Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ተስለክላኪ ዘንዶ – “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ”

$
0
0

“ወእምዝ ወጽአ ካልዕ አርዌ እምነ ምድር፤ ወበሥልጣኑ ለቀዳማዊ አርዌ ይገብር ኩሎ በቅድሜሁ፤ ወይረስያ ለምድር ከመ እለ ይነብሩ ውስቴታ ይሰግዱ ሎቱ ለቀዳማዊ አርዌ ” (ራዕይ 13፡12) ።

ሰሞኑን በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ በውስጥና በውጭ የሚካሄደውን አየሁ። የሚንጫጫውንም ሰማሁ። ተጽፎ ባነበብኩትና በመገናኛ ዘዴዎች በሰማሁት ጫጫታወች ውስጥ ያለችውን ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ልግለጻት ብየ አሰብኩ። በዚህ የሀሳብ ማእበል ውስጥ ሳለሁ፤ በአባይ በርሀ፤ በፊላው ስር ተከሰተ እየተባለ በልጅነቴ ሲነገር የሰማኌት ቀውጢ ትዝ አለችኝ። በዚያች ቅጽበት በተከሰተችው ቀውጢ ክስተት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያኔን አየኋት።

ታሪኩ እንደዚህ ነው፦ ሁለት ወንድማማቾች በአባይ ዳር በፊላው ስር ሲሄዱ። ረሀብ አስክሮት የሚያድነውን ነገር እየፈለገ በመቀነዝነዝ ላይ የነበረ የቀትር ዘንዶ ከፊላው ውስጥ ተስለክልኮ ባንዱ ላይ ተጠመጠመበት። የሰውየውና የዘንዶው ሰውነት እንደገመድ ተፈተሉ። ወንድሙ ለተወሰነ ደቂቃ በድንጋጤ ደንዝዞ ቆመ። በሰውየው ላይ የተጠመጠው ዘንዶው ሰውየውን ለመዋጥ እያደቀቀው ነው። ዘንዶው በሰውየው አካል ላይ እንደገመድ ሰለተጠመጠመ በያዘው ነፍጥ ዘንዶውን ከሰውየው ለይቶ መምታት አልቻለም። ሁለቱንም ደርቦ በመምታት ወንድሙን የሚገድለው ሆነ። በድንጋጤ የሚመለከተው ወንድም መላው ጠፋበት። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

<!–

–>


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles