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ይዘን መገኘት ይኖርብናል፡፡

በሌላ በኩል አዲሱ የመንግስት ፖሊሲ በማንኛዉም መንገድ ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት የማያደርግ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረዉም የሚሉ ወገኖች በርካታ ናቸዉ፡፡  የባህር በር ጥያቄ እንደ ቀድሞዉ በሰበብ አስባቡ ወደ ጎን የሚገፋ አንዳይሆን ወቅቱ የግድ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትራችን አዲሱ ፖሊሲያቸዉ ይህን ቁልፍ ጉዳይ በአጀንዳነት ማካተቱን እርግጠኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡

በተረፈ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በአንድ በኩል ዛሬዉኑ እርምጃ ካልወሰድን ለሚሉ ጦርነት ናፋቂ በሆኑ ጀብደኞች ምክር ተገፋፍተዉ ያልተገባ እርምጃ እንዳይወስዱና እንዲሁም ምንም ችግር አይኖርም የሚሉ አዘናጊና ልፍስፍስ አስተያየቶች ተጫጭኖአቸዉ መዘናጋት እንዳይፈጠር በቅድሚያ ማሳሰብ የዜግነት ግዴታችን ነዉ፡፡

ይህ ጉዳይ በተለይ በአሁኑ ወቅት መነሳቱ ለምንድነዉ? የሚል ጥያቄ እንደሚነሳም አዉቃለሁ፡፡ እኔ በበኩሌ ከዓመታት በፊት መነሳት የነበረበት ግን ደግሞ በቁምነገር ባለመቆጠሩ ሳይነሳ የቀረ ጉዳይ በመሆኑ አሁን በሁሉም አቅጣጫ ስጋት ባጠላበት ወቅት ላይ ነቃ እንድንል ያደርገናል ከሚል ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ በዙሪያችን ወዳጅ ባልሆኑ ኃይሎች ከበባ ዉስጥ እየገባን በመሆኑ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት አለብን፡፡ የኛ ሰላም ወዳድነታችን የታሪካዊ ጠላቶቻቸንን አንጀት ሊያራራልን አልቻለም፡፡ አልሻባብ፤ኤርትራና ግብጽ የሚፈጥሩብን ስጋት ሳያንሰን እነ ኳታር፤ቱርክ፤ሳዉዲ አረቢያ፤ኢራን ፤ኢራቅ አረብ አምሬትስ ወዘተ የመሳሰሉ አገሮች በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያለወትሮአቸዉ በከፍተኛ ጥድፊያ የጦር ሰፈር እየገነቡ ነዉ፡፡

ያን ተከትሎ በኤርትራ፤በጂቡቲና በሶማሊያ ያልሰፈረ ምድረ አረብ የለም፡፡ ጂቡቲ ላይ ጦር ሰፈር ያላቸዉ ፈረንሳይ፤አሜሪካና ቻይናም ሁኔታዉ በኛ ላይ ሊፈጥር ስለሚችለዉ ስጋት ደንታ ያላቸዉም አይመስሉም፡፡ ትንሽ በሁኔታዉ መረበሽ የታየባት ኢስራኤል ብቻ ነች፡፡ እሷም ብትሆን መጨነቋ ለራሷ ብላ እንጂ የኛ ደህነነት አስግቷት አይደለም፡፡

በተለይ ኤርትራ በዚህ አጋጣሚ ያልጠበቀችዉን ዶላር ማፈስ ከጀመረች ወዲህ ኢሳይያስና ባለስልጣኖቻቸዉ ያለወትሮአቸዉ  ወደ ዉጭም ወጣ ወጣ ማለት መጀመራቸዉና ከግብጾች ጋርም አብረዉ ሲዶልቱ እንደነበር መዘገቡ ለነገ ምን እየተደገሰልን እንደሆነ በማሰብ መስጋታችን አይቀርም፡፡

ይህ ሁሉ እየሆነም መከላከያ ሰራዊታችን የጸጥታ ችግር በታየበት ጎረቤት አገር ሁሉ እየተላከ የነሱን ሰላም ለማረጋገጥና በተዘዋዋሪ መንገድም  ቢሆን ለኛም ደህንነት የስጋት ምንጭ የሆኑ ኃይሎችን እዚየዉ ከምንጩ ለማድረቅ እየተንቀሳቀሰ አኩሪ ስራ እየሰራ እንደሆነ እናዉቃለን፡፡ የደቡብ ሱዳን ጉዳይም ለብቻዉ ሲታይ ከኤርትራም ያለነሰ የስጋት ምንጭ ሊሆንብን እንደሚችል ገና ከአሁኑም ደህንነታችንን የሚፈታተኑ ምልክቶች መታየታቸዉ አልቀረም፡፡

ይህ ሁሉ እያለም እዚህም እዚያም በየስርቻዉና በየጎጡና መንደሩ በየዞኑና በየክልሎች በሰበብ ባስባቡ የሚነሱ የርስበርስ መቆራቆዝና የህዝቦች ግጭት ለሻዕቢያና መሰሎቹ እንደመልካም አጋጣሚ የሚቆጠር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ይህን የመሰሉ የዉስጥ ችግሮቻችን ለመፍታት እየተጠቀምን ያለነዉ ዜዴ ፍጥነት የጎደለዉ መሆኑ ሲታሰብ ለወደፊቱ ለአንድነታችን እንቅፋት እንዳይሆን መስጋታችን አይቀርም፡፡

በዚህ ምከንያትም መላዉ የጠፋቸዉ ዜጎች ከየማህበራዊ ሚዲያዉ እንደ ልብ የሚገኘዉን ወሬ ከዚህም ከዚያም እየቃረሙ እዉነቱንና ሃሰቱን በደንብ እንኳን ሳያጣሩ በስጋት መንፈስ “ነገ ምን ይፈጠር ይሆን?” እያሉ እርስበርሳቸዉ በጭንቀት መነጋገራቸዉ አልቀረም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያዉም ግልጽ የዉጭ ጥቃት ሊኖር ይችላል ከሚል ስጋት በመነሳት በመንግስት ወይም በመከላከያ አካባቢ የተለየ የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆንም ለማረጋገጥ ሲጠይቁና ሲያጠያይቁ ይታያሉ፡፡

መከላከያችን በምን ያህል ደረጃ ሉአላዊነታችንን ለመጠበቅ ዝግጁ እንደሆነም ለማወቅ የሚሞክሩም አሉ፡፡ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊታችን የትኛቹን አዳዲስ ትጥቆች ገዝቶ እንዳስታጠቀም ለማወቅ ይኳትናሉ፡፡ ምናልባት ኤርትራ ድጋሚ ብትተናኮለን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት የሚያበቃን በቂ ዝግጅት እንዳለን ለማወቅ ብዙ ይደክማሉ፡፡ በተለይ  ከህዳሴዉ ግድብ ጋር ተያይዞ ግብጽና ኤርትራ ተባብረዉ ለጠብ ቢፈልጉን ወይንም የህዳሴ ግድባችን ላይ አንዳች ደባ ለመፈጸም ቢቃጡ ለመከላከልም ሆነ የአጸፋ እርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችለን አቅም እንዳለን ለማጣራት ብዙ ይሞከራል፡፡

መቼም ህዝብ ሲጨንቀዉ ብዙ ያስባል፡፡ የሚያሳዝነዉ ግን የህዝቡን ስሜት ተረድቶ የሚያጠግብ ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጥ ባለስልጣን አለመኖሩ ነዉ፡፡  ለህዝቡ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ስለሚገኝበት ሁኔታ፤ አቅሙን ለማሳደግ አስካሁን ምን እንደተሰራ ፤ ለወደፊቱም ምን ለመስራት እንደታሰበ ፤ በአካባቢያችን ካንዣበበዉ ስጋት አንጻር በምን ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ የሚያስረዳ አንዳችም አካል የለም፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማም ቢሆን ሰራዊታችን ስለሚገኝበት ሁኔታ በቦታዉ ተግኝቶ ለማጣራት ከመሞከር ይልቅ የመከላከያ ባለስልጣናት በስንት ግዜ አንዴ በሸንጎዉ አዳራሽ ተገኝተዉ የሚሰጡትን ገለጻ ከማዳመጥ በስተቀር ለምን እንዲህ አልተደረገም? ለምንስ ይሄ ሆነ? የሚባልበት አሰራር አልተለመደም፡፡ የሀገሪቱ ህግ አዉጭ አካል  የሀገሪቱን የደህንነት ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ  ለመረዳት የሚያስችለዉ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገዉ የራሱ የሆነ ሌላ አማራጭ የመረጃ ምንጭም የለዉም፡፡

የሀገሪቱ የግል ሚዲያዎች የመከላከያና የደህንነት ጉዳይ ላይ የራሳቸዉን ነጻ ዘገባ ለመስራት ፈጽሞ የሚመርጡት ነገር አይደለም፡፡ በሀገራችን ከሁሉም ከፍተኛዉ ስልጣን አካል የሆነዉ የሀገሪቱ ህግ አዉጭ አካል (ፓርላማ) የደህንነትና ሉአላዊነት ጉዳይ ላይ ተቀዳሚ ኃላፊነት ያለበተን ያህል አልፎ አልፎ ካልሆነ በስቀተር የመከላከያን ሁኔታ ከስር ከስሩ አዘወትሮ ስለማይከታተል አንድ ቀን ስለ ኤርትራ ድጋሚ ወረራ ወይም ስለግብጽ ጥቃት መሰንዘር ከዜጎች ጋር እኩል ለመጀመሪያ ግዜ በዜና ለማድመጥ እንዳይገደድ እሰጋለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆን የቱንም ያህል ኑሮ ቢከብደዉም፤ “ዲሞክራሲ!” የምትባለዋ ነገር አልሟላ እያለች ቢታስቸግረዉም ሀገሩ ሰላም ትሁን እንጂ በሌላዉ ነገር ብዙም የሚማረር ህዝብ አይደለም፡፡ ምንም ባይሟላለት ምንም ያህል በኑሮዉ ቢማረር ምንግዜም በመንግስት ተስፋ የማይቆርጥ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ከቶ ያለ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ህዝቡ በጭራሽ በይቅርታ የማያልፈዉ ጉዳይ ቢኖር የሀገሩ ሉአላዊነት ጉዳይ ነዉ፡፡ በሀገሩ ሉአላዊነት መደፈር ላይ ምንም ዓይነት ተልካሻ ምክንያትና ሰበብ እንዲነገረዉ አይሻም፡፡ ለዚህም ነዉ በሀገሩ ጉዳይ ላይ የሆነ አሳሳቢ ነገር በሰማ ቁጥር መብከንከኑ፡፡

2/ የኢትዩኤርትራ ጦርነት የሕዝብና የመንግስት አንድነት እንደገና የታደሰበትና የህዝቡ አልበገር ባይነት በድጋሚ የተረጋገጠበትአጋጣሚ ነበር፡፡

የኢትዮ–ኤርትራ ጦርነት ሳንፈልገዉ የተቃጣብን መጥፎ አጋጣሚ ቢሆንም ነገር ግን መላዉን ህዝብ በአንድነት እንደ አንድ ሰዉ ሆኖ እንዲቆም ማድረግ ያስቻለ አንድ ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ነበር፡፡ በእኔ እድሜ ይሄኛዉ ሁለተኛ አጋጣሚ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያዉ በ1969 ዓ/ም ሲሆን የሶማሊያ የእብሪት ወረራ እንደተሰማ መላዉ ህዝብ በቁጣ የተነሳበት ወቅት ነበር፡፡

ህዝቡ በዚያን ጊዜ በደርግ ስርአት ግራ ተጋብቶ በቀይ ሽብር  እርምጃ ተስፋ ቆርጦ በነበረበት ወቅት ላይ ነበር ጦርነቱ የተጀመረዉ፡፡ ህዝቡ ለአገዛዙ (ለደርግ) ጥላቻ እንደነበረዉ ባይካድም  ነገር ግን ይህን ጥላቻዉን ለጊዜዉ ወደ ጎን አድርጎ ከመንግስት ጎን በመቆም ለዘመቻዉ እንደ አንድ ሰዉ ሆኖ  በጋራ ተንቀሳቅሷል፡፡ (እንደ ኢህአፓና መኢሶን ከሃዲ ከሆኑ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ዉጭ)፡፡ ስለዚህ የኤርትራ ወረራ ለእኔ በህይወቴ ለሁለተኛ ጊዜ ህዝብ በሉአላዊነቱ ላይ የማይደራደር መሆኑን ያሁበት አጋጣሚ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በነበሩት ስርአቶችም  ሆነ በመንግስታቱ ላይ ደስተኛ ሆኖ ባያዉቅም በሃገሩ ሉአላዊነት ላይ ግን ተደራድሮ አያዉቅም፡፡ በሶማሊያ ጦርነትም ሆነ ከኤርትራ ጋር በነበረዉ ጦርነት ወቅት የታዬዉ የህዝብና የመንግስት አንድነት መነሳሳት በብዙ መልኩ ተመሳሳይ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጦርነት ግን ጠንከር የሚል ይመስለኛል፡፡ ለዚህም ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶችን መጥቀስ እችላለሁ፡፡

2.1/ ከሶማሊያ ጋር ያደረግነዉ ጦርነት በብዙ መጥፎ አጋጣሚዎች የተሞላ ነበር

በወቅቱ ጠንካራ የሚባል ማእከላዊ መንግስት ያልነበረበትና ህዝብና መንግስት  የማይደማመጥበት  እጅግ መጥፎ ጊዜ ነበር፡፡ የሶማሊያ  ወረራ ባካሄደችብን  ወቅት አገሪቱ እጅግ ዉስብስብ ሁኔታ ዉስጥ ስለነበረች ጦርነት ለማካሄድ የሚያስችላት ፤ፖለቲካዊ ፤ወታደራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲዊ  አመቺ ሁኔታዎች ጨርሶ አልነበረም፡፡ ለምሳሌ አንዳንዶቹን የወቅቱን ሁኔታዎች ለማስታወስ ያህል፤

* በአብዮትና በጸረአብዮት ፤በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር እርስበርስ ስንፋጅና ስንተላለቅ የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ ህዝቡም ሆነ ወጣቱከመንግስት ጋር ዓይንና ናጫ የሆነበት ወቅት ነበር፡፡ ማንም ከማንም ጋር የማይስማማበት ይልቁንም ለግዲያ የሚፈላለግበት ወቅት ነበር፡፡የአንድ እናትና አባት ልጆች በፖለቲካ አቋም ልዩነት እርስበርስ ለግድያ አመቺ ጊዜ የሚጠብቁበት፤ የመንግስት አመራሮችና የደርግባለስልጣናት አንዱ ሌላዉን ባለማመኑ ሰበብ እየፈለጉ የሚገዳደሉበት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ነጭና ቀይ ሽብር እየተባባሉ አርስበርስየሚጨራረሱበት መጥፎ ጊዜ ነበር፡፡ በዚያ መጥፎ ጊዜ ሁሉም ስለራሱ እጣፋንታ እርግጠኛ ባልነበረበትና ለራሱ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያጭራሽ የሚያስብላትና የሚያስታዉሳት ባልነበረበት ወቅት ነበር ጦርነት የተከፈተብንም፡፡

* መላዋ ኤርትራ በአማጽዉ ኃይል (ሻእቢያ) ከአስመራና ከምጽዋ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በቁጥጥር ስር  ዉላ አስመራንምተቆጣጥረዉ ከዛሬ ነገ ነጻነታቸዉን ያዉጃሉ ተብሎ በሚሰጋበት ወቅት ነበር ሶማሊያ ወረራ ያደረገችዉ፡፡ በተጨማሪ እንደ ኢዲዮን የመሳሰሉታጣቂ ቡድኖችም የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረጉ የነበረበት ወቅት ነበር፡፡

* አንዳንድ በወቅቱ የነበሩ የመንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሶማሊያን ወረራ በግልጽ በመደገፍ የገዛ ህዝባቸዉን በማደናገርና ሰራዊታችንወራሪዉን ጦር አምርሮ እንዳይዋጋ በማሻጠር ታሪክ ይቅር የማይላቸዉን በደል ሲፈጽሙ የነበረበት ወቅት ነዉ፡፡ ተራዉ ተዋጊ ሰራዊት ብቻሳይሆን ከፍተኛ የጦሩ አዛዦች ሳይቀሩ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በመታቀፋቸዉ የድርጅት ስሜት ስየተጫጫናቸዉ የሰከነ አመራርለመስጠትም ተነሳሽነቱ ያልነበራቸዉ ነበሩ፡፡ የአገራቸዉን ሉአላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም ከአገዛዙ ከደርግ ለይተዉ ማዬት የተሳናቸዉፖለቲከኞች  ህዝቡ ለመንግስት ድጋፍ እንዳይሰጥና ሰራዊቱም እንዳይዋጋ ለማድረግ ብዙ ጥረዋል፡፡ በሰራዊቱ ዉስጥ ሰርገዉ በመግባትእንዳይዋጋ ቅስቄሳ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ምርጥ አዛዦችን እየነጠሉ ከጀርባ ተኩሰዉ በመግደል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፡፡ በዚያ ሁኔታዉስጥ ነበር ከሶማሊያ ወራሪ ጦር ጋር ሰራዊታችን ተፋልሞ ሉአላዊነታችንን ያስከበረዉ፡፡

* በወቅቱ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ከአራት ክፍለ ጦር የማይበልጥና በሰዉ ኃይልም ቢሆን 35 ሺህ አካባቢ ብቻ የነበረና ለዚያዉምበመላ ሀገሪቱ እንደጨዉ የተበተነ በትጥቅ ደረጃም ከታዬ እጅግ አሮጌ መሳሪያ የታጠቀ ነበር ፡፡ በአንጻሩ ለአስራ አራት ዓመታት በዘመናዊመሳሪያ ሲደራጅ የቆየዉን የሶማሊያን ወራሪ ግዙፍ ሰራዊት ለመመከት የምንችልበት አቅም አልነበረንም፡፡ አገራችን ግልጽ ወረራተቃጥቶባትና በሶማሊያ ጦር ህዝባችን አየተጨፈጨፈ በነበረበት ሰዓት ስለጉዳዩ የተሟላ መረጃ የነበራትና የረዥም ዘመን ወዳጃችን የነበረችዉ አሜሪካ ሌላዉ ቀርቶ አስቀድመን ለከፈልናት $100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘቡን ተቀብላ መሳሪያዉን ግን ለመስጠትፈቃደኛ ባለመሆኗ ራሳችን ለመከላከል እንዳንችል በመደረጋችን ሌላ አማራጭ መፍትሄ የጠፋበት ወቅት ነበር፡፡ አሜሪካ ይባስ ብላ በሳዉዲአረቢያ በኩል $200 ሚሊዮን እርዳታ ለሶማሊያ እንዲደርሳት እንዳደረገች ይታወቋል፡፡ የሶማሊያን  የጦር ዝግጅት ደረጃንና የኛን ለጦርነቱያለመዘጋጀት  በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችለን  አንዱ ማሳያ የሶማሊያ ጦር ወረራዉን በጀመረ በጥቂት ወራት ዉስጥ ያን ሁሉ ርቀት ተጉዞ እስከሐረርና ድሬዳዋ መድረስ መቻሉ ነዉ፡፡

* የጊዜዉ መንግስት (ደርግ) ዘዉዳዊዉን ስርአት አስወግዶ ስልጣን ከያዘ ገና ሁለት ዓመት እንኳን ባልሞላበትና  ራሱም እንደ መንግስትባልተጠናከረበት ወቅት ላይ የተሰነዘረ ወረራ ነበር፡፡

* ደርግ ጁኒየር በሆኑ መኮንኖችና የበታች ሹሞች የተቋቋመና ሰፊ የጦርነት ተሞክሮ የነበራቸዉን ሲኒየር መኮንኖችን፤  ጄነራሎችንናኮሎኔሎችን ግማሹን ያለጊዜያቸዉ በጡረታ አሰናብቶ፤ ግማሾቹን አስሮና ገድሎ ሰራዊቱን አመራር አልባ ባደረገበት ወቅት ነበር ጦርነቱየተነሳዉ፡፡

አገራችን በወቅቱ ደርግ ይከተለዉ በነበረዉ የተዛባ የርዕዮተዓለም አቅጣጫ ምክንያት ለዘመናት የቅርብ አጋራችን የነበረችዉ አሜሪካ ፊቷን ማዞሯ ሳያንስ በምትኩ ሌላ አጋር የሚሆነን ወዳጅ አገር ባላዘጋጀንበትና ደርግም ራሱ እንደ መንግስት በሌሎች መንግስታት በደንብ እዉቅና ባላገኘበት ወቅት ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሶማሊያ ለወረራ እየተዘጋጀች መሆኑን ደርግ ከሰባት ወራት በፊት ጀምሮ መረጃዉ ቢኖረዉም አጋር የሚሆነዉ አንድም አገር አስቀድሞ ባለማዘጋጀቱና የዉጭ ድጋፍ ሊያሰጠዉ የሚችል ዲፕሎማሲያዊ ስራም መስራት ባለመቻሉ በሁሉም ነገር ተበልጠን እጃችንን አጣጥፈን ወረራዉን ተቀበልነዉ፡፡

በኋላ የጎረፈዉ ወታደራዊም ሆነ ዲፕሎማሲዊ ድጋፍ (ሶቭየት ህብረት ፤ኩባ፤ የመን፤ምስራቅ ጀርመን) እጅግ ዘግይቶ ቢሆንም ለሉአላዊነታችን መከበር ትልቅ እገዛ አድርጎልናል፡፡ በዚህም ባለዉለታችን ናቸዉ፡፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት  በሰዉ ኃይሉም ሆነ በትጥቁ ደካማ ሆኖ እንዲቆይ በማድረግ ለሶማሊያ ወረራ እንድንጋለጥ በማድረግ ረገድ ንጉሱም ጭምር ከታሪክ ተጠያቂነት አያመልጡም፡፡ ይህ ሲባል ንጉሱ አንዳችም ጥረት አላደረጉም በሚል አሰተሳሰብ አይደለም፡፡

አጼ ኃይለሥላሴ በወቅቱ እጅግ ዘግይተዉም ቢሆን የሶማሊያ አዝማሚያ ሲላሰጋቸዉ የጦር መሳሪያ ፍለጋ በ1965ዓ/ም የወቅቱ ወዳጃቸዉና ዋነኛ የመሳሪያ አቅራቢያቸዉ ወደነበረችዉ አሜሪካ አቅንተዉ ፕሬዝዳንት ኒክሰንን ቢማጸኑም “ሱማሊያ አትወጋችሁም” በሚል ማጽናኛ ይሁን ማዘናጊያ አንድም መሳሪያ ሳይሰጧቸዉ ነዉ ያሰናበቷቸዉ፡፡ ንጉሱ በዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ሩሲያ በማቅናት ተመሳሳይ ጥያቄ ቢያቀርቡም የሩሲያ ባለስልጣናትም ከአሜሪካ ጋር የተመካካሩበት ይመስል ልክ አሜሪካኖች እንዳሉት “ሶማሊያ አትወጋችሁም” የሚል መልስ ነበር ለንጉሱ የሰጡት፡፡ ንጉሱ በመጨረሻ ወደ ቻይና በመብረር ጥቂት መሳሪያዎች ከማግኘት በስተቀር የረባ ድጋፍ ሳያገኙ ቀሩ፡፡

ንጉሱ መሳሪያ በነጻ ወይንም በብድር ማግኘት እንደማይችሉ ዘግይተዉም ቢሆን በመረዳታቸዉ በገንዘብ መግዛት ይሻላል በሚል እንደምንም የዉጭ ምንዛሪ  አፈላልገዉ ለአሜሪካ መንግስት ቅድመ ክፍያ ቢያደርጉም የተጠየቁት መሳሪያዎች ወደ ሀገር ቤት ከመግባታቸዉ በፊት ንጉሱ ከስልጣን ወረዱ፡፡ ከዚያ በኋላ አሜሪካ ለጥቂት ጊዜ የተወሰኑ መሳሪያዎችን መስጠቷ ባይቀርም ነገር ግን የካርተር ወደ ስልጣን መዉጣት ተከትሎና ደርግ በተከታታይ በወሰዳቸዉ እርምጃዎችና በተከተለዉ የሶሻሊስት ርዕዮተዓለም በመከፋት በአጸፋዉ አሜሪካ አንዳችም መሳሪያ ለኢትዮጵያ እንደማታቀብል አስታወቀች፡፡ የሶማሊያ ለወረራ መዘጋጀት  ከጥርጣሬ በላይ ተግባራዊ በሆነበትና የአሜሪካ የረዥም ዘመን ወዳጅ የሆነችዉ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ወረራ ተፈጽሞባት እያዩ አሜሪካኖች ከኢትዮጵያ ፊታቸዉን አዞሩ፡፡

በአጭር ጊዜ ዉስጥ 90% የሚሆነዉ የኦጋዴን ግዛታችን በሶማሊያ ወራሪ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ዉሎም አሜሪካ ልታግዘን አልሞከረችም፡፡ ደርግ የኋላ ኋላ ከሶሻሊስቱ ጎራ የመሳሪያና ፖለቲካዊ ድጋፍ ስለጎረፈለት በመልሶ ማጥቃት ሉአላዊነታችንን በማስመለስ አስመስጋኝ ስራ መስራቱ ባይቀርም ሃላፊነት እንዳለበት መንግስት ሲታይ ግን በሀገሪቱ ዉስጥ ፈጥሮ በነበረዉ ምስቅልቅል ሁኔታ ምክንያት በመጀመሪያ ሰባት ወራት ሶማሊያ ላደረሰችብን  አንገት የሚያስደፋ ዉርደት በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን አይድንም፡፡ የሀገሪቱ ሉአላዊነት በጠላት ተደፍሮ እያለ በአንድነት መቆም የተሳነዉን የመንግስት ስርአት የፈጠረዉ ደርግ በመሆኑ ተጠያቂ ቢሆን አይበዛበትም፡፡  አገሪቱን ወዳጅ አልባ ያደረጋት ደርግ በመሆኑ ጭምር ነዉ፡፡

2.2/ በሱማሊያ ወረራ ወቅት ህዝቡ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጥላቻ በሰራዊቱ ላይ ደግሞ ጥርጣሬና ፍርሃት ነበረዉ

የሶማሊያዉ ወረራ ከመነሳቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ጀምሮ ህዝቡ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጥላቻ መኖር ብቻ ሳይሆን በሰራዊቱ ላይም ቢሆን የነበረዉ አመለካከትም በፍርሃትና በጥርጣሬ የተሞላ ነበር፡፡ በራሱ በደርግ አመራር ዉስጥም ሳይቀር ከፍተኛ ልዩነትና የመጠፋፋት መንፈስ ነፍሶ አንዱ ሌላዉን በዓይነ ቁራኛ የሚጠብቅበት ወቅት ነበር፡፡

የኤርትራ ጉዳይም ሊያበቃለት የመጨረሻዉ ጫፍ ላይ የደረሰበት ወቅት የነበረና የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊትም ጦርነት ለማካሄድ የሚችልበት አንዳችም አቅም ያልነበረዉና አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች በሚነዙት አፍራሽ ፕሮጋንዳ ሰራዊቱን በመከፋፈል ጠንክሮ እንዳይዋጋ ያደረጉ ክስተቶች የተሞሉበት ወቅት ነበር፡፡ ለማስታወስ እንኳን በሚያስጠላ ደረጃ  የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና መንግስቱ ኃይለማሪያምን ለይተዉ ማዬት ያልቻሉት እነ ኢህአፓና መኢሶን ወራሪዉን ሰራዊት በመደገፍና በኛ ሰራዊት ላይ በማሻጠር በአገርና በህዝብ ላይ የፈጸሙትን ታሪክ ይቅር የማይላቸዉን ደባ ስናስታዉስ በወቅቱ የተሟላ የመንግስትና የህዝብ አንድነት መንፈስ ነበር ለማለት ያዳግታል፡፡

የማይካድ ነገር ሀዝቡ የሀገሩ ሉአላዊነት ጉዳይ ሆኖበት መንግስትን እየጠላም ቢሆን ለሉአላዊነት የሚደረገዉን ተጋድሎ ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ሴት ወንድ ሳይባል በነቂስ ወጥቶ የተጠየቀዉን ሁሉ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በአጭር ግዜ ዉስጥ በመቶ ሽህ ዩሚቆጠር ሚሊሽያ ሰራዊት አሰልጠኖ አስታጥቆ ማዝመት የተቻለበት ከፍተኛ ብሄራዊ መነሳሳት የታየበት አጋጣሚ ነበር፡፡

ያሁኑ ከኤርትራ ጋር የተደረገዉ ጦርነት ከምንግዜም የበለጠ መላዉን ህዝብ በወራሪዉ የሻዕቢያ ሰራዊት ላይ በአንድነት ማቆም ያስቻለ የመንግስትና የህዝብ አንድነት ከምንግዜም በላይ የተረጋገጠበት ታላቅ ታሪካዊ አጋጣሚ ነበረ ማለት ይቻላል፡፡ የሻዕቢያን የድፍረት ወረራ ተከትሎ በጊዜዉ የነበሩት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለህዝቡ ጥሪ ባደረጉለት መሰረት ጥሪዉን እንደሰማ ኦሮሞዉ፤ ትግራዩ፤ አማራዉ፤ ሶማሌዉ፤ ጉራጌዉ ፤ኮንሶዉ ፤ደራሼዉ ፡ጋሞዉ፡ ወላይታዉ፤ ሲዳማዉ አፋሩና ጋምቤላዉ ወዘተ አንዱ ሌለዉን ሳይቀድሙኝ ልቅደም በሚመስል ሩጫ ጦር ግንባር ለመገኘት የበቃበት ወቅት ነበር፡፡

እንደ ደርግ ወቅት የግዴታ አፌሳ የለ! በግድ ዝመት የለ! በግድ ለጦርነቱ ገንዘብ አዋጣ የለ! ህዝቡ ራሱ ልጆቹን መርቆ ከላከ በኋላ ጭራሽ ይሄም አንሷል ብሎ ሰንጋ በሬና የፍዬል ሙክቱን እየነዳ ጦር ግንባር ምሽግ ድረስ የመጣበት ወቅት ነበር፡፡ ከአፋርና ከሶማሌ ክልል ልጆቻቸዉንና ባሎቻቸዉን ለማበረታታት ያን ሁሉ አገር አቆራርጠዉ ጦር ግንባር ድረስ የሚመጡ ዜጎች ብዙ ነበሩ፡፡

በዉጭ አገር የሚኖሩ የመንግስት ተቃዋሚ የነበሩት ሳይቀር ከአሜሪካ ከአዉሮፓ ከመካከለኛዉ ምስራቅ በቡድንና በግል እየመጡ በየጦር ግምባሩ እየዞሩ ሰራዊታችንን ሲያበረታቱ ማዬትን የመሰለ የሚያስደስት ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ በወቅቱ ከታዘብኩትና እጅግ ከአስገረሙኝ ሁኔታዎች ዉስጥ አንዱ እድሜያቸዉ ለዉትድርና ብቁ የማያደረጋቸዉና በዚህ ምክንያት ላንመለመል እንችላለን ብለዉ የተጠራጠሩ ወጣቶች ሰራዊት ጭነዉ ወደ ጦር ግንባር በሚያመሩ መኪናዎች ላይ እየተንጠላጠሉ ጦር ግንባር ድረስ በገዛ ፈቃዳቸዉ የመጡ በርካታ ወጣቶች እንደነበሩ አስታዉሳለሁ፡፡

3/ አገራችን ከኤርትራ ጋር ያደረገችዉ ጦርነት ለበርካታ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች መከሰት አጋጣሚና ምክንያት የሆነ ታሪካዊ ጦርነት ነዉ

ጦርነቶች አዉዳሚ ባህሪያቸዉ እንዳለ ሆኖ አንዳንዴ የጦርነቱን ፍጻሜ ተከትሎ በሌላ ጊዜ ብዙም የማይጠበቁ ለየት ያሉ ሁኔታዎች በሀገሪቱ ዉስጥ መከሰት ምክንያት ሲሆኑ ይታያል፡፡ በዚህ ረገድ በእኔ እይታ ትልቅ ፋይዳ አላቸዉ ብዬ ከማስባቸዉ መካከል ጎላ ጎላ ያሉትን ለአብነት ያህል ቀጥዬ ለመጠቃቀስ እሞክራለሁ፡፡

* የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስርአት ህዝቡንበጠባብ ጎሰኝነት ስሜት እርስበርስ እንዲቃቃር ስላደረገ አንድ ችግር  ቢፈጠር አገሪቷ ከመቅፅበትትበታተናለች እንዳልተባለ የመንግስትንና የህዝብን አንድነት የስርአቱንም ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያስቻለ አንድ አጋጣሚ ይመስለኛል፡፡

* የኢትዮጵያ መንግስት በቀጥታ ወደ ጦርነት ከመግባቱ በፊት በቅድሚያ ችግሩን በሰላም ለመፍታት ያደረገዉ ጥረትና ለሰላም ያሳየዉቁርጠኝነት አገራችንን በዉጭዉ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትና ተሰሚነት እንድታገኝ አስችሏል፡፡

* ከጦርነቱ መከሰት ጋር ተያይዞ በመንግስት ፖለቲካ አመራር አካባቢ በተለይም በገዢዉ ፓርቲ ዉስጥ ለተከሰተዉ እርስ በርስ መከፋፈልዋነኛዉ መንስኤም ይሄዉ ጦርነት መሆኑን የሚታወቅ ነዉ፡፡ በተጨማሪ በመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችና በሀገሪቱ የሲቪል አመራር መካከልምጤናማ ግኑኝነት እንዳልነበር ይልቁንም የሲቪልወታደር ግንኝነቱ ትልቅ ክፍተት ያለዉ እንደነበር ያመላከተ አጋጣሚ ነዉ፡፡ ገዢዉ ፓርቲምችግር እንዳለበት ተረድቶ ራሱን በሚገባ እንዲፈትሽና አንዳንድ ማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ሲላስቻለዉ ከዚያ በኋላ በነበሩትጊዜያት በፊት ያልነበረዉን ጥንካሬ በሂደት ይዞ እንዲገኝ ማድረግ ያስቻለ ክስተት ይመስለኛል፡፡

* በመከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥም ከጦርነቱ በፊት ብዙ ግምት ያልተሰጣቸዉ በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮች፤ የመብት ጥሰቶችና አድሎአዊአሰራሮች በበላይ አመራሮች ቸልተኝነት መፍትሄ ሳይሰጣቸዉ ተከማችተዉ የነበሩበትና የጦርነቱ ማብቃት ተከትሎ በተደረጉት የተሃዲሶእንቅስቃሴዎችና ሰፋፊ ግምገማዎች ታፍነዉና ወይም ችላ ተብለዉ የነበሩ የተከማቹ  ችግሮች በከፍተኛ ጥረት ሊቀረፉ የቻሉበት ሁኔታነበር፡፡ ከጦርነቱ በኋላ በነበሩ ግምገማዎች ይፋ የተደረጉ ችግሮችን ዓይነትና ብዛት ለታዘበ ሰዉ ይሄን ሁሉ ችግር ተሸክሞ ሰራዊታችንበጦርነቱ እንዴት ሊያሸንፍ ቻለ? ብሎ መደነቁ አይቀርም፡፡

* ከደርግ ዉድቀት በኋላ የቀድሞዉን ሰራዊት ሳያካትት በአዲስ መልክ ለተቋቋመዉ መከላከያ ሰራዊት ብቃቱን ለመፈተሽ ያስቻለ ትልቅአጋጣሚም ነበር፡፡ መንግስት የሀገሪቱን ነባር ሰራዊት አፍርሶ አገሪቱን ለአደጋ ተጋላጭ አድርጓል የሚሉ ትችቶች በፊት በተደጋጋሚ ሲነሱእንዳልነበር ከጦርነቱ በኋላ ስለዚህ ጉዳይ እምብዛም ሲነገር አልተደመጠም፡፡ በጦርነቱ ወቅት በርካታ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ፈቃደኛና ብቁሆነዉ የተገኙት ተመልምለዉ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዳደደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በዉጭ ሀገር በጥሩ ደሞዝ በሙቸዉተቀጥረዉ ጥሩ ኑሮ ሲኖሩ የነበሩ የአየር ኃይል ፓይለቶች ሀገራቸዉ መወረሯን እንደሰሙ ጨርቄን ሳይሉ ገስግሰዉ በመድረስ በጦርነቱላይ አኩሪ ስራ ሰርተዋል፡፡ በዚህ መንገድ ከዉጭ ከመጡት መካካል ዛሬም ድረስ በአየር ኃይሉ ዉሰጥ እያገለገሉ የሚገኙ ፓለቶች አሉ፡፡

* የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ላይ ጦር ከማዝመቱ በፊት ከሱዳን፤ ከየመንና በጅቡቲ ጋር እየተጋጨና የሽብር ተግባራትን በተደጋጋሚበመፈጸም ቀጠናዉን እያወከ መሆኑን እያወቁ ምእራባዉያን መንግስታት በኤርትራ መንግስት ላይ አንዳችም ግሳጼም ሆነ ከድርጊቱእንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ሊሰጡት አልሞከሩም፡፡ የሻዕቢያ መንግስትም በዚህ ተበረታትቶና የልብ ልብ ተሰምቶት በኢትዮጵያ ላይም ጦርበመስበቁ የኢትዮጵያ መንግስት ግን የኤርትራን ዉንብድና እንዲጋለጥ በማድረግ በተከታታይ ጠንከር ያሉ መዕቀቦች እንዲጣልባትና ከዓለምማህበረሰብ እንድትገለል ለማድረግ አስችሎአል፡፡

* ከሁሉም በላይ ደግሞ የሻዕቢያ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብት በግላጭ መበዝበሩ ሳያንሰዉ በዚሁ በራሳችን ህዝብ መሃል ሆኖዜጎቻችንን በጠራራ ፀሐይ እያፈነ የዉንብድና ተግባር ሲፈጽም ህዝባችን እያዬ ከማዘንና ዉጭ ምንም ማድረግ ባልቻለበት ሁኔታ የተነሳዉይህ ጦርነት ይህን ሁሉ ህገወጥ ድርጊት ለማስቆም መልካም አጋጣሚ አልነበረም ማለት አይቻልም፡፡

* በኤርትራ መገንጠል (ራሷን የቻለች መንግስት በመሆኗ) በጣም ሲቆጩና ሲያዝኑና ኤርትራን የማታካትት ኢትዮጵያን ለመቀበል በጣምየተቸገሩ ኢትዮጵያዉያንን ብቻ ሳይሆን እንደ ዋዛ የተነጠሏትንየቀድሞ እናት አገራቸዉንኢትዮጵያንድጋሚ እንቀላቀል ይሁን? በሚልበተስፋ መኙ ለነበሩ ኤርትራዉያን  ጭምርዳግመኛ እንድ እንሆለንየሚለዉን ምኞት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያዳፈነ መጥፎ አጋጣሚነዉ፡፡

4/ ጦርነ የመከላከያ ሰራዊታችን ተጋድሎ ታሪክ ተገቢዉ ቦታ አልተሰጠዉም!

ለኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አነስተኛ ግምት የሠጠነዉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ላይ ያደረግነዉ ተጋድሎ የከፈልነዉ መስዋእትነትና የደረሰብን ጉዳት ሁሉ ገና በዚህ አጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲህ በቀላሉ መዘንጋት ነበረበት ብዬ አላስብም፡፡ ከኤርትራ ጋር ገና ያልተቋጨ ብዙ ጉዳይ እያለን በቀላሉ ሊዘነጋ አይገባዉም፡፡

ሁላችንም እንደምናዉቀዉ በ1990 ዓ/ም ስለተቀሰቀሰዉ የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት የሚያወሱ ጥቂት መጻህፍትና የተወሰኑ መጣጥፎች በስተቀር በተለይ በአማርኛና የጉዳዩ ባለቤት በሆነዉ በጦርነቱ ተሳታፊ የመከላከያ አባላትም ሆነ በመንግስት ባለስልጣናት ብዙ አልተጻፈም፡፡ ስለዚያ ጦርነት በግልም ሆነ በመንግስት መገናኛ ብዙሃንም ብዙ የተወራበት አይመስለኝም፡፡ ፡ስለ ጦርነቱ የሚተርኩ ድርሳናት ጭራሽ የሉም ባይባልም በሚፈለገዉ መጠን አይመስለኝም፡፡ ለዚያዉም በዉጭ ቋንቋ የተጻፉት ይበዛሉ፡፡

ግን ለምን ይሆን ያን ያህል ልጆቻችን በጀግንነት የወደቁበትና  በርካታ ኢኮኖሚያዊ ዉድመትና ፖለቲካዊ መመሰቃቀል  ያስከተለ ጦርነት በታሪክ ፀሃፊዎች፤ በተመራማሪዎች ይሁን በወታደራዊ ጠበብቶች ወዘተ በተገቢዉ መንገድ አለመዳሰሱ? በተለይ ጦርነቱ ከአነሳሱ እስከ አፈጻጸሙ የነበረዉን ጠንካራና ደካማ ጎን ሙያዊ በሆነ መንገድ ገለልተኛ በሆኑ አካላት አለመገምገሙስ ለምን ይሆን?

አሜሪካ አንድ ወር ብዙም በማይበልጥ  አጭር ቀናት ስለተጠናቀቀዉና ይሄን ያህል ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ኪሳራ ባልከፈለችበት (በጦርነቱ የሞተዉ የአሜሪካ ወታደር ቁጥሩ ከአራት መቶ አይበልጥም) የመጀመሪያዉ የባህረ ሰላጤዉ  ጦርነት ላይ የሚተነተኑ በሺህ የሚቆጠሩ የምርምር ጽሁፎችና የታሪክ ዘጋቢ መጽሀፍት መጻፋቸዉን ላወቀ ሰዉ እኛ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ስለወደቁበትና ያለማቋረጥ ለሁለት ዓመት ላላነሰ ጊዜ ለጠየቀዉ ጦርነት  በጣት የሚቆጠሩ  መጻፍት እንኳን መነፈጋችን እጅግ ያስቆጫል፡፡

አሁን አሁንማ  አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ስለጦርነቱ የሚነሳ ወግም ሆነ የርስበርስ ጭዉዉት ብዙም አይሰማም ፡፡ ሁሉም ነገር የተረሳና ምንም እንዳልተፈጠረ የተቆጠረ መስሏል፡፡ ነገር ግን በዚያ ጦርነት ላይ ልጆቻቸዉ መስዋእት የሆኑባቸዉና በዚያ ጦርነት ምክንያት ቤት ንብረታቸዉ የወደመባቸዉና ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ በጦርነቱ ቀጠና አካባቢ የነበሩ ወገኞቻችን መቼም ቢሆን ይዘነጉታል ብዬ አላስብም፡፡

በመቀለ አይደር ትምህርት ቤት ህጻናት ላይ የደረሰዉ አረመናዊ ጭፍጨፋስ እንዴት ሊዘነጋ ይችላል? በጭራሽ ሊዘነጋ የማይችል ፤ሊዘነጋም የማገባዉ ነዉ፡፡ በርግጥ የመከላከያ ሰራዊታችን አሁንም በዚያዉ በኤርትራ አዋሳኝ ድንበር ላይ ሃያ አራት ሰዓት ያለማቋረጥ በተጠንቀቅ ቆሞ ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ስለምናዉቅ ሰራዊታችንንም ሆነ መንግስት ጉዳዩን ትቶታል ለማለት አያስደፍርም፡፡

እንደሚታወቀዉ መከላከያ ሰራዊታችን አስገራሚ በሆነ ጀግንነት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያሻዕቢያን ወራሪ ኃይል እየደመሰሰ የተወሰደበትን ሁሉ ለማስመለስ ሁለት ዓመት በላይ አልፈጀበትም፡፡ ያ ሁሉ ድል ያለ መስዋእትነት የመጣ እንዳልነበር ይታወቃል፡፡ በጦርነቱ ስለተከፈለዉ መስዋእትነት መጠን በይፋ ባይነገርም ነገር ግን ቀላል የማይባል መስዋእትነት እንዳስከፈለን ለማንኛችንም ግልጽ ነዉ፡፡

ህዝቡን ያስከፋዉ የመስዋትነቱ መብዛት አይደለም፡፡ ለሀገር ሉአላዊነት በሚከፈል መስዋትነት ላይ በህዝባችን ዘንድ እንደ ጥያቄ የሚነሳ አይደለም፡፡ የህዝቡ መከፋት መነሾ የልጆቻቸዉን ደም ዋጋ በሚያሳጣ መልኩ ተገቢዉ ክብር አልተሰጠም በሚል ነዉ፡፡ ታዲያ ጥያቄዉ ለምንድነዉ ደራሲዎች፤ ጋዘጤኞች ፤ የታሪክ ጸሃፊዎች፤ወዘተ መጭዉን ትዉልድ ሊያስተምር  በሚያስችል ደረጃ በብዕራቸዉ መዳሰስ ያልፈለጉት የሚል ነዉ?

ለመሆኑ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተዉ መከላከያ ሚኒስቴርስ ጦርነቱን በሚመለከት ያደረገዉ ጥልቀት ያለዉ ግምገማስ ነበር? ስለጦርነቱ በባለሙያ አስጠንቶ ጠንካራና ደካማ ጎኑን ለይቶ ሰራዊቱ እንዲማርበት ያላደረገዉስ ለምንድነዉ? (ምናልባት ከቅርብ ግዜ ወዲህ አድርጎ እንደሆነ አላዉቅም)፡፡ እንዳይገመገም የሚከለክለን የተለየ ምስጢር ያዘለ ቢሆን ነዉ ወይንስ መገምገም የማይገባዉ ስለሆነ ነዉ?

ሰራዊታችን ለሰራዉ አኩሪ ገድልና ለከፈለዉ መስዋእትነት ሃዉልት ባይቆምለት እንኳን ቢያንስ ህዝቡ ስለ ልጆቹ ጀግንነት እንዲያዉቅ፤ መጭዉ ትዉልድም እንዲማርበት ተደርጎ የማይዘገበዉስ ለምንድነዉ? የሻዕቢያ መንግስት እንደሆነ በሱ ጠብ ጫሪነት ተጀምሮ በሱ ሽንፈት ስለተጠናቀቀዉ ጦርነት ማዉራትና መተረክ ስለማይችል ከዚያ ይልቅ በየጊዜዉ ለህዝቡ የሚያሳየዉ የቆየዉን የድሮዉን ከደርግ ጋር ተደርጎ የነበረዉን የናቅፋን፤ የአፋበትን ፤የከረንን ፡የምጽዋን ወዘተ ዉጊያ ላይ ሰራሁ ስለሚለዉ ገድል ብቻ ነዉ፡፡

ስለ ባድመ ጦርነት ግን ሻዕቢያ ብዙ ሲያወራ አይደመጥም፡፡ ያን ማድረግም አይጠበቅበትም፡፡ ምክንያቱም  በባድመ ጦርነት ምንም የሚያኮራ ታሪክ ስለሌለዉ ማዉራት አይችልም፡፡ በእኛ በኩል ግን ከኤርትራ ጋር የተደረገዉ ጦርነት በአስደናቂ ገድሎች የታጀበና አኩሪ ታሪክ የተሰራበት ሆኖ እያለ ብዙ ሊባልበት ሲገባ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም መባሉ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ትላንት በጦርነቱ ወቅት ድንቅ አመራር ሲሰጡ የነበሩ ጄኔራሎች፤ የመንግስት አመራሮችም፤ ጋዜጠኞችና ታሪክ ምሁራን  ዛሬ በህይወት እያሉ ያልተነገረ ታሪክ ነገ ይነገራል ብዬ አላስብም፡፡

ሻዕቢያ ስለ ናቅፋ ስለ ምጽዋ፤አፋበት፤ ስለ ከረን ወዘተ ለማዉራት የማይሰንፈዉን ያህል እኛም ከዚያ ባልተናነሰ ሁኔታ በርስ በርስ ጦርነቱ ወቅት (ደርግን ለመጣል የተደረገዉን ትግል) ተሰራ ስለተባለዉ ገድል ሰፋ ያለ የአየር ሰአት ተሰጥቶት ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በከፍተኛ ግለትና ወኔ ስንተርክ ቆይተናል፡፡ ያ የደርግን ስርአት ለመጣል በተካሄደዉ ጦርነት የተሰራዉ ገድል የታሪካችን አንድ አካል በመሆኑ መተረኩ ማንኛችንንም አስከፍቶን አያዉቅም፡፡

ነገር ግን ቅር የሚያሰኘን ነገር የኤርትራን ወረራ ለመቀልበስ ስለተደረገዉ  ጦርነት  የዚያን አንድ አስረኛዉን ያህል እንኳን ለመተረክ አለመሞከሩ ነዉ፡፡ እንዲያዉም ስለዚያ ጦርነት በመንግስት ሚዲያ ሳይቀር ለመጨረሻ ግዜ የተነገረበትን ወቅት መቼ እንደነበር ለማስታወስም  አልችልም፡፡

ባለፈዉ ዓመት ይመስለኛል በርካታ ጋዜጠኞችና የጥበብ ሰዎች ከደርግ ጋር ጦርነት የተደረገባቸዉን ቦታዎች ለመጎብኘት ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸዉ ትልቅ ባጀትም ተመድቦ እንዲጎበኙ ተደርጎ ለበርካታ ሳምንታት ያለመቋረጥ ሲተርኩ ከርመዋል፡፡ እንደዚያ በመደረጉ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ከደርግ ጋር የተደረገዉ ትግል የታሪካችን አንድ አካል በመሆኑ በሚገባ ሊዘገብ የሚገባዉ ነዉ፡፡ እኔም እያንዳንዱን የትግሉን ዘመን ትረካ በከፍተኛ ፍላጎት ነዉ ስከታተል የቆየሁት፡፡ ዛሬም ቢሆን እንደ አዲስ ታሪኩን ማንበብ ያስደስተኛል፡፡

ነገር ግን ጥያቄ የሚያስነሳዉ ራሱን የቻለ የጉብኝት ፕሮግራም ባይዘጋጅለት እንኳን ቢያንስ እግረ መንገዳቸዉን ከኤርትራ ጋር ጦርነት የተደረገባቸዉን ቦታዎችን እንዲጎበኙ ያልተደረገዉ ለምንድነዉ? የሚለዉ ጥያቄ ነዉ፡፡ ሌላዉ ቢቀር ጦርነቱ የተቀሰቀሰበትን ባድመን እንኳን ማስጎብኘትስ አይቻልም ነበር እንዴ?

ለመሆኑ በሻዕቢያ ጄቶች አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተደረገበትን አይደር ት/ቤትን ጎብኝተዋል? በሻዕቢያ ሆነ ተብሎ በፈንጂ የፈራረሰዉን ዛላምበሳንስ አስጎብኝተናቸዋል? የኤርትራን ወረራ ለመቀልበስ ከሰባ ሺህ የማያንሱ ጀግኖች የወደቁበትና በርካቶች አካለ ጎደሎ የሆኑበት ጦርነት ለመወራትና ለመነገር ስለማይመጥን  ነዉ ችላ የተባለዉ? እንዲህ በቀላሉ የሚዘነጋስ ነበር እንዴ የባድመ ጦርነት?

ስለኤርትራ ጦርነት ሲነሳ በርካታ ጠንካራ ጎኖች የመኖራቸዉን ያህል በሌላ ጊዜ ሊደገሙ የማይገባቸዉ ድክመቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልጽ ነዉ፡፡ በየትኛዉም ጦርነት ቢሆን ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን ድክመትም ሊኖር መቻሉ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ ከሁሉም ትልቁ ጥፋት ግን ስለጦርነቱ ጭራሽ አይወራ አይነሳ የተባለ የሚያስመስለዉ ዝምታ ነዉ፡፡

በዚያ ጦርነት የወደቁ የኢትዮጵያ ጀግኖች ቢወደሱበት ፤የኢትዮጵያ  ህዝብ ለጠላት አይበገሬነቱን በድጋሚ ስላስመሰከረበት ስለዚያ ጦርነት መነገር ብቻ ሳይሆን ቅኔ ቢቀኝበት፤ ቢዘመርለትና ፊልም ቢሰራበት ፤መታሰቢያ ሃዉልት ቢቀረጽለት የሚከፋዉ ወይም መብቱ የሚነካበት ከመካከላችን ይኖር ይሆን? ከኤርትራ ጋር የተደረገዉ ጦርነት በታሪካችን ትልቅ ስፍራ የሚይዝ መቼም የማይዘነጋ ጦርነት ሆኖ እያለ ከድክመታችንና ከጥንካሬአችን ልንማር በሚያስችለን ደረጃ የሀገሪቱ መከላከያ አስካሁን በአግባቡ ያልገመገመበትስ  ምክንያት ምንድነዉ?

በአንድ ወቅት ከጦርነቱ በኋላ የጦርነቱ ግምገማ መሰል ነገር ተጀምሮ በኋላ አቅጣጫዉን እየሳተ ጣት መጠቋቆም ሲመጣ እንዲቆም መደረጉ ይታወቃል፡፡ ምስጢራዊነቱን ለመጠበቅ ከተፈለገ ቢያንስ በሚመለከታቸዉ ከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እንኳን ግምገማ ማድረግ እየተቻለ ጭራሽ ለማድረግ አልተፈለገም፡፡ ለመሆኑ በጦርነቱ አሸናፊዎቹ እኛ ለመሆናችን ማረጋገጫ ለሚጠይቁንስ እንዴት ነዉ የምናስረዳዉ? ስለ ትላንቱ ጦርነት በሚገባ ሳንገመግም ነገ ከኤርትራ ጋር ለሚኖረን ሌላ ዙር ጦርነትስ እንዴት ነዉ መዋጋት የምንችለዉ?

ጦርነቱ ያለአንዳች ችግርና አንድም መስዋትነት ሳንከፈል አንድም ጉዳት ሳይርስብን እንደዋዘ የተገኘ እንዲመስል ለሚፈልጉ አንዳንድ ወገኖች ኤርትራ ገና እንደ ሀገርና እንደ መንግስት አንድ አስር አመት እንኳን እድሜ ባልነበራት ወቅት እንደዚያ ያንቆራጠጠችን ዛሬ ከሃያ ዓመታት በኋላ ልትደርስበት የምትችልበት ጦርነት የማካሄድ አቅም (war making capability) ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት የሚችሉ አይመስለኝም፡፡ ከአስራ ስምንት ዓመታት በኃላ አሁን ያለችዋ ኤርትራ የድሮዋ ኤርትራ እንዳልሆነችና ለዛሬዋ ኤርትራ አቅም የሚመጥን ምላሽ ለመስጠት በቅድሚያ ስለአለፈዉ ጦርነት በሚገባ መገምገም በተገባ ነበር፡፡

የጦርነት ግምገማ ደግሞ የመከላከያ ጄኔራሎች ማድረግ ሲፈለጉ የሚደረግ ስላልፈለጉ ደግሞ የሚተዉት ሊሆን አይገባዉም፡፡ ግምገማዉን መምራት የሀገሪቱ ፖለቲካ አመራር ሃላፊነት በመሆኑ መከላከያ ፍላጎት ባይኖረዉ እንኳን የሀገሪቱ ፖለቲካ አመራሩ(ጠቅላይ አዛዡ ፤መከላከያ ሚኒስትሩና የፓርላማ የመከላከያ ኮሚቴ) ግምገማዉን በራሱ አመራር ሰጭነት ማድረግ ይገባዉ ነበር፡፡ ከዚያ ዉጭ ግን የኤርትራን ሰራዊት ረግጠን ፤አይቀጡ ቅጣት ቀጥተን አፈር ድሜ አስግጠን፤ ደምስሰን ወዘተ ዓይነት ፉከራዎች አንዳችም ጥቅም የላቸዉም፡፡

እኛ ብቻ ሳንሆን ኤርትራዉያን ራሳቸዉ ጠንቀቄዉ የሚያዉቁትን ሽንፈታቸዉን እኛ ደጋግመን ስላወራንና ስለፎከርን  ትርጉም አይኖረዉም፡፡ ትልቅ ትርጉም ሊኖረዉ ይችል የነበረዉ ጦርነቱን ከአነሳሱ እስከ ፍጻሜዉ በሚገባ በመገምገም ትምህርት ወስደንበት ቢሆን ነበር፡፡ ያለፉ ጦርነቶችን ጠንካራና ደካማ ጎናችንን በጥንቃቄ ሳንገመግም ከኤርትራም ሆነ ከሌላ ባላጋራ ጋር ወደፊት ለሚገጥመን ጦርነት በድሮዉ ያረጀ አሰተሳሰብ ወደ ጦርነቱ ልንገባ ስለምንገደድ ገና ሳንዋጋ ለሽንፈት የሚዳርገን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ሌላዉ ቀርቶ በራሱ በመከላከያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች እንኳን አልፎ አልፎ ስለጦርነቱ ለማዉሳት ያልበቃነዉ መናኛ ጉዳይ ስለነበረ ነዉ? ለምን ተገቢዉን ቦታ እንዳልሰጠነዉ ምክንያቱ ለእኔ  በጭራሽ አይገባኝም፡፡ ከዛሬ አራት አስርት ዓመታት በፊት በሶማሊያ የተቃጣብንን ወረራ ለመመከት የተደረገዉን እልህ አስጨራሽ ጦርነት አስመልክቶ በሚገባ ተቀምሮ የተዘጋጀ የታሪክ ሰነድ ባለመኖሩ ስንቆጭ እንዳልነበርን ዛሬ እንደልብ መረጃ ማግኘት በሚቻልበት ዘመን ላይ ሆነን ከኤርትራ ጋር ስላደረግነዉ ጦርነት በመረጃ የተደገፈና በሚገባ ተቀምሮ የተዘጋጀ የታሪክ ሰነድ አለመኖሩ መልካም አይመስለኝም፡፡

በተለይም የሀገራችን ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት በዋነኛነትም የከፍተኛ የአመራርነት የእስታፍ ኮሌጅ ሀገራችንን በተለያዩ ጊዜያት ከዉጭ ወራሪዎች ጋር ስላደረገችዉ ጦርነቶች ላይ ሰፊ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉበትና  ሰልጣኞችም የመመረቂያ ጽሁፍ የሚያቀርቡበት ሁኔታ መመቻቸት ያለበት ይመስለኛል፡፡

ለመሆኑ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት የምርምር ጽሁፎችን የሚያቀርቡበት አዳዲስ የጦርነት ንድፈሃሳቦችና ተሞክሮዎች፤ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ትዉዉቅ ለመድረግ የሚረዱ፤ የዩንቨርስቲ ምሁራንና የምርምር ተቋማት በመከላከያና በደህንነት ጉዳይ ላይ የጥናት ጽሁፎችን የሚያቀርቡበት፤ ሰራዊታችንን ስለሃገሩ ብሄራዊ ደህንነት የዉጭ ግኑኝነት ፖሊሲና ስለ ብሄራዊ ጥቅም እንዲያዉቅ የሚያግዝ  አንድ እንኳን የህትመት ዉጤት አለዉ? ዘጠና ሚሊዮን ህዝብን የሚወክልና በቢሊዮኖች የሚገመት ዓመታዊ ባጄት ያለዉ ግዙፍ የመከላከያ ተቋም ከስምንት ገጽ የማትበልጥ “ወጋገን” ከምትባል አነስተኛ ጋዜጣ ዉጭ በመከላከያ የሚዘጋጅ ሌላ ወታደራዊ መጽሄት አለዉ እንዴ?

ከኢትዮጵያ ጦር ኃይል ዉጭ በመከላከያ አባላት ብቻ ሳይሆን በሲቪሉ ህብረተሰብም የሚነበብ ወታደራዊ መጽሄት የሌለዉ ሌላ አገር አለ እንዴ? እኔ አስከማዉቀዉ ድረስ የለም፡፡ እንዴት አድርገን ነዉ ሰራዊቱን ነገ ለሚጠብቀዉ ለህገ መንግስታዊ ሃላፊነቱ የምናዘጋጀዉ? ለመሆኑ በተጠቀሰችዉ “ወጋገን“ ጋዜጣም ሆነ በመከላከያ ሬዲዮና ቴሌቭዥኝ ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ዝግጅቶችን ሌላዉ ህዝብ ይቅርና ራሳቸዉ ኃላፊነት ያለባቸዉ የመከላከያ ባለስልጣናት እንኳን በቅጡ ይከታተሉታል እንዴ?

መከላከያ ኃይላችንን ማዘጋጀት፤ ማስተማርና መገንባት ያለብን ነገና ከነገ ወዲያ ግብጽን ከመሳሰሉ ግዙፍና ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ካላቸዉ ስትራቴጂያዊ ጠላቶች ጋር ለሚጠብቀን ፈታኝ ጦርነት እንጂ ለትናንንሽ ተልእኮዎችና ከሽፍታ ጋር ለሚደረግ ገጭት ሊሆን እንደማይገባዉ ግልጽ ነዉ፡፡ ግን በዚያ መልኩ እየተሰራ አይመስለኝም፡፡ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላትን  ወቅቱ ከሚጠይቀዉ ልዩ ሁኔታ ወደ ኋላ እንዳይቀሩ ማድረግ የምንችለዉ በትጥቅ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብ ደረጃም እያዘመንና ከሌሎች ብቻ ሳይሆን ከራሳችንም ያለፉ ታሪኮች ልምድ ለመቅሰም ስንችል ነዉ፡፡ ለዚህም ሲባል ራሳችንን ለመፈተሸና የዉስጥ ገበናችን ለመመርመር ዝግጁ መሆን ይገባናል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን ገና የተዘጋጀን አይመስለኝም፡፡ ከራሳችን የኋላ ታሪክ ለመማር ፍላጎት ቢኖረን ኖሮ ስንት ጀግና የወደቀበትን ጦርነት ችላ ባላልን ነበር፡፡

5/ ያለፉ ጦርነቶችን ገምግሞ ድክመትን በጸጋ ተቀብሎ ለወደፊቱ ትምህርት በመዉሰድ ረገድ አሜሪካ መማር የሚገባን ተሞክሮ

ታላቋ አሜሪካ ከቬትናም ጋር ሲታደርግ የቆየችዉንና በርካታ ወታደሮቿ አልቀዉባት በአሜሪካ ተሸናፊነት ስለተጠናቀቀዉ ጦርነት ያለምንም መደባበቅ ቁጭ ብለዉ ገምግመዉ፤ በርካታ መጽሀፍትን ጽፈዉበት፤ ፊልም ተቀርጾበት፤ ብዙ ነገር ተምረዉበት ለወታደራዊ ኮሌጆችና ዩንቨርስቲዎች ሳይቀሩ ሰፊ ምርምር ሲያደርጉበት ቆይተዋል፡፡ ከአርባ ዓመታት በኋላም፡ስለዚያ ጦርነት ሲተርኩ ልክ ዛሬ የተደረገ ያህል በጥልቅ ስሜት ተዉጠዉ ያለ አንዳች መሸማቀቅ ነዉ፡፡

አሜሪካኖች የቬትናምን ጦርነት እንደ ትልቅ ማስተማሪያ ነዉ የሚጠቀሙት፡፡ የአሜሪካ ጦር ኃይል ዛሬ ለደረሰበት ብቃት የቬትናምን ጦርነት እንደ ባለዉለታ ነዉ የሚቆጥሩት፡፡ ሌላ ጊዜ ሊያገኙ የማይችሉትን ትምህርት ነዉ የሰጣቸዉ፡፡

የአሜሪካ መንግስት ከቬትናም ጦርነት በኋላ በብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲ፤በፖለቲካዊና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች፤ በወታደራዊ አስተሳሰብና በጦር ኃይሉ አደረጃጀትና ቁመናና በሌሎች በርካታ ፖሊሲዎች ላይ መሰረታዊ ማሻሻያ ለማድረግ ተገዷል፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በወታደራዊ ኃይል አጠቃቀም ረገድ የህግ አዉጭዉንና የፕሬዝዳንቱን ስልጣን በሚመለከት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ህገመንግስታዊ ማሻሻያ አስከማድረግ ድረስ ትኩረት ሰጥተዉ ሰርተዋል፡፡

አሜሪካና ታላቋ ብሪታንያ አስር ወታደር ሲሞትባቸዉ ስህተቱ ሌላ ጊዜ እንዳይደገም መፍትሄ ፍለጋ ፍዳቸዉን ይበላሉ፡፡ እኛ ስልሳና ሰባ ሺህ ጀግና ለወደቀበት ጦርነት ብዙ ትኩረት እንሰጥም፡፡ ለማንኛዉም ይህን ሃሳብ ለማጠናከር እንዲረዳኝ አሜሪካ ከቬትናም ጦርነት ከወጣች በኋላ ያለ አንዳች መደባበቅ ድክመቶቻቸዉን አንድ በአንድ እየነቀሱ በመዉጣት በርካታ ማስተካከያዎችን አድርገዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ በከፊል  የተወሰኑትን ቀጥዬ ለመጠቃቀስ እሞክራለሁ፡፡

* የቬትናምን ሽንፈት ተከትሎ ህዝባቸዉ በሰራዊታቸዉ ላይ ከፍተኛ ንቀትና ጥላቻ አድሮበት ነበር፡፡ የአሜሪካንን ጥቅም ለማስጠበቅየማይችል ሰራዊት ነዉ በሚል ወታደሮቻቸዉ ዓይንህን ለአፈር የተባሉበት ነበር፡፡ ለደረሰዉ ሽንፈት ጥፋቱ ያፖለቲካ አመራሩ ነዉ ወይንስጦር ኃይሉ ችግር ነዉ በሚል መልሱን ለማግነጥ ብዙ ደክመዋል፡፡

* የሀገሪቱ ፕሬዝዳነት ያለ ኮንግረሱ ፈቃድ ጦር ኃይሉን ከሀገር ዉጭ ለጦርነት መላክ የሚከለክልና ፕሬዝዳንቱ በጠቅላይ አዛዥነታቸዉ ጦርኃይሉን ወደ ጦርነት ለማስገባት ምን ምን ቅደም ተከተሎችን በቅደሚያ ማሟላት እንዳለባቸዉ የሚደነግግና የፕሬዝዳንቱ ስልጣን ላይተጨማሪ ገደብ የሚጥል (war powers resolution) የተባለ አዲስ ድንጋጌ በሪቻርድ ኒክሰን ዘመን .. በኖቬምበር ወር 1973 /እስከማዉጣት ደርሰዋል፡፡ እንደሚታወቀዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ያለ ኮንግሬሱ እዉቅናና ፈቃድ በተደጋጋሚ ጦር ይላቸዉን ወደ ጦርነትበማስገባት ይታወቃሉ፡፡ ይህ ደንብ የወጣዉ የአሜሪካ ጦር ቬትናምን ለቆ እንዲወጣ ከተደረገ ከሁለት ወራት በኋላ ነዉ፡፡

* አሜሪካ ያለምንም በቂ ምክንያት ያን ሁሉ ርቀት ተጉዛ በሰዉ አገር ላይ የከፈተችዉ ጦርነት የሕዝብ ድጋፍ ያልነበረወና መንግስትንምየሕዝብ አመኔታ ያሳጣ ነበር፡፡ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ሊንደን ጆንሰንም በድጋሚ ለመመረጥ እንኳን ያልደፈሩበት ትልቅ ዉርደት ነበርየደረሰባቸዉ፡፡

* በዚያ ጦርነት ሽንፈት ሳቢያ በአሜሪካ ለረዥም ዘመናት ሲሰራበት የቆዉ የብሄራዊ ዉትድርና አገልግሎት ከቬትናም ጦርነት በኋላ ለአንዴናለመጨረሻ ጊዜ እንዲቋረጥ ነዉ የተደረገዉ፡፡ ዛሬ በአሜሪካ ዉስጥ የግዴታ አገልግሎት የሚባል አሰራር የለም፡፡

* በጦርነቱ ወቅት ሲከተሉት የነበረዉ ወታደራዊ ዶክትሪን እጅግ የተዛባ መሆኑን ተረድተዉ ከጦርነቱ በኋላ በአዲስ ዶክትሪን እንዲቀየሩአድርገዋል፡፡ መከላከያቸዉንም በአዲስ መልክ ለማዋቀር የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የጦር ኃይላቸዉ አወቃቀር፤ እዝና ቁጥጥሩ ሁሉዋጋ እንደለዉና በሌላ መስተካከል እንዳለበት የተረዱት የቬትናምን ጦርነት ከገመገሙ በኋላ ነዉ፡፡

* የቬትናም ጦርነት ትክክለኛና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፖለቲካዊ ዓላማ ሳይስቀምጡ በድፍረት የገቡበት ጦርነት ስለነበር ከፍተኛ የኃይልብልጫ እያላቸዉም ጦርነቱን ማሸነፍ አልቻሉም፡፡

* የአሜሪካ ወታደሮች በጦርነቱ ወቅት የተከለከሉ የጅምላ ጨረሽ ጦር መሳሪያዎችን ሳይቀር ከመጠቀም አልፈዉ አንዳችም ትጥቅያልነበራቸዉን ሲቪል ህጻናትና በእድሜ የገፉ ሰዎችን ከቤት አውጥተዉ በጅምላ በመፍጨፍ የጦር ሜዳ ወንጀል የሰሩበትና በኋላበሚዲያዎቻቸዉ ብርታት ሁኔታዉ ተጋልጦ ምንገስትም ትፋቱን አምኖ ለመቀበል የተገደበትና አጥፊዎችም የቀጡበት ሁኔታ ነበር፡፡

* በሲቪል ፖለቲከኞችና በወታደራዊ  ቃን መካከል የነበረዉ አለመግባበት ፤አለመደማመጥና በተለይም ፖለቲከኞች በጣም ዝርዝርየጦርነት አካሄድ ዉስጥ ሁሉ ያለአግባብ እየገቡ መበጥበጣቸዉና አላሰራ ማለታችዉ ለሽንፈቱ አንዱ መነሾ እንደነበር ተረድተዉ በሂደትእንዲስተካከል አድርገዋል፡፡ በዚህ ረገድ በተደጋጋሚ ሲጠቀስ የነበረዉ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆንሰን ሳይቀሩ አጠቃለይፖለቲካዊ አቅጣጫ ወይም ግብ ከማስቀመጥ ይልቅ አላስፈላጊ ወደ ሆነ ዝርዝር ጉዳይ ዉስጥ በመግባት የትኛዉ ኮረብታ በአየር መደብደብእንዳለበት ሁሉ ሳይቀር ዋሽንግተን (ኋይት ሃዉስ) ቁጭ ብለዉ መመሪያ ይሰጡ እንደነበር ተነግሮአል፡፡ በጦርነቱ ግንባር የተሰለፉ አዛዦችእያሉ በብዙ ሺህ ማይል ርቀት ላይ ሆነዉ መመሪያ ለመስጠት ያደረጉት ሙከራ ለሽንፈታቸዉ ዋናዉ ምክንያት እንደነበረ ይጠቀሳል፡፡

* የቬትናም ጦርነት ምክንያት በወቅቱ ሁለቱ ተፎካካሪ ኃይሎች የነበሩት አሜሪካና ሶቭየት ህብረት አዳዲስ የዉጊያ ጥበቦችንና የጦርመሳሪያዎችን ለመፈብረክና በተግባር ለመፈተሽ እድል ፈጥሮላቸዉ ነበር፡፡  

* በቬትናም ህዝብ ላይ የተጣለዉ ቦንብ ብዛት በሰዉ ልጅ የጦርነት ታሪክ ዉስጥ የዚያን ያህል ብዛት ያለዉ ቦንብ ተጥሎ አይታወቅም፡፡በቬትና ላይ ብቻ የተጣለዉ የቦንብ ብዛት  በሁለተኛዉ የአለም  ጦርነት ባጠቃላይ በጥቅም ላይ ከዋለዉ ቦንብ ብዛት በእጅጉ የበለጠ ነበር፡፡ለብዙ ቀናት ያለማቋረጥ በየቀኑ 1500 sorties በላይ (የዓይሮፕላን ምልልስ) እየተደረገ ነበር ሲቀጠቀጡ የነበሩት፡፡ ይሁን እንጂ የቬትናምህዝብ ሁሉ ግፍ እየተፈጸመበት እስከመጨረሻዉ በቆራጥነት ተቋቁሞ አሜሪካ በሽንፈት ለቃ እንድትወጣ በማድረግ ባሳየዉ ጅግንነትናበመጨረሻም ሁለቱን ቬትናሞች ለማዋሃድ መቻላቸዉ ለዚህ ሁሉ ያበቃቸዉ ጥንካሬ ከምን የመነጨ እንደሆነ ለመረዳት ከጦርነቱ በኋላራሳቸዉ አሜሪካኖች ቬትናም ድረስ በመመላለስ ጥናት በማድረግ ምስጢሩ ላይ ለመድረስ ብዙ መድከም ነበረባቸዉ፡፡

* የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች፡ ፖለቲከኞች፤ ታሪክ ፊዎች፤ ሲቪልና ወታደራዊ የትምህርትና  የምርምር ተቋማት የሚዲያ ሰዎችወዘተ ሁሉ ባደረጉት ያላሰለሰ የጋራ ጥረት ዛሬ የአሜሪካ ጦር ኃይል ለደረሰበት የማይበገር ቁመና ያበቃ የቬትናምን ጦርነት ሳይደባብቁበግልጽ መገምገማቸዉ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አሜሪካኖች ከዚያ ተምረዉ ከእያንዳንዱ ጦርነትና ዉጊያ በኋላ መገምገምና ምርምርና ጥናትማድረግን እንደልማድ ይዘዋል፡፡ በቬትናም ጦርነት ጦስ ክብሩን ተገፎና ህዝባዊ ቅር ርቆት የቆየዉ የአሜሪካ ጦር ኃይል ዛሬ በአሜሪካ ህዝብዘንድ ከማንኛዉም በሀገሪቱ ዉስጥ ካሉት ተቋማት በበለጠ ከፍተኛ ከበረታ፤ተአማኒነትና ተቀባይነት ያለዉ ጦር ኃይሉ ለመሆን የበቃዉ ራሱን ገምግሞ  በማረም ከቬትናም ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በገልፍ ጦርነት (ኢራቅ) የተሳካ ግዳጅ  ለመፈጸም በመብቃቱ እንደገናየተገፈፈዉን ክብርና ሞገሱን ሊያስመልስ በመቻሉ ነዉ፡፡

6/ ማጠቃለያ

የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት በሚመለከት ትኩረት ተሰጥቶት አለመገምገሙና በሚዲያም ሆነ በሌሎች መድረኮች  ትኩረት መነፈጉ ጦርነቱ በታረክ የሚኖረዉን ትልቅ ስፍራ የሚያስቀር አይሆንም፡፡ ትላንት ቁጥር አንድ ወዳጅ የነበረችዉ ኤርትራ ጋር ጦር የተማዘዝንበት ምክንያት ምን እንደነበር፤ ለምንስ የኤርትራ ወረራ ድንገተኛና ያለተጠበቀ እንደሆነ፤ ለምንስ መንግስታችን ማንኛዉም መንግስት እንደሚያደርገዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ እንዳላደረገ ፤ከጦርነቱ አወጣጣችን አወዛጋቢ የሆነበት ምክንያት በከፈልነዉ መስዋእትንት የሚመጣጠን ነገር ይዘን አልወጣንም የሚለዉ ጥያቄ ሊመረመርና ሊገመገም የሚገባዉ ነበር፡፡

ኤርትራን በሚመለከት ሌላ ፖሊሲ ያስፈልገናል ሲባል በቅድሚያ ከዚህ ቀደም ስለተፈጠረዉ ሁኔታ የማያዉቅና እንደ አዲስ የሚጠይቅ አዲስ ትዉልድ እንዳለ መዘንጋት የለበትም፡፡ የኤርትራ ጉዳይ በኢህአዴግ የስልጣን ቆይታ ግዜ ዉስጥ የማይፈታ ለወደፊቱም የሚቀጥል ሊሆን ይችላል፡፡

ከመቶ ዓመት በፊት ኤርትራን በሚመለከት ምንሊክ ፈጸሙ ስለተባለዉ ስህተት ዛሬ ሂሳብ እንድናወራርድበት የተገደድንበትን ያህል ወደፊት ከኢህአዴግ በኋላ ለሚተካዉ መንግስት ዉዥንብር እንዳይፈጠርና የታሪክ ተጠያቂነትም እንዳይኖር በግልጽ የተብራራና ጥርት ያለ ነገር ማስረከብ ይገባናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ወደድንም ጠላንም የኤርትራን ጦርነት በሚመለከት በሚገባ መገምገምና ለታሪክ ማስቀመጥ ይኖርብናል፡፡

መንግስትን እየመራ ያለዉ ኢህአዴግ በትግሉ ወቅት “ደርግን የሚያህል ግዙፍ ሰራዊት ያሸነፍኩበት ዋንኛ ምስጢር…..” እያለ ሲነግረን የነበረዉ ከአያንዳንዷ ዉጊያ በኋላ ቁጭ ቢለዉ መገማገማቸዉን ነበር፡፡ እኛም በኢህአዴግ ጉብዝና ተደንቀን እንደ ኢህአዴግ ለመሆን ስንፍጨረጨር እንዳልነበርን ዛሬ ያን የመሰለ ለግምገማ አመቺ የሆነ ጦርነት ለመገመግም ችላ ማለቱ ግራ ቢያጋባን አይፈረድብንም፡፡

ጦርነቱ እንደሆን ባስከፈለን መስዋእትነት መጠን ከየትኛዉም ጦርነት የሚያንስ አይደለም፡፡ በዚህ ጦርነት ሳቢያ የደረሰብንን ሌላ ሌላዉን ኪሳራ ትተን የህይወት መስዋእትነት በመክፈል ደረጃ ብቻ ካየነዉ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ መዉደቃቸዉ ትንሽ ነዉ የሚባል አይደለም፡፡

ጦርነቱ አሳዛኝነቱ እንዳለ ሀኖ ለአንዳንዶች በረከት ይዞ የመጣ ነበር የሚመስለዉ፡፡ ምስጋና ለዚህ ጦርነት ይሁንና ባንድ ግዜ ለጄነራልነት ማእረግ የበቁ አሉ፡፡ እድሉን ያገኙትና  አጋጣሚዉን በሚገባ የተጠቀሙበት ጥቂቶች ደግሞ ጦርነቱ ሲያበቃ ባንድ ግዜ ወደ ሚለዮነርነት የተቀየሩም አይጠፉም፡፡ ከዚህም ሌላ ማእረግና ችሎታቸዉ አልጣጣም ብሎባቸዉ በጦርነቱ ላይ ከፍተኛ ዉድቀት በማስከተላቸዉና ሰራዊታቸዉን ያለአግባብ በማስጨረሳቸዉ ማእረጋቸዉ የተገፈፈ ለእስርም የተዳረጉና የተባረሩ አመራሮችም አሉ፡፡

በጦርነቱ ለዓመታት በረሃ አብረዉ ሲታገሉ ቆይተዉ ድርጅቱን ለስልጣን ያበቁ  ቁልፍ አመራሮች ከድርጅቱ ለመባረር  ያበቃቸዉ መዘዘኛ  ጦርነትም ነዉ፡፡  በሀገሪቱ ወታደራዊ እርከን ከፍተኛዉ የሆነዉን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ደረጃ የነበሩትና ሌሎችም እዉቅ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ያለ ፍላጎታቸዉ ከሰራዊቱ እንዲወገዱ ያደረገ ጠንቀኛ ጦርነት ነዉ፡፡

በገዥዉ ፓርቲ ዉስጥ በተፈጠረዉ መከፋፈል ፓርቲዉን አደክሞና የህዝብ አመኔታን አሳጥቶት ለነቅንጀትና ለእነ ኢዴፓ መጫወቻ ለመሆን የዳረገ ጦርነት ነዉ፡፡ ታዲያ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ሁኔታ የዳረገንን ጦርነት ሳንነጋገርበት፤ ሳንገመግመዉ፤ በሚዲያ ሰፊ ዘገባ ሳይሰራበት እንደተራ ክስተት ተድበስብሶ ሲቀር እንዴት አያስከፋም? ያስከፋል እንጂ! መንግስትና መከላከያ ስለዚያ ጦርነት  መገምገምም ሆነ መዉራት ባያስፈልጋቸዉ እንኳን ቢያንስ በዚያ ጦርነት ለወደቁት ጀግኖች ክብር ሲባል የግድ ማድረግ ነበረባቸዉ፡፡ ከዚህ በኋላ ይሄ ተግባራዊ ሆኖ እንደማየዉ  እተማመናለሁ፡፡

*********************

(የዚህን ፅሁፍ ቀጣይ ክፍሎች በተከታታይ የምናትም መሆኑን ለአንባቢያን መግለፅ እንወዳለን፡፡)

 

 

—————————————————-

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት 2

በየዘመኑ የነበሩ መሪዎቻችን የኤርትራን ጉዳይ ያስተናገዱበት አግባብና ሲከተሉት የነበረዉ ፖሊሲ

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ፃድቅ)

+ የኤርትራ ችግር የአንድ ዘመንና የአንድ ወቅት መንግስት የብቻ ስህተት ሳይሆን  የቀደመዉ  መንግስት የሰራዉን ስህተት ተተኪዉ መንግስት በከፋ ሁኔታ  እያወሳሰበ ለመፍትሄም አስቸጋሪ እያደረገዉ በመጨረሻም ለይቶለት ለግንጠላ የዳረገ በቅብብሎሽ የተሰራ ጥፋት ነዉ፡፡ ክፋቱ ደግሞ ኤርትራ ራሷን ችላ ወይንም ከኛ ተነጥላም ከኛ ራስ አልወርድ እያለች ስታስቸግረን መቆየቷ ነዉ፡፡

+ የኤርትራ መገንጠልና እንደ ዋዛ እዉቅና ማግኘት የአንድ ክልል ወይም ህዘብ የመነጠል ጉዳይ ብቻ ተደርጎ የሚቆጠር አይደለም፡፡ የኤርትራ መገንጠል በቀጥታ ካስከተለዉ ዉጤት በላይ ለኢትዮጵያ የወደፊቱ ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ የስጋት የፈጠረዉ መጥፎ አርአያነት (dangerous precedent) ለሌሎች ብሄሮችና ህዝቦች መገንጠል እንደሚቻል ያስተማረና ሁልጊዜም ስለመገንጠል እንዲያስቡ ያደረገ መጥፎ ክስተት መሆኑ ነዉ፡፡

+ በተለይ ካለፈዉ ሁለት ዓመት ግዜ ወዲህ በሀገራችን አንዳንድ ክልሎች የታየዉ “ራስን በተለየ ተበዳይና ተጎጂ” የማድረግ፤ የክልሉን የተፈጥሮ ሃብት ለብቻ መጠቀም አለብን ከሚል አመለካካት በመነሳት ማንም አይደረስብን የሚለዉ ሌላዉን ህዝብ የመጥላትና ከዚሁ ጋር አብሮ በአንዳንድ ክልሎች መካካል የታየዉ የመስፋፋት አባዜና የወሰን ግጭቶች ወዘተ ሁሉ በድምር ሲታይ በሀገሪቱ አንድነት መጻኢ እድል ላይ አደጋ  ሊያስከትል የሚችል አዝማሚያ በመሆኑ አስቀድሜ ለጠቀስኩት ስጋት ጥሩ ማሳያ ነዉ፡፡

+ እንደሚታወቀዉ በየዘመኑ የነበሩት የኢትዮጵያ መንግስታት ከሚነቀፉበት አንዱና ትልቁ ጉዳይ ኤርትራን በሚመለከት ሲከተሉት የነበረዉ ፖሊሲ ነዉ፡፡ ኤርትራን በሚመለከት ከሚሰነዘረዉ ወቀሳ ጣሊያንን ድባቅ በመምታት እንጸባራቂዉን የአድዋ ድል የተገኘበትን ጦርነት በመምራት ስመ ገናና የሆኑት ዳግማዊ ምንሊክም ከወቀሳዉ ሊያመልጡ አልቻሉም፡፡ ምንሊክ በሽሽት ላይ የነበረዉን የጣሊያንን ሰራዊት መረብን አሻግረዉ ከሚተዉት አስከመጨረሻዉ አሳዳዉ መደምሰስ ነበረባቸዉ በሚል ነዉ የሚተቹት፡፡

በምንሊክ ላይ ወቀሳ አቅራቢዎቹ ሁኔታዉን አቅለዉ እንደሚናገሩት ሳይሆን ምንሊክ በወቅቱ እንደዚያ ለማድረግ ቢፈልጉ እንኳን ማድረግ የሚችሉበት አቅም (ሁኔታ) አልነበራቸዉምና ወቀሳዉ ያለቦታዉ የተሰነዘረና አግባቢነት የሌለዉ መሆን ብቻ ሳይሆን እንዲያዉም ለምንሊክ ካላቸዉ ጥላቻ ስማቸዉን ለማጉደፍና ዉለታቸዉን ለማሳነስ የሚደረግ አጉል ሙከራ ነዉ፡፡ በምንሊክ ላይ የሚሰነዘረዉ ትችት የአንድነት ስሜት ከነበራቸዉ ኤርትራዉያንም ጭምር ነዉ፡፤“እኛ ኤርትራዉያን  ንጉስ ምኒሊክ ለጣሊያን ሸጠዉን ነዉ እንጂ ኢትዮጵያዉን ነን ”የሚሉ የቁጭት ንግግሮች ከራሳቸዉ ከኤርትራዉን ይደመጥ እንደነበር አምባሳደር ዘዉዴ ረታን ጨምሮ በተለያዩ ታሪክ ጸሃፊዎች ተዘግቧል፡፡

የደርግ ባለስልጣን የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርግስም “የደም እምባ” በሚለዉ መጽሀፋቸዉ ላይ እንደጠቀሱት  በኤርትራ ከሁሉም ከብረ በዓላት ሁሉ በቀዝቃዛ መንፈስ የሚከበረዉ የአድዋ ድል በዓል መሆኑንና የዚህ ዋነኛ ምክንያትም “ምንሊክ ጣሊያንን ከመረብ ምላሽ አባረዉ የቀረዉን የኤርትራን ህዝብ ለጣሊያን ባሪነት አሳልፈዉ ሰጥተዉናል” ከሚል ቁጭት  ነዉ፡፡ ይህንን ቁጭት መንፈስ ገልብጠዉ ለራሳቸዉ ኣላማ ለመጠቀም የሞከሩ ገንጣዮች ምንሊክ ይሄን ያደረጉት ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረች በመረዳታቸዉ ስለሆነ“ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆና አታዉቅም” ለሚለዉ ክርክራቸዉ እንደ አንድ ትልቅ መከራከሪያ የሚያቀርቡት ይሁንን ከስተት ነዉ፡፡

+ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴን በሚመለከት ደግሞ ፌዴሬሽኑን በማፍረስ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት በመፈጸማቸዉ ከዚያ በኋላ ለተከሰቱት ችግሮች ሁሉ መነሻ ሆኗል በሚል ይወቀሳሉ፡፡ ይህን ወቀሳ ብዙዎቹ የሚስማሙበት ነዉ፡፡ ንጉሱ ይህን እርምጃ ለመዉሰድ የበቁት ሁኔታዉ ለአስተዳደራቸዉ ስለአላመቻቸዉ በተለይም ይሄ ሪፌሬንደም የሚባለዉ ጣጣ ወደ ሌሎች ክልል ህዝቦችም ተጋብቶ መጥፎ አርአያነት እንዳይሆን በመስጋትና በተጨማሪ የምጽዋና የአሰብ ወደብ ዕጣ ፈንታ ስለአሰጋቸዉ እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡

ንጉሱ ወደዚህ ዉሳኔ የደረሱት በራሳቸዉ ተነሳሽነት ሳይሆን አንድነትን እንጂ ፌዴረሽኑን እንፈልግም በሚሉ የራሳቸዉ የኤርትራ ፓርላማ አባላትና በአብዛኛዉ የኤርትራ ህዝብ ጥያቄ ተደፋፍረዉ ያደረጉት ነዉ፡፡ የንጉሱ ዉሳኔ ምንም ይሁን ምን የኤርትራን ጉዳይ ማወሳሰቡ ግን እርግጥ ቢሆንም እሳቸዉ (ንጉሱና) አክሊሉ ሃብተወልድ ኤርትራን መጀመሪያ ከጣሊያን ቅኝ አገዛዝ ከዚያ ደግሞ ሞግዚት አስተዳደር አላቀዉ መጀመሪያ በፌደረሽን ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያ አካል እንድትሆን ለበርካታ አመታት ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ጥረት እጅግ የሚደነቅና የሰሩት ስህተት ቢኖር እንኳን ለኢትዮጵያ ጥቅም ተብሎ መሆኑ ሊዘነጋ የሚገባዉ አይደለም፡፡

+ ደርግ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነትን ያደረገዉን ተጋድሎ መካድም  ሆነ ማጣጣል ትልቅ ታሪካዊ ግድፈት ነዉ፡፡ የደርግ ትልቁ ችግር ለአንድነት መታገሉ ወይም ኤርትራን እንዳትገነጠል ለማድረግ መዋጋቱ ሳይሆን አጠቃላይ ችግሩን ያስተናገደበት መንገድ የተሳሳተ መሆኑ ነዉ፡፡

ጦርነትን እንደ ብቸኛ መፍትሄ በመቁጠሩ ከጦርነቱ ጎን ለጎን ወይም አስቀድሞ በሰላማዊ መንገድ ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ አስከመጨረሻዉ ድረስ ጥረት አለማድረጉ ጥልቁ ችግሩ ነዉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኤርትራ ህዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍ በማድረግ የኤርትራን መገንጠል እንዲያወግዙ ካደረገዉ ጥረት ይልቅ በተቃራኒዉ ህዝቡ እንዲማረር በማድረግ አማጽዉን ቡድን በሞራልና በሰዉ ኃይል እንዲያጠናክሩ ሁኔታዉን ምቹ ማድረጉ  ዋነኛዉ ተጠቃሽ የደርግ ስህተት  ነዉ፡፡

+ የእኔ አመለካከት መነሻ መለስ ግትር በሆኑ አንዳንድ አክራሪ የድርጅቱ ሰዎች ተጽኢኖ ስር በመዉደቃቸዉ እንዳሰቡት ሊሆን ባይችልም ነገር ግን በኢትዮጰያ አንድነት ላይ የማያወላዉል አቋም የነበራቸዉና ኤርትራ ከመገንጠል ይልቅ በአንድነት እንድትኖር  ጽኑ ፍላጎት የነበራቸዉ መሆናቸዉን ስለምረዳ ነዉ፡፡ በእኔ እምነት መለስ በኤርትራ ጉዳይ ከቀሩት የኢህአደግ አመራሮች ጋር ተዳብለዉ እኩል መወቀስ አይኖርባቸዉም፡፡ መወቀስ ካለበትም መወቀስ ያለበት ደርጅቱ ነዉ፡፡

አሰብን ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ በማንኛዉም መንገድ ማስመለስ ነበረባቸዉ በሚል መለስን የሚወቅሱ ወገኖች በርካታ መልካም አጋጣሚዎችን ሳንጠቀምባቸዉ የቀረነዉ በመለስ ፍላጎት ማጣት ነዉ በሚል መለስን በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ይደመጣሉ፡፡ ከነዚህ መልካም አጋጣሚዎች ከሚባሉት መካከልም የጦርነቱ መነሳት ሲሆን ያን አጋጣሚ በመጠቀም በኃይል ማስመለስ ይቻል ነበር የሚል ነዉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ አሁንም ድረስ በህይወት ያሉ ከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች ይህን አመለካከት ይጋሩት እንደሆነ አርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቢያንስ ግን አጋጣሚዉ ፈቅዶልኝ ከጦርነቱ በኋላ መለስ ሲመሩት በነበረዉ አንድ ስብሰባ ላይ መለስ ሲናገሩ ከነበረዉ የተረዳሁት ነገር ቢኖር በጦርነቱ ወቅት መከላከያ ሰራዊታችን አሰብን እንዲቆጣጠር ለማድረግ መለስ መመሪያ ሰጥተዉ እንደነበርና ነገር ግን በተግባር እዉን ማድረግ አለመቻሉን ነዉ፡፡ በወቅቱ መለስ ሲናገሩ እንደሰማሁት የጦርነቱን አጋጣሚ በመጠቀም አሰብን በእጃችን ለማድረግ መሞከራቸዉን ነዉ፡፡

+ የኤርትራ ህዝብ በተለይ በደርግ ስርአት ኢትዮጵያዊ መባሉ ያስገኘለት አንዳች ጥቅም ቢኖር ኖሮ ደርግ ከወደቀ በኋላ አብሮ ለመኖር ፍላጎት ሊያሳይ ይችል ነበር፡፡ ግን አንድም በመልካም ጎኑ የሚያስታዉሰዉ ነገር ስላልነበረ በሪፌሬንደሙ ወቅት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለብቻዉ መሆኑን መርጧል፡፡ ይህ ሁኔታ ማለትም የኤርትራ ህዝብ በደርግ ምክንያት ከኢትዮጰያ ጋር አብሮ መኖርን እጅግ አደርጎ በመጥላቱ መለስም ሆነ ኢህአዴግ ይሄን ነገር መለወጥ የሚችሉበት አንዳችም አድል አልነበራቸዉም፡፡

+ ስለዚህ ገና ለገና የመለስን ሆነ የድርጅቱን የሚያሳጣ ነገር ሊኖርበት ይችል ይሆናል ተብሎ ሚሊዮኖች የሚያዉቁትን ታሪክ ለመደበቅ መሞከር የዋህነት እንጂ ሌላ ሊሆን  አይችልም፡፡ አቶ መለስን ፍጹምና ጨርሶ የማይሳሳቱ አድርገዉ የሚቆጥሩ ሰዎች የመኖራዉን ያህል የሳቸዉን ቅንጣት ስህተት በማጉላት ያበረከቱትን ዉሌታ ለመካድ የሚፈልጉ ሁለቱም ዓይነት ሰዎች ለእኔ አይስማሙኝም፡፡

+ ሰራዊታችን በኤርትራ ዉስጥ ገብቶ በጥልቀት ሲያደርግ የነበረዉን ማሳዳድ ,እንዲያቆም መለስ ከማዘዛቸዉ በፊት የጄኔራሎቻቸዉን ሃሳብ ለማወቅ በቅድሚያ እንዳማከሯቸዉና እነሱም ከዚ በላይ ወደፊት መግፋት እንደማይችሉ መልስ እንደሰጧቸዉ ይታወቃል፡፡ መጀመሪያም ወደዚህ ዉሳኔ ለመምጣትም ጉትጎታ የነበረዉ ከሌሎቹ የፓርቲዉ አመራሮችና ከአንዳንድ ወታደራዊ ሹሞች እንደነበርም ግልጽ ነዉ፡፡

መለስ ጄኔራሎቹን አማክረዉ ወደፊት ለመግፋት አንደማይችሉ መልስ ከሰጡዋቸዉ በኋላ ነዉ ዉሳኔዉን የወሰኑት፡፡ መለስ ሰራዊቱ ማጥቃቱን እንዲያቆም ትዕዛዛ ከመስጠታቸዉ በፊት ወታደራዊ ሽማምንቱን አማክረዋል፡፡ ስለዚህ ሁኔታ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ እሳቸዉ በሚመሩት አንድ ስብሰባ ላይ ሁኔታዉን አስታዉሰዉ በድጋሚ ስናገሩ ከጀኔራሎቹም ሆነ በቦታዉ ከነበሩት አንዳንድ የፓርቲያቸዉ አመራሮች መካከል ይሄን ጉዳይ ያስተባበለ አንድም ሰዉ አልነበረም፡፡

+ መለስ በሉአላዊነት ጉዳይ ላይ ያለአግባብ ሲወቀሱ እንደነበር ጥሩ ማሳያ የሚሆነን ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ዓለም መሳቂያ መሳለቂያ ያደረገን “ባድመ ለኛ ተወስኗል! ”ተብሎ ህዝብን ያለአግባብ አስጨፍረን ስናበቃ በማግስቱ እንደተባለዉ አለመሆኑ የታወቀበት አሳፋሪ ክስተት ነዉ፡፡ ይሄን ግዙፍ ስህተት የሰራዉ (ነገሩ ስህተት ሳይሆን ሆን ተብሎ የተደረገ ነዉ የሚመስለዉ) ባለስልጣን መለስ እንደዚያ በህዝብ ላይ እንዲቀልድ ሰላዘዙት እንዳልነበር ሁላችንም ጠንቅቀን እናዉቃለን፡፡

+ ኢህአዴግ በተደጋጋሚ በተግባር ያረጋገጠልን አንድ መሰረታዊ ችግሩ በኢትዮጵያ ህዝብና በፓርቲዉ መካከል በሆነ ጉዳይን በሚመለከት የግድ አንዱን የመምረጥ ጉዳይ ሲኖር ብዙዉን ግዜ ለፓርቲዉ ማድላቱ ነዉ፡፡ ፓርቲዉንና የፓርቲዉን ቁልፍ አመራር ከማሳጣት ይልቅ የ90 ሚሊዮን ህዝብ ጉዳይን ችላ ማለት እንደሚቀለዉ አስቀድሜ የጠቀስኩት ”የባድመ ለኛ ተወስኗል“ ታሪክ ጥሩ ማሳያ ነዉ፡፡

+ ዶክተር ቴድሮስ ከአብዛኛዎቹ የህወሃት/ኢህአደግ ባለስልጣናት በብዙዎቹ ኢትዮጵያዉን ዘንድ ጥሩ ስም ያላቸዉና ተወዳጅ እንደሆኑ ጠንቅቄ አዉቃለሁ፡፡ እኔም ብሆን ለሳቸዉ የተለየ አክብሮት አለኝ፡፡ በመመረጣቸዉ የከፋቸዉ ጥቂት ሰዎች ባይጠፉም አብዛኛዎቻችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል፡፡

ይሁን እንጂ መንግስትና ኢህአዴግ ዶክተር ቴድሮስ እንዲመረጡ ያደረገዉን ከፍተኛ ጥረት ሲነገር የሰማን ሰዎች መንግስት አንድን ግለሰብ ለማሾም ይሄን ያህል ከደከመ ምንአለበት ታዲያ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ጉዳይ ላይ በተለይ ከኤርትራ ጋር በነበረዉ ሙግትና በአሰብ ጉዳይ የዚህን ግማሽ ያህል እንኳን ጥረት አለማድረጉ የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡

+ መለስ ስህተት የሚባል ነገር አልሰሩም በሚል እየተሟገትኩላቸዉ አይደለም፡፡ ስህተትማ ይኖራል፡፡ መለስ እንደመሪም እንደዜጋም የሰሩት ስህተት ይኖራል፡፡ ነገር ግን የስህተቶች ሁሉ ተሸካሚ ለማድረግ መሞከሩ ግን ተገቢ ስላልሆነ ነዉ፡፡ መለስ በመጨረሻም የመሳሪያ ግዥዉ እንዲከናወን ቢፈቅዱም መቼም እሳቸዉ (መለስ) በየሀገሩ እየዞሩ በመሳሪያ ግዥዉ ላይ እንደማይሳተፉ ግልጽ ነዉ፡፡ በርካታ የዉጭ ምንዛሪ ወጥቶ መሳሪያ ካልተገዛ እያሉ ሲጎተጉቱ የነበሩ ሰዎች ለዚህ ተብሎ የተረከቡትን የዉጭ ምንዛሪ ገንዘብ በሙሉ ለታለመለት ዓላማ ለመሳሪያ ግዥ አዉለናል ብለዉ ቢነግሩን ማን ያምናቸዋል?

+ ለማናዉቃቸዉ ለእነ ሌኒንና ማርክስ ሃዉልት ሲቆምላቸዉ በነበረ ሀገር እንዲሁም በየክልል ከተሞች ከዚያዉ አካባቢ ዉጭ ለመላዉ ሀገሪቱና ለኢትዮጰውያ ህዝብ ምን እንደሰሩ በዉል ታሪካቸዉ ለማይታወቁ ግለሰቦች በፉክክር በየስርቻዉ መታሰቢያ ሃዉልት በሚቆምባት ጉደኛ የሆነች ሀገር ዉስጥ የመላዉ ኢትዮጵያን ክብር ከፍ እንዲል ላደረጉና ሀገራችንን ከወደቀችበት አንስተዉ ተገቢዉን የክብር ቦታዋን እንዲታገኝ እድሜ ልካቸዉን ለደከሙት ለመለስ እንድ እንኳን መታሰቢያ ሃዉልት በሀገሪቱ እምብርት በዋና ከተማዋ አለመኖሩ እጅግ የሚያስተዛዝብ ነዉ፡፡ ይህ ግን የሳቸዉን በተለየ መታወስ የማይሹ ጥቂት ግለሰቦች ሴራ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ህዘብ ፍላጎት እንዳልሆነ እረዳለሁ፡፡

+ የኤርትራ ነጻ መዉጣት ጉዳይ መጀመሪያዉኑ በትጥቅ ትግል መልስ ያገኘና  የኤርትራ ህዝብ የነጻነት ትግል ዉጤት እንጂ የመለስ ሴራ ዉጤት አይደለም፡፡ ወይንም ኢሳይያስ ያለፍላጎቱ በመለስ ሴራ ተገፋፍቶ እንዲገነጠል የተደረገበት ሁኔታም አይደለም፡፡

ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ ሰሞን ራሱ የኤርትራዉ ኢሳይያስ በታዛቢነት በተገኘበት የአዲስ አበባዉ የሰላም ጉባኤ ላይ አሁን በህይወት የለሉት ፕሮፌሰር አስራት ስለ ኤርትራ መገንጠል ጉዳይ አንስተዉ ተቃዉሞ ሲያቀርቡ ኢሳይያስ “ኢትዮጵያ አንድነት ምናምን የምትሉትን ተረት ተረት ወዲያ አድርጉት፤ የኤርትራ ነጻ መዉጣት ጉዳይ በጦርነት መልስ ያገኛና ያበቃለት ጉዳይ  ነዉ” በሚል ነበር በቁጣ የገለጹት፡፡

ኢህአዴግን በሚመለከት ለየት የሚያደርገዉ የቀድሞዎቹ መንግስታት ከሰሩት ጥፋት ተቃራኒ በሆነ መልኩ ለኤርትራ መነጠል ከሞላ ጎደል“ ቀላል የማይባል  ሚና” መጫወቱ ነዉ፡፡ ይህ የኢህአዴግ ሚና ከአንድነት ይልቅ የኤርትራ መገንጠል ይበጃል በሚል የተደረገ ሳይሆን ህዝቡ ከጨቋኝ ስርአት ጋር ሲያደርግ የነበረዉን ትግል በመርህ ደረጃ ትክክል ነዉ ብሎ ስላመነበት ነዉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዉጤቱ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጎዳ መሆኑ ባይቀርም ነገር ግን ሆን ተብሎ መገንጠል አለባቸዉ በሚል የኢትዮጵያን አንድነት በመቀናቀን  እንደተከናወነ አድርገን እንድንቆጥር አያደርግም፡፡ የኢህአዴግ ሚና ለኤርትራ መገንጠል ምንም ይሁን ምን እንደ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ሲታይ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት መሆኑ ላይ አያከራክርም፡፡ 

+ ብዙዎቹ እንደሚስማሙበትና እኔም እንደማምንበት ለኤርትራ ነጻ መዉጣት ወሳኙ የኤርትራ ህዝብ ተጋድሎ እንጂ የህወሃት ድጋፍ ማድረጉ አልነበረም፡፡ ይህ ማለት ግን ሻእቢያ የህወኃትን ሚና በመካድ አኮስሶ እንደሚገልጸዉ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ህወኃት ሆን ብሎ ለኤርትራ መገንጠል ለዓመታት ሲሰራ የቆየ ድርጅትና ለኤርትራ መገንጠል ወሳኝ ድርሻ እንደነበረዉ አድርገዉ እንደሚናገሩትም አይደለም፡፡ ለኤርትራ መገንጠል የህወኃትን ሚና ወሳኝ ማድረግም ሆነ ለኤርትራ ህዝብ ነጻነት ኢህአዴግ ያደረገዉን በጎ አስተዋጽኦ መካድ ሁለቱም አስተያየቶች የተዛቡ ናቸዉ፡፡

+ የቀድሞዎቹ መሪዎች ያጠፉት ነገር ካለ እንደ ራሱ ጥፋት ቆጥሮ ማስተካከልና መስመር ማስያዝ ይጠበቅበታል እንጂ የቀድሞዎቹ ባበላሹት እኔ ምን አገባኝ ማለት አይችልም፡፡ ምንኒሊክ ከአቅም በላይ ሆኖባቸዉ ወይም በዚያን ዘመን የነበረዉ ልዩ ሁኔታ ሳይፈቅድላቸዉ ቀርቶ በዘመናቸዉ የሰሩት ስህተት ካለ የአሁኑ መንግስት ስህተቱን ለማረም መጣር አለበት እንጂ የቀድሞዎን ስህተት ለራሱ ስህተት እንደሰበብ መጠቀም አይኖርበትም፡፡ ይሄን ታሪካዊ ሃላፊነትን ኢህአዴግ በትክክል ለመረዳቱ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

+ ደርግ ብዙ ነገሮችን በማበላሸቱ ኤርትራዉያን ከእንግዲህ ወዲያ ከኢትዮጵያ ጋር በአንድነት ለመኖር በጭራሽ ፍላጎት እንዳልነበራቸዉ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ዛሬ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜት ቢፈተሽ ድሮ በነበረዉ አቋም እንደማይገኝ መገመት አያዳግትም፡፡ በኤርትራ በኩል መገንጠሉ የፈለጉትን ዲሞክራሲ፣ ፍትህ፣ ነጻነትና ብልጽግና ባያመጣላቸዉም በዚህ ምክንያት ብቻ በሪፌረንደሙ ወቅት ነጻነትን መምረጣቸዉን እንደ ስህተት ይቆጥሩታል ብሎ ለመገመት አይቻልም፡፡ ኤርትራዉያን  ለነጻነት የሚሰጡትን ትርጉም በነሱ ቦታ ሆነን ከላየን በስተቀር ከኛ ፍላጎት አንጻር ብቻ መፍረድ አንችልም፡፡

+ ሻዕቢያ የእስመራን ቤተመንግስት የተቆጣጠረዉ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነዉ፡፡ በወቅቱ ሻዕቢያ ከኢህአዴግ የበለጠ ወታደራዊ ኃይል አለኝ በሚል የሚኩራራ ስለነበር ኢህአዴግ የሚለዉን ለመቀበል የሚገደደድበት ሁኔታም አልነበረም፡፡ እንደሚታወቀዉ የኤርትራ ሪፈረንዴም ከመከናወኑ በፊት ቢያንስ ለሁለት ዓመት ያህል ሻዕቢያ ኤርትራን ለማስተዳደር ችሎም ነበር፡፡ ለሁለት ዓመታት ነጻነቱን ሳያዉጅ የቆየዉም የኢህአዴግን ፈቃድ ለማግኘት ብሎ ሳይሆን ለሪፌሬንደሙ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ግዜ ስላስፈለገዉ በራሱ ምክንያት ነዉ፡፡

+ በኢህአዴግ በኩል ያደረገዉ ነገር ቢኖር ማድረግ የሚገባዉን ነዉ፡፡ ኢህአዴግ የሪፌሬንደሙ ሂደት ላይ አንዳችም እንቀፋት አለመፍጠሩና ከዚያ በኋላ እንደ ማንኛዉም አገር እዉቅና መስጠቱ ነዉ፡፡ እንደዚያ ባያደርግም ዞሮ ዞሮ የኤርትራ ለብቻዋ መሆን ሊያስቀር የሚችል ሁኔታም አይሆንም ነበር፡፡

+ ከትችቶች መካካል ተገቢነት የሚኖረዉ ሪፌረንደም ከመደረጉ በፊት የሁለቱን አገራት በጋራ በሚነካኩ ጉዳዮች ላይ በተለይ በድንበርና በወደብ ጉዳይ አንድ እልባት ላይ መደረስ ነበረበት የሚለዉ ነዉ፡፡ ኤርትራና ኢትዮጵያ ወደፊት እንደሁለት አገር የሚኖራቸዉ ወሰን የት ላይ መሆን አለበት የሚልና የባህር በር አጠቃቀምም ሆነ ባለቤትነትን በሚመለከት በመግባባት ላይ የጠመሰረተ ዉል መደርግ ነበረበት የሚለዉ ነዉ፡፡ ይህ ግን በምንም መንገድ ሪፈረንደሙን ለማዘግየት ወይንም እስከነአካቴዉ እንዳይደረግ ለማገድ  ያለመ መሆን እንደለለለበት ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፤ይሄን ማድረግ በጭራሽ አንችልም፡፡

+ የኤርትራ ጉዳይ ገና በደርግ ግዜ ያባለቀለት ጉዳይ በመሆኑ ኢህአዴግን በአለቀለት ጉዳይ ላይ መተቸትም ሆነ ማመስገን ትርጉም አይኖረዉም፡፡ የኤርትራ ከኢትዮጵያ መነጠል ጉዳይ ከዚህ በኋላ መጸጸቱና መቆጨቱ ግዜዉ ያለፈበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ኤርትራን በሚመለከት ከዚህ በኋላ ዋናዉ ተፈላጊ ጉዳይ ቢቻል መልካም ጎረቤታሞች ሆነን እንዴት በሰላም እንኑር ካልሆነም ደግሞ ኤርትራ በየግዜዉ ከምታደርስብን ትንኮሳ እንዴት እንድትተቃብ እናድርጋት የሚለዉ ነዉ፡፡ ከዚያ ዉጭ ባለፉ ጉዳዮች እንዲህ ቢሆን ኖሮ እያልን መቆጨቱ ስለማይጠቅመን ከዚያ ይልቅ ከዚህ በኋላ ማስተካከል በምንችለዉ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገን ብንሰራ ነዉ የተሻለ ይመስለኛል፡፡

 

——————————————————

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት 3

የኤርትራ ወረራ ድንገተኛና ያልተጠበቀ ነዉ መባሉ አግባብ ነበር?

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ፃድቅ)

(የዚህን ፅሁፍ የመጀመሪያ ክፍል ለማንበብ በዚህ ሊንክ እና ሁለተኛ ክፍል ለማንበብ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ)

Highlights

* ‹‹ …ሻዕቢያ ከጦርነቱ አስቀድሞ ቀደም አድርጎ ሲያደርግ ከነበረዉ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅትና የሻዕቢያ አመራሮች ከበፊት ጀምሮ የሚታወቅ  የጠብጫሪነት ባህሪይ በመነሳት ትንሽ እንኳን አለመጠራጠር ትልቅ ስህተት ነዉ የሚል አቋም ያላቸዉም አሉ፡፡ ....ህዝቡ ስለጦርነቱ ሲሰማ መገረሙና መደናገጡ ተገቢ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ይልቁንም የመከላከያና የደህንነቱ አካላትና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ ተሸለዉ መገኘት ሲገባቸዉ ህዝቡ ግራ ሲጋባ አብረዉ ግራ መጋባታቸዉ በፍጹም የማይጠበቅና መሆን የሌለበትም ነዉ፡፡››

* ‹‹መንግስታችን “የኤርትራ ወረራ ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነበር” ሲል ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም “ከኤርትራም ሆነ ከሌላ ከዬትኛዉም ወገን ሊሰነዘርብን ለሚችል ጦርነት አስበንበትም ተዘጋጅተንበትም አናዉቅም፡፡ እንዲያዉም ለጦርነት ተብሎ የተዘጋጀ ሰራዊትም አልነበረንም” የሚል ሳይሆን ከኤርትራ ጋር ጦር ሊያማዝዝ የሚችል አንዳችም ዓይነት ቅራኔ፤ አለመግባባትና የጠላትነት ስሜት ስላልነበረ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል ብሎ ለማሰብ የሚያበቃ አሳማኝ ምክንያት የለም የሚል ነዉ፡፡››

* ‹‹ከጦርነቱ በፊት በርከት ያለ የዉጭ ምንዛሪ አዉጥተን አዳዲስ መድፎች፤ አይሮፕላኖች፤ታንኮች፤ ሚሳይሎች ወዘተ አልገዛንም ይሆናል፡፡ …..ነገር ግን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማይጎዳና የአካባቢያችን የወደፊቱን ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአንጻራዊነት አነስ ያለ ግን ደግሞ ብቃት የለዉ መከላከያ ተቋም ለመመስረት ጥረቶች እየተደረጉ እንደነበሩ መካድ አይቻልም፡፡››

* ‹‹ከጦርነቱ በፊት በነበረችዉ አጭር የሰላም ጊዜ ዉስጥ ሲሰሩ የነበሩ  የልማት እንቅስቃሴዎች ጦርነቱን ለመቋቋም ትልቅ እገዛ አድርጎልናል፡፡ ሻዕቢያ ለሰባት ዓመታት በድብቅ ሲዘጋጅ ለቆየበት ጦርነት እኛ በአጭር ጊዜ ዝግጅት በልጠን የተገኘንበት አንዱ ምስጢር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከኤርትራ ሲነጻጸር የተሻለ እንዲሆን ማድረግ በመቻላችን ነዉ፡፡ ….ጦርነቱ በልማት ጥረታችን ላይ ትልቅ እንቅፋት መሆን መቻሉ እርግጥ ነዉ፡፡ ለጦርነቱ ሲባልም በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት የዉጭ ምንዛሪ ማዉጣታችንና የሀገራችን የመከላከያ ባጄት ከጂ.ዲ.ፒ. (GDP) 11 % በላይ መድረሱ ጦርነቱ ለልማታችን ምን ያህል እንቅፋት እንደነበር ያሳያል፡፡››

* ‹‹ በዘመናዊ ዉጊያ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ዝግጅት ያለማድረጉ ችግር ለምድር ኃይሉ ብቻ ሳይሆን በአየር ኃይላችንም ላይ የታዬ ትልቅ ጉድለት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ እንደሚታወቀዉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከጠላት አየር ኃይል ጋር ወደ ጦርነት የገባበት አጋጣሚ በታሪኩ ዉስጥ ሁለት ጊዜ ብቻ ይመስኛል፡፡ አንደኛዉ የዛሬ 40 ዓመት በፊት ማለትም በ1969 ዓ/ም ከሶማሊያ ወራር ጦር ጋር በተለይ ከሶማሊያ አየር ኃይል ጋር የተደረገዉ ጦርነት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አሁን አያወሳን ባለነዉ ጦርነት ማለትም ከኤርትራ አየር ኃይል ጋር ነዉ፡፡››

* ‹‹ የኤርትራ ጦርነት እንደተጀመረ የዘመናዊ ትጥቅ ባለቤት ለነበረዉና ከተመሰረተ በርካታ አመታትን ላስቆጠረዉ አየር ኃይል ግን የራሱ ዶክትሪን ሰነድ ፈልጎ ማግኘትም አልተቻለም ነበር፡፡ አየር ኃይሉን ለጦርነት በማዘጋጀት ላይ ለነበሩት የወቅቱ አዛዥ ለጄ/ል አበበ (ጆቤ) ሁኔታዉ ቢያስገርማቸዉም የአሜሪካን ዶክትሪን ከኢንተርኔትና ከሌሎች መረጃዎች እያፈላለጉና መሰረታዊ በሆነዉ የአየር ኃይል ዶክትሪን (basic air doctrine) ላይ ይበልጥ ትኩረት በማድረግ በማስተርጎምና ከኛ ሁኔታ ጋር እያዛመዱ የሚመለከታቸዉ አመራሮች እንዲወያዩበት ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡››

* ‹‹ በተለያዩ ጊዜያት ሲደረጉ ከነበሩ አካባባዊ የሥጋት ትንታኔ ጥናቶች ኤርትራ እንደ ጠላት ቀርቶ በአጠራጣሪ ወዳጅ ደረጃ እንኳን አንድም ጊዜ አለመመደቧ የሚታወቅ ነዉ፡፡ እኔ ራሴ እንደማስታዉሰዉ ከጦርነቱ አንደ አመት ቀደም ብሎ የሀገራችንን የወደፊቱን አየር መከላከያ ሲስተም ለመዘርጋት መነሻ ጥናት እንዳቀርብ ታዝዤ በሰራሁበት ወቅት በካርታ ንድፍ ላይ የኤርትራን ኤር ቤዝ ምልክት የጠላት መለያ በሆነዉ በሰማያዊ ቀለም በማድረጌ የቅርብ አለቃዬ የነበረዉ ክፉኛ ተቆጥቶኝ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ አለቃዬ ራሱ ኤርትራን “ወዳጅ” ለማለትም ቸግሮት እንደነበረም ትዝ ይለኛል፡፡››  

* ‹‹ ከጦርነቱ በፊት በኤርትራና በኢትዮዮጵያ መንግስታት መካከል በብዙ ጉዳዮች የመተባበርና የወዳጅነት መንፈስ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ትንሽ በተለየና ጠንከር ባለ መንገድ ከኤርትራ ጋር ወዳጅነት መመስረቷ የሚጠበቅና ተገቢም ነበር፡፡ ኤርትራና ኢትዮጵያ ወቅቱ አስገድዶአቸዉ ቢለያዩም አንድ አገር የነበሩ በመሆናቸዉ ከኬንያና ከሱዳን የበለጠ ወዳጅነት በመመስረቱ መንግስትን የሚያወቅስ አይደለም፡፡››

* ‹‹ የሻዕቢያ  መሪዎች እንደ እስራኤል ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በመገንባት የሪጀኑ (የአካባቢዉ) ወሳኝ ሃይል ለመሆንና በኢኮኖሚ ደግሞ የምስራቅ ኤሽያዋን ሲንጋፖር ለማድረግ ማለማቸዉ የሚያስወቅሳቸዉ አይደለም፡፡ ….. ችግሩ ግን ይህን ህልማቸዉን እዉን  ለማድረግ ያሰቡበት መንገድ በኛ ኪሳራ መሆኑ ነዉ፡፡››

* ‹‹ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት ለኤርትራ ህዝብ ነጻነት ሙሉ ድጋፍ ከማሳየት ዉጭ አንድም ጊዜ የኤርትራን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነግር አድርገዉ አያዉቁም፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ነባሮቹ ታጋዮች ለኤርትራ ገዢ ፓርቲ ለሻዕቢያ አመራሮች የነበራቸዉ አመለካከት ግን ከዚህ የተለየና በጥላቻ የተሞላ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ ሻዕቢያ ገና ከትግሉ ጊዜ ጀምሮ ዲሞክራሲያዊ አመለካከት የሚባል ነገር ያልነበረዉ ሰብአዊነትና ለህዝብ ከበረታ ያልነበረዉ አምባገነን ድርጅት እንደነበርና አሁንም መንግስት ከሆነም በኋላ ይህንኑ ባህሪይዉን ሳይቀይር በመቆየቱ የኤርትራን ህዝብ ለባሰ ጭቆና መዳረጉን በማዉሳት ለሻእቢያ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸዉ ለሚቀርቧቸዉ ሲገልጹ በቁጭትና በሃዘን ነበር፡፡ ››

* ኤርትራ ከኛ ስታገኝ የነበረዉና በኋላ የተቋረጠባት የገዛ ንብረቷ ስለነበረና ያንን ማግኘት ህጋዊ መብቷ ስለነበረም አይደለም፡፡ በፊት እንደዋዛ ያስለመድናትን ጥቅም በድንገት ስናቋርጥባት አንድም ሌላ አማራጭ ያልነበረዉ የኤርትራ አገዛዝ ከጦርነት የተሻለ ነገር ይኖራል ብሎ ስለማያስብ በኛ ላይ ጦርነት ቢከፍት ለምን ያስገርመናል? በእኛ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ህጋዊም ተገቢም እንዳልነበረ እንኳን እኛ ወረራ የፈጸመብን ሻዕቢያም ቢሆን ይሄን  አይረዳም ማለት አይቻልም፡፡ ችግሩ ያለዉ እኛ ዘንድ ነዉ፡፡ ይሄ እንደሚደርስ አስበን አለመጠርጠራችንና በቂ ዝግጅት በቅድሚያ አለማድረጋችን የኛ ድክመት ነዉ፡፡

* ‹‹በሽግግሩ ወቅት አየር ኃይላችን እንደገና በማቋቋም ስራ እንዲያግዙ በጊዜያዊነት በመንግስት ተመድበዉ የነበሩት ብርጋዲር ጄነራል ሰለሞን በየነ  ኤርትራም በበኩሏ አየር ኃይል ለማቋቋም ስታደርግ በነበረዉ ጥረት ኢትዮጵያ ማገዝ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ለመመካከር አስመራ ድረስ በመሄድ ከባለስልጣናቱ ጋር ሲመካከሩ ዓይን አዉጣዎቹ  የኤርትራ መከላከያ ባለስልጣናት ለጄነራሉ አቅርበዉ የነበረዉ ሃሳብ እጅግ የሚገርም ነበር፡፡ ያቀረቡትም ጥያቄ ደብረዘይት ያለዉ የአየር ኃይል ማስልጠኛ ተቋም እንዳለ ተነቅሎ እዚህ አስመራ ላይ ተቋቁሞ ለሁለቱም አገሮች ስልጠና ከአስመራ ላይ ይስጥ የሚል ነበር፡፡ ››

1/የኤርትራወረራድንገተኛናያልተጠበቀነዉስለመባሉ

የሻዕቢያ ወረራ ጉዳይ ሲነሳ እስከዛሬም ትልቅ ጥያቄ የሚያስነሳዉ “ወረራዉን ያልጠበቅነዉና ድንገተኛ ነዉ” መባሉ ሲሆን በርግጥ ድንገተኛ ሊባል ይችል ነበር ወይ በሚለዉ ላይ በሁለት ጎራ የተከፈለ አቋም እንዳለ መገመት አያዳግትም፡፡

በወቅቱ ከነበረዉ ሁኔታ መረዳት እንደሚቻለዉ ባንድ በኩል በሁለቱ አገራት መካከል መልካም ግኑኝነት የነበረ በመሆኑና ኤርትራ ከዚህ ግኑኝነት የበለጠ ተጠቃሚ ስለነበረች ይህን መልካም አጋጣሚ በምንም ምክንያት የሚያበላሽ የጠብ አጫሪነት ድርጊት  አትፈጽምም ብሎ መንግስት ማሰቡ ተገቢ ነበር የሚለዉ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሻዕቢያ ከጦርነቱ አስቀድሞ ቀደም አድርጎ ሲያደርግ ከነበረዉ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅትና የሻዕቢያ አመራሮች ከበፊት ጀምሮ የሚታወቅ  የጠብጫሪነት ባህሪይ በመነሳት ትንሽ እንኳን አለመጠራጠር ትልቅ ስህተት ነዉ የሚል አቋም ያላቸዉም አሉ፡፡

የኤርትራ መንግስት ከአካባቢዉ አገሮች ጋር ሁሉ እንድ በአንድ ሲላተም ላዬ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አንድ ቀን ለኛም አይቀርም ብሎ መጠርጠር ይገባዋል፡፡ እንደ ሀገር እዉቅና ካገኘ በአምስት አመታት ዉስጥ ከሁሉም አጎራባች አገሮች ጋር ጦር የተማዘዘ እንደ ኤርትራ አይነት ሌላ አገር በአፍሪካ ምድር የለም፡፡

ምናልባት እንደ ሀገር ከታወቀችበት ከ1948 ጀምሮ  ከዚህም ከዚያም የምትላተም አገር ብትኖር አስራኤል ብቻ ነች፡፡ እሷስ የግድ ሆኖባት ነዉ፡፡ ኤርትራ ግን አንድም ዉጫዊ ስጋት ሳይኖርባት ራሷ ነች ጠብ የምትጭረዉ፡፡ ኤርትራ ጦር ለመስበቅ ምንም የተለየ ሰበብ አያስፈልጋትም፡፡ ባሻት ግዜ ጥቃት መሰንዘር ነዉ ስራዋ፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸዉ ከነበረዉ ጠንካራ ወዳጅነትና መደጋገፍ እንዲሁም ሁለቱም አገሮች ህዝቦች በጦርነት የተሰላቹ ስለነበሩ ሙሉ ትኩረታቸዉን ወደ ልማት ያደርጋሉ ከሚል ግምት በግኑኝነታቸዉ መካከል የተከሰቱ አንዳንድ አለመግባባቶችንም በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ የሚችሉ እንጂ ለጦርነት መነሾ ምክንያት ሊሆኑ ባልተገባቸዉ ነበር ብንልም ነገር ግን መንግስት ካለበት ኃላፊነት አንጻር ተገቢዉን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መዉሰድ ይገባዉ እንደነበር ግልጽ ነዉ፡፡

አስቀድመን መጠንቀቃችን አስቀድመን እንድንዘጋጅ ስለሚረዳን ሻዕቢያ ለጥቃት እንዳያስብ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ ካልሆነና አይኑን ጨፍኖ ጦርነትን ከመረጠም ጦርነቱን አንስተኛ በሆነ ኪሳራ በአጭር ጊዜ ማሸነፍ እንችል ነበር፡፡ በሻዕቢያ ሰራዊት ላይም ከአሁኑ የከፋ ጉዳት ማድረስ በተቻል ነበር ፡፡

1.1/የሻዕቢያወረራለምንድንገተኛናያልተጠበቀሆነ?ወይምተባለ?

ስለ ኤርትራ ወረራ ማድረግ በኢትዮጵያ መንግስት በይፋ መግለጫ እሰከተሰጠበት ድረስ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ግምት በአብዛኛዎቻችን ዘንድ የነበረ አይመስለኝም፡፡ ባድመ እንደምክንያት በተሰኘዉ መጽሀፋቸዉ እዉቁ የመረጃ ሰዉ ኮ/ል ተወልደ ገ/ተንሳይ ስለወረራዉ ያልተጠበቀ መሆን “…….አስደንጋጭ፤ ያልተገመተ፤ ከማይገመት ኃይል ምንም ዝግጅት ባልተደረገበት ወቅት ወረራ ተካሂዷል፤ ድንበራችን ተጥሷል፤ ሉአላዊነታችን ተደፍሯል፡፡ ……ህዝባችን በታንክ ሰንሰለት እየተረገጠ ነዉ” በሚል የወቅቱን ሁኔታ በአጭሩ ገልጸዉታል፡፡

ኮ/ል ተወልደ እንኳን የጦርነት ዝግጅትን የሚያክል ግዙፍ ክስተት ቀርቶ ጥቃቅን ጉዳዮች እንኳን እንደማያመልጣቸዉ ለምናዉቅ ሰዎች ልክ እንደኛዉና እንደ ቀረዉ ተራዉ ዜጋ የኢሳይያስን ወረራ ከኛ ጋር እኩል መስማታቸዉ እጀግ አስገራሚ ነዉ፡፡ ስለ ኮ/ል ተወልደ መነሳቱ ካልቀረ በዚህ አጋጣሚም በሳቸዉ ላይ የተሰማኝን አንዳንድ ቅሬታዎች መጥቀስ ያለብኝ ይመስለኛል፡፡

ብዙዎቻችን እንድምናወቀዉ ኮ/ል ተወልደ ገ/ትንሳይ እድሜ ልካቸዉን በመረጃ ላይ ሲሰሩ የቀዩና በመረጃ ሙያ እጅግ የተካኑና በታታሪነታቸዉም መልካም ስም የነበራቸዉ ናቸዉ፡፡ በጦርነቱ ወቅት ስለጠላት ሲደርሱን የነበሩ እጅግ ጠቃሚ መረጃዎች ሁሉ የሳቸዉና የሳቸዉ ባልደረቦች ጥረት ዉጤት እንደሆነ አዉቃለሁ፡፡

ይሁን እንጂ ኮ/ል ተወልደ በጻፉት አስቀድሜ በጠቀስኩት መጽሀፍ እንዴ መረጃ ሙያተኝነታቸዉና በጦርነት ሰፊ ልምድ እንዳለዉ የጦር ሰዉና ኃላፊነትና ተጠያቂነትም እንደነበረዉ የመከላከያ አመራር ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳወቅ የሚገባቸዉን ብዙ ሃቆች ሆን ብለዉ አድበስብሰዉ አልፈዋል፡፡ ኮ/ል ተወልደ በመጽሀፋቸዉ ዉስጥ ያልነካኩዋቸዉና የግድ ማንሳት ከነበረባቸዉ በርካታ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ እሞክራለሁ፡፡

* የሀገሪቱ መከላከያ ተቋም የመረጃ ሃላፊ ሆነዉ እያለ ሻዕቢያና የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደገሱለት የነበረዉን የጦርነት ዝግጅት እንደማንኛዉም ተራ ዜጋ “አላዉቅም ፤ አልሰማሁም” ማለታቸዉ አጅግ አስተዛዛቢ ነዉ፡፡

* ከወረራዉ ድንገተኛነት የተነሳ መንግስት ተገቢዉን ወታደራዊ ዝግጅት ሳያደርግ በመቆየቱ ምክንያት በኛ በኩል ለተከፈለዉ መጠነ ሰፊ መስዋእትነት፤ በህዝቡና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ለደረሰዉ መንኮታኮትና የህዝባችን ህይወት መመሰቃቀል በአጠቃላይ በጦርነቱ ሰስለደረሰብን  ዘርፈ ብዙ ኪሳራ  አንድም ነገር ትንፍሽ አለማለታቸዉ፤

* በጦርነቱ መካከል ቢያንስ በሁለት አጋጣሚዎች በሽሽት ላይ የነበረዉን የሻእቢያ ሰራዊት አሳደን መደምሰስ ሲገባን በይቅርታ (በቸልታ) የታለፈበት ሁኔታ፤ አንደኛዉ አጋጣሚ በ1991 ዓመተምህረት በዘመቻ ጸሀይ ግባት ሁለተኛዉ ደግሞ በጦርነቱ የመጨረሻዉ ምእራፍ በ1992 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ አስካሁንም ብዙ ሰዎችን ሲያወዛግብ የነበረ ከመሆኑ አንጻር ኮሎነሉ ከዉገና ነጻ የሆነ የራሳቸዉን የግል አመለካከት መነሻ ያደረገ ሙያዊ ትንቴና ሊሰጡበት ይገባ ነበር፡፡

እሳቸዉ ግን አስቀድሜን ጠንቅቄን የምናዉቀዉን ታሪክ ደግመዉ ሊነግሩን ከመሞከራቸዉ  ዉጪ በዉሳኔዉ ተገቢነት ላይ የሳቸዉን አቋም ሊነግሩን ይገባቸዉ ነበር፡፡ ግን በዚያ መንገድ አላደረጉትም፡፡ በደርግ ዘመን ስንት መስዋእትነት ተከፍሎ የተገኘን ድል በኮ/ል መንግስቱ ትዕዛዝ ሰራዊቱ ለሻእቢያ አስረክቦ ይዞታዉን ለቆ ወደ ኋላ እንዲመለስ ሲደረግ ከነበረዉ አሳዛኝ ክስተት የአሁኑ ሁኔታ በምን እንደሚለይ ኮ/ል ተወልደ ሊነግሩን ይገባ ነበር፡፡

* በጦረነቱ የተከፈለዉን ያን ሁሉ ኪሳራ ዋጋ በሚያሳጣ ደረጃ በፍርድ መድረክ የተነጠቅነዉን መብት አስመልክተዉ የሚሰማቸዉን አስተያየት መስጠት ይገባቸዉ ነበር፡፡

* በጦርነቱ ስለከፈልነዉ መስዋእትነተና ስለደረሰብን አጠቃላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አንዳችም ነገር ሳይጠቅሱ በዝምት አልፈዋል፤፤በተጨማሪ ስለኤርትራ ሰራዊት አቅም እጅግ አንኳሰዉና ደካማ አድርገዉ በአንጻሩ የኛን ሰራዊት አንዳችም አንከን እንዳልነበረዉ አድርገዉ የገለጹበት መንገድ በፍጹም አሰተማሪ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለ ጦርነት ጠንቅቆ ከሚያዉቅና  ስለእኛ ሰራዊትም ሆነ ስለኤርትራ በቂ መረጃ ካለዉ እንደ ኮ/ል ተወልደ ካለ ሰዉ የምንጠብቀዉ ሚዛናዊ የሆነ ግምገማ ነዉ፡፡ እሳቸዉ ግን ራሳቸዉን እንደ ወታደር ሳይሆን እንደ ካድሬ አድርገዉ በመቁጠር ወደ አንድ ወገን ያደላ አስተያየት ነዉ የሰጡት፡፡ ለመንግስትም ሆነ ለመከላከያችን ይበልጥ ይጠቅም የነበረዉ ሚዛናዊ የሆነ የሙያ አስተያየት ቢሰጡ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደጠበቅነዉ ሊሆን ባለመቻሉ እጅግ ተከፍተናል ፡፡

* እጅግ ያዘንበትና እሳቸዉን የታዘብንበት አንዱ ጉዳይ የሀገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት አንዳንዴ የወያነ ሰራዊት በሌላ ግዜ ደግሞ የኢህአዴግ ሰራዊት እያሉ በተደጋጋሚ መግለጻቸዉ ነዉ፡፡ የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት የአንድ ድርጅት ሰራዊት አድርጎ ደጋግሞ ደጋግሞ መግለጽ በአጋጣሚ ወይም በስህተት ሳይሆን እንደዚያ እንዲሆን በመፈለግ ሆን ተብሎ የተገለጸ ነዉ ያስመሰለዉ፡፡

በተረፈ ኮ/ል ተወልደ በጦርነቱ አነሳስ፤ ሂደትና ፍጻሜ ላይ የሰጧቸዉ ግሩም የሆኑ ትንታኔዎችና ያቀበሉን መረጃዎች በጦርነቱ ላይ ስለመከላከያ ሰራዊታችን አኩሪ ገድል እንዲናዉቅ በማድረጋቸዉ እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ አስቀድሜ በጠቋቆምኳቸዉ እንከኖች ምክንያት የኮ/ል ተወልደን ጥረት አሳንሶ እንደማየት እንዳይቆጠርብኝ ላስገነዝብ እወዳለሁ፡፡  ይህን ጉዳይ እዚህ ላይ ላብቃና አስቀድሜ ወደ ጀመርኩት የጦርነቱ ድንገተኝነት ላምራ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ወረራዉ ፈጽሞ ያልጠበቀዉና ያልገመተዉ ስለነበር ስለወረራዉ ሲሰማ መደንገጡና ግራ መጋባቱ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ ህዝቡ መንግስት ከኤርትራ ጋር የፈጠረዉ ያልተለመደና ያልተመጣጠነ ግኑኝነት ባያስደስተዉም ግኑኝነታቸዉ ተበላሽቶ ሁለቱ አገሮች ወደ ጦርነት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ግምት በጭራሽ አልነበረዉም፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ስለጦርነቱ ሲሰማ መገረሙና መደናገጡ ተገቢ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ይልቁንም የመከላከያና የደህንነቱ አካላትና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ ተሸለዉ መገኘት ሲገባቸዉ ህዝቡ ግራ ሲጋባ አብረዉ ግራ መጋባታቸዉ በፍጹም የማይጠበቅና መሆን የሌለበትም ነዉ፡፡ ምክንያቱም የዘወትር ስራቸዉና ሃላፊነታቸዉ ስለሆነ ነዉ፡፡ ይህ ሆኖ እያለ መንግስት “ወረራዉ ያልጠበኩትና ድንገተኛ ነዉ” እያለ በተደጋጋሚ መግለጫ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ጥያቄ የሚነሳዉም እዚህ ላይ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ወረራዉ ድንገተኛና ያልተጠበቀ ነዉ ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነዉ? ለመሆኑ እንደዚያ ማለትስ ነበረበት እንዴ? ኢህአዴግ የሀገር ሉአላዊነትንና የህዝቡን ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት እንዳለበት መረዳት የነበረበት ገና ድሮ በግንቦት 20/1983 ዓ/ም አራት ኪሎ የምኒሊክ ቤተ-መንግስት የገባ ዕለት መሆን አልነበረበትም እንዴ? ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ለመግዛት ሲያስብ ሃላፊነቱን እንዴት ነበር የተረዳዉ?

ለዚህ ዓይነት ከፍተኛ ሃላፊነት ያለበት መከላከያ ኃይሉም ከኤርትራም ሆነ ከሌላ ከማንኛዉም ወገን ሊሰነዘር ለሚችል ጥቃትም ሆነ ትንኮሳ አስቀድሞ መዘጋጀት ሲገባዉ “አልተዘጋጀሁም፤ አልጠረጠርኩም” ማለትስ ምን አመጣዉ? መንግስት ድንገተኛ ነዉ ሲል “ኤርትራን ጨምሮ ከየትኛዉም ወገን ሊሰነዘር ለሚችል ትንኮሳም ሆነ ጥቃት አስቀድሜ አልተዘጋጀሁም ነበር“ እያለን ነዉ? ወይንም “በወቅቱ ሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የሚባል ተቋም ጭራሽ አልነበራትም ነበር“ ማለትስ ነዉ? አንድ መንግስት የዜጎቹን ደህንነትና የሀገሪቱን ሉአላዊነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሃላፊነት ያለበት ከመሆኑ አንጻር “ኤርትራ ትወረኛለች ብዬ አላስብኩም ነበር” ማለቱስ ተቀባይነቱ ምን ያህል ነዉ?

መንግስት ወረራ መኖሩን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ዝም ብሎ ወደ ዉጊያ ከመግባት ይልቅ “ያልጠበኩትና ድንገተኛ” እያለ ያን ያህል ተጨንቆ እየደጋገመ መናገሩ ፋይዳዉ ምንድነዉ? የሚለዉ ጥያቄ መልስ የሚሻ ነዉ፡፡ በዚህ ላይ የእኔን ግምት ባጭሩ ለማስቀመጥ ልሞክር፡፡

የመንግስት ይህንን ነገር አለቅጥ የመደጋገሙ ምክንያት ጠላት ወረራ ያደርጋል ብሎ አስቀድሞ ተገቢዉን ጥንቃቄና ዝግጅት ሳይደረግ ወደ ጦርነት በድንገት በመግባትና አስቀድሞ አዉቆና ተዘጋጅቶ ወደ ጦርነት በመግባት መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ስለሚረዳ ይመስለኛል፡፡

ጉዳዩ በጦርነቱ የማሸነፍ ወይም የመሸነፍ ነገር አይደለም፡፡ አስቀድመን ሳንዘጋጅ ድንገተኛ ወረራ ተደርጎብንም ልናሸንፍ እንችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ሳይዘጋጁ በድንገት ወደ ጦርነት ተገብቶ በሚመጣ ድልና በደንብ ተዘጋጅቶና ታስቦበት ወደ ጦርነት በመግባት በሚመጣ ድል መካከል ሰፊ ልዩነት ይኖራል፡፡ ከሁሉም በላይ ተጠቀሽ የሚሆነዉ ታስቦበት የተገባ ጦርነት ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራዉ አነስተኛ የመሆን አድሉ ከፍተኛ መሆኑ ነዉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ለአብነት እንዲሆኑን የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦችን  እንመልከት፡-

አንደኛ፡- የጠላትን ሁኔታና ፍላጎት አስቀድሞ መረዳት ከተቻለ ወደ ጦርነት መግቢያ እድሎችን ሁሉ ለመዝጋት ሰፊ እድል ይኖራል፡፡ ያለምንም የህይወትም ሆነ የማቴሪያል ኪሳራ በድርድር በመፍታት ጦርነትን ማስቀረትም ይቻላል፡፡ በተጨማሪ የጠላት የጦርነት ፍላጎትን ለማምከንና “ጦርነት ስለማያዋጣኝ ይቅርብኝ” እንዲል ዲተር (deter) የማድረግ ሌላ እድልም ይኖራል፡፡

ሁለተኛ:- አስቀድሞ ባልተገመተ ወቅትና በጠላትነት ካልተፈረጀ ወገን በድንገት የሚሰነዘርን ጥቃት መክቶ ወደ ድል ለመምጣት የሚከፈለዉ ኪሳራ እጅግ የበዛ ይሆናል፡፡ በመንግስት ቸልተኝነት ምክንያት ተገቢዉ ጥንቃቄ ባለመደረጉ ለደረሰዉ ጉዳት ሁሉ ተጠያቂ ከመሆን አድንም፡፡

ሶስተኛ:- ጦርነቱ በኛ ፍላጎት የተከናወነ ባለመሆኑ የማታ የማታ ድል ማድረግ ብንችል እንኳን ከጦርነቱ ይዘን የምንወጣዉ ወይም እንደ ጦርነት ግብ የምናስቀምጠዉ በጣም በትንሹ ይሆናል፡፡

አራተኛ፡- አስቀድሞ ባልተዘጋጀንበት ጦርነት አነስተኛ ኃይል ያለዉ ጠላትም ቢሆን ስትራቴጂያዊ ድንገተኝነት ማትረፍ ስለሚያስችለዉ በጦርነቱ የማሸነፍ እድላችንን በጣም አጠራጣሪ ያደርገዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሀገሪቱን ሉአላዊነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ኃላፊነት ያለበት መንግስት ይሄን ሃላፊነቱን መወጣት ካልቻለ በህዝብ ተጠያቂነት መኖሩ የግድ ነዉ፡፡ በዚህ ድርጊቱም መንግስት ሃላፊነት የማይሰማዉ መንግስት ተደርጎ ስለሚቆጠር የህዝብ አመኔታ ማጣት ሊያስከትል ይችላል፡፡

እንግዲህ በነዚህና በሌሎችም እዚህ ባልተጠቀሱ ምክንያቶች ሊሆን ይችላል መንግስት ከጦርነቱ በፊት፤ በጦርነቱ መካከልም ሆነ ጦርነቱ ካበቃ ከብዙ ዓመታት በኋላም ይሄንኑ ነገር እየደጋገመ መግለጹ፡፡ ለማንኛዉም ይሄ የኔ ግምት ስለሆነ ወደ ጀመርነዉ ጉዳይ እናምራ፡፡

መንግስታችን “የኤርትራ ወረራ ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነበር” ሲል ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም “ከኤርትራም ሆነ ከሌላ ከዬትኛዉም ወገን ሊሰነዘርብን ለሚችል ጦርነት አስበንበትም ተዘጋጅተንበትም አናዉቅም፡፡ እንዲያዉም ለጦርነት ተብሎ የተዘጋጀ ሰራዊትም አልነበረንም” የሚል ሳይሆን ከኤርትራ ጋር ጦር ሊያማዝዝ የሚችል አንዳችም ዓይነት ቅራኔ፤ አለመግባባትና የጠላትነት ስሜት ስላልነበረ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል ብሎ ለማሰብ የሚያበቃ አሳማኝ ምክንያት የለም የሚል ነዉ፡፡

በርግጥ አንዳችም የረባ ምክንያት ከሌለ ከባዶ መሬት ተነስቶ ወዳጅን እንደጠላት ማዬት የሚደገፍም አይደለም፡፡ ጥያቄዉ ግን ከኤርትራ ጋር አንዳችም አለመግባባትና ቅራኔ ወይም ዉዝግብ አልነበረም ወይ? የሚለዉ ነዉ፡፡

1.2/መንግስትየሻእቢያወረራድንገተኛነዉሲለንለዬትኛዉምጦርነትአልተዘጋጀሁምነበርእያለንይሆንእንዴ?

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርብ ጊዜ የሚታሰብ ጠላት ኖረ አልኖረ መከላከያ ሰራዊቱን በቋሚነት የማደራጀት፤ የማስታጠቅ፤ የማሰልጠን፤ በዘመናዊ የዉጊያ አስተሳሰብ የማነጽና የዝግጁነት ደረጃዉን የሚያሳድጉ አስፈላጊ እርምጃዎችን ሁሉ የመዉሰድ ሃላፊነት እንዳለበት ግልጽ ነዉ፡፡

ከዚህ አኳያ ሲታይ በቅርብ ጊዜ የሚጠበቅ ምናልባታዊ ጠላት ወይም ስጋት ላይ ያተኮረ ባይሆንም ወደፊት ሀገሪቱ ሊገጥማት ከሚችል ስትራቴጂያዊ ስጋት አንጻር በሚገባ ታስቦበት በተጠናናና ዘለቀታዊ አቅም በሚፈጥር መልኩ የሠራዊት ግንባታ እየተሰራ እንደነበር በሚገባ የሚታወቅ ነዉ፡፡

ከጦርነቱ በፊት በርከት ያለ የዉጭ ምንዛሪ አዉጥተን አዳዲስ መድፎች፤ አይሮፕላኖች፤ታንኮች፤ ሚሳይሎች ወዘተ አልገዛንም ይሆናል፡፡ የሀገሪቱ አቅም መሸከም ከሚፈቅደዉና ሀገራችንም በተጨባጭ ከሚያስፈልጋት በላይ ግዙፍ ሰራዊት መልምለንና አስልጥነን አላስመረቅን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማይጎዳና የአካባቢያችን የወደፊቱን ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአንጻራዊነት አነስ ያለ ግን ደግሞ ብቃት የለዉ መከላከያ ተቋም ለመመስረት ጥረቶች እየተደረጉ እንደነበሩ መካድ አይቻልም፡፡

ምናልባት ጥረቱ በቂ አልነበረም ወይንም ደግሞ  አዝጋሚ ነበር ከተባለ በዚህ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱን ያለ መከላከያ ባዶዋን በማስቀረት ለአደጋ አጋልጧት ነበር የሚለዉ የአንዳንድ ወገኖች ትችት ግን ሚዛናዊነት የጎደለዉ ይመስለኛል፡፡

የአፌዲሪ መንግስት ደርግ ከወደቀ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን በሀገር ግንባታ ወይም በልማት ላይ ማድረጉ በሁላችንም ዘንድ የሚታወቅና ተገቢም ይመስለኛል፡፡ ደርግ ከወደቀ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመንግስት ይጠብቅ የነበረዉ ሌላ ጦርነት፤ ሌላ ግጭት፡ ሌላ የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ስላልነበረ የሀገሪቱን ሀብት ለግዙፍ ሰራዊት ግንባታ ማዋልን ህዝብ የሚፈልገዉ ጉዳይም አልነበረም፡፡ በመሆኑም መንግስት የጦርነትን አጀንዳ ዘግቶ ሙሉ ትኩረቱን በልማት ላይ ማድረጉ የህዝብንና የሀገሪቱን ፍላጎት የተከተለና ወቅታዊ የሆነ ተገቢ እርምጃ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

መንግስት የእኛን ብሄራዊ ጥቅም የሚነካ አስከሌለና እኛም የሌሎችን ጥቅም አስካልጎዳን ድረስ ያለ ምክንያት ከመሬት ተነስቶ ጦር የሚሰብቅ ሀገር ስለማይኖር የግድ የሚያስፈልገንን ያህል መከላከያ ኃይል እየገነባን ከድህነት ለመዉጣት መጣር አለብን እንጂ ኢኮኖሚዉን የሚበላ ለአካባቢዉ አገሮችም የስጋት ምንጭ ሊሆን የሚችል አለቅጥ የገዘፈ ሰራዊት አያስፈልገኝም ማለቱ የሚያስመሰግንና ተገቢም ይመስለኛል፡፡

በዚህ መሰረትም ከጦርነቱ በፊት ለጠንካራ መከላከያ ሰራዊት ምስረታ መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ የአቅም ግንበታ ስራዎች ሲሰሩ ነበር፡፡ ጥራት ያላቸዉ የስልጠና ስራዎችና የማሰልጠኛ ተቋማትን የማደራጀት ስራ፤ የግድ አስፈላጊ የነበሩ ኢንፍራስትራክቸር ግንባታ ፕሮጀክቶች፤ ከዉጭ ተጽእኖ ሊያላቅቅ የሚችሉ በደርግ ጊዜ ተጀምረዉ የነበሩ የጦር መሳሪያ እድሳትና ማምረቻ ተቋማትና የመከላከያ ኢንዱስትሪዎችን በአዲስ መልክ የማደራጀት፤ የማጠናከርና በጥናት ላይ የተመሰረተ ማስተካከያ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነበር፡፡

የጥናት፤ የምርምርና ስርጸት ስራዎችም ከሞላ ጎደል ለመስራት ተሞክሯል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የአንድ መከላከያ ሰራዊት ብቃት የሚለካዉ በብዛቱና በትጥቁ ዓይነት ብቻ ሳይሆን ይልቁንም በህዝባዊ አመለካከቱና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በእምነት ተቀብሎ እሰከመጨረሻዉ መስዋእትነት ለመክፈል ባለዉ ቁርጠኝነት ጭምርም በመሆኑ ይህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሰፊ የግንባታ ስራዎች ሲሰሩ ነበር፡፡

በተለይም ለህዝብ ከበሬታ ያለዉ፤ ለህገ-መንግስቱ በቁርጠኝነት የሚቆምና ድስፕሊንድ የሆነ ሰራዊት ለመመመስረት መንግስት ብዙ ተንቀሳቅሷል፡፡ አብዛኛዉ የመከላከያ ሰራዊት አባል የቀድሞ የኢህአዴግ ታጋይ የነበረና የመደበኛ ሰራዊት ቁመናና አሰራር ተሞክሮ ያልነበረዉ መሆኑ ሲታሰብ የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት በአዲስ መልክ ለማደራጀት ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች አበረታች ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡

እነዚህን ስራዎች ከጦርነቱ በኋላ በተጠናከረ መልኩ የመቀጠል ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ጥረቱ የተጀመረዉ ግን ከጦርነቱ  በፊት በተለይም ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ ነበር፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ በህገ-መንግስቱ መሰረት በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ ደግሞ ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ሲሰራ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱን ያለ ጠባቂ አስቀርቶ፣ ሰራዊቱን በትኖ፣ ራሳችንን የመከላከል አቅማችንን አዳክሞና ለጥቃት ተጋላጭ አድርጎን ወዘተ የሚባሉ ክሶችና ትችቶች በተጨባጭ እየተሰራ ከነበረዉ ጋር የሚስማማ አይደለም፡፡ ቢያንስ ሲሰራ የነበረዉን ስራዎች በቅርበት ለሚያዉቁ ሰዎች ይህንን ትችት ለመቀበል ያዳግታል፡፡

ከጦርነቱ በፊት እኮ ቢያንስ ከ50 እሰከ 60 ሺህ አካባቢ የሚሆን የሰራዊት ኃይል ነበረን፡፡ ይህ ኃይል በወቅቱ ሻዕቢያ ለጦርነት ካዘጋጀዉ ሩብ ሚሊዮን (250ሺህ) አካባቢ ከሚገመት ሰራዊት አንጻር ሲታይ በቂ እንዳልነበረ ግልጽ ነዉ፡፡ ጦርነቱን በድል ለመወጣት በዚህ ኃይል ብቻ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻልም ማንም ሊገነዘብ የሚችለዉ ሃቅ ነዉ፡፡ ነገር ግን ጦርነት በሌለበትና ሰላም በሰፈነበት ሁኔታ ዉስጥ እንደ ኢትዮጵያ ላለች ደሃ አገር 60ሺህ ሰራዊት ትንሽ ነዉ የሚባል አይደለም፡፡

ለነገሩ የኤርትራን የመጀመሪያ ወረራ ጥቃት መክቶ በማቆም የሻዕቢያን የመስፋፋት ህልም ያጨናገፈዉ ይሄዉ ሰራዊት እንደነበር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ሻዕቢያ ለሰባት ዓመታት የተዘጋጀበትን ጦርነት በተለይ የሰኔ 3/1990 የሻዕቢያን ማጥቃት ሰራዊታችን ሶስት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ በማክሸፍ ኢሳይያስን ተስፋ በማስቆረጥ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በመክፈታቸዉ አደገኛ ስህተት እንደፈጸሙ እንዲረዱ ያደረጋቸዉ ይሄዉ አነስተኛ ኃይል በጀግንነት የፈጸመዉ እንጂ በተአምር የሆነ አልነበረም፡፡

Photo - An Eritrean tank destroyed in a battle with Ethiopian troops around Barentu town on May 20, 2000 [Getty Images/AFP]

Photo – An Eritrean tank destroyed in a battle with Ethiopian troops around Barentu town on May 20, 2000 [Getty Images/AFP]

2/ከኤርትራበተሻለኢኮኖሚላይመገኘታችንለጦርነቱትልቅእገዛአድርጓል

ጦርነትን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ሁሉ ለሟሟላት የጠንካራ ኢኮኖሚ መኖር የግድ ነዉ፡፡ በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ መንግስት ገና ከጅምሩ በኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ መቆዬቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ የልማት ስራ በኋላ ተገደን የገባንበት ጦርነትን በአሸናፊነት እንድንወጣ ትልቅ እገዛ እንዳደረገልን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም፡፡

ከጦርነቱ በፊት በነበረችዉ አጭር የሰላም ጊዜ ዉስጥ ሲሰሩ የነበሩ  የልማት እንቅስቃሴዎች ጦርነቱን ለመቋቋም ትልቅ እገዛ አድርጎልናል፡፡ ሻዕቢያ ለሰባት ዓመታት በድብቅ ሲዘጋጅ ለቆየበት ጦርነት እኛ በአጭር ጊዜ ዝግጅት በልጠን የተገኘንበት አንዱ ምስጢር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከኤርትራ ሲነጻጸር የተሻለ እንዲሆን ማድረግ በመቻላችን ነዉ፡፡

ጦርነቱ የማይቀር መሆኑ ከታመነበት በኋላ ያን ሁሉ ሰራዊት መልምለን፤ አሰልጥነን ያዘጋጀነዉ፤ ለጦርነቱ የሚያስፈልገንን ታንክ፤ መድፍ ፤ መገናኛ መሳሪያዎች፤ ጄት አይሮፕላኖች፤ ራዳሮች፤ ሚሳይሎች ፤ተሸከርካሪዎችና ተተኳሾች ወዘተ ሁሉ እንዳሻን መሸመት የቻልነዉ ገና በሰላሙ ጊዜ ከኤርትራ የተሻለ የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ማድረግ በመቻላችን ነዉ፡፡ እነሱ ከጦርነቱ በፊትም ሆነ በጦርነቱ መካከል መግዛት ከቻሉት በጥራትም በብዛትም የተሻለ ትጥቅ ገዝተን መታጠቅ ችለናል፡፡

ከኤርትራ ጋር ሲነጻጸር የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም (ኢኮኖሚክ ፖቴንሻል) ባይኖረን ኖሮ ጦርነቱን ማሸነፍ መቻላችንን አጠራጣሪ ሊያደርገዉ  ይችል ነበር፡፡ ጦርነቱ በልማት ጥረታችን ላይ ትልቅ እንቅፋት መሆን መቻሉ እርግጥ ነዉ፡፡ ለጦርነቱ ሲባልም በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት የዉጭ ምንዛሪ ማዉጣታችንና የሀገራችን የመከላከያ ባጄት ከጂ.ዲ.ፒ. (GDP) 11 % በላይ መድረሱ ጦርነቱ ለልማታችን ምን ያህል እንቅፋት እንደነበር ያሳያል፡፡

እንደዚያም ሆኖ በጦርነቱ መካከልም በተቻለ መጠን ልማቱን ለማፋጠን መንግስት ጥረት ማድረጉን ለአፍታም አላቋረጠም ነበር፡፡ ጦርነቱ በእኛ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ ኢኮኖሚያችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ማንሰራራት የቻለበት ምክንያትም አስቀድመን ለልማት ስናደርግ የነበረዉ ትኩረት ዉጤት ይመስለኛል፡፡ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ባይጠናቀቅ ኖሮ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በተሻለ  ሁኔታ ዘለግ ላለ ጊዜ በጦርነቱ ዉስጥ ለመቆዬት የሚያስችላት እድል ነበራት፡፡

በአንጻሩ ኤርትራ የነበራትን ዉስን የሆነ ጥሪትም ለጦርነቱ አዉላ ስለነበረና ጦርነቱ ካበቃ በኋላም መጀመሪያኑ ትኩረት አድርጋ ያልሰራችዉ ኢኮኖሚ ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ ጭራሽ ተንኮታክቶ ህዝባቸዉን ለዳቦ ሰልፍ ዳርገዉታል፡፡  አስከዛሬም ከዚህ ችግር ሊላቀቁ አልቻሉም፡፡

በእኛ በኩል ከጦርነቱ በፊት በልማት መጠመዳችን በጦርነቱ ወቅት በጦርነቱ ቀጠና ከነበረዉ ዉጭ ያለዉ ህዝባችን በጦርነት ላይ ባለች አገር መከሰቱ የግድ የሆነዉን የከፋ የኑሮ መመሰቃቀል ችግር ብዙም ሳይገጥመንና ህዝባችንን ለስቃይ ሳይዳርግ ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ችለናል፡፡

በጦርነቱ ወቅት ወደ መሃል አገርና ወደ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ወዘተ ተዘዋዉሮ የተመለከተ የዉጭ አገር ጎብኚ ሀገሪቱ ጦርነት ላይ የነበረች መሆኑን የሚያሳብቅ አንድም የጦርነት ዘመን ሁኔታዎችን ለማዬት ስለሚቸገር “በእዉነት ሀገሪቱ ጦርነት ላይ ነች?” ብሎ ቢጠራጠር በጭራሽ አይደንቅም፡፡ መንግስት እንደ ደርግ ዘመን መላዋን ኢትዮጵያን ወደ ጦር ካምፕነት ሳይቀይርና ብዙ ትርምስ ሳይፈጠር ጦርነቱን አካሂዶ ማጠናቀቅ መቻሉ የሚያስመሰግነዉ ነዉ፡፡

የወቅቱ የሀገራችን የመንግስት አመራሮች እጅግ አሰልቺና የተራዘመ ጦርነት (ለ17 ዓመታት የዘለቀዉ ፀረ -ደርግ ትግል) በኋላ ገና ሰላምን ማጣጣም የጀመሩበትና የታገሉለትን የልማት ጥያቄን እዉን ለማድረግ ከፍተኛ ጉጉት ስላደርባቸዉ ከልማት ዉጭ ያሉ ሌሎች ጉዳዮች ላይ በቂ ትኩረት እንዳያደርጉ ተጽእኖ ሳያደርግባቸዉ እንዳልቀረ መገመት ይቻላል፡፡

በተለይ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ ሲገልጹ እንዳዳመጥነዉ “የግድ ካልሆነና ልማታችንና ሰላማችንን የሚያስቆም መሆኑን እርግጠኛ ሳንሆን የትኛዉም ዓይነት ጦርነት ዉስጥ ተቻኩለን አንገባም„ የሚለዉ ጠንካራ አቋማቸዉና “የኛ ዋነኛ ጠላት ድህነት ነዉ“የሚለዉ ቋሚ መፈክራቸዉ ምን ያህል ለልማት ቅድሚያ እንደሰጡና ለጦርነት ያላቸዉን የመረረ ጥላቻ  የሚያመላክት ነዉ፡፡ እንግዲህ ምናልባት መንግስት በልማት አጀንዳ ተዉጦ አካባቢዉን በደንብ እንዳይፈትሽ ተጽእኖ አድርጎበት ይሆን እንዴ? ብለን ብንጠራጠር ተገቢ ይመስለኛል፡፡

3/አጠቃላይመዘናጋታችንእንዳለሆኖወደጦርነቱ ስንገባበርካታየዝግጅትጉድለትነበረብን

ተገቢዉን ትኩረት ተሰጥቶት ያልተሰሩና በክፍተት ሊታዩ የሚችሉ አንዳንድ ጉድለቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ለመረዳት አያዳግትም፡፡ ለምሳሌ የሀገሪቱን መከላከያ ኃይል በስትራቴጂክ ደረጃ ለሚታሰብ ምናልባታዊ ጠላት ታሳቢ ባደረገ መልኩ የአቅም ግንባታ ከመስራት ጎን ለጎን በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ሊነሳ ለሚችል ጠላት (ተለይቶ የሚታወቅ ጠላት ባይኖርም) ፈጣን መልስ ሰጪ የሆነ ኃይል ዝግጅት ማድረግ ይገባ ነበር የሚለዉ አንዱ ነዉ፡፡

እንደዚሁም የመከላከያ ሰራዊቱ በፊት ይዞትና ለምዶት ከቆዬዉ የጉሬላ የዉጊያ አስተሳሰብ አዉጥቶ በዘመናዊ ወታደራዊ ዶክትሪን የሚመራ አዲስ የዉጊያ አስተሳሰብ ያለዉ ሰራዊት የመገንባት ስራ በጥልቀት አለመሰራቱ ሌላዉ ተጠቃሽ ክፍተት ነዉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ኮ/ል ተወልደ ገ/ትንሳይ አስቀድሜ በጠቀስኩት “ባድመ እንደ ምክንያት” በሚል ርአስ ስለ ጦርነቱ ጽፈዉ ለንባብ ባበቁት መጽሀፍ ላይ ከወረራዉ በፊት በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የነበረዉ አንዱ ትልቁ ችግር ይሄ እንደ ነበር አጽንኦት ሰጥተዉ ገልጸዋል፡፡

ኮ/ል ተወልዴ በማስረጃነት የጠቀሱት የአሁኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥና በወቅቱ የግንባሩ አዛዥ የነበሩትንና የሻቢያን እብሪት ወረራ በማክሸፍ ለሀገር ባለዉለታ የሆኑት ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በአንድ ወቅት በጦርነቱ ቀጣይ አካሄድ ላይ የተናገሩትን ንግግር ነዉ፡፡

በወገንናበጠላትመካከልከፍተኛየኃይልናየአስተሳሰብልዩነትአለ፡፡ ጠላትከመደበኛዉጊያአስተሳሰብፍጹምአልተላቀቀም፡፡ ይህንንአስተሳሰብበማጎልበትላይነዉየነበረዉ፡፡ በኛበኩልከመደበኛዉጊያአስተሳሰብወጥተንበጉሬላአስተሳሰብላይነዉየቆዬነው፡፡ ይህንንአስተሳሰብለመቀየርጊዜያስፈልገናል፡፡”  ብለዉነበር፡፡ 

በመቀጠልም የኛ መከላከያ ሰራዊት በሰዉ ኃይል ብዛት የተበለጠ መሆኑን የጠቀሱበት ንግግራቸዉ ላይ እንዲህ ብለዉ ነበር፡፡

አሁንያለንየኃይልልዩነትምእጅግበጣምየተራራቀነዉ፡፡ ከቻልንምመከላከልብቻነዉየምንችለዉ፡፡ ስለሆነምአሁንራሳችንንእየተከላከልንእንዘጋጅእንጂአሁንወደዉጊያእንግባየሚለዉአስተሳሰብከጥቅሙጉዳቱያመዝናልነበር ያሉት፡፡ 

ይህ በዘመናዊ ዉጊያ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ዝግጅት ያለማድረጉ ችግር ለምድር ኃይሉ ብቻ ሳይሆን በአየር ኃይላችንም ላይ የታዬ ትልቅ ጉድለት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ እንደሚታወቀዉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከጠላት አየር ኃይል ጋር ወደ ጦርነት የገባበት አጋጣሚ በታሪኩ ዉስጥ ሁለት ጊዜ ብቻ ይመስኛል፡፡ አንደኛዉ የዛሬ 40 ዓመት በፊት ማለትም በ1969 ዓ/ም ከሶማሊያ ወራር ጦር ጋር በተለይ ከሶማሊያ አየር ኃይል ጋር የተደረገዉ ጦርነት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አሁን አያወሳን ባለነዉ ጦርነት ማለትም ከኤርትራ አየር ኃይል ጋር ነዉ፡፡

አየር ኃይላችን ከ1969ኙ የሶማሊያ ጦርነት በኋላ ከመደበኛ አየር ኃይል ጋር ድጋሚ ለመፋለም የበቃዉ በዚህ የኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነት ላይ ነዉ፡፡ ከዚያ በፊት በመካከሉ በነበሩት ሃያ አመታት ዉስጥ አየር ኃይሉ ሲያደርገዉ የነበረዉ መደበኛ ያልሆነ ዉጊያ ማለትም ፀረ- ጉሬላ ዉጊያ ብቻ ነበር፡፡ በወቅቱ ሻዕቢያም ሆነ የህወኃት/ኢህአደግ ሰራዊት የጉሬላ ሰራዊት የነበሩና አይሮፕላን ለመታጠቅ እድል ያልነበራቸዉ በመሆናቸዉ አየር ኃይሉ የዉጊያ ባህሪይም ይህንኑ የተከተለ መሆኑ የግድ ነበር፡፡

አየር ኃይሉ ሙሉ ትኩረቱ በመሬት ላይ ባለዉ የጠላት ጦር ማጥቃት ላይ በማድረግ የአየር ለአየር (air to air) የሚባል ዉጊያ ስላልገጠመዉ አስተሳሰቡ ሁሉ ፀረ- ምድር ዉጊያ (counter land warfare) ብቻ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ጊዜያት ወቅት አየር ኃይሉ ሲገጠመዉ የነበረዉ ከፍተኛ ተግዳሮት ቢኖር ምድር ላይ ከተተከሉ የጠላት ፀረ-አይሮፕላን መቃወሚያ መሳሪያዎች (anti aircraft) ሲደርስበት የነበረዉ ጫና ነዉ፡፡

የኢህአዴግና የሻዕቢያ ሰራዊት ከደርግ አይሮፕላን ጥቃት ራሳቸዉን ለመጠበቅ እንቅስቃሴያቸዉን በገደብ ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆኑም በኋላ ግን የአየር መቃወሚያ መሳሪያዎችን በስፋት መታጠቅ በመቻላቸዉ የአየር ኃይሉን አይሮፕላኖች ጭራሽ አላስደርስ ያሉበትን ሁኔታን መፍጠር ችለዉ ነበር፡፡  በዚያ የርስበርስ ጦርነት ወቅት በሻዕቢያም ሆነ በኢህአደግ አየር መቃወሚያ መሳሪያዎች ተመትተዉ የወደቁ አየር ኃይል አይሮፕላኖች በርካታ ነበሩ፡፡

አየር ኃይላችን ሰፊ የጦርነት ተሞክሮ የነበረዉና በተለይ ከሶማሊያ ጋር ባደረግነዉ ጦርነት በጥቂት ቀናት ዉስጥ ብቻ ከደርዘን በላይ የሶማሊያን አይሮፕላኖች በአየር-ለአየር ዉጊያ  መትቶ በመጣል አስደናቂ ገድሎችን በመፈጸሙ በምእራቡም ሆነ በምስራቁ ዓለም አድናቆትን አትርፎ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ስንት ጀግና ፓይለቶችን ያፈራና ስንት ጦርነቶች ላይ የተሳተፈ አየር ኃይል ለምን የራሱ ኤር ዶክትሪን (air doctrine) እንዳልኖረዉ በጭራሽ ለመረዳት አልቻልኩም፡፡

ከኤርትራ ጦርነት በፊት አየር ኃይሉ ከሶማሊያ ጦርነት በኋላ ባሉት ጊዜያት (ለሃያ ዓመታት) ከሌላ አየር ኃይል ጋር ጦርነት ገጥሞ ስለማያዉቅና የዉጊያ አስተሳሰቡ ሁሉ በአንድ የዉጊያ አቅጣጫ ላይ ብቻ እንዲወሰን በመደረጉ ከዘመናዊ የአየር ኃይል ዶክትሪን ጋር አለመተዋወቁም ሆነ ትኩረት አድርጎ አለመሰራቱ በዚያ ምክንያት ይሆናል የሚል ግምት አለ፡፡

የኤርትራ ጦርነት ሲጀመር ከአርሚዉ ባልተለየ ሁኔታ አየር ኃይሉም የዘመናዊ ዉጊያ አስተሳሰብ ደሃ መሆኑ አስገራሚ ነበር፡፡ አየር ኃይሉ ከተመሰረተ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረና በርካታ ልምድ ያካበተ፤ ስመጥር የሆኑ  ጀግና ፓይሌቶችና አዛዦች የነበሩት  ቢሆንም  ይሄ ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል የዉጊያ ዶክትሪንና አሰተሳሰብ ሳይኖረዉ ቆይቷል፡፡

በወቅቱ አየር ኃይሉ በዘመናዊ የዉጊያ አስተሳሰብ ረገድ ከአርሚዉ ተሸሎ ሊገኝ አልቻለም፡፡ እንዲያዉም የአርሚዉ አብዛኛዎቹ ተዋጊዎችና አመራሮች የቀድሞ ታጋዮቸች የነበሩ በትግሉ የመጨረሻዎቹ  አመታት ላይ መደበኛ ካልሆነ የዉጊያ (Unconventional Warfare) አስተሳሰብ ተላቀዉ ከመደበኛ ዉጊያ አስተሳሰብ ጋር ከሞላ ጎደል ትዉዉቅ የነበራቸዉ ነበሩ፡፡

ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ታጋይ ሰራዊት ወደ መንግስት መከላከያ ሰራዊትነት ከተቀየረ በኋላ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ትቶት ነዉ እንጂ በትግሉ መጨረሻ አካባቢ ራሱን ወደ መደበኛ ሰራዊት እየቀየረ  እንደነበር ይታወቃል፡፡ በትግሉ መጨረሻ አካባቢ የኢህአዴግ ወታደራዊ ቁመና ምናልባት አይሮፕላን ስላነበረዉ ካልሆነ በስተቀር አቋሙ የአንድ አገር መንግስት ከሚኖረዉ የመከላከያ ተቋም የሚያንስ አልነበረም፡፡

የኤርትራ ጦርነት እንደተጀመረ የዘመናዊ ትጥቅ ባለቤት ለነበረዉና ከተመሰረተ በርካታ አመታትን ላስቆጠረዉ አየር ኃይል ግን የራሱ ዶክትሪን ሰነድ ፈልጎ ማግኘትም አልተቻለም ነበር፡፡ አየር ኃይሉን ለጦርነት በማዘጋጀት ላይ ለነበሩት የወቅቱ አዛዥ ለጄ/ል አበበ (ጆቤ) ሁኔታዉ ቢያስገርማቸዉም የአሜሪካን ዶክትሪን ከኢንተርኔትና ከሌሎች መረጃዎች እያፈላለጉና መሰረታዊ በሆነዉ የአየር ኃይል ዶክትሪን (basic air doctrine) ላይ ይበልጥ ትኩረት በማድረግ በማስተርጎምና ከኛ ሁኔታ ጋር እያዛመዱ የሚመለከታቸዉ አመራሮች እንዲወያዩበት ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡

እንግዲህ በወቅቱ ከነበረዉ የጊዜ እጥረትና ከጉዳዩ ዉስብስብነት አንጻር ሲታይ አስተሳሰቡ በሚገባ በተፈለገዉ ደረጃ ተጨብጦ ነበር ለማለት ቢያስቸግርም ጥረት መደረጉ ግን በመልካም ጎኑ መጠቀስ ያለበት ነዉ፡፡ ስለዶክትሪን ስለተነሳ እግረ መንገዴን እዚያ ላይ አተኮርኩ እንጂ ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት ስንገባ አየር ኃይሉ በርካታ እጥረቶች እንደነበሩበት ለማንም ያልተሰወረና ግልጽ ነዉ፡፡

ነገር ግን በጦርነቱ ሂደት ራሱን እያስተካካለ የተሻለ ብቃት ለመያዝ ቻለ እንጂ እንደ አጀማመሩና እንደነበረበት ሁኔታ ቢሆን ኖሮ በተለይም ከደካማና ልምድ ከሌለዉ የኤርትራ አየር ኃይል ጋር መሆኑ በጀዉ እንጂ ከጠንካራ  አየር ኃይል ጋር ሆኖ ቢሆን ኖሮ ብዙ ችግር ሊገጥመን ይችል ነበር፡፡ ለማንኛዉም ይሄን ጉዳይ ያነሳሁት ወደ ጦርነቱ ስንገባ በዝግጁነት ረገድ ጉድለት እንደነበረብን ለመጥቀስ ያህል እንጂ ስለ አየር ኃይል ሁኔታ በዝርዝር ለመተረክ አይደለም፡፡

4/ስለኤርትራየነበረንግምገማየተዛባመሆኑናኢሳይያስንከሚገባዉበላይማመናችን

ስለ ጦርነቱ ሲወሳ በተደጋጋሚ ሲገለጽ የነበረዉ ኤርትራ ኢትዮጰያ ላይ ወረራ ለመፈጸም የበቃችዉ ስለኛ በነበራት የተሳሳተ ግምገማ ምክንያት ነዉ የሚል ነዉ፡፡ በርግጥም የኤርትራ መሪዎች የግምገማ ችግር እንደነበረባቸዉ እኛ ብቻ ሳንሆን ራሳቸዉም ዘግይተዉም ቢሆን ለመረዳት የቻሉ ይመስለኛል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ኤርትራ ከሰራችዉ ያላነሰ ምናልባትም የከፋ የግምገማ ችግር የነበረብን እኛ ነን፡፡ እነሱ ራሳቸዉ በቆሰቆሱት ጦርነት ሳቢያ በደረሰባቸዉ ዉርደት ምክንያት የግምገማ ስህተት መስራታቸዉን አምነዉ ሲቀበሉ እኛ ግን አስከዛሬም የሰራነዉን ስህተት ለመቀበልም ሆነ ስለጦርነቱ ለመነጋገር ፍላጎቱ አላሳየንም፡፡

በእኛ በኩል በተሳሳተ ግምገማ ላይ ተመስርተን ለወረራ ተመቻችተን መቆየታችን ትልቅ ስህተት ነበር፡፡ እነሱ የራሳቸዉ ያልሆነን ነገር ለመንጠቅ አስበዉና  ለትርፍ ፍለጋ ብለዉ ስህተት ሰሩ፡፡ እኛ ግን የራሳችንን ላለማስነጠቅ መስራት የሚገባንን ሳንሰራ በመቆየት እነሱ ከሰሩት የበለጠ ትልቅ ስህተት ሰራን፡፡ ስለ ኤርትራ መንግስት የነበረን የተሳሳተና የተዛባ ግምገማ እኛን ለስህተት መዳረጉ ብቻ ሳይሆን እነሱ ራሳቸዉንም ተሳስተዉ እንዲወሩን አደርገናቸዋል፡፡

እንደምንጠረጥራቸዉ ቢያዉቁ ኖሮ ለጥቃት አያስቡንም ነበር፡፡ ደካማ መስለን ባንታያቸዉ ኖሮ በአስርሺዎች ለሚቆጠሩ ጅግኖቻችን መዉደቅ ምክንያት የሆነዉን ጦርነት ባላስነሱብን ነበር፡፡ እኛን የጎዳን ከነሱ ስህተት ይልቅ የኛ ስህተት ነዉ፡፡ የኤርትራ መሪዎች በተሳሳተ ግምገማ ላይ ተመስርተዉ ወረራ እንዲፈጽሙብን የእኛ የተሳሳተ ግምገማ በተዘዋዋሪ መንገድ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ከወረራዉ በፊት መንግስታችን ማንኛዉም ሃላፊነት ያለበት መንግስት እንደሚያደርገዉ የአካባቢያችንን ሁኔታ የሚቃኝ  የስጋት ትንታኔ  አላደረገም ለማለት አልችልም፡፡ ምክንያቱም የዚህ ዓይነት ስራዎች ሲሰሩና ጥናቶችም ሲደረጉ እንደነበር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አዉቃለሁ፡፡ ምናልባት ሊነሳ የሚችለዉ ጥያቄ መንግስት በስጋት ትንታኔዉ ግምገማ ኤርትራን በምን ደረጃ ነበር የፈረጀዉ የሚለዉ ነዉ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ሲደረጉ ከነበሩ አካባባዊ የሥጋት ትንታኔ ጥናቶች ኤርትራ እንደ ጠላት ቀርቶ በአጠራጣሪ ወዳጅ ደረጃ እንኳን አንድም ጊዜ አለመመደቧ የሚታወቅ ነዉ፡፡ እኔ ራሴ እንደማስታዉሰዉ ከጦርነቱ አንደ አመት ቀደም ብሎ የሀገራችንን የወደፊቱን አየር መከላከያ ሲስተም ለመዘርጋት መነሻ ጥናት እንዳቀርብ ታዝዤ በሰራሁበት ወቅት በካርታ ንድፍ ላይ የኤርትራን ኤር ቤዝ ምልክት የጠላት መለያ በሆነዉ በሰማያዊ ቀለም በማድረጌ የቅርብ አለቃዬ የነበረዉ ክፉኛ ተቆጥቶኝ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ አለቃዬ ራሱ ኤርትራን “ወዳጅ” ለማለትም ቸግሮት እንደነበረም ትዝ ይለኛል፡፡

የሀገራችን የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂና የዉጭ ግኑኝነት ፖሊሲ ከጦርነቱ በፊት ስለመዘጋጀቱ መረጃ የለኝም፡፡ ቢያንስ ይህ ጠቃሚ ሰነድ ለህዝብ በይፋ ለዉይይት የቀረበዉ ከጦርነቱ በኋላ በ1993 መጨረሻና 94 መጀመሪያ ላይ ይመስለኛል፡፡  በበኩሌ የዚያ ዓይነት ዶክመንት መኖሩንም ያወኩት በተጠቀሰዉ ወቅት  ነዉ፡፡

ይህ ሰነድ ስለኤርትራ በተገቢዉ መንገድ ትንታኔ የሰጠ ቢሆንም የዚህ ዓይነት ግምገማ ከወረራዉ በፊት የነበረ ስለመሆኑ ግን እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱም “ሳናስበዉ ፤ሳንጠረጥር፤ በድንገት ተወረርን” የሚባሉ ሰበቦችን መደርደር ባላስፈለገ ነበርና፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ከሁሉም አገሮች ጋር በሰላምና በወዳጀነት ተከባብሮ የመኖር፤ በሌላዉ አገር ሉአላዊ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ ይከተል ስለነበር እኛ የሌላዉን መብት አስካልነካን ማንም የኛን መብት ሊነካ አይነሳሳም የሚል እምነትም ስለነበረዉ የኤርትራን ጉዳይ በጥርጣሬ  ደረጃ እንኳን አለማዬቱና  አጎራባች አገሮችን በሙሉ አንዱንም ከሌላዉ ሳይለይ በጅምላ ወዳጅ አድርጎ መቁጠሩ ለዚህ ይመስለኛል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የቱንም ያህል ሰላም ወዳድ ቢሆን  የኤርትራን  መንግስት የጸብ ጫሪነት ባህሪይ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ ለተከታተለዉ ሰዉ መንግስታችን ኤርትራን ከጂቡቲ፤ ከኬንያና ከሱዳን ጋር እኩል ማዬቱን ተገቢ ነበር አይልም፡፡ የሆኖ ሆኖ የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ የነበረዉ አቋም ከጂቡቲ፤ ከኬንያ ወዘተ በተለዬ መልኩ በጥርጣሬ ዓይን ያለማዬቱ ጉዳይ የግምገማ ችግር ያመጣዉ ድክመት ካልሆነ በስተቀር መንግስት ሆን ብሎ ያደረገዉ ነገር አይመስለኝም፡፡

መንግስታችን ስለ ኤርትራ አመራሮች ክፉ ባህሪይ ገና ከትግሉ ጊዜ ጀምሮ ጠንቅቆ ያዉቅ እንደነበር ነገር ግን ኤርትራን እንደ ጠንቀኛ ጎረቤት እንዳያይ ዓይኑን የጋረዱት ሁኔታዎች በመኖራቸዉ ምክንያት ለድንገተኛ ወረራ እንደተጋለጥን ለመረዳት አይከብድም፡፡

5/ወረራዉንድንገተኛእንዲሆንአስተዋጽኦያደረጉሁኔታዎች

ከኤርትራ በኩል ለጥቃት ሊሰነዘርብን ይችላል ብሎ መንግስት እንዳያስብ ያደረጉና የወረራዉ ድንገተኛነትና ያልተጠበቀ መሆን የብዙ ሁነቶች ድምር ዉጤት ነዉ፡፡ መንግስታችንን  ለመዘናጋትም ሆነ ኤርትራን  እንዳይጠራጠር በማድረግ ጫና ያደረጉበት ሁኔታዎች ምን እንደነበሩ ግምቴን ቀጥዬ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡

5.1/በኢትዮጵያናበኤርትራመካከልየነበረዉግኑኝነትሻዕቢያንለጦርነትየሚያነሳሳገፊምክንያትሊሆንአይችልም

ከጦርነቱ በፊት በኤርትራና በኢትዮዮጵያ መንግስታት መካከል በብዙ ጉዳዮች የመተባበርና የወዳጅነት መንፈስ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ትንሽ በተለየና ጠንከር ባለ መንገድ ከኤርትራ ጋር ወዳጅነት መመስረቷ የሚጠበቅና ተገቢም ነበር፡፡

ኤርትራና ኢትዮጵያ ወቅቱ አስገድዶአቸዉ ቢለያዩም አንድ አገር የነበሩ በመሆናቸዉ ከኬንያና ከሱዳን የበለጠ ወዳጅነት በመመስረቱ መንግስትን የሚያወቅስ አይደለም፡፡ ግኑኝነቱ ወደ ኤርትራ ያደላ ይመስላልና ይስተካከል በሚል በወቅቱ ቅሬታና ጥርጣሬያቸዉን ሲገልጹ በነበሩ ወገኖችም ቢሆን ከኤርትራ ጋር እስከነአካቴዉ ወዳጅነት መመስረት የለብንም የሚል አስተያየት የተሰጠ አይመስለኝም፡፡

ኤርትራና ኢትዮጵያ በነበራቸዉ ወታደራዊ የትብብር  ስምምነት መሰረትም ችግር ሲያጋጥማቸዉ በጋራ የመተጋገዝ ሁኔታ ነበራቸዉ፡፡ ለምሳሌ የካርቱም መንግስት የእስልምና አክራሪዎችን በማሰማራት ጉዳት ለማድረስ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ሁለቱም አገሮች በጋራ ተባብረዉ አደጋዉን ለመቀነስ ሞክረዋል፡፡ ሁለቱም መንግስታት ለሱዳን ነጻ አዉጭ ድርጅት(SPLA) በቅንጅት በጋራ እገዛ ያደርጉ ነበር፡፡

በተጨማሪ ለኮንጎዉ ሎሬንት ካቢላ በ1990 ዓ/ም ለስልጣን መብቃት ሁለቱም ድርጅቶች አስተዋጽኦ አድርገዉ ነበር፡፡ ለሱዳን ተቃዋሚ ቡድኖች ስብስብ ለሆነዉ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ጥምረት (NDA) በጋራ የፖለቲካ እገዛ አድርገዋል፡፡ ሁለቱም አገሮች ከአሜሪካ ጋር በእኩል ደረጃ ወዳጅነት መስርተዉ እገዛ እያገኙ ነበሩ፡፡

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኤርትራዉያን በኢትዮጵያ ዉስጥ ከኢትጵያዉያኑ በተሻለ ሁኔታ ሃብት አፍርተዉ ይኖሩ ነበር፡፡ ለየትኛዉ ሌላ አገር ዜጋ በማይደረግ ደረጃ ለኤርትራዉያኑ በተለየ ሁኔታ ገንዘብ ከባንክ እንዳሻቸዉ እንዲበደሩ ሁኔታዉ ተመቻችቶላቸዉ በዚህም እጅግ ተጠቃሚ ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለኤርትራ ህዝብ ካደረገዉ ትብበር ጎልቶ የሚታየዉ ኤርትራ የራሷን ነጻ መንግስት ለመመስረት ለሚያስችላት ሪፌሬንደም ስትዘጋጅ የኤርትራን ህዝብ ነጻ የመሆን መብትና ፍላጎት ለማደናቀፍ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል አንዳችም ሙከራ አለመደረጉ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ እገዛና ትብብር ማድረጉ ነዉ፡፡ እንዲያዉም ገዢዉን ፓርቲ “ኢህአዴግን “አስከሚያስተቸዉ ድረስ  ለሪፌሬንደሙ መተባበሩና ከሌሎች አገሮች ቀድሞ ለኤርትራ ነጻ መንግስትነት እዉቅና መስጠቱ ኤርትራ መንግስት በኩል በቀላሉ መታዬት የነበረበት ጉዳይ አልነበረም፡፡

ምናልባት የኢትዮጵያ መንግስት ከራሷ አካል ለተገነጠለችዋ ኤርትራ እዉቅና ባይሰጥ ኖሮ የኤርትራን መገንጠል ማስቀረት ባይቻል እንኳ ነገር ግን እንደ ሉአላዊ አገር ፈጥና እዉቅና ማግኘት መቻሏ እጅግ አጠራጣሪ ይሆን ነበር፡፡ ቢያንስ ዘለግ ያለ ጊዜ ሊጠይቅ ይችል ነበር፡፡ እንደአብነትም የሶማሊ ላንድን ሁኔታን እዚህ ላይ ማስታወሱ በቂ ይመስለኛል፡፡ የኤርትራ መንግስት ግን ይሄን እንደ ትልቅ ትብብር ወይም ዉለታ የቆጠረዉ አይመስለኝም፡፡

የኢህአዴግ መንግስት ገና ከመነሻዉ አቅሙ በፈቀደዉ ሁሉ እገዛ ማድረጉ እንደ ጥፋት ቆጥረዉት ካልሆነ በስተቀር  የኤርትራን ሉአላዊነት የሚጋፋ እርምጃ ወስዷል የሚል አንዳችም ትችት ወይም ክስ አልቀረበበትም፡፡ በወቅቱ የሻዕቢያ መንግስት ደርግን አሸንፎ አስመራ መቆጣጠር ከቻለ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ደገፈም አልደገፈ የኤርትራን ለብቻዋ መሆን ሊያስቀር የሚችልበት አንዳችም ሁኔታ አልነበረም፡፡ ሪፈረንዴም መደረጉም ለሻዕቢያ ዓለም አቀፍ እዉቅና ለማግኘት ስለሚያግዘዉና በተጨማሪ ህጋዊ መንገድ የመከተል ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የኤርትራ ነጻ አገርነት ጉዳይ ቀድሞዉኑ የደርግ መንግስት በተሸነፈ ጊዜ ያበቃለት ጉዳይ ነበር፡፡

በርካታ ኢትዮጵያዉያን ግን የኤርትራ ከእናት አገሯ እንዲህ እንደዋዛ መነጠል በወቅቱ  እጅግ ሲያንገበግባቸዉ እንዳልነበር ዉለዉ ሲያደሩና የኤርትራን አመራሮች ጋጠ ወጥነት ሲያዩ ግን  “ግልግል ነዉ” ነበር ያሉት፡፡ እንኳን ቀረብን ነበር ያሉት፡፡ ለነገሩ ሻዕቢያ የመገንጠል ሃሳቡን ቀይሮ አንድ ላይ እንሆናለን አንገነጠልም ቢሉ ቢሆን ኖሮ  ምን ዓይነት ወጥ መንግስትስና ስርአት መመስረት ይቻል ነበር?

ሁለቱ ድርጅቶች የተለያዬ ስርአት ለመመስረት በሚያስቡበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት አገር ልትሆን ትችል ነበር? የአገሪቱን ገዢ ፓርቲ ሊሆን ይችል የነበረዉስ ሻዕቢያ ነዉ ወይስ ኢህአዴግ? የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይሆን የነበረዉ የኢህአዴግ ወይስ የሻዕቢያ ሰራዊት ነበር? ግራ የሚያጋባና ምስቅልቅል ያለ ሁኔታ ሊፈጠር ይችል ነበር፡፡ ለዚህም ነዉ በኋላ ሁኔታዉን ሲረዱ ብዙዎቹ ኢትዮጵያዉን “አረ እንኳን ያልሆነ “ለማለት የበቁት፡፡ እንዲያዉም አንዳንዶቹ ኢህአዴግን በዚህ ጉዳይ ክፉኛ ተቀይመዉ የነበሩ ሳይቀሩ የኢሳይያስን ድርጊት ካዩ በኋላ ኢህአዴግን “ደግ አደረገ” በማለት አመስግነዉታል፡፡

የሻዕቢያ  መሪዎች እንደ እስራኤል ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በመገንባት የሪጀኑ (የአካባቢዉ) ወሳኝ ሃይል ለመሆንና በኢኮኖሚ ደግሞ የምስራቅ ኤሽያዋን ሲንጋፖር ለማድረግ ማለማቸዉ የሚያስወቅሳቸዉ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንደ አንድ የሀገር መሪ ኢሳይያስም ለሀገራቸዉ ህዝብ መልካም ነገር ቢመኙለት ተገቢና የሚያስመሰግናቸዉም በመሆኑ ነዉ፡፡ እኛም የኢሳያስን ኤርትራን የመልማትና ታላቅ ሀገር የማድረግ ህልም አልተቃወምንም፡፡ ችግሩ ግን ይህን ህልማቸዉን እዉን  ለማድረግ ያሰቡበት መንገድ በኛ ኪሳራ መሆኑ ነዉ፡፡

ኤርትራን በኢንዱስትሪ ለማበልጸግ ሲያቅዱ ኢትዮጵያን በጥሬ ዕቃ ምንጭነት እንደሚጠቀሙ ታሳቢ በማድረግ ነዉ፡የዉጭ ምንዛሪ ለማግኘትም ከኢትዮጵያ ቡናና የቅባት እህሎች ወዘተ በኛዉ ብር እየገዙ ወደ ዉጭ መላክ እንደሚችሉ በጣም እርግጠኛ ሆነዉ ነዉ፡፡ ኢሳይስ ይህን ህልማቸዉን አልመዉ ብቻ አልተቀመጡም፡፡ በተግባርም ብዙ ተራምደዋል፡፡ ለሰባት ተከታታይ አመታት ያለመቋረጥ ግጠዉናል፡፡ ከዚያ በላይ ግን ልንተባበራቸዉ አልፈቀድንም፡፡ በዚህ ምክንያትም እኛን እያደሙ እነሱ የሚለሙበት አንዳችም ምክንያት ስለለለ ዘግይተንም ቢሆን አስቁመናቸዋል፡፡

ኤርትራ ከተገነጠለችበት እለት ጀምሮ ኢትዮጵያ የድሮ “ቅኝ ግዛቷን“ ኤርትራን መልሳ የማቋቋምና የማበልጸግ ሃላፊነትና ግዴታ ያለባት በሚያስመስል ደረጃ ኤርትራን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉና ያደረጉ በእኩልነት ላይ ያልተመሰረቱ ግኑኝነቶች ሲካሄዱ እንደነበረ በወቅቱ  ሁኔታዉን የተረዱ ዜጎቻችን  በሃዘንና በቁጭት ሲገልጹት የነበረ ነዉ፡፡ በጣም የሚገርመዉና የኤርትራን ባለስልጣናትን ዓይን አዉጣነትና አጭበርባሪነት የሚያሳዬዉ በወቅቱ በነበረዉ የተዛባ ግኑኝነት ከኤርትራ ይልቅ ኢትዮጵያ የበለጠ ተጠቃሚ ነበረች ሲሉ መደመጣቸዉ ነዉ፡፡

የኤርትራ ስግብግብነትና ዓይን ያወጣ ዝርፊያ ገደቡን አልፎና ህዝቡን አበሳጭቶና የኢትዮጵያን መንግስትን አስቆጥቶ ዘግይቶም ቢሆን መንግስታችን አንዳንድ ማስተካከያ እርምጃዎችን መዉሰድ ሲጀምር “ኡኡ” ማለት የጀመሩት እነሱ ናቸዉ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ ከቀድሞዉ ግኑኝነት የበለጠ ተጠቃሚዎቹ እኛ ሆነን ቢሆን ኖሮ መቆጣት ያለብን እኛ መሆን ሲገባን ሻዕቢያ የበቀል እርምጃ ሊወስድብንም ሆነ ጦርነት ሊያዉጅብን ባልተገባዉ ነበር፡፡

በሻዕቢያ ድርጊት ሲበግኑ የቆዩ ኢትዮጵያዉያን ከሻዕቢያ ጋር ወደ ጦርነት መግባታችን ሲሰሙ ከአንግዲህ የሻቢያን ዝርፊያና ብዝበዛን ያስቀራል በሚል እሳቤ ከፍተኛ ደስታ ነበር የተሰማቸዉ፡፡ ስለዚህ በኛ መንግስት በኩል የእነሱን መብትም ሆነ ሉአላዊነት የሚጎዳ አንዳችም ነገር አላደረግንም፡፡

5.2/በወታደራዊመስክምበመካከላችንየነበረዉትብብርከኛይልቅኤርትራየበለጠተጠቃሚየሚያደርግነበር

ኤርትራ ገና አዲስ ጎጆ ወጭ የነበረች በመሆኑ እንደ ሀገር ሊኖራት የሚገቡ ተቋማት ስለአልነበሯት ኢትዮጵያ እገዛ ማድረጓ የሚያስደንቅ አልነበረም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይብዛም ይነስም ከኤርትራ የተሻለ ሁኔታ ላይ ስለነበር ራሳቸዉን አስከሚችሉ በገንዘብ ሊተመኑ የማይችሉ እጅግ ብዙ እገዛዎች ሲያደረግ እንደነበረ ይታወቃል፡፡

ከነዚህም አንዱ በወታደራዊ መስክ በተለይም አየር ኃይሏን በማቋቋምና በማደራጀት፣ የአየር ኃይል ጄት አብራሪዎችን በማሰልጠን ረገድ ኤርትራን ለማገዝ ኢትዮጵያ አሰተዋጽኦ አድርጋለች፡፡ በወታደራዊ መስክ ኢትዮጵያ ለኤርትራ ያደረገችላት ትብብር ረገድ ሳይጠቀስ የማይታለፍ ነገር ቢኖር ኤርትራ በማንአለብኝነት ተነሳስታ የየመን ህጋዊና ታሪካዊ ይዞታ የሆነዉን የሃኒሽ ደሴትን በኃይል ወርራ ከተቆጣጠረች በኋላ ኢትዮጵያ የአየር ኃይል አካል የነበሩ የአየር መከላከያ ክፍሎችን አሰብ ላይ ማስፈሯ ነዉ፡፡

በሁለቱ አገሮች መካከል በነበረዉ ወታደራዊ ስምምነት መሰረት አትዮጵያ በወቅቱ የአሰብ ወደብን ከአየር ጥቃት ለመታደግ የሚችል የአየር መከላከያ ክፍሎችን ልካ በአሰብ አካባቢ የአየር ክልል ጥበቃ በማድረግ ትብብሯን አሳይታለች፡፡ በወቅቱ ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፉ ሚሳይሎችንና እና የቅኝት ራዳሮችን (serveillaence radars) የታጠቁ ሶስት የአየር መከላከያ ዩኒቶችን (anti aircraft missile squadrons) አሰብ ላይ አስፍራ እንደነበርና ከሁለት ዓመት ላላነሰ ጊዜ በዚያ እንደቆዩ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ ይህን እርምጃ የወሰደቸዉ ከኤርትራ ጋር በነበራት ወታደራዊ ስምምነት መሰረት ነበር፡፡ በዚሁ ስምምነት መሰረትም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወረራ መደገፏ ብቻ ሳይሆን ሃኒሽ ደሴት የኤርትራ ንብረት እንደሆነ እዉቅና መስጠቷን በቅርቡ የወጣ አንድ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ያ ብቻ ሳይሆን ለጦርነቱ እገዛ እንዲያደርጉ ተብሎ አራት ሄሊኮፕተሮችን በወቅቱ ኢትዮጵያ ለኤርትራ መስጠትዋም ተወስቷል፡፡ በወቅቱ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ሰለመፈራረሟ የሀገራችን ፓርላማ የሚያዉቀዉ ነገር አልነበረም፡፡ በፓርቲዉ ደረጃም ቢሆን ከጥቂት የህወሓት አመራሮች ዉጭ ሌሎቹ  ኢህአደግ አመራሮችም ሆኑ የመንግስት ካቢኔ አባላቱ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር አልነበረም ነዉ የተባለዉ፡፡  

የኢትዮጵያ መንግስት ሻዕቢያን ለማገዝ ወደ አሰብ ጦር መላኩን ባወቁ አንዳንድ ወገኖች ኢትዮጵያ ለኤርትራ ህገወጥ ድርጊት የተባበረችና ወረራዉንም የደገፈች ያህል ማስቆጠሩና ማስተቸቱ አልቀረም፡፡ በሌላ በኩል ሁኔታዉን በቀና መንፈስ የተመለከቱ ወገኖች ኢትዮጵያ በብቸኝነት ስትጠቀም የነበረዉ አሰብ ወደብን ደህንነት ለማስጠበቅ ወይም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ተብሎ የተደረገ እንጂ የኤርትራን ወረራ ለመደገፍ ተብሎ አልነበረም የሚሉ አሉ፡፡

ያም ሆነ ይህ ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላና የየመንና የኤርትራ ዉዝግብም እልባት በማግኘቱ ኢትዮጵያ ጦሯን ማለትም የአየር መከላከያ ክፍሉን ከአሰብ ካስወጣችም በኋላ ኤርትራን በወታደራዊ- ቴክኒካዊ ጉዳዮች ማገዟን አላቋረጠችም ነበር፡፡  ለምሳሌ በአስመራ ዉስጥ ያለ ስራ ተከማችተዉ ይገኙ የነበሩና ሩሲያ ሰራሽ የሆኑ የሶስት የአየር መከላከያ ስኳድሮኖች መሳሪያዎችን የሻዕቢያ አመራሮች አስጠግነዉ ለመጠቀም በነበራቸዉ ዉጥን መሰረት ከሩሲያና ከዩክሬይን ጋር ያደረጉት  ድርድር በዉጭ ምንዛሪ እጦት ሊሳካላቸዉ ባለመቻሉ የወቅቱ ወዳጇን ኢትዮጵያን ትብብር በመጠየቋና መንግስታችንም ጥያቄያቸዉን በመቀበል ተባብሯል፡፡

በዚሁ መሰረትም ለረዥም ዓመታት በዚህ ሙያ የተካኑትን የአየር መከላከያ ኢንጂነሮችንና ቴክኒሻኖችን አስመራ ድረስ በመላክ እዚያ ተከማችተዉ ይገኙ የነበሩትን የአየር መከላከያ መሳሪያዎች በሙሉ በሚገባ ጠግነዉና አስተካክለዉ ካስረከቡ በኋላ ወደ ሃገራቸዉ ተመልሰዋል፡፡ የሻዕቢያ ባለስልጣናት በኢትዮጵያዉያኑን ባለሙያዎች በተሰራዉን ስራ እጅግ ከመደሰታቸዉ የተነሳ እንደምንም አግባብተዉና በገንዘብ አታለዉ እዚያዉ ሊያስቀሯቸዉ አንዳንድ ሙከራዎችን ከማድረግ ባይቆጠቡም እንዳሰቡት ግን ሊሳካላቸዉ አልቻለም፡፡

ከአስመራ እንደተመለሰ ስለሁኔታዉ ያጫወተኝ በወቅቱ የቡድኑ አባል የነበረና አሁን በህይወት የሌለ የአየር መከላከያ ሙያተኛ የሆነ ኮሎኔል ነዉ፡፡ ይህ የአየር መከላከያ አባል በወቅቱ የሻዕቢያ ዓላማና ዉጥን ምን እንደነበረ በዉል ለመረዳት ባይችልም አጉል ብልጣብልጥነታቸዉ ግን አበሳጭቶት ነበር፡፡

በነገራችን ላይ የተጠቀሱት እነዚህ መሳሪያዎች ባለፈዉ የደርግ መንግስት ወደ መጨረሻዉ አካባቢ በብዙ ሚሊዮን ዶላር በብድር ከሩሲያ ተገዝተዉ የመጡና ገና አንድ ዓመት እንኳን ያላገለገሉ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት የነበሩ ናቸዉ፡፡ ሻዕቢያ በ1983 መጨረሻ ላይ አሰብን ከተቆጣጠረ በኋላ በመርከብ አጓጉዞ ወደ አስመራ ወስዶ ያከማቻቸዉ ናቸዉ፡፡

የኤርትራ መንግስት እነዚህን መሳሪያዎች ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ አዉጥቶ በሩሲያ ባለሙያዎች ካላስጠገነና ለዘለቀታዉም ወጣቶችን ሩሲያ ድረስ በመላክ ባለሙያዎችን እንዲያሰለጥኑለት ካላደረገ በስተቀር መቼም ቢሆን መሳሪያዎቹን ለመጠቀም እንደማይችል ሲገነዘብና የዉጭ ምንዛሪም እንደለለዉ ሲረዳ እንደአማራጭ የወሰደዉ አሁንም የኢትዮጵያ መንግስት አሰልጣኞችን አስመራ ድረስ በመላክ ኤርትራዉያንን እንዲያሰለጥንላቸዉ ማድረግ ነበር፡፡

በዚህ መሰረትም ትብብር የጠየቁበት ደብዳቤ በኢፌድሪ አየር ኃይል በወቅቱ አዛዥ በነበሩት በሜ/ጄል አበበ (ጆቤ) በኩል ደርሶን አንዳንድ ዝግጅቶች በማከናወን ላይ እያለን ነዉ የሻዕቢያ ወረራ ማድረግ የተሰማዉ፡፡ በነሱ ጥያቄ መሰረት ተቻኩለን አሰልጣኞችን ልከን ቢሆን ኖሮ እዚያዉ ምርኮኛ ሆነዉ ሊቀሩ ይችሉ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ሻዕቢያ ምን ያህል ልቡ የማይገኝ መሆኑን ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሌም ሳስታዉሰዉ ከሁሉም በላይ የሚያናድደኝ የሻዕቢያ ተንኮል ቢኖር አስመራ የነበረዉን የኛኑ መሳሪያ በእኛዉ ባለሙያዎች አስጠግኖና አሰልጥኖ መልሶ የኛኑ አይሮፕላኖች ለመምታት አቅዶት የነበረዉን  ሴራ ነዉ፡፡

ከኤርትራ ጋር የነበረዉ ወታደራዊ ትብብር በዚህ ብቻ ሳይገደብ አየር ኃይላችን ለኤርትራ የተለያዩ ትብብሮችን አድርጓል፡፡  ለኤርትራ የመጀመሪያዎቹ የሆኑትን ጄት አብራሪዎች እዚሁ ደብረ -ዘይት (ሐረር-ሜዳ) ላይ አሰልጥኖ እስመርቋል፡፡ ከዚህም ሌላ የኛ ሄሊኮፕቴሮች አስመራ ዉስጥ በቋሚነት ተመድበዉ ለኤርትራ ባለስልጣናት በትብብር የማጓጓዣ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዉ ጦርነቱ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ ሲቀረዉ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱበት ሁኔታ የአጋጣሚ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ከዚህም ሌላ በሽግገሩ ወቅት አየር ኃይላችን እንደገና በማቋቋም ስራ እንዲያግዙ በጊዜያዊነት በመንግስት ተመድበዉ የነበሩት ብርጋዲር ጄነራል ሰለሞን በየነ  ኤርትራም በበኩሏ አየር ኃይል ለማቋቋም ስታደርግ በነበረዉ ጥረት ኢትዮጵያ ማገዝ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ለመመካር አስመራ ድረስ በመሄድ ከባለስልጣናቱ ጋር ሲመካከሩ ዓይን አዉጣዎቹ  የኤርትራ መከላከያ ባለስልጣናት ለጄነራሉ አቅርበዉ የነበረዉ ሃሳብ እጅግ የሚገርም ነበር፡፡

ያቀረቡትም ጥያቄ ደብረዘይት ያለዉ የአየር ኃይል ማስልጠኛ ተቋም እንዳለ ተነቅሎ እዚህ አስመራ ላይ ተቋቁሞ ለሁለቱም አገሮች ስልጠና ከአስመራ ላይ ይስጥ የሚል ነበር፡፡ ሻዕቢያ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ መጠየቁ ለኢትዮጵያ መንግስት ምን ያህል ንቀት እንደነበረዉ የሚያሳይ ነዉ፡፡

ለማንኛዉም በዚህና በሌሎች ባልተጠቀሱ አጋጣሚዎች የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራን እንደራሱ አይቶ ያለባቸዉን ችግር ተረድቶ ያለአንዳች ክፍያ በብዙ ነገር ሊያግዛቸዉ መሞከሩ ወንድም ለሆነዉ የኤርትራ ህዝብ ያለዉን ቅን አመለካከት የሚያሳይ ካልሆነ በስተቀር ኤርትራን የሚያስከፋ ድርጊት አልነበረም፡፡ ለምንስ ተብሎ ጦርነት ትከፍትብናለች ተብሎ ይታሰባል?

5.3/መንግስትብቻሳይሆንመከላከያሰራዊታችንአባላትምኤርትራህዝብየጠላትነትአመለካከትአልነበራቸዉም  

ከጦርነቱ በፊት ኤርትራን እንደ ወዳጅ የማየት ነገር በመንግስት ደረጃ ብቻ የነበረ አቋም ሳይሆን በመከላከያ ሰራዊታችን አባላት ዘንድም ኤርትራን በጠላትነት የሚፈርጅ አመለካከት ጨርሶ አልነበረም፡፡ ደርግ ከወደቀ ከ1983 መጨረሻ ጀምሮ አብሮ የመስራት አጋጣሚ በፈጠረልኝ ምቹ ሁኔታ ያወቅኳቸዉ ነባር ታጋዮች በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ የኤርትራን ህዝብ በሚመለከት አንዳችም የጥላቻ አመለካከት አልነበራቸዉም፡፡

የኤርትራን ህዝብ ነጻነት በሚመለከትም የተቃዉሞ አመለካከት በጭረሽ አልነበራቸዉም፡፡ ይሄ ህዝባዊ አመለካከት ከላይ ያለዉ የድርጅታቸዉ መሪዎች እንደዚያ እንዲያደርጉ መመሪያ ስለሰጧቸዉ ሳይሆን ገና ከትግሉ ጊዜ ጀምሮ በእምነት የያዙት የጸና አቋማቸዉና አመለካከታቸዉ መሆኑን ነዉ የተረዳሁት፡፡

የኤርትራ ሪፌሬንደም ሊከናወን አካባቢም ታጋዮቹ ከህዝቡ ጋር ይበልጥ የመቀራረብና በአንዳንድ ማህበራዊ ጉዳዮችም በአካባቢያቸዉ ካለዉ ህዝብ (ነዋሪ) ጋር  አብሮ መሳተፍና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸዉ ጉዳዮች ላይም በግልጽ መወያት የጀመሩበት ወቅት ስለነበር የሕዝቡን አመለካካት በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ያስቻላቸዉ ይመስለኛል፡፡ በሪፌሬንደም ወቅት ከሚቀርቧቸዉ ነዋሪዎች ጋር በግል መወያዬት በመቻላቸዉ በህዝቡ ዉስጥ በስፋት ሲንሸራሸሩ የነበሩ አስተያየቶችን በማድመጥ በተለይ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ለምን ብዙ ሰዉ ቅሬታ እንደተሰማዉ ግራ መጋባታቸዉ አልቀረም፡፡

የኤርትራ ነጻ መዉጣት (መገንጠል)ላይ  አብዛኛዉ ህዝብ ደስተኛ እንዳልሆነና ይልቁንም ቅር መሰኘታቸዉ ሲገነዘቡ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለማስረዳት ጥረት ያደርጉ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ እንደሚታወቀዉ ብዙዎቹ ታጋዮች በወቅቱ ገና በወጣትነታቸዉ ትምህርት አቋርጠዉ ወደ ትግሉ በመቀላቀላቸዉ በትምህርት የገፉ ባይሆንም ነገር ግን በሚያምኑበት ጉዳይ ላይ በከፍተኛ የራስ መተማመን መንፈስ ለማሳመን ሲሞክሩ ሳይ በጣም ይገርመኝ ነበር፡፡ ያኔ ያየሁባቸዉ ግልጽነት፤ ቅንነት፤ ህዝባዊ አመለካከት፤ በራስ የመተማመን መንፈስና አልበገር ባይነት ዛሬም እብሮአቸዉ ይኖር ይሆን?

የኢህአዴግ ታጋዮች በወቅቱ የሪፈሬንደሙን ፋይዳ እንደ ህዝብ የኤርትራን ህዝብ ፍላጎት መግለጫ መንገድ አድርገዉ ነበር የቆጠሩት፡፡ “ህዝብ ምንጊዜም የፈለገዉን መወሰን ይችላል፡፡ የኤርትራ ህዝብም ለነጻነቱ ለዘመናት ሲታገል ቆይቷል፡፡ ብዙ መስዋእትነትም ከፍሏል፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ከእኛ ጋር መኖር ካልፈለገና ብቻዬን ልሁን ካለ ሊገደድ አይገባዉም” የሚል አመለካከት ነዉ የነበራቸዉ፡፡ ይሄ አመለካከት የሁሉም ታጋዮች  አመለካከት ይመስለኛል፡፡

ከዚያም በኋላ ኤርትራ በሪፌሬንደሙ መሰረት ተነጥላ እንደሀገር መታወቅ ከጀመረች በኋላም ይሄዉ ለኤርትራ ህዝብ የነበራቸዉ ቀና አመለካከት በፍጹም አልቀነሰም ነበር፡፡ እንዲያዉም ኤርትራ ወረራ ማድረጓ በይፋ ከመገለጹ አንድ  ወር ቀደም ብሎ በርካታ የአየር ኃይል አባለት በተገኙበት አንድ ሰብስባ ላይ በሆነ አጋጣሚ ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዱ ነባር መኮንን ስለ ኤርትራ መንግስት በጥላቻ የታጀበ አስተያዬት ሲሰጥ ሰብሳቢዉ ነባር ታጋይ ተናጋሪዉን መኮንንን “ትምክህተኛ  ነህ” በሚል በተሰብሳቢዎች መሀል ከፍተኛ ትችት ካደረሰበት በኋላ መኮንኑ ከስራ መታገዱን አስታዉሳለሁ፡፡

የሚያሳዝነዉ ደግሞ ለኤርትራ ጥብቅና ቀሞ የነበረዉ ይሔዉ አመራር (ሰብሳቢዉ) በጦርነቱ የመጀመሪያ ሳምንት በግዳጅ ላይ እያለ በኤርትራ አየር መቃወሚያ ተመትቶ መስዋእትነት መሆኑ ነዉ፡፡ አጋጣሚዉ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ይሄን ጉዳይ ያስታወስኩትም አንዱን ለመተቸት ሌላዉን ለማድነቅ ሳይሆን ሰራዊታችን እሰከ ጦርነቱ ድረስ ለኤርትራ ህዝብ መልካምና ቀና አመለካከት እንደነበረዉ ማሳያ ይሆናል በሚል ነዉ፡፡

የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት ለኤርትራ ህዝብ ነጻነት ሙሉ ድጋፍ ከማሳየት ዉጭ አንድም ጊዜ የኤርትራን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነግር አድርገዉ አያዉቁም፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ነባሮቹ ታጋዮች ለኤርትራ ገዢ ፓርቲ ለሻዕቢያ አመራሮች የነበራቸዉ አመለካከት ግን ከዚህ የተለየና በጥላቻ የተሞላ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ ሻዕቢያ ገና ከትግሉ ጊዜ ጀምሮ ዲሞክራሲያዊ አመለካከት የሚባል ነገር ያልነበረዉ ሰብአዊነትና ለህዝብ ከበረታ ያልነበረዉ አምባገነን ድርጅት እንደነበርና አሁንም መንግስት ከሆነም በኋላ ይህንኑ ባህሪይዉን ሳይቀይር በመቆየቱ የኤርትራን ህዝብ ለባሰ ጭቆና መዳረጉን በማዉሳት ለሻእቢያ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸዉ ለሚቀርቧቸዉ ሲገልጹ በቁጭትና በሃዘን ነበር፡፡

በአንድ በኩል የኤርትራን ህዝብ ነጻነትና መብት አክብሮ በሌላ በኩል ደግሞ የሻቢያን ፀረ- ህዝብነት መተቸት ተገቢ ቢሆንም በጣም ከሚያምኑት ሰዉ ጋር በግል የርስበርስ ጭዉዉት ካልሆነ በስተቀር በመድረክ ላይ በይፋ የዚህ ዓይነት አስተያት የተሰነዘረበት ወቅት አላስታዉስም፡፡ ታጋዮቹ በትግሉ ወቅትም ለኤርትራ ህዝብ ቀና አመለካከት ከመያዝና ከወታደራዊ አስፈላጊነት አኳያ በዉጊያ ወቅት ዉስን ለሆኑ ጊዜያት ከመተባበር ባለፈ ከሻዕቢያ ጋር በዓላማም በአመለካከትም የማይመሳሰሉና የማይጣጣሙ እንደነበሩ ነዉ፡፡

ስለዚህ በመንግስት ደረጃም ሆነ በሰራዊቱ ዘንድ የኤርትራን ህዝብ ነጻነት የሚጋፋ አንዳችም ደባ እንዳልተሰራ መረዳት ይቻላል፡፡ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት ከጦርነቱ በፊት ይቅርና አሁንም በሻዕቢያ ጦስ ብዙ ምስቅልቀል ሁኔታዎችና ብዙ መስዋትነት ከተከፈለም በኋላም ቢሆን ለኤርትራ ህዝብ አንዳችም ጥላቻ አላሳደሩም፡፡ ለዚህም ጥሩ ምስክር የሚሆነዉ ትላንት ሲወጉን የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ሰራዊት፤ መንግስትና ህዝብ በማመን ሻዕቢያን እየከዱ በየዕለቱ ወደኛ በገፍ መጉረፋቸዉ ነዉ፡፡

5.4/የኢትየጵያመንግስትባህሪይናየሚከተለዉየዉጭግኑኝኘትፖሊሲለኤርትራየስጋትምንጭሊሆንየሚችልአልነበረም

የሁለቱም አገሮች ህዝቦች ለዘመናት ሲካሄድ በነበረ የርስበርስ ጦርነት እጅግ የተጎዱና ጦርነት የሚባል ነገር ያንገሸገሻቸዉ የነበሩ ስለነበር ለዬትኛዉም ዓይነት ሰበብ ተፈልጎ ለሚደረግ ጦርነት ህዝቡ ድጋፍ አይሰጥም የሚል አመለካከት በተለይ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ነበር፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል አስቀድሜ በገለጽኩት ዓይነት ጠንካራ የወዳጅነት ግኑኝነት በመኖሩ አልፎ አልፎ አንዳንድ አለመግባባቶችና አለመጣጣም መከሰቱ ባይቀርም ወደ ደም አፋሳሽ ጦርነት የሚያስገባ ቅራኔ ግን አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ሲከተለዉ የነበረዉና አሁንም አጠንክሮ የቀጠለበት የዉጭ ግኑኝኘት ፖሊሲ ከሁሉም ጋር በሰላም ተከባብሮ የመኖርና የሌላዉን ጥቅምና ሉአላዊነት ማክበር ከሚሏቸዉ የተለመዱ መርሆችም በላይ በመሄድ የዉጭ ዲፕሎማሲ ትልቁ ስራዉ ልማትን የሚያግዝና ኢኮኖሚን ማምጣት ነዉ በሚል ትክክለኛ መሪህ ከመከተል ዉጭ ኤርትራን የሚጎዳ አንዳችም ድርጊት አልፈጸመም፡፡

መንግስታችን ከሌላ ከዬትኛዉም አገር ጋር ኤርትራንም ጨምሮ በጠላትነት የማይተያይ በመሆኑ ለየትኛዉም የጎረቤት አገር በተለይም ለኤርትራ የስጋት ምንጭ የሚሆንበት አንዳችም ምክንያት አልነበረም፡፡ ሌላዉ ቀርቶ መንግስት ግዙፍ የሆነ ሰራዊት ግንባታ አለማድረጉና ደርግን ያሸነፈዉን ሰራዊቱን ግማሽ በግማሽ ቀንሶና አሰናብቶ በቂ ነዉ ብሎ ያሰበዉን ያህል መጠነኛ ኃይል በያዘበት ሁኔታ ለኤርትራ ስጋት የሚሆንበት ምክንያት አይኖርም፡፡

መንግስት ለሌላ አገር ስጋት አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ራሱም ከየትኛዉም ወገን  የሚያሰጋኝ ነገር የለም በሚል አቋም በመደፋፈሩ ከጦርነቱ በፊት የተለየ ወታደራዊ  ግንባታ አላደረገም፡፡ ከጦርነቱ በፊት አንዳችም የጦር መሳሪያ ግዢ አልፈጸም፡፡ በወቅቱ ወታደራዊ ባጄቱ ራሱ እጅግ አነስተኛ የነበረ በመሆኑ መንግስት የተለዬ የጦርነት ዝግጅት እንዳልነበረዉ የሚያሳይ ነዉ፡፡

ሌላ ቀርቶ በኤርትራ አዋሳኝ ድንበር ላይም ይህን ያህል ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል የተለየ ወታደራዊ ክምችት አልነበረም፡፡ በወቅቱ ከሁመራ እስከ ዛላአንበሳ ባለዉ ሰፊ መሬት ላይ ቢበዛ በድምሩ ከሁለት ብርጌድ የማበልጥ ሰራዊት ነዉ የነበረን፡፡ የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ግንባታም ሆነ የጦርነት ዝግጅት አጠራጥሮአቸዉና አስግቶአቸዉ ሳንቀደም እንቅደም ብለዉ ነዉ ወረራዉን የጀመሩት እንዳይባል አስቀድሜ እንደገለጽኩት ለዚህ ጥርጣሬ የሚያበቃ በኛ በኩል አንዳችም ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያዉም በተቃራኒዉ ወደ መዘናጋቱ ያደላ ዓይነት ሁኔታ ነዉ የነበረዉ፡፡

አስቀድሜ ለመጠቆም እንደሞከርኩት  በሁለቱ አገሮች መካከል መልካም ግኑኝነት የነበረና እንዲያዉም ኤርትራ ከኢትዮጵያ በበለጠ ከዚህ ግኑኝነት ተጠቃሚ እንደነበረች፤ በመንግስት ደረጃም ሆነ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ደረጃ ኤርትራን ለጦርነት የሚገፋፋ አንዳችም ሁኔታ አልነበረም፡፡ ባጠቃላይም ኤርትራን ለጦርነት የሚጋብዝ ምክንያት ይኖራል ብሎ  ለማሰብ የሚያስችል አንዳችም አሳማኝ ሁኔታ ስላልነበረ መንግስት ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል ብሎ አለመገመቱ በወቅቱ የነበረዉን እዉነታ ለመግለጽ ካልሆነ በስተቀር ለመሸፋፈን ወይንም ከትችት ለማምለጥ የፈጠረዉ ምክንያት  አይመስለኝም፡፡

6/የሆነስሆነናሌላዉቢቀርመጠንቀቅስአይቻልምነበርእንዴ?

አስቀድሜ በገለጽኳቸዉ ሁኔታዎች ምክንያት ወረራዉን ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነዉ ለመባል በቂ ምክንያት ነዉ ብንል እንኳን ሃላፊነት እንደሚሰማዉ መንግስት ቢያንስ መጠራጠርና መጠንቀቅስ አልነበረበትም ወይ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ የግድ ነዉ፡፡

በኤርትራ የተሰነዘርብን ጥቃት ኢሳይያስ ድንገት ከእንቅልፋቸዉ ሲነቁ ድንገት ወስነዉ በዚያኑ ዕለት የፈጸሙት አይደለም፡፡ የትኛዉም ዓይነት ጦርነት እንደተረገጠ ፈንጂ ድንገት የሚፈነዳ አይደለም፡፡ ሰበብ ተፈልጎለት በሃሳብ ተጸንሶ አስፈላጊዉ ዝግጅት ተደርጎበት ፤ታቅዶና ታስቦበት ጊዜ ተወስዶ የሚደረግ ነዉ፡፡ ጦርነት ምናልባት እንደ ጥንቱ የሀገራችን ልማድ ሁለት በላጋራዎች አስቀድመዉ ጊዜና ቦታ መርጠዉ እዚህ ቦታ በዚህ ጊዜ እንገናኝ ተብሎ ፤እንደ ኳስ ጫወታ ዳኛ አቁመዉና ፍሽካ ተነፍቶ የሚጀምር አይደለም፡፡

ያለ ምክንያት የሚካሄድ አንዳችም ጦርነት የለም፡፡ ፖለቲካዊ ዓላማ የሌለዉ ጦርነትም በጭራሽ አይኖርም፡፡ የክላዉስዊዝ (Clausewitz) የጦርነት አስተምህሮም የሚያረጋግጠዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ ወደ ጦርነት የምንገባዉ ያሰብነዉን ፖለቲካዊ ዓላማ ለማሳካት ነዉ፡፡ ጦርነት የራስን ፍላጎት በሌላዉ ለመጫን የሚደረግ የኃይል ድርጊት ነዉ፡፡ ጦርነት የሚመነጨዉ ወይም የሚቀሰቀሰዉም ከሆነ ፖለቲካዊ ዓላማ ነዉ (war springs from some political Purpose)፡፡

ጦርነት ለመቀስቀስ ፖለቲካ ዓላማዉ የግድ ትክክል መሆን አይጠበቅበትም፡፡ ለጦርነት የሆነ ዓላማ መኖር ብቻዉን በቂ ነዉ፡፡ ጦርነት ከፖለቲካ ዓላማ መመንጨቱ ብቻ ሳይሆን ራሱ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሳሪያም ጭምር (political tool) ሆኖ ያገለግላል፡፡ ጦርነት የፖሊሲ ማስፈጸሚያ መሳሪያ በመሆኑ ጦርነቱ  የፖሊሲ አዉጭዎችን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ መሆን ይገባዋል (wars are deliberate instruments of policy, and in their essence reflect the motives of the policymakers.) የጦርነት ዋነኛዉ ገላጭ ባህሪም አጋጣሚ ወይም ዕድል ሳይሆን የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሳሪያነቱ ነዉ፡፡  (The primary characteristic of war is not chance, but rather its nature as a political tool.)

እንግዲህ ከነዚህ ጥቂት መሪሆዎች (ጥቅሶች) መረዳት እንደሚቻለዉ የኤርትራ መንግስት ጦርነት ሲከፍትብን ይብዛም ይነስም ጦርነት ለመቀስቀስ በቂ የመሰለዉን ፖለቲካዊ ዓላማ ይዞና ከጦርነት መንገድ ዉጭ በሌላ በማናቸዉም መንገድ ማሳካት እንደማይችል ተገንዝቦና ያን ለማሳካትም የሚያስችለዉን በቂ ወታደራዊ ዝግጅት አድርጎ ነዉ፡፡

ከጦርነቱ ምን ለማግኘት እንደፈለገም በቅድሚያ አስቦበት ነዉ፡፡ ሊገጥመዉ የሚችለዉን ተግዳሮትም በሚገባ አስቦበት ነዉ፡፡ ዝም ብሎ ዘሎ ጦርነትን ያህል ነገር ዉስጥ አልገባም፡፡ ምናልባት ኤርትራ ድሮ የለመደችዉና በኋላ ያጣችዉ ወይም የተቋረጠባት አንድ የሆነ ጥቅም ይኖራል፡፡ ሰበቡ ለኛ ከግምት የማይገባና እርባና ቢስ ሆኖ ቢታዬንም ለነሱ ግን ጦርነት ለመቀስቀስ በቂ ምክንያት አድርገዉ ሊያስቡ ይችላል፡፡ ጦርነትን እንደ ችግር መፍቻ ብቸኛ መንገድ ለሚቆጥር እንዴ ኤርትራ ላለ መንግስት ጦርነት ለመቀስቀስ ማንኛዉም ምክንያት (ተልካሻም ቢሆን) በቂ ምክንያት ነዉ፡፡

የእነሱ ምክንያት እኛን እንዲያሳምነን መጠበቅ አይገባንም፡፡ ኤርትራ ከኛ ስታገኝ የነበረዉና በኋላ የተቋረጠባት የገዛ ንብረቷ ስለነበረና ያንን ማግኘት ህጋዊ መብቷ ስለነበረም አይደለም፡፡ በፊት እንደዋዛ ያስለመድናትን ጥቅም በድንገት ስናቋርጥባት አንድም ሌላ አማራጭ ያልነበረዉ የኤርትራ አገዛዝ ከጦርነት የተሻለ ነገር ይኖራል ብሎ ስለማያስብ በኛ ላይ ጦርነት ቢከፍት ለምን ያስገርመናል? በእኛ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ህጋዊም ተገቢም እንዳልነበረ እንኳን እኛ ወረራ የፈጸመብን ሻዕቢያም ቢሆን ይሄን  አይረዳም ማለት አይቻልም፡፡ ችግሩ ያለዉ እኛ ዘንድ ነዉ፡፡ ይሄ እንደሚደርስ አስበን አለመጠርጠራችንና በቂ ዝግጅት በቅድሚያ አለማድረጋችን የኛ ድክመት ነዉ፡፡

እንዲያዉም ኤርትራ መንግስት የነሱን ለጦርነት ዝግጅት እያደረጉ መሆን የኛ መንግስት አለመጠርጠሩ እጅግ ሳያስገርማቸዉ አይቀርም፡፡ ለነገሩ እኮ ኤርትራዉያን የጦርነት አዋጅ በገሃድ ያለማወጃቸዉ ካልሆነ በስተቀር በተቀረዉ ሁሉ ዝግጅታቸዉን ለመደበቅ ያደረጉት ሙከራ እምብዛም አልነበረም፡፡ የኛ ደደብነት ካልሆነ በስተቀር ፡፡  ለዚህም ነዉ የሻዕቢያ ጥቃት ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነዉ ለማለት የማይቻለዉ፡፡

6.1/የሻዕቢያአመራሮችባህሪይብቻዉንለመጠንቀቅበቂነበር

የኤርትራን መንግስት በተለይም የመሪዉን የፕሬዝዳንት ኢሳይያስን ነባር ባህሪይን የሚያዉቅ ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ የግድ እንደሆነ ይረዳል፡፡ የኤርትራ ህዝብ ያን ያህል ዘመን ታግሎና ልጆቹን ገብሮ የተመኘዉን ሰላምና ልማት ገና በደንብ ሳያጣጥም ሻዕቢያ ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ስራዉን እንደመንግስት “ሀ” ብሎ የጀመረዉ እዚህም እዛም ጦርነት በመለኮስ ነዉ፡፡

ከሻዕቢያ ጋር እኩል በአንድ ሰሞን ሀገር የማስተዳደር ሃላፊነት የተቀበለዉ ኢህአዴግ በከተማና በገጠር ጤና ጣቢያና ሆስፒታሎችን ሲያቋቁም፤ ዩንቨርስቲና ኮሌጆችን ሲከፍትና የመገናናኛ አዉታሮችን ሲዘረጋ ህዝቡን ከድህነት በአጭር ጊዜ መላቀቅ ይገባኛል ብሎ በልማት ስራ ላይ ተጠምዲ ሲዉተረተር፤ አዲስ ህገመንግስት ሲያረቅና አዲስ ፌዴራላዊ ስርአት ሲመሰርት ፤ ዲሞክራሲን ለማስፋፋት የሚያግዙ ዲሞከራሲያዊ  ተቋማትን ሲያቋቁምና ከሞላ ጎደል ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ ደፋ ቀና ስል ሻዕቢያ ግን ስራዉ ሁሉ ጦርነት ሆኖ ቁጭ አለ፡፡

በኤርትራ የነበረችዉ አንድ ለናቱ የተባለላትን ዩንቨርስቲም እስከነአካቴዉ ዘግቶ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛነት ቀየረዉ፡፡ መምህራንና ሀኪሞችን መሃንዲሶችን ማፍራት ሲገባዉ በየስድስት ወሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ብሄራዊ ዉትድርና ሰልጣኞችን ማስመረቅ ስራዬ ቢሎ ተያያዘዉ፡፡ ሀገሪቱ በሌላት የዉጭ ምንዛሪ የጦር መሳሪያ መሸመት ጀመረ፡፡ ለነጻነት ተብሎ ለተከፈለዉ መስዋእትነት ዉጤት ነዉ ብለዉ ለህዝቡ የሚያሳዩትና የደረሱበትን ዕድገት መጠን የሚለኩት ባስመረቁት ወታደር ብዛት ሆኖ ቁጭ አለ፡፡

አንድ ጊዜ የመንን ሌላ ጊዜ ሱዳንን ሲፈልጉ ደግሞ ጅቡቲን ያለምንም ምክንያት በመዉጋት የዓለም ህዝብን ግራ አጋቡ ፡፡ ኤርትራን የመሰለች ከህዝቧ የመንፈስ ጥንካሬ በስተቀር አንድም የሚቆጠር ሃብት የሌላትን አገር የሚመራ መንግስት ከልማት ይልቅ ጦርነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ብሎ ማንም ሊገምት አይችልም፡፡

ኤርትራ ለሰላሳ ዓመታት በተካሄደዉ ጦርነት ስትፈራርስ የኖረችና ሊጠቀስ የሚችል አንዳችም ፋብሪካና ሌላዉ ቀርቶ ለግብርና ተስማሚ የሆነ አንድ ጋሻ የሚሞላ ለም መሬት የለላት አገር መሆኗን ለሚያዉቁ ታዛቢዎች ከኢትዮጵያ ተነጥላና ነጻ አገር ሆና በምን ተአምር ነዉ እንደ አገር ልትቀጥል የሚትችለዉ? ብለዉ ሲጨነቁ ኢሳይስ ግን ልማቱን ከማቀላጠፍ ይልቅ የጦርነት አጀንዳቸዉን አጠናክረዉ ቀጠሉበት፡፡

ኢሳይያስ ጦር ልከዉ በቀጥታ መዉጋት በማይፈልጉበት ጊዜ ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ሽብርተኛ ቡድኖችን በማስተባበር፡መጠለያ በመስጠት፤በማሰልጠን፤ በማስታጠቅና ለጥፋት ተልዕኮ በማሰማራት ሀገራችንን በሚችሉት ደረጃ ሁሉ ሲያደሙና ሰላማችንን ሲያደፈርሱ  ቆይተዋል፡፡ በኤርትራ ዲሞክራሲ ለጭላንጭል ያህል እንኳን የሌለባት፤ሰብአዊ መብት ጥሰት በየቀኑ የሚፈጸምባት ህገመንገስት፤ አማራጭ ፓርቲዎች ፤ምርጫ ወዘተ ብሎ ነገር ጭራሽ በማይታወቅበት አገር ህዝባቸዉን ሰጥ ለጥ አድርገዉ በባሪያ አሳዳሪ ስርአት አገዛዝ ስልት እየገዙ እንደሆነ በሚገባ የሚታወቅና ምስጢርም ያልነበረ አሁንም በባሰ ሁኔታ የሚታይ ድርጊት ነዉ፡፡

ኤርትራን አሁን የአለም ህዝብ የሚያዉቃት በሽብርተኝነት ነዉ፡፡ በአካባቢዉ በሪጂኑ የሆነ ቦታ ላይ የሽብር ድርጊት በተፈጸመ ቁጥር ሁሉ የኢሳይያስ እጅ እንደሚኖርበት በርግጠኝነት መናገር የተለመደ ሆኗል፡፡ ለሻዕቢያ ምስጋና ይግባዉና ኤርትራ በአሁኑ ወቅተት ከአፍሪካ ህብረትም ሆነ በመንግስታቱ ድርጅት እንደ አገር ጠንካራ ተሳትፎ የማታደርግና መሪዋም ዓይንህን ላፈር የተባሉ ከዓለም መድረክ የተገለለች አገር ሆኗለች፡፡ ኤርትራ ከቅርብ ጊዜዋ ደቡብ ሱዳንም ሆነ የሶማሊያ መንግስት ያህል እንኳን ትኩረት ያልተሰጣት አሳዛኝ አገር ሆናለች፡፡ የኤርትራ ህዝብ ወይ ከልማት ልማት የለዉ፤ ወይ ከሰላም ሰላም የለዉ፤ ብቻ ከአንዱም ሳይሆን ዕጣ ፈንታዉ እንዲህ መሆኑ በጣም ያሳዝናል፡፡

አሁን አሁንማ የኤርትራ ህዝብ ግፉና በደሉ ሲበዛበት በዚያ በተረገመ ሪፌሬንደም ስም ከእናት ሀገሩና ከወንድሞቹ የተነጠለበትን ቀን ሳይረግም የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ታዲያ እንደዚህ ዓይነቱን የማፍያ ቡድን እንደ መንግስት እዉቅና መስጠታችን እንደ ጥፋት ተቆጥሮብን ጭራሽ ጦር ሲሰብቅብን በጣም ያሳዝናል፡፡ ሻዕቢያ አዲስ ባህሪይ ካላመጣና ድሮም የምናዉቀዉን ክፉ ምግባሩን አሁንም በየጊዜዉ አጠናክሮ እየሰራ መሆኑን እያየን እኛ ላይ ጥቃት ማድረሱን “ያልተጠበቀ ነዉ” መባሉን ለመቀበል የሚከብደዉም በዚህ ምክንያት ነዉ፡፡ ቢያንስ በአካባቢዉ ከሚገኙ  አገሮች ሁሉ ጋር ሲጋጭ የነበረ መንግስት ቀጣዩ ከኛ ጋር እንደሆነ ለመረዳት እንዴት ተሳነንና ነዉ “ያልተጠበቀ” የምንለዉ?

6.2/የኢትዮጵያመንግስትየኤርትራንቅጥያጣብዘብዛለማስቆምየወሰዳቸዉእርምጃዎችኤርትራንሊያስቆጣእንደሚችልበመገመትተገቢዉንጥንቃቄማድረግይገባዉነበር

የጦርነቱ ዋነኛዉ መንስኤ የኢኮኖሚ ጥገኝነት ጥያቄ በመሆኑ ሻዕቢያ የራሱን ፍላጎትና ጥቅም በኃይል በኛ ላይ ለመጫን የቆሰቀሰዉ ጦርነት እንደነበር በሚገባ ይታወቃል፡፡ የኤርትራ መንግስት ለዓመታት በግላጭ የኢትዮጵያን  ሃብት ሲዘረፍ ኖሮ መንግስታችን ሁኔታዉ ገደቡን በማለፉ በርካታ ማስተካከያ እርምጃ በመዉሰድ ቁጥጥር ማድረግ ሲጀምር በፊት በነበረዉ ብዝበዛ አንጀቱ እያረረ ሲበግን የነበረዉ ህዝባችን የመንግስትን ቆራጥ እርምጃ መዉሰድ በእጅጉ ያስፈነደቀዉ ቢሆንም ያን ተከትሎ ሌላ መዘዝ ሊከተል እንደሚችል ስጋታቸዉንና ጥርጣሬአቸዉን ሲገልጹ የነበሩ አልጠፉም፡፡

መንግስታችን የኤርትራን ብዝበዛ የሚያስቀር ቆራጥ እርምጃ ሲወስድ (የራሱን አሳልፎ ላለመስጠት) ኤርትራ የለመደችዉ ጥቅም ሲቀርባት ሊያስኮርፋትና ሊያስቆጣት እንደሚችል ለመረዳት አያዳግትም፡፡ መንግስታችን ሻዕቢያን በማበሳጨቱና በማስቆጣቱ የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስትን አደነቀ እንጂ ለምን ሻዕቢያን አስቆጣህብን ቢሎ አልወቀሰዉም፡፡ ነገር ግን የመንግስት እርምጃ ሻዕቢያን ማስቆጣት መቻሉ ብቻ ሳይሆን ዝርፊያዉ የኤርትራ ዋነኛዉ የገቢ ምንጫቸዉን የሚያደርቅባቸዉ በመሆኑ ዝም ብለዉ ያያሉ ብሎ ማሰቡ ነዉ ትልቁ ስህተት፡፡

የኢኮኖሚ ጥቅም ከድንበር ግጭት የበለጠ የጦርነት ቀስቃሽ እንደሆነ መንግስት በሚገባ ይረዳል፡፡ መንግስታችንም የጦርነቱ መንስኤ የድንበር ጥያቄ ሳይሆን የኢኮኖሚ ጥገኝነት ነዉ ሲልም በተደጋጋሚ ሰምተናል፡፡ አሜሪካም ሆነ ሌሎች አገሮች በብዙ ሺህ ማይሎች ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ጦርነት ዉስጥ ዘለዉ የሚገቡት የድንበር ወይም የወሰን ጉዳይ ሆኖባቸዉ ሳይሆን  የኢኮኖሚ ጥቅማቸዉ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ለመከላከል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ስለዚህ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የዚህ ዓይነት ቆራጥ ዉሳኔ ለመዉሰድ ሲያቅድ ያን ተከትሎ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል ተረድቶ አስቀድሞ የመከላከያ ሰራዊቱን የዝግጁነት ደረጃዉ ከፍ የሚያደርጉ ስራዎችን እንዲሰሩ ከማድረግ በተጨማሪ በኤርትራ አዋሳኝ ድንበር ላይ ወይም በቅርብ ርቀት የተወሰነ መልስ ሰጪ ሊሆን የሚችል የተጠናከረ ኃይል ማስፈር ይገባዉ ነበር፡፡ መንግስት ግን ይህን አላደረገም፡፡ ከወትሮዉ የተለየ አንዳችም የጥንቃቄ እርምጃም አልወሰደም፡፡

ሌላዉ ቀርቶ መንግስት በኤርትራ ላይ የዚህ ዓይነት የኢኮኖሚ ቁጥጥር እርምጃ ስለመዉሰዱም በሰራዊቱም ሆነ በህዝቡ ዘንድ የሚታወቅ ነገርም አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ ከሻዕቢያ ጋር አድርጎት ስለነበረዉ  የንግድ ስምምነት በድርጅት ደረጃ ካልሆነ በስተቀር ህዝብን በሚወክለዉ ፓርላማ ደረጃ የተወሰነም የሚታወቅም ስለማይመስለኝ ነዉ፡፡ በኤርትራ ላይ ቁጥጥር ማድረግ ሲጀመርም አሁንም ጉዳዩ በገዢዉ ፓርቲ አመራሮች ደረጃ ካልሆነ በስተቀር እንደ መንግስት በህግ አዉጭዉም ሆነ በአስፈጻሚዉ ካቢኔ ምክር ቤት ደረጃ ምክከር ተደርጎበት የተወሰነ ነገር አይመስለኝም፡፡

ኢህአደግ የኤርትራን ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የሚመለከተዉ የጋራ አጀንዳ አድርጎ ሳይሆን የሁለት ግንባሮች ጉዳይ ብቻ አድርጎ በመቁጠሩ የተፈጠረ ችግር ይመስለኛል፡፡ አስመራና አዲስ አባበ እየተመላለሱ በኢትዮጵያ ስም ድርድር ሲያደርጉ የነበሩት የመንግስት ባለስልጣናት ሳይሆኑ የፓርቲዉ አመራሮች ነበሩ፡፡ በዚህ ረገድ የኢህአዴግ (መንግስት) ሶስት ስህተቶችን እንደፈጸመ መገመት ይቻላል፡፡

አንደኛ ከኤርትራ ጋር ተመስርቶ የነበረዉ ግኑኝነት ዝርዝር ጉዳይ ህዝብ እንዲያዉቅ አላደረገም፡፡ በህግ አዉጭዉም ቀርቦ የተመካከሩበትና የተወሰነበት አይመስለኝም፡፡ ሁለተኛ ይሄዉ ግኑኝነት ሲቋረጥም አሁንም ለህዝቡ አንዳችም ነገር አልነገረም፡፡ ሶስተኛ የኢህአዴግን እርምጃ ተከትሎ በኤርትራ በኩል ሊኖር ስለሚችለዉ ግብረ መልስ (reaction) በሚገባ ታስቦበት ለምናልባቱ ተብሎ እንኳን መከላከያ ሰራዊታችን ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርገን አለመዘጋጀታችን እንደ ድክመት መቁጠር የሚገባን እንጂ ድንገተኛ ነዉ የሚያሰኝ አይሆንም፡፡

6.3/ከጦርነቱበፊትኤርትራስታደርግየነበረዉወታደራዊዝግጅቶችጦርነትሊኖርእንደሚችልከበቂበላይአመላካችነበሩ  

የሻዕቢያን ለወረራ መዘጋጀት ከጥርጣሬም በላይ እንድናምን የሚያደርገን ሻዕቢያ ሲያደርጋቸዉ የነበሩ ወታደራዊ ዝግጅቶች ናቸዉ፡፡  እነዚህ ዝግጅቶች ማንኛዉም አገር ለጦርነት ሲዘጋጅ  የግድ መፈጸም የሚገባዉ ተግባራት እንደሆኑ ስለሚታወቅ ሻዕቢያም ለጦርነት እየተዘጋጀ እንደነበር ከበቂ በላይ አመላካችና ፍንጭ ሰጪ ናቸዉ፡፡  እሰኪ አንዳንዶቹን አለፍ አለፍ እያልን እንመልከት፤

* ሻዕቢያ ደርግ እንደወደቀ በእጁ ከነበረዉ 85 ሺህ የሚገመት የሰዉ ኃይል ዉስጥ አብዛኛዉን ሰራዊት ቀንሶ ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሱ እርግጥ ነዉ፡፡ ሻዕቢያ ደርግ ከወደቀ በኋላ ከ27 ሺህ የማይበልጥ ሰዉ ኃይል ብቻ ይዞ ነዉ እንደመንግስት የቀጠለዉ፡፡ በዚህ እርምጃዉ ሻዕቢያን ለልማት የቆረጠ አስመስሎት ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ በጀመረዉ የብሄራዊ ዉትድርና የግዴታ አገልግሎት አስከ ሰባት ዙር ድረስ አሰልጥኖ ከ117 ሺህ የማያንስ የሠዉ ኃይል ሲያዘጋጅ እንደዋዛ እየሰማን ዝም አልን፡፡ ያን ያህል ወታደር አሰልጥኖ ሲያስመርቅ ሻዕቢያ ከእኛ ለመደበቅ ያደረገዉ ሙከራ አልነበረም፡፡ ሁሉን ነገር በይፋ ነዉ ያደረገዉ፡፡

ስለዚህ ኤርትራ ሰፊ የሠራዊት ዝግጅት እያደረገች መሆኑን መንግስታችን በሚገባ ያዉቅ ነበር ማለት ነዉ፡፡ መጀመሪዉኑ ሃያ ሰባት ሺህ ወታደር ኤርትራን ለምታክል ትንሽ አገር ከሚገባዉ በላይ ብዙ ነዉ፡፡ ኤርትራ እጅግ ደካማ በሆነ ኢኮኖሚያዋ ለዚያዉም አንዳችም የዉጭ ወረራ ስጋት በሌለበት ሁኔታ ያን ያህል ሰራዊት ለኤርትራ እጅግ ብዙ ነበር፡፡ ነገር ግን በጥቂት ዓመታት ዉስጥ ከአምስት እጥፍ በላይ አሰልጥና በይፋ ስታስመርቅ ያለምክንያት እንዳልሆነ መጠራጠር ይገባን ነበር፡፡ ኤርትራ ሰራዊቷን በፊት ከነበረዉ 27 ሺህ ወደ ሩብ ሚሊዮን ከፍ ስታዳርግ ምን አስበዉና ለምን እንደዚያ እንደሚያደርጉ መጠርጠር ይገባን ነበር፡፡

* የኤርትራ የጦርነት ዝግጅት የሰራዊቷን ቁጥር በመሳደግ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ለጦርነት እስፈላጊ የሆነ የዉጊያ አስተሳሰብ ለዉጥ ማድረግንም ጭምር የሚያካትት ነበር፡፡ በዚሁም መሰረት ኤርትራ ሰራዊቷን በፊት ከነበረዉ የጉሬላ (guerilla) ቁመና አላቃ ወደ መደበኛ ሰራዊትነት ቀይራ ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠናና ልምምዶችን ሲታደርግ ቆይታለች፡፡ ከዚያ በኋላም ወታደራዊ አቅሟን በተግባር ለመፈተሽ እዚህም እዚያም የጎረቤት አገሮች ላይ ትንኮሳ በማድረግ እንደ ወታደራዊ ልምምድ (military exercise)ና እንደ ኢላማ መለማመጃ ወረዳ ስትጠቀምበት ነበር፡፡

በዚህም መሰረትም ኤርትራ ከሱዳን፤ ከጂቡቲና ከየመን ጋር በተለያዩ ጊዜያት በራሷ ተንኳሽነት ሲታደረግ የቆየችዉን ግጭቶች የዚህ ማሳያ ናቸዉ፡፡ ኤርትራ ከነዚህ አገሮች ጋር ሲታደርግ የነበረዉን ግጭቶችና የገባችበትን ቅራኔዎች  ለተከታተለ ለማንኛዉም ሃላፊነት ለሚሰማዉ ዜጋም ሆነ ባለስልጣን ቀጣዩ ኢላማ እኛ ልንሆን እንደምንችል ለመገመት ባላዳገተዉ ነበር፡፡ ነገር ግን በእኛ በኩል ለጥንቃቄ ያህል እንኳን ያደረግነዉ እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ ልክ እንደማያሳስበን ሆነን የኤርትራና የየመን ዉዝግብ በሚዲያዎቻችን ቀዳሚ ዜና አድርገን ከማቅረብ ባለፈ ለመጠርጠር እንኳን አልሞከርንም፡፡

* ኤርትራ በኛ ላይ ጦርነት ከመክፈቷ ትንሽ ቀደም አድርጋና  ጦርነቱን ለመጀመር የመጨረሻዉ የዥግጅት ምእራፍ ላይ እንደደረሰች የሁለት ዓመቱን የብሄራዊ ዉትድርና የግዴታ አገልግሎት ጨርሰዉ ወደ ሰላማዊ ህይወት የተመለሱትን በሙሉ ድጋሚ ጥሪ በማድረግ በአንድ ቦታ አሰባስባ ለሚሰጣቸዉ ግዳጅ እንዲጠባበቁ አድርጋለች፡፡ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም አታስፈልጉም ተብለዉ ከሰራዊቱ የተቀነሱ በርካታ ነባር ታጋዮችንና ሚሊሻዎችን ጥሪ ተደርጎላቸዉ ወደ ካምፕ እንዲከቱ ተደርገዋል፡፡ የዚህ ዓይነት “ክተት ሰራዊት” ሲደረግ በኛ በኩል በሚገባ ይታወቅ  ነበር፡፡

* ኤርትራ በዚህ ዓይነት የኃይል ማሰባሰብ በማድረግ ሃያ ሰባት ሺህ (27,000) የሰዉ ኃይል የነበራትን ባጭር ጊዜ ዘጠኝ እጥፍ አድርጋ ወደ ሩብ ሚሊዮን አካባቢ (232,000) አደረሰችዉ፡፡ ሻዕቢያ ያን ያህል ሰራዊት ማሰባሰቧ ብቻዉን ለጦርነት እየተዘጋጀች እንደነበር የሚያመላክት ነበር፡፡

* ሻዕቢያ ሌሎች ዝግጅቶችንም አጠናክሮ መስራት የጀመረዉ ከጦርነቱ ሰባት ወራት አስቀድሞ ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት ለጦርነቱ ብቁ የሚያደርጉ ጠንከር ያሉ ስልጠናዎችን በስፋት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ቴክኒካዊ አቅማቸዉን ለማሳደግ የጥገና ስራ በስፋት ሰርተዋል፡፡ ለጦርነት የሚያስፈልጋቸዉንንና የሚጎላቸዉን ትጥቅ አቅም በፈቀደ ከዉጭ ሸምተዋል፡፡ ስለኢትዮጵያ ወታደራዊ አቋም የተሟላ መረጃ ለማግኘትም እንዲያስችላቸዉም በድንበር አካባቢ ባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰፊ የስለላ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

* ከዚህም በላይ ከወረራዉ አንደ ወር በፊት መከላከያ ሚኒስትራቸዉ ከፍተኛ የጦር አዛዦቻቸዉን ሰብስበዉ ሊጀመር አንድ ወር ብቻ ለቀረዉ ጦርነት የመጨረሻዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ለአዛዦች ዝግጀት እንዲያደርጉ መመሪያ ሲሰጣቸዉም ጦርነቱ ከማን ጋር እንደሆነ ለምስጥራዊነቱ ሲባል በግልጽ ባይነግሩአቸዉም አዛዞቹም ሆኑ የሰራዊቱ አባላት ባልተለመደ ሁኔታ ያን ያህል ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ያስፈለገዉ ለየመን ፤ለጂቡቲ ወይንም ከሱዳን ጋር ለሚደረግ  ጦርነት ሳይሆን  ይልቁንም ከኢትዮጵያ ጋር ሊሆን እንደሚችል አልጠረጠሩም ማለት አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጁ መሆኑን ጦርነት የተደገሰለት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያለጊዜዉ እንዳያዉቁ ለማድረግ የሻዕቢያ መሪዎች ጥንቃቄ ማድረጋቸዉ ባይቀርም ነገር ግን ያን ሁሉ መጠነ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል አንዳችም ጥርጣሬ አለማድረጉ ኢሳይያስን ሳያስገርማቸዉ የቀረ አይመስለኝም፡፡

* የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መጀመር ይፋ ከመሆኑ በፊት የኤርትራ ታጣቂዎች ወደ ትግራይ መሬት እየገቡ የነዋሪውን ሀብትና ንብረት መዝረፍ ብቻ ሳይሆን በኤርትራ ላይ ጥላቻ አላቸዉ ተብለዉ የተገመቱ የአካባቢዉን ሰዎችም ጭምር እያፈኑ በመውሰድ ሲገድሉ  በነበረበት ጊዜ የትግራይ ህዝብ ሁኔታዉ ስላላማረዉ ሻዕቢያ ለጦርነት እየተዘጋጀ  ስለሆነ አንድ ነገር አድርጉ እያለ ለባለስልጣናቱ ሪፖርት ሲያደርግና ሲያስጠነቅቅ ባለስልጣናቱ ግን “ሻዕቢያ በጭራሽ አይወራችሁም”  በሚል የሕዝቡን አቤቱታና ጥቆማ ሲያጣጥሉ እንደነበር በጦርነቱ ወቅትና በኋላም በስፋት ሲነገር ነበር፡፡

ከዚህም ሌላ ከወረራዉ ሶስት ወራት አስቀድሞ በገዥዉ ፓርቲ አመራሮች በተለይም በህወኃት ስራ አስፈጻሚ ደረጃ ኤርትራ ለጦርነት ዝግጅት እያደረገች ነዉ የሚል ሀሳብ በስብሰባ ላይ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም “ኤርትራ ካላበደች በስተቀር አታደርገዉም” በሚል ሃሳቡ ዉድቅ እንደተደረገ ተሰምቷል፡፡ በወቅቱ በአስመራ ተመድቦ የነበረዉ አመባሳደራችን አቶ ሃዉአሎም ወልዶ (የአቶ አባይ ወልዱ ወንድም) ኤርትራ እያደረገች ስለነበረዉ የጦርነት ዝግጅት በጭራሽ አላውቅም ነበር ብለዉ እንደማይናገሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ኤርትራዉያን ከጠበቁት በላይ መዘናጋታችንን ከተረዱ በኋላ አንዳችም ዝግጅት ሳናደርግ በድንገት ወረራ ፈጸሙብን፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ጭብጦች መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን የጦርነት ዝግጅት ለማወቅ የማይሳነዉ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ይብዛም ይነስም መረጃዉ እንደነበረዉ ነገር ግን ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንደተሳነዉ ለመረዳት አያዳግትም፡፡ ምናልባት የኤርትራ መንግስት ከጦርነቱ በፊት ሲያደርግ የቆየዉን ሰፋፊ የጦርነት ዝግጅቶች ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰወሩና የመረጃ ሰዎቻችንም ጭራሽ ያልደረሱበት ምስጢር ከነበረ በመረጃ ተቋሙ አመራሮች አካባቢ ድክመት እንደነበረ መቀበል ይገባል፡፡

መንግስት ስለሻዕቢያ  የጦርነት ዝግጅት በቂ መረጃ እያለዉ ነገር ግን መረጃዉን በመጠራጠር ወይም ሻእቢያዎች አብደዉ ካልሆነ በስተቀር አያደርጉትም የሚል አቋም ይዞ ከነበረም መንግስት የግምገማ ችግር እንደነበረበት አምኖና በዝግጅት ማነስ ለጠፋዉ ህይወትና ንብረት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ለወደፊቱ ትልቅ ትምርት እንዲሆን ማድረግ ያለበት ይመስለኛል፡፡

የብዙ ሀገሮችን የጦርነት ታሪክ ስንዳስስ ከተጠቀሰዉ ከኛ ሁኔታ ጋር በእጅጉ ተመሳሳይ የሆነ ችግሮችን እናገኛለን፡፡  የብዙ ሀገራት መሪዎች በሀገራቸዉ ላይ የዉጭ ወረራ እንደታሰበ የሚገልጹ አስተማማኝ መረጃዎች እየተሰጣቸዉም ቢሆን  መረጃዉን በማጣጣልና ችላ በማለት  አንዳችም ዝግጅት ሳያደርጉ ለጥቃት ሲጋለጡ እንደነበር በብዛት ተጽፎ አንብበናል፡፡

ለመሪዎች መዘናጋትና መረጃዎችን ችላ ማለት ዋነኛ ተጠቃሽ ምክንያቶች ዉስጥ፤ በወራሪ አገር መሪዎች በሚገቡላቸዉ ቃል በመታለል አስመሳይና አዘናጊ የሆኑ ዉሎች ላይ አጉል መተማመን፤ የራስን መረጃ ተቋም በማናነቅ ትክክለኛ መረጃዎች ላይ አለመተማመንና መረጃዉን በደንብ ሳያገናዝቡ ማጣጣል እንዲሁም  አርቆ ማሰብና ማመዛዘን በተሳናቸዉ “የቅርብ አማካሪ” በሚባሉ ጥቂት የአመራሩ የቅርብ ሰዎች ሃሳብ መጠለፍ ናቸዉ፡፡

ምናልባት ይህን ሃሳብ ለማጠናከር ሁለት አብነቶችን ቀጥዬ አቀርባለሁ፡፡ አንደኛዉ በ2ኛዉ የአለም ጦርነት ወቅት የናዚ ሰራዊት በሶብዬት ህብረት ላይ የሰነዘረዉን ጥቃት የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በባህረ ሰላጤዉ ጦርነት የኢራቁ ሳዳም ሁሴን ኩዌትን የወረረበትን ጦርነት የሚመለከት ነዉ፡፡

ሀ. የናዚ ወረራ

 በ2ኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ሰራዊት ሶቭየት ህብረትን የወረረዉ በድንገትና ሳይጠበቅ ሳይሆን ለወረራ እየተዘጋጀ መሆኑ ከበቂ በላይ መረጃ በነበረበት ሁኔታ ነበር፡፡ ሂትሌር ሶቭየትን ለመዉረር እንዳሰበ የሶቭየት የመረጃ ሰዎች ለጥቃት የተመረጠዉን አቅጣጫና መቼ ጥቃቱን ለመሰንዘር እንደታሰበ ሳይቀር ለሶቭየቱ መሪ ስታሊን በተደጋጋሚ መረጃ ቢያቀብሉም መረጃዉን በማጣጣልና ከራሱ ሰዎች ይልቅ ሂትለርን በማመን ያለአንዳች ዝግጅት ተዘናግተዉ ቆዩ፡፡

ስታሊን ከሂትለር ጋር አድርጎት የነበረዉን ምስጢራዊ ስምምነት በመተማመን አንዳችም ዝግጅት ሳይደረግ  በመቆየቱ ሀገሪቱ ለናዚ ሰራዊት ጥቃት ክፉኛ ተጋለጠች፡፡ የናዚ ጀርመን ሰራዊትም ልክ እንደታሰበዉና የመረጃ ሰዎች እቀድመዉ በገመቱት አቅጣጫና ቀን ማጥቃት ሰነዘረ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ ጥቃት መሰንዘሩ ከታወቀም በኋላ እንኳን አንዳችም የአጸፋ እርምጃ እንዳይወስዱ ስታሊን መከልከሉ ነዉ፡፡

የስታሊን ግምት ከጦርነቱ በፊት ከሂትለር ጋር ያደረገዉ አንዱ ሌላዉን ያለመዉጋት ምስጥራዊ ስምምነት (Hitler-Stalin non agration pact) በመተማመን በሂትለር ቃል ተሸዉዶ ሲሆን ዝግጅት እንዳይደረግ የከለከለዉ ደግሞ ሁኔታዉን በጣም አቅልሎ በማዬትና የእለት ግጭት እንጂ ጦርነት ስላልሆነ አላስፈላጊ ከሆነ የጠብ አጫርነት ድርጊት ተቆጠቡ እያለ አዛዦቹን ይገስጽ ነበር፡፡ ስታሊን ከራሱ ሰዎች ይልቅ ለወረራ የተዘጋጀዉን ጠላቱን ሂትለርን በማመኑ ከሃያ ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎቹን ህይወት አስከፍሎታል፡፡

ስታሊን ከራሱ መረጃ ሰዎች ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከነበሩት ፍራንክሊን ሩዝበልት ሳይቀሩ ሂትለር ፈረንሳይን ከወረረ በኋላ ቀጥሎ ሶቭየትን ለመዉረር እቅድ እንዳለዉ ለስታሊን በምስጢር አሰጠንቅቀዉት ነበር፡፡ የተባለዉም አልቀረም ጁን 22 ፡1941 ዓ/ም ሂትለር በዓለም የጦርነት ታሪክ በግዙፍነቱ ተወዳዳሪ የለለዉን በሚሊዮን የሚቆጠር ኃይል አሰልፎ ሶቭዬት ህብረትን ወረረ፡፡ ከጦርነቱ  ቀደም ብሎ ማለትም በ1937 እና በ1938 ላይ ስታሊን “ግሳንግሱን ሁሉ ማጽዳት” (purge) በሚል በሚታወቀዉ የጭፍጨፋ ዘመቻ በርካታ የሀገሪቱን ከፍተኛ የጦር አዛዦችን ያለምንም ምክንያት በማስገደሉና ወደ ሳይቤሪያ በግዞት በመላኩ ጦር ኃይሉ ያለ አመራር በመቅረቱ እጅግ ተዳክሞ በነበረት ሰዓት ነዉ ወረራዉ የተጀመረዉ፡፡

በወቅቱ ሂትለር የስታሊንን መዘናጋት በመጠቀም በርካታ ሰራዊት በሶቭዬት ህብረት ድንበር አካባቢ ማከማችት ከመቻሉም ሌላ የጀርመን አይሮፕላኖችም የሶቭየት የአየር ክልል ጥሰዉ በመግባት እንዳሻቸዉ የአየር ቅኝት እያደረጉ መሆናቸዉ ሪፖርት እየተደረገለትም ሂትለር የሚሰጠዉን የሃሰት ምክንያት እየሰማና የራሱን መረጃ ሰዎች ችላ በማለት ሀገሩን ለጥቃት አጋለጠ፡፡ ሂትለር “operation Barbarossa” ዘመቻ ባርባሮሳ የሚል ስያሜ በተሰጠዉ ዘመቻ በሶቭየት ድንበር በኩል ከሶስት ሚሊዮን የሚበልጡ ወታደሮችን  አሰልፎ ጥቃት ሰነዘረ፡፡

ስታሊን ቢያንስ መረጃዉ ከደረሰዉ ጊዜ ጀምሮ  በቂ ዝግጅት አድርጎ ቢሆን ኖሮ ያን ያህል ጉዳት በህዝቡ ላይ ባልደረሰ ነበር፡፡ የሶቭየት መንግስት ዝግጅት ላለማድረጉና ለመዛናጋቱ ማሳያ የሚሆነዉ በወረራዉ የመጀመሪያ ሳምነት ብቻ 150000 በላይ የሶቭየት ህብረት ወታደሮች ማለቃቸዉና  ሉፍትወፍ (Luftwaffe) በተሰኘዉ የሂትለር አየር ኃይል  በሁለት ቀን ብቻ በቁጥር ከ2000 የሚበልጡ  የሶቭየት ህብረትን የጦር አይሮፕላኖችን  ገና መሬት ላይ እያሉ መዉደማቸዉ ነዉ፡፡ ሂትለር የንቀቱ ንቀት ሶቭየት ህብረትን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ስምንት ሳምንታት ብቻ ነበር የመደበዉ፡፡

በወቅቱ ብዙዎቹ የዉጭ ታዛቢዎች  ሁኔታዉን በመገምገም መላዋ ሶቭየት ህብረት በጥቂት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ በጀርመን ቁጥጥር ስር እንደምትሆን ገምተዉ ነበር፡፡ ጀርመኖች በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያን ሁሉ ሰፊ የሶቭየት ህብረትን ግዛት አቆራርጠዉ ሌንንግራድ (ፒተርስበርግ)ና ከዋና ከተማዋ  ከሞስኮም  በ25ኪ/ሜ ርቀት ላይ ለመድረስ ችለዉ ነበር፡ስታሊን ዘግይቶም ቢሆን  በኋላ ላይ ስህተቱን አርሞ  በጠቅላይ አዛዥነቱ  የሚደነቅ አመራር በመስጠቱ የጀርመንን ናዚ ሰራዊትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ከሶቭየት ህብረት ግዛት በማስወጣት ብቻ ሳይገደብ ምስራቃዊዉን የጀርመን ግዛት ዋና ከተማዉን በርሊን በቁጥጥሩ ስር በማድረግና መላዉን የምስራቅ አዉሮፓን አገሮችን ነጻ በማዉጣት ታሪክ የማይረሳዉ ታላቅ ስራ ስርቷል፡፡

በዚህም በሀገሩ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በምእራቡም ጭምር ታላቅ አድናቆት ተችሮታል፡፡ ይሁን እንጂ ስታሊን ስለ ናዚ የጦርነት ዝግጅት በግልጽ አየተነገረዉ ችላ በማለቱ ሂትለርን ለወራራ እንዳያስብ የማድረግ እድሉን ባለመጠቀሙ  በሀገሩ ላይ ለደረሰዉ መጠነ ሰፊ ጉዳት ጦርነቱ ካለፈ ከሰባ ዓመታት በኋላም አስካሁንም  ከመወቀስ አልዳነም፡፡

ለ. የሳዳም ሁሴን የኩዌት ወረራ

ሌላዉ አብነት በመጀመሪያዉ የባህረ ሰላጤዉ ጦርነት ወቅት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቡሽ (ትልቁ) በወቅቱ የእራቁ ሳዳም ሁሴን የአሜሪካ ወዳጅ የነበረችዉን ኩዌትን ለመዉረር እየተዘጋጀ መሆኑን መረጃዉ በተደጋጋሚ ቢቀርብላቸዉም የፕሬዝዳንቱ የቅርብ አማካሪዎች መረጃዉን በማጣጣላቸዉ ፕሬዝደንቱ አንዳችም እርምጃ ባለመዉሰዳቸዉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሳዳም ሁሴን ጦር ኩዌትን ሙሉ በሙሉ በወረራ ተቆጣጠራት፡፡ ፕሬዝዳንቱ በደረሳቸዉ አስተማማኝ መረጃ መሰረት ተገቢዉን የዲቴረንስ እርምጃ አስቀድመዉ ወስደዉ ቢሆን ኖሮ ሳዳም የጥቃት ዉጥናቸዉን በሰረዙ ነበር፡፡ ያ ሁሉ ግርግርና ትርምስም ባልተፈጠረ ነበር፡፡

በዚህ አጋጣሚ የመሪዎች አማካሪዎች የሚባሉ ሰዎች ጉዳይ አጠያያቂ ነዉ፡፡ ምንድነዉ የሚያማክሩት?ስራቸዉ መልካም ነገር ማማከር ሳይሆን ማሳሳት የሆነ ይመስላል፡፡ አስቀድሜ ባነሳሁት ታሪክ ቡሽን አሳስተዉ እርምጃ እንዳይወስዱ  አደረጉት፡፡  ከጥቂት ጊዜ በኋላ በትንሹ ቡሽ ጊዜ ደግሞ የሌለዉን ነገር እንዳለ በማድረግ ኢራቅ የኑክሌር መሳሪያ አላት በሚል የተሳሳተ መረጃ አቅርበዉ  በቀሰቀሱት ጦርነት ጦስ እነሆ ኢራቅ መሪዋን ሳዳምን ማጣት ብቻ ሳይሆን  አገሪቷም ራሷ ተንኮታኮተች፡፡ በኛም ሁኔታ መለስን በማሳሳት በኤርትራ ጉዳይ ያዘናጉት የቅርብ ሰዎቻቸዉ እንደሆኑ እንገምታለን፡፡

7/ማጠቃለያ

የኤርትራ ጥቃት በመንግስት ብቻ ሳይሆን በህዝቡም ቢሆን ፈጽሞ ያልተጠበቃና ይሆናል ተብሎም ያልተገመተ ነዉ፡፡ የወረራዉ ድንገተኛነት እንዳለ ሆኖ በኛ በኩል እንደ መንግስት ማድረግ የሚገባንን ተገቢዉን ጥንቃቄ ባለማድረጋችን ለኤርትራ ጥቃት ሰለባ ለመሆን ችለናል፡፡ መንግስት የኤርትራን አመራሮች ባህሪይ በሚገባ እያወቀና ኤርትራ ከሁሉም አጎራባች ሀገሮች ጋር አንድ በአንድ ጦር ስትማዘዝ እያየ ይሄ ነገር ነገ ተራዉ ለኛ ነዉ ብሎ አለመጠንቀቁ እንደ መንግስት ጥፋተኛ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

ከዚያ ዉጭ ግን መንግስት ከኤርትራ ጋር መልካም ጉርብትና መመስረቱና መረዳዳቱ እንደጥፋት ሊቆጠር የሚገባዉ አይደለም፡፡ የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት በሚመለከትም ለዘለቀታዉ ለስተራቴጂክ ደረጃ ለሚገመት ጠላት አነስ ብሎ በግዳጅ አፈጻጸሙ ጠንካራ የሆነ ሰራዊት ለመገንባት ጥረት እያደረገ ስለነበረ ”የሀገሪቱን መከላከያ  ሰራዊት አፍርሶ ለጥቃት አጋልጦ ወዘተ “የመሳሰሉት ትችቶች ተገቢነት የለላቸዉና የመንግስትን ባህሪይ የማይገልጹ ናቸዉ፡፡

******

የዚህን ፅሁፍ ምንጭ HornAffairs.com

 

The post የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ክፍል 1, 2, 3 | በየዘመኑ የነበሩ መሪዎቻችን የኤርትራን ጉዳይ ያስተናገዱበት አግባብና ሲከተሉት የነበረዉ ፖሊሲ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ወትሮም ያለ ነው ከጥንት- ሎሌ መጮሁ ከጌታው ፊት – በይገረም አለሙ

$
0
0

ይህ ዋዛና ፈዛዛ ያናፈዘው ትውልድ ደግሞ ከንቱ ነገሮችን ሁሉ ሳይመረምር ይቀበላል፡፡ ብዙዎች የዚህ ትውልድ አባል በመሆናቸው ደስተኛ አይደሉም፡፡ ህሊናውን በሜዞ የሚሸጥ፣በኩርማን እንጀራ የሚሸነግል በፍርፋሪ የሚደልል ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ ይህን ትውልድ ያለ ግብሩ ግብር ያለ ጠባዩ ጠባይ ሰጥተው የፈጠሩት ፖለቲከኞችና አንዳንድ አድርባዮች እንደፈለጉት እየነዱት ይገኛሉ፡፡ፍጡሩም ፈጣሪውን መስሏል፡፡ (ራማቶሓራ  ገጽ 80)

……………//……………..

የሰው ልጅ ለመሰሉ ሎሌ ሆኖ የሚያድርበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ ፣የሎሌነት ሁኔታውም እንደ ምክንያቱ ይለያያል፡፡ባለሥልጣን ሆኖ ለባለሥልጣን ሎሌ የሚሆን ነበረ አለ ወደፊትም ይኖራል፤አሁንማ ነገር ብሶ ውርደት ተባባብሶ ጠቅላይ ምኒስትርም ተኩኖ በሎሌነት መኖርን እያየን ነው፡፡ አማራጭ አጥቶ፣ ልኑር ብሎ ተቸግሮ በሎሌነት የሚያድረው እሱ ቀን ሲወጣለት ሁኔታዎች ሲመቻቹለት ወደ እራሱ የሚመለስ በመሆኑ ጌታው ሲያስነጥሰው መሀረብ ለማቅረብ አይዳዳውም፣ከሎሌዎቹ በላይ ሎሌ ለመሆን እዩኝ እዩኝ አይልም፣ማደሪያ ስራውን ያውቃል ያንን ተጠንቅቆ ይሰራል፡፡

በተቃራኒው በራሱ መኖር እየቻለ ወይ ተፈጥሮ ሆኖበት ወይንም በሎሌነት አገኘዋለሁ ብሎ የሚያስበው ጥቅም ልቆ ታይቶት በሎሌነት ያደረ ግን ከሎሌዎቹ በላይ ልቆ በመታየት የጌታውን ጎሽታ ለማግኘት፣ እንዲያም ሲል በግብርዎም በወንበርዎም አይርሱኝ ለማለት የማይሆነው ነገር የማይፈጽመው ድርጊት አይኖርም፡፡

ታዲያ እንዲህ አይነቱ ክብረ ቢስ ተፈጥሮ የበደለችው ሰው  ሲያጋጥመው   የሀገሬ ሰው “ እሱም አይደል ልቡ ነው እውሩ፣ ጥንድ በሬ እያለው ለጌታ ማደሩ” ይለዋል ይልለታል፡፡ ልብ ከታወረ ሊሆን የሚችለውን አስቡት፡፡ በወያኔም ሆነ በተቀዋሚው  ሰፈር የዚህ አይነት ብዙ ሰዎችን እናያለን እንሰማለን፡፡ አንዳንዶች  “እኔው በገዛ እጄ እያልኩ ወረደ ወረድ እመቤቱን ልቤን አደረኩት ገረድ” እንዳለችው ሴትዮ ከውርደቱ ሰፈር፣ ከሎሌነት አደሩ ምግባር በመገኘታቸው ልባቸው ምነው አለ ቦታየ ብሎ ሲጠይቃቸው፣ ህሊናቸው ሲጸየፋቸው ውርደቱ ተስምቶአቸው በግዜ ከሎሌነት ራሳቸውን በማላቀቅ የቻሉት በንስሀ ታጥበው፣ በይቅርታ ከህዝብ ታርቀው በአደባባይ በኩራት ሲሄዱ እያየናቸው ሲናገሩ እየሰማናቸው ነው፡፡ ለንሰሀውም ሆነ ለይቅርታው ያልበቁት ወይንም ለዚህ ወኔ ያጡት ደግሞ አንገታቸውን ደፍተው ድምጻቸውን አጥፍተው ይኖራሉ፡፡ በሎሌነት ላደረሱት ጥፋት ንስሀ ባይገቡም፣ በይቅርታ ከህዝብ ባይታረቁም ቢያንስ ከሎሌነት ተገላግለዋልና የተሟላም  ባይሆን ግማሽ እፎይታ ይሰማቸዋል፡፡

በተለይ ሥልጣን ፈልገው፣ ሳይወጡ ሳይወርዱ ላብ ሳያፈሱ መከበር ከጅለው፣ወይንም ዘር ቆጥረው ወዘተ ሎሌነት የሚገቡ ወይንም ለሎሌነት ደጅ የሚጠኑ ሰዎች ምግባራቸው ሲታይ ህሊና የሚባለውን ነገር አውልቀው የጣሉ ነው የሚመስለው፡፡ ጌቶቹን ያስደስታቸዋል በዚህም ትንሽ ሥልጣን ወይንም ትንሽ ዳረጎት አገኛለሁ ብለው ካሰቡ ከውሻ ብሰው ለንክሻ ይሰለፋሉ፤ከበቀቀን በልጠው የሰሙትን ሲደግሙ እንደውም አግንነውና አጉልተው ሲናገሩ ይውላሉ፣የጌቶች ጠላቶች ናቸው ያሉዋቸውን ወይንም ጌቶች ክፉ ፊት ሲያሳዩዋቸው ያዩትን ወይንም በጌቶች አፍ በክፉ የሚነሱትን ሰዎች ለመዝለፍ ለመስደብ ስም ለማጥፋት ይሉኝታ፣ ባህል ፣እምነት፣ ፈሪሀ እግዚአብሄር ወዘተ የሚባል ነገር አይገድባቸውም፡፡

በ1985/86 ዓም ነው ወያኔ ሰራተኛውን እየበተነ ሴፍቲኔት በሚባል ከየት መጣሽነቱ በማይታወቅ ሁኔታ እያደራጀ ሳለ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው  ከዚህ የተሻለ አማራጭ በማጣታችን በሁኔተዎች ተገደን የገባንበት ነው በማለት ይመልሳሉ( ከጊዜው ርዝመት አንጻር በትክክል አልጠቅሼ ይሆናል፣ ከዛ ወዲህ አቶ ታምራት አንኳዋን ስንቱን ሆነዋል)

በወቅቱ የትራንስፖርትና መገናኛ ኢንደሰትሪ ፌዴሪሽን የሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር የነበሩት ሰው ( ባልሳሳት መኮንን ኃለስላሴ ይመስለኛል ስማቸው) የአጠቃላዩ የኢሰማአኮ ፕሬዝዳንት ለመሆን በመመኘት ሎሌነታቸውን አሳምረው፣ ከፍላጎታቸው ለመድረስ የጀመሩት ተግባር ዙሪያ ገባውን ማየትም መስማትም ነስቷቸው አቶ ታምራት የተናገሩትን እንኳን ባለማገናዘብ ሴፍቲኔት ሰራተኛው ለአመታት ሲመኘውና በጉጉት ሲጠብቀው የነበረ ነው በማለት ተናገሩ፡፡ የሚያሳዝነው እንዲህ ቀለው የተመኙትን አለማግኘታቸው ነው፡፡

አንዳንዴ የፈጣሪ ስራ ይገርማል አግራሞታችን የአንድ ሳምንት፣ አስተውሎታችን ከወየው ጉድ አልፎ ለመማር የሚያበቃን አልሆነም እንጂ፡፡ እንዲያ ከጳጳሱ ቄሱ ይሉ አይነት ሆነወ ሰው ምን ይለኛል እንኳን ሳይሉ የቀላመዱ ሰው የተመኙትን ሳያገኙ ለቀላመዱት ንስሀ ሳይገቡ በአጭር ግዜ ወደ ዛኛው ዓለም ሄዱ፣ነብሳቸውን ይማር ይባል ይሆን!

በ1993 ዓ.ም የህውሀት ክፍፍል ወቅት ከሁለቱም ሰፈር በተለይ ሪፖርተር መጽሄትና ጋዜጣ ላይ ብዙ ይጻፍ ነበር፡፡አቶ መዝሙር ፈንቴ ከየትኛው ጎራ ሆነው እንደጻፉት ባልረዳም “ኢህአዴግ አዝማች ብቻ ሳይሆን ዘማችም የሚዘመትበትም ይሁን”  የሚል ርዕስ በሰጡት አንድ ጽሁፋቸው ውስጥ በፖለቲካው ሰፈር ያለውን ሎሌነት ቁልጭ እድርገው ነበር ያሳዩት፡፡

አንድ አንቀጽ ልጥቀስ፡፡ “በየስብሰባው ምላሳቸውን አርዘመው አድርባይነታቸውን የሚለፍፉ፣ ንጹሀንን አጥላልተውና አዋርደው ‹የታጋይነት ጥንካሬያቸውን› ሊያስመሰክሩ  የሚፈልጉ አፈ ጮሌዎች ታማኝና ጠንካራ ተደረገው ይቆጠራሉ፡፡ አለቆቻቸውን እንደ ጣኦት የሚያመልኩ፣ እንደ ፅላት የሚሳለሙ፣ የግል ጉዳያቸውን በተላላኪነት የሚያስፈጽሙ፣ የፖለቲካ ኩሊዎች ይሾማሉ፤ ይሸለማሉ፡፡ ለቅርብ አለቃ ማደግደግ፣ ወሬ ማቀበል፣ ጆሮ መጥባት፣ እንደ እጅ መንሻነት እየተቆጠረ ያሳድጋል ያስመነድጋል፣”ነበር ያሉት ፡፡ በዚህ መልኩ ያደገ የተመነደገ ሰው ዴሞክራሲን ሲያሰፍን የህግ የበላይነትን አክብሮ ሲያስከብር፣ ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዘብ ሲቆም ለእኩል የሀብት ተጠቃሚነት ሲጥር ይታያችሁ፡፡ በተቀዋሚው ጎራ ከሆነ ደግሞ ለነጻነት በጽናት ሲቆም፣ለለውጥ ከምር ሲታገል፣ ቃል የእምነት እዳ ሲሆንበት ይታያችሁ፡፡

በስልጣን ላይ ያሉ ጌቶችም ሆኑ የፓርቲ ወንበር የሚይዙ ሰዎችም የዋዛ አይደሉም፣ከፊት ወጥተውም ይሁን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዳሻቸው ያውም እንደ ሰው ሳይሆን በርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ እንደሚታዘዝ ሰው ሰራሽ ሰው የሚታዘዙ ሰዎችን አያጡም፡፡ዙሪያቸውን በሎሌዎች ይከበቡና መሬት ላይ ያለው እውነታ አይታያቸውም፡፡

ሎሌነት በተቀዋሚው መንደር ፣

በ2001 ዓ.ም ሊቀመንበሩን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በሁለተኛ ግዜ እስር ያጣው ገና በሁለት እግሩ መቆም ቀርቶ ዳዴ ማለት ያልጀመረው አንድነት መታመስ ሲጀምር አለመስማማቱን በውይይት ችግሩን በፓርቲው ህገ ደንብ ለመፍታት ሲሞከረር ወንበሩን በያዙት ሰዎች ዙሪያ ተኮልኩለው ያስቸገሩትን ሰዎች ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም  ሎሌዎች በማለታቸው በውስጥም በውጪም ያሉ ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ የሚለውን ብሂል የማያውቁ ላይ ላዩና ጋላቢዎች ብዙ ተንጫጭተው ነበር፡፡ ብዙም ውሎ ሳያድር  ሎሌ ከተባሉት አንዳንዶቹን በአካል አግኝቼአቸው ስናወጋ ያኔ የሚባለው ሁሉ አይታየንም፣ እውነትም አይመስለንም ነበር፣ለዚህም ነው እነ ፕ/ር መስፍንን እንደ ጠላት እናያቸው የነበረው፣ነገሩ የተገለጠልን ዘግይቶ ነገሮች ከተበላሹ በኋላ ነው ነበር ያሉኝ፡፡ እንደነገሩኝ ነፋስ አይንካቸው ሲሉዋቸው ለነበሩት ሰዎች ተቀዋሚ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡ይህን ያነሳሁት ስለ አንድነት ላወራ አይደለም፣ለማሳየነት እንጂ፡፡

ዛሬም እነዚህን መሰሎች የሚነገራቸውን ማገናዘብ፣ የሚያዩትን መረዳት የቸገራቸው ጌቶቻቸው የሚሉትን ብቻ እየተቀበሉ የሚያስተጋቡ አንዳንዴም ከጌቶቻቸው አብልጠው የሚጮሁ በተለያየ ቦታና አጋጣሚ እያየን እየሰማን ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ልጅ በአምሳሉ ፈጠረው ሲባል ወርድና ቁመት መልክና ሰውነት አመሳስሎ ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ቁመና ማን ያውቅና፡፡ ዋናው ቁም ነገር የሚያስብ አንስሳ አድርጎ ስለ ፈጠረው ይመስለኛል፡፡

ታዲያ የሰው ልጅ ወይ ስልጣን አማሎት ወይ ጥቅም ደልሎት ወይ የዘር ፍቅር አቆራኝቶት ይህን ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰውን የማስተዋል ችሮታ ወደ ጎን ብሎና ለሰው ልጅ በተለየ የተሰጠውን ህሊን አውልቆ ጥሎ ከእውነት ተጣልቶ በዚሁ ተግባሩ ሆዱን ሞልቶ ሲኖር እንደምን አለማዊ ደስታ ሊሰማው እንደሚችል የሚያውቀው የሆነው ብቻ ነው፡፡

በሎሌነት ያደሩ ሰዎች ለሚናገሩትም ሆነ ለሚጽፉት አይደለም ማስረጃ መረጃ ለማቅረብ እንኳን አይጨነቁም፡፣ከድርጊታቸው መረዳት እንደሚቻለው ዓላማቸውም ሆነ ግባቸው ጌቶቻቸውን ማስደሰትና የሚገኘውን ማግኘት የሚመኙትን መጠበቅ በመሆኑ ጌቶቻቸውን የሚያሞግሱ የሚያወድሱበትን ጠላት የሚሉትን የሚሰድቡ የሚዘልፉበትን ቃላት ከየት እንዲሚያመጡት ፈጣሪ ይወቀው፡፡ በሬ ወለደ ብለው ቢዋሹ ቅንጣት እፍረትም ሀፍረትም አይሰማቸውም፡፡በዚህ ደረጃ የተባሉ የተጻፉ ነገሮችን በማሳያነት ማቅርብ የእነርሱኑ ባህርይ መጋራት ይሆናልና ደግሞም ማህበራዊ መገናኛዎችን የሚከታተል ሁሉ የሚያውቀው ነውና አልሞክርም፡፡

እነዚህ ሰዎች በሎሌነት ያሳደራቸው ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን  ለጌቶቻውም ምን አልባት የድርጅት አባል ወይም ደጋፊም ከሆኑ ለድርጅቱም አይበጁም፡፡ ሰው መሻሻል የሚችለው ስህተቱን ሲረዳ ድክመቱን ሲያውቅ ነው፡፡ ድርጅትም እንደዚሁ፡፡ ሎሌዎች ግን ጌቶቻቸውን ማሞገስ የተለየ ሀሳብ የሚያነሳውን መዝለፍ መፈረጅ መወንጀል ስለሆነ ስራቸው ግለሰቡም ሆነ ድርጅቱ የሌለውን አለኝ፣ ያልሆነውን ነኝ እያለ ከእነ ስህተቱ አይደለም ከእነ ግዙፍ ድክመቱ ወደ ውድቀት እንዲጓዝ ነው የሚረዱት፡፡ሎሌነት አመላቸው ነውና የወደቀውን ሸኚተው የሞተውን በወጉም ባይሆን ቀብረው ሌላ ጌታ ማፈላለጉን ያውቁበታል፡፡ ለባለቤቱም በዙሪያው ላሉም ሳይታወቅ ለሚጠናወተወና መፍትሄ ለሌለው የአንባገነንነት በሽታ እየተዳረጉ ለብዙ ሲታሰቡ በአጭር የተቀጩ ብዙዎች ለዚህ የበቁት ለምን እንዴት መቼና ወዴት ብለው በማይጠይቁ ሎሌዎች በመከበባቸው ነው፡፡

የሚበጀው፡

በተለይ የድርጅት አባላት (የፖለቲካም የሌላውም) አባል እንጂ ተከታይ አትሁኑ፡፡ድርጅታችሁ ቆሜለታለሁ የሚለውን ዓላማ አጢኑ እንጂ የመሪዎች ምርኮኛ አትሁኑ፡፡ ጣታችሁን ወደ ሌላ ከመቀሰራችሁ በፊት ራሳችሁን እዩ፣ ድርጅታችሁን መርምሩ፣ መሪዎቻችሁን እወቁ፡፡ ከአንድ ወገን ብቻ ሰምታችሁ አይታችሁ ወይንም አንብባችሁ ለጩኸት አትቸኩሉ፣አንገት የተሰራው አዙሮ ለማየት ነው ይባላልና ዙሪያችሁን ቃኙ፣ተቃራኒ አስተሳሰቦችን መዝኑ፣ እውነትን ፈልጉ፡፤እንጂ እንደገደል ማሚቶ ወይ እንደ ድምጽ መቅጃ መሳሪያ የተነገራችሁን ብቻ የምትደግሙ አትሁኑ፡፡ ሙግት ክርክራችሁ ለመሸናነፍ ሳይሆን ለጋራ አሸናፊነት ይሁን፣ በመረጃ ማስረዳትን በማስረጃ መሞገትን ባህል አድርጉት፡፡ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ከሎሌነት ተላቆ በራስ በመቆም ህሊናን ማሰራት ሲቻል ነው፡፡

ሌሎቹም ፣ እዩኝ እዩኝ ባዮችን ጠብቋቸው ተጠንቀቋቸው፤እነርሱ ለሀገራዊ ጠቀሜታ ብለው ሳይሆን ለመታየት የሚያደርጉትን መወራጨት ባለመረዳት አድናቂም አድማቂም ሆናችሁ በመሰለፍ ሳታውቁት የሎሌዎች ሎሌ ላለመሆን ንቁ፣ሎሌ አደሩንና ሰርቶ አደሩን፣ ነጋዴውንና ታጋዩን ለዩ፣ ይህን በማድረግ እነርሱንም መታደግ ይቻል ይሆናል፣ከሎሌነት ነጻ ማውጣት፡፡ ችግር የሆነው ለምን አንዴት መቼ ማን የት ወዘተ ብሎ የሚጠይቀው ቁጥሩ አንሶ የሰማውን እንዳለ ተቀብሎ የሚያናፍሰው መብለጡ ነው፡፡የወሬ ገበያ መድራት የአሉባልታ መስፋፋት ወዘተ ደግሞ ለሎሌዎች ምቹ ነው፡፡ በአንጻሩ አብዛኛው ሰው እውነትን ፍለጋ ላይ ቢሰማራ ለራሱም በእውነት መሰረት ላይ መቆም ቢችል ሎሌውም አሉባልተኛውም አውርቶ አደሩም ወዘተ ባልተስፋፋ ነበር፡፡ወሬ ለኢትዮጵያ ምንም አልጠቀማት የሚል ዘፈን ነበር የሚያስታውስ ካለ ጀባ ይበለን!

The post ወትሮም ያለ ነው ከጥንት- ሎሌ መጮሁ ከጌታው ፊት – በይገረም አለሙ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ጉባዬና ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በስኬት ተጠናቀቀ

$
0
0

በአሰግድ ታመነ

በዛሬው ህዝባዊ ጉባዬ የአገራዊው ንቅናቄ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታና ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በእንግድነት የተገኙ ሲሆን የጉባዬው አዘጋጅ የዴሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ይበልጣል የመግቢያ ንግር አድርገዋል።
በማስከተልም አቶ ሌንጮ ለታ ስለ አገራዊው ንቅናቄ ምስረታ ገለፃ አድርገዋል ።
አቶ ሌንጮ በተለይ ከጠቀሷቸው ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ስለሆነ ነው እንጂ እንዲህ ተርቦ ተቸግሮና በድህነት ተሰቃይቶ ዝም ብሎ አይቀመጥም ነበር ብለዋል ። ሲቀጥሉም ወያኔን ማስወገድ የምንችለው እኛ ተቀራርበን ስንመካከር ነው ። ስለዚህ የተስማማንባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ልዮነታችንን ለመፍታትና ወደቀጣይ ስራ ለመጋዝ በቀርጠኝነት መነጋገር ይገባናል ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው ወደ አገራዊ ንቅናቄውን የመሰረቱበትን ምክንያት ሲያስረዱ ሁለት በሆኑ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መጀመርያ ተስማማን እነሱም
፩ኛ አንድነታ የተጠበቀ ነፃነትና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን በመቀበል።
፪ኛ ልዮነታችንን በግልፅነት በመነጋገር ለመፍታት የሚሉት ናቸው ብለዋል።
ህነዚህ ለህብረታችን መሰረት ናቸው ያል ሲሆን ሌሎች ልዩነታችንን ሁሉ በመነጋገር እንፈታዋለን ብለዋል በተጨማሪም ወደፊት ከኦብነግ፣ከትፕዴም፣ከየአማራ አይል ንቅናቄ ጋር ተነጋግረር ወደ አንድነት እንመጣለን ብለዋል በዚህም ወያኔ ህወሀት ሊያፈርሳት ያሰባትን ሀገራችንን እንደማትፈርስ እናረጋግጥለታለን ብለዋል።
በመጨረሻም የገቢ ማሰባሰብ ስነስርሀት ተካይዶ አንድ መቶ አምሳ ሺ የኖርዌይ ገንዘብ ከተሰበሰበ በኃላ ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የለቱ ጉባዬ ተጠናቋል።

The post የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ጉባዬና ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በስኬት ተጠናቀቀ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ኢትዮዽያ ኤርትራ በጅቡቲ ላይ የፈፀመችውን ወረራ የሚከታተል ኮማንድ ልታቋቁም ነው

$
0
0

ዋዜማ ራዲዮ- የኳታር ወታደሮች ከአወዛጋቢው የጅቡቲና የኤርትራ ድንበር  ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ኤርትራ አወዛጋቢውን የራስ ዱሜራ ኮረብታ ወራ መያዟ ተሰምቷል።
ኤርትራ ወረራ ስለመፈፀሟ ማስተባበያ አልሰጠችም፣ ይልቁንም በኳታር ድንገተኛ ለቆ መውጣት ግራ መጋባቷን ገልፃለች። ጅቡቲ በበኩሏ የኣአፍሪቃ ህብረት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ተማፅናለች።

በአካባቢው የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የኢትዮዽያ መንግስት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ሲከታተለው እንደነበረ ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ።
የኤርትራ መንግስት አዲስ እርምጃ ያሳሰባት ኢትዮዽያ በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ምክክር በማድረግ ጉዳዩን የሚከታተል የደህንነት የመስክ ቡድንና የመንግስትን ቀጣይ እርምጃ የሚመራ ኮማንድ ፖስት ለማቋቋም ሀሳብ ቀርቧል።
የኢትዮዽያ የፀጥታና የደህንነት ምክር ቤት የተወስኑ አባላት ባደረጉት ውይይት በቀጣዩ ሳምንት ሲቪልና ወታደራዊ አካላትን ያካተተ ምክክር ለማድረግ መታቀዱን የዋዜማ ምንጮች ነግረውናል።
“በጅቡቲ ላይ የሚፈፀም ወረራ የኢትዮዽያን የወደብ አገልግሎት አደጋ ላይ እንዳይጥል ከዚህ ቀደም የተቀመጠ አቅጣጫ ስላለ አዲስ እርምጃ ይኖራል ብዬ አልገምትም” ይላሉ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው የፀጥታ አማካሪ።
ኢትዮዽያ የወደብ አገልግሎቷን ለመከላከል ወታደር እስከመላክ ድረስ ዝግጁ መሆኗን ግን ደግሞ በጅቡቲ በርካታ የውጪ ሀይላት በመኖራቸው የአስመራ መንግስት ከድንበር አካባቢ አልፎ ጅቡቲ ላይ ወረራ የመፈፀም አቅምም ፍላጎትም ሊኖረው አይችልም ብለው እንደሚያምኑ አማካሪው ይናገራሉ።
በጅቡቲ የባህር መስመርን ደህንነት ለመጠበቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የያዘ ልዩ ተወርዋሪ ሀይል ከዓመታት በፊት ተቋቁሞ እንደነበር ይታወሳል።
የኢትዮዽያ መንግስት በኤርትራ ላይ አዲስ የፀጥታ ፖሊሲ ስነድ አዘጋጅቶ የጨረሰ ቢሆንም መወሰድ ባለበት እርምጃ ላይ ከስምምነት ባለመደረሱ እንዲሁም ወደ ጦርነት የሚወስድ አማራጭ ላይ በተፈጠረ ሙግት ፖሊሲው በእንጥልጥል ተይዟል።

The post ኢትዮዽያ ኤርትራ በጅቡቲ ላይ የፈፀመችውን ወረራ የሚከታተል ኮማንድ ልታቋቁም ነው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

እናቴ ሆይ ናፍቀሽኛል!

$
0
0


ላለፉት ተከታታይ አመታት ሰርክ ስለእናቴ አስባለሁ፤ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ስለሷ መንፈሰ ጠንካራነት ለመመስከር አንደበቴ ይደነቃቀፋል። ብእሬ ይዝላል! እንደው ባጭሩ እማዋይሽ የኔ፣ የምንግዜም ጀግና፣ ልጆቿን የሀገር ፍቅርን እና ከህዝብ. የመወገንን ፅናት፤ በአግባቡ ያስተማረች እና ምሳሌ እንደሆነች እኔ ልጇ ህያው ምስክር ነኝ።
እስርንና መከራን ለመቀበል መዘጋጀት፣ ሞትን ከመጋፈጥ በላይ እንደሚከብድ ብትረዳም ቅሉ መከራውን ለመቀበል ያልሰነፈች ብርቱ፤ የእናትነት ፍቅሯን ብቻ ሳይሆን ፅኑ የሀገር ፍቅሯን ያጋባችብኝ፤ ዘመኗን ሙሉ ከበዳዮች ያልወገነች ብርቅ ናት እናቴ።

እማዋይሽ! በዚህ ጨቋኝ ስርዓት ስር ለመኖር ማንነቷ የበቀለችበት ጀግና አብቃይ ምድር በጅ አይላትም፡፡ እንደ ማንም እናት ሰቆቃን መቀበል ምርጫዋም አይደለም፤ በተመቸ ቤትና በሞቀ አልጋ ላይ ከልጆቿ ጋር ማሳለፍንም ከቶ አትጠላም፤ ከዚህ በላይ ግን የታመነችለት የእውነት እዳ በእጅጉ ያስጨንቃታል። ከሴትነቷ በላይ የገዘፈው ልበ-ሙሉነቷ ጭቆናን ለመቀበል አሻፈረኝ እንድትል አድርጓታል፡፡

እናቴ ሆይ ዛሬ በጉልበተኞች እጅ ብትገኝም፤ ነገ ዘመን ሲፈቅድ አዋቂዎችና አስተዋዮች ወደ አደባባዩ ሲመጡ ተገቢውን ክብር ማግኘትሽ አይቀርም፤ በእውነተኞቹ ዘንድ አንቺም በፅናትሽ ትወደሻለሽ።

እናቴ ሆይ በጣም ናፍቀሽኛል! በጣም!!! ግን ምን ማድረግ እችላለሁ?
ስቃይሽ፣ እየከፈልሽ ያለውን መከራ ሳስበው…! ለሴት ክብር ባለው ማህበረሰብ ውስጥ እንደመብቀላችን፤ በእናትና በሴት ላይ ፈፅሞ ይደረጋል ተብሎ የማይታመን በደል ተፈፅሞብሻል፤ ከሁሉም ከሁሉም ልጅነቴን የምናፍቅባቸው ያለስስት የጠባሁት ጡቶችሽ በዱላ ተደብድበዋል! እስካሁንም ህመሙ እያሰቃየሽ ነው። ህመምሽ ያለጥርጥር የኔም ነው። ለኔ ከሌላው ስቃይሽ ሁሉ ይልቅ ይህንን ሳስብ ሆድ ይብሰኛል! አቅም አልባነቴ ጎልቶ ይሰማኛል። ይህን ስቃይ ያቀመሱሽ ከምን ተፈጠሩ? ብዬ እንድጠይቅ ያደርገኛል።
መልካም መጥፎን ድል እንዲነሳና ያዘኑ ልቦች እንደሚፅናኑ በእጅጉ ኣምናለሁ! እናም ከጥንካሬሽ ተለቅቼ በመንገድሽ እፀናለሁ… መልካም ነገን በማሰብ እፅናናለሁ

!#Justice4Ethiopia
#Justice4Emawayesh

The post እናቴ ሆይ ናፍቀሽኛል! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

እኔ የምለው ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው? (ዲያቆን ዳንኤል ከብረት)

$
0
0

♦♦የግሪክ፣ የካቶሊክ፣ የሶርያ፣ የሕንድ፣ የሩሲያ፣ የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትን ስንክሳሮች ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ በእነዚህ ቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ለቅድስና የበቁ አባቶች እና እናቶች ታሪክ ጾም፣ ጸሎት፣ ትምህርት፣ ሱባኤ፣ ትኅርምት፣ ተጋድሎ፣ ሰማዕትነት፣ በድፍረት መመስከር፣ ንጽሕና፣ ተባሕትዎ፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድረግ፣ ለሌሎች መሠዋት አና ሌሎችንም የእምነት እሴቶችን እናያለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡
የሂንዱይዝምን፣ የኮንፊሺየዝምን፣ የዞራስተሪዝምን እና የሌሎችንም የቀደምት ሰዎች እምነቶችንም እንይ፡፡ ጾም እና ጸሎት፣ ምናኔ እና ተጋድሎ፣ ራስን መግዛት እና ይህንን ዓለም መናቅ፣ ማስተማር እና መማር፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድርግ እና ለሌሎች መሥዋዕት መሆን የእምነቶቹ መሠረታውያን እሴቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡

♦♦ነዚህ ነገሮች እንድ ነገር ያመለክቱናል፡፡ ሃይማኖት ስሙ እና ሕግጋቱ ቢለያዩም ከመማር እና ከማስተማር፣ ለራስ የእምነቱን ሕግጋት ከመጠበቅ፣ ከውሳጣዊ ንጽሕና እና ለሌሎች በጎ ነገር ከማድረግ ጋር ፍጹም የተገናኘ መሆኑን፡፡

♦♦የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሳስታለች፤ መሥመርዋን ለቅቃለች ልናስተካክላት ይገባል ብለው የሚያምኑ ሰዎች መነሣታቸውን ከልዩ ልዩ ምንጮች ስንሰማ ከረምን፡፡ እኔ በሃሳባቸው መቶ በመቶ ባልስማማም፤ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ማሰቡ ግን መብቱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የሚከራከርበትን ሃሳብ በግልጽ አውጥቶ፤ የማምነው እንደዚህ ነው ብሎ፣ የማይቀበለውን ኮንኖ በሠለጠነ መንገድ ሃሳቡን ካቀረበ ይኼ ሰው ጤነኛ ሰው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
እንዲህ ካለው ጤነኛ ሰው ጋር መከራከር፣ ሃሳቡን በሃሳብ፣ መጣፉን በመጣፍ፣ አባባሉን በአባባል፣ ነቀሳውን በነቀሳ መሟገት እና ቢቻል መግባባት ባይቻል ደግሞ ከነ ልዩነት መኖር ይቻላል፡፡

♦♦በቅርብ አመታት የምንሰማው ግን ከዚህ የከፋውን ነው፡፡ ይህንን ዓይነት አመለካከት የያዙ ሰዎች በመማር እና በማስተማር፣ በመከራከር እና በማስረዳት፣ በግልጽ አውጥተው በማሳየት እና በማሳመን ሳይሆን በማጭበርበር እና በስለላ፣ በማጥፋት እና በማውደም መንገድ እምነታቸውን ለማሥረጽ መሞከራቸውን አየን፡፡
ይኼ ከጤነኛነት ያለፈ መንገድ ስለሆነ እንቃወመው ዘንድ ግድ ነው፡፡

♦♦አንድ ሰው በታቦት ክብር እና ሃይማኖታዊ ዋጋ አላምንም ብሎ የሚያምነውን ማስተማር ይችላል፡፡ ከፈቀድን እንቀበለዋለን፤ ካልፈቀድን በጨዋ ደንብ አንቀበልህም እንለዋለን፡፡ እርሱ በታቦት ሥርዓት ስላላመነ የኢትዮጰያ ቤተ ክርስቲያን ታቦታትን ለማጥፋት፣ ለማስሰረቅ፣ አስሰርቆም ለመሸጥ ከተነሣ ግን ስለ እምነትም ስለ ሀገርም፣ ስለ መብትም ብለን ሰው የተባልን ሁሉ እንቃወመዋለን፡፡
አንድ ሰው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት ላይ ጥያቄ በመጠየቁ ጠላት ነው ብለን አናምንም፡፡ ምናልባት የተለየ አመለካከት ያለው ሰው እንለዋለን እንጂ፡፡ ከራሱ እይታ እና መረጃ ተነሥቶ «ስሕተት ናቸው» ብሎ ማስተማሩንም ባንወድድለትም እናከብርለታለን፡፡ ምናልባት ማስረጃውን በማስረጃ፣ ሃሳቡን በሃሳብ እየተነተንን መልስ እንሰጠው ይሆናል፡፡ ጠላታችን ነው ብለን ግን አንነሣበትም፡፡

♦♦ከዚህ ድንበር ተሻግሮ እርሱ የማይፈልጋቸውን አዋልድ መጻሕፍት ለማቃጠል፣ ለመቆንጸል፣ ከየዕቃ ቤቱ ወጥተው ወደ ባዕድ እጅ እንዲገቡ ለማድረግ፣ ብራናውን ለማበላሸት፣ ቀለሙን ለማጥፋት፣ ዕቃ ቤታቸውን ለማቃጠል ከተነሣ ግን ይህ በእምነት ብቻ ሳይሆን በሀገርም ላይ የተነሣ የታሪክ እና የቅርስ፣ የመብት እና የጤነኛ አስተሳሰብ ጠላት ነውና እንቃወመዋለን፤ እንታገለዋለንም፡፡

♦♦ገዳማዊ ሕይወትን የተቃወሙትን ሁሉ አንጠላቸውም፤ ስላልገባቸው ነው፤ የዕውቀት ማነስ ነው ብለን እንገምታለን፤ ያለበለዚያም ደግሞ ጫፋችንን እስካልነኩን ድረስ በዚህ መንገድ ማመን መብታቸው ነው ብለን እንተዋቸዋለን፡፡ ከዚህ አልፈው ወደ ገዳማት እየገቡ ቅርስ የሚዘርፉ፣ ሴት ገዳማውያንን የሚደፍሩ፣ የተሣሣተ መረጃ በገዳማት ውስጥ የሚነዙ ከሆነ ግን እምነታችንን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ እና ሕጋዊ መብታችንን ተዳፍረዋልና እናጋልጣቸዋለን፤ በሕግ መንሽም ለፍርድ ነፋስ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፡፡

♦♦አንድ ክርስቲያን እስልምና የተሳሳተ እምነት ነው ብሎ ሊያምን ይችላል፡፡ ይህንን አመለካከቱንም ማስተማር እና የተቀበሉትን ማሳመን ይችላል፡፡ የራሱ እምነት ከእስ ልምና የተሻለ ነው የሚልበትን ምክንያት እና ማስረጃ እያቀረበ መከራከር እና መሟገት መብቱ ነው፡፡
ከዚህ አልፎ መስጊድ ውስጥ ገብቶ የጸሎት ሥርዓትን መበጥበጥ፣ የመድረሳ ት/ቤቶችን ማፍረስ፣ የሙስሊም ልብስ ለብሶ ተመሳስሎ በመግባት የእስልምና እምነት አማኞችን ሰላም መንሣት፣ ቁርዓን ማቃጠል፣ የእስልምናን ጥንታውያን ቅርሶች ማጥፋት፣ በእስል ምና ጉዳዮች ምክር ቤት የአሠራር ሥርዓት ውስጥ ሠርጎ የአሠራር ሥርዓቱን መበጥበጥ ከጀመረ ግን ከጤነኛ እና ከሕጋዊ መንገድ አልፏልና ከሙስሊሞቹ ጋር አንድ ሆነን እንቃወመዋለን፤ እንታገለዋለንም፡፡

♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥

♦♦ማንኛውም እምነት ሰይጣናዊነትን ይቃወማል፡፡ በራሱ በሰይጣን የሚያምን ካልሆነ በቀር፡፡ የሰይጣናዊነት ሁለቱ ዋና ዋና መገለጫዎች ደግሞ ክፋት እና ተንኮል ናቸው፡፡ በእምነት ስም ወንጀል ለመሥራት ካልታሰበ በቀር ከእምነት ጋር ክፋትን እና ተንኮልን አሥተሣሥሮ መጓዝ ወተት እና ኮምጣጤን አብሮ ከማኖር በላይ የማይቻል ነው፡፡

♦♦አሁን አሁን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እናድሳለን ብለው በተነሡ አካላት ዘንድ የምናየው እና የምንሰማው ነገር የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በመቃወም የተነሣ ሌላ ንቅናቄ አይደለም፡፡ክፋትን እና ተንኮልን አንግቦ የተነሣ አለም አቀፍ ምስጥራዊ ማህበረስ ሰይጣናዊ ንቅናቄ እንጂ፡፡ ዓላማውም ማደስ አይደለም፡፡ኦርቶዶክስን ማፍረስ እንጂ፡፡

♦♦እስካሁን ድረስ በየትኛውም የእምነት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ስለላን፣ ሤራን፣ ማፍረስን፣ ስርቆትን፣ ዘረፋን እና ማታለልን የእምነቱ ማራመጃ መንገዶች ያደረገ ብቸኛ የእምነት ንቅናቄ አለ ከተባለ እርሱ ዛሬ ዛሬ የምንሰማው «የተሐድሶዎች ንቅናቀ» ብቻ ነው፡፡

♦♦ትክክለኛ ነገር አለኝ፤ በያዝኩት ነገር አምንበታለሁ፤ ለያዝኩት ነገርም እከራከርበታለሁ፤ ማስረጃ እና መረጃም አለኝ፤ የኔ መንገድም የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ የሚል አካል ራሱን በይፋ ገልጦ፣ ፊት ለፊት ወጥቶ፣ ሃሳቡን አንጥፎ፣ ማስረጃውን አሰልፎ በብርሃን ይጓዛል እንጂ በጠላት ከተማ እንደ ገባ ሰላይ የድብቅ መንገድ አይጓዝም፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊም መንፈሳዊም ተቋም ናት፡፡ መብቶቿ እና ጥቅሞቿ በሕግ ልዕልና ያላቸው ናቸው፡፡ ተቋሞቿ፣ ንብረቶቿ፣ ት/ቤቶቿ እና ቅርሶቿን የመጠቀም፣ የመጠበቅ፣ የመከባከብ እና ለትውልድ የማስተላለፍ መብት አላት፡፡ በእነዚህ ክልሎች ገብቶ ማንም ሌላ ወገን ያልፈቀደችውን ተግባር በድብቅ እንዳይፈጽም ሕግም ሞራልም ይከለክለዋል፡፡

♦♦አሁን እያየነው ያለነው ተግባር ግን የሃይማኖት አስተምሮን ተቃውሞ ሌላ የተሻለ አስተምህሮ የማምጣት ተግባር ሳይሆን ክፋት እና ተንኮልን ገንዘብ ያደረገ የሤራ ተግባር ነው፡፡ በገዳማት ገብቶ ብራና መፋቅ፣ የአብነት ት/ቤቶችን መበተን፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ገብቶ በርዳታ ስም ሀብቷን መበከል፤ ቅርሶቿን መዝረፍ እና መሸጥ፣ ጥንታውያን ተቋማቷን ማውደም፤ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ንዋያተ ቅድሳትን እና መጻሕፍትን ማበላሸት በምን መመዘኛ ነው የሃይማኖት ሥራ የሚሆነው?

♦♦የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጥንታዊ የክርስትና ትምህርት ጠባቂ፣ የጥንታዊ እና ታሪካዊ የክርስትና ሀብቶች ባለቤት፣ የጥንታዊ መጻሕፍት ግምጃ ቤት፣ የቀደምት ኢትዮጰያዊ ባህሎች እና ትምህርቶች መገኛ፣ የሀገራዊ የአስተምህሮ ጥበብ ማዕከል፣ የቀዳሚ ክርስቲያናዊ ዜማ መፍለቂያ፣ በብዙዎች ዘንድ የጠፉ የአበው ድርሳናት ማከማቻ፣ ልዩ ክርስቲያናዊ ማዕከል ናት፡፡

♦♦በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በሤራ የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በሦስት ነገሮች ላይ የሚሠራ ወንጀል ነው፡፡ በክርስትና ላይ፣ በሰው ልጅ ታሪክ ላይ እና በሀገር ላይ፡፡
በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ተጀምሮ ምዕራቡን ዓለም መንፈሳዊነት ወደ ተለየው ክርስትና የከተተው የተሐድሶ ነፋስ በክርስትና እና በክርስቲያናዊ ሀብቶች ላይ የማይተካ ጥፋት አድርሷል፡፡ በወቅቱ በተቀሰቀሰው ስሜታዊነት በተሞላው ነውጥ ምክንያት አያሌ ክርስቲያናዊ ትምህርቶች እና ቅርሶች ላይመለሱ ጠፍተዋል፡፡ ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላ ብዙ ሀገሮች ከቀበሩበት ሊያወጧቸው እንደ ዔሳው በዕንባ ቢፈልጓቸው ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡

♦♦በዚህ የተነሣ ታላላቅ የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ማኅበራትን አቋቁመው በሌሎች ሀገሮች ያሉ ቅርሶች ተመሳሳይ ውድመት እንዳይደርስባቸው የቻሉትን ሁሉ በፀፀት ሠርተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ከደረሰው ጥፋት በእግዚአብሔር ቸርነት ከተጠበቁት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለዚህ ነበር አያሌ ሚሲዮናውያን እና አሳሾች ቅርሶቻችንን ሲዘርፉ እና ሲተረጉሙ የኖሩት፡፡

♦♦አውሮፓውያን በክርስትና ላይ የሠሩት የማይካስ ወንጀል አምላክ የለሽ ትውልድ እንጂ ጻድቃንን አላፈራላቸውም፡፡ ይህንን ወንጀል ኢትዮጵያ ላይ ለመድገም መነሣት ክርስትናን ያለ ጥግ ማስቀረት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ኦርጅናሌው ክርስትና ምን እንደሚመስል በትክክል ማሳየት ከሚችሉ ጥቂት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት፡፡ ለዚህ ነው በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በክፋት የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በክርስትና ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against Christianity) ነው የምንለው፡፡

♦♦በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታላላቅ ለውጦች ካመጡት ታሪኮች ዋነኛው ክርስትና ያመጣው ለውጥ ነው፡፡ ለዚህም ነው የክርስትና ታሪክ ከሰው ልጆች ታሪኮች መካከል ዋነኛው ታሪክ የሚሆነው፡፡ ክርስትና ትምህርት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብ፣ የትምህርት መንገድ፣ ርዕዮተ ዓለም፣ የሥነ መንግሥት ምንጭ፣ ፍልስፍና፣ የሥልጣኔ መዘውር፣ የዓለምን መልክዐ ምድር ቀያሪ፣ የሥነ ጽሑፍ መንገድ፣ የሥነ ሥዕል መርሕ፣ የሥነ ጥበብ ትልም፣ የሥነ ዜማ ስልት፣ የሕዝቦች መገናኛ ድልድይም ሆኗል፡፡ በመሆኑም የክርስትና ሀብቶች እና ቅርሶች የአንድ እምነት ሀብቶች እና ቅርሶች ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሀብቶች እና ቅርሶች ሆነዋል፡፡ በእነዚህ ሀብቶች እና ቅርሶች ላይ እናድሳለን በሚሉ አካላት የሚሠነዘረው ጥፋት በሰው ዘር ሀብት ላይ የሚሠነዘር ጥፋት (crime against human heritage) የሚሆነውም በዚህ የተነሣ ነው፡፡

♦♦ጥፋቱ ከዚህም አልፎ ሀገራዊ መልክም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያን አብዛኛውን ሕዝብ የምትወክል፣ አስተሳሰቡን እና ርዕዮቱን የምትቀርጽ ተቋም ናት፡፡ ታሪኳ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ባህልዋ የሀገሪቱ ባህል፣ ቅርሷ፣ የሀገሪቱ ቅርስ፣ ጥበቧ የሀገሪቱ ጥበብ፣ ዘመን መቁጠርያዋ የሀገሪቱ ዘመን መቁጠርያ ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀሪቱ አንዷ እና ዋነኛዋ መገለጫ ናት፡፡ እናም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ሀብቶች ላይ የሚሠነዘር ጥፋት ሁሉ በሀገር ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against the mother land) ነው፡፡ የሚመለከተውም የቤተ ክርስቲያኒቱን አማንያን ብቻ ሳይሆን መላውን ኢትዮጵያዊ፣ የሀገሪቱን መንግሥት እና የኢትዮጵያን ወዳጆች ሁሉ ነው

♦♦ኢየሱስና ሐዋሪያት በግልጽ እንጂ እንደ ማፊያ እና ሴጣን በስውር በጓሮ በር አልገቡም ፤ክርስትና ስለላ፣ ሤራ፣ ዝርፊያ፣ውድመት እና ደባ አይደለም። የክርስትናም መንገድ ቀና እና ግልጥ እንጂ ተንኮል እና ክፋት አይደለም።ይህ የክርስትና ሃይማኖትን፤ሊያፈርስ፣ክርስትያኖች ፤ሊያርድ፣ ሊዘርፍ፣በተሃድሶ ስም የተደራጀ አለም አቀፍ የኢሊሙናንት ምስጥራዊ ቡድንን ኢትዮጲያዊ ሁሉ አንድ ሆነን ልንቃወመውና፤ ልናስቆመውምና በትልቅ ቁጣ ልንጋደለው ይገባል፡፡

♦♦ልዑል እግዚአብሔር አለም ሁሉ ውበት የሆነችሁን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ከእነዚህ ሴጣናዊ ምስጥራዊ ማህበረሰቦች ይጠብቅልን፡፡

The post እኔ የምለው ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው? (ዲያቆን ዳንኤል ከብረት) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ አወጣ

$
0
0

የዚህች ጦማር ዋና ዓላማ፡ “ያዲስ አበባው ሲኖዶስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ከቀሩት አኀት አብያተ ክርስቲያናት ተነጥላ ከሀያ በላይ ስህተት ሰርታለችና ትመርመር የሚል ክስና ወቀሳ አቀረበ” ብሎ ሀራ ዘተዋህዶ ባቀረበው ዜና፤ ግራ የተጋባችሁ ክርስቲያኖች፤ “በአኀት አብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያዊ ትውፊት አንጻር እንዴት ትመለከተዋለህ“ ብላችሁ ላቀረባችሁልኝ ጥያቄ ለመመለስ ነው።

ይህ የቀረበው ሀሳብ የሀራ ዘተዋህዶ ድረ ገጽ ፈጠራ ከሆነ፡ ”አባት ሆ ይ!እኔ በአንተ አንተ በእኔ እንዳለህ እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ”(ዮሐ 17፡ 21“)በሚለው ክርስቶሳዊ ቃል፤ አንድነታቸውን አጽንተው በኖሩት በአኀት አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየዘመተ ነው ማለት ይቻላል። ምናልባትም ከጥንት ጀምሮ እነዚህን ጥንታውያት አብያተ ክርስቲያናትን ለማጥፋት የሚታገሉት የሰባልዮስ ወይም የአርዮስ ተከታዮች ሊሆን ስለሚችል የአኀት አብያተ ክርስቲያናት አካላት በመተባበር አወቅንብህ ልንለው ይገባናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live