Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ታላቅ የድል ዜና ከቋራ – አስናቀው አበበ

$
0
0

የወያኔ 3 ኦራል ሰራዊት በሙሉ ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይቀር ተደምስሷል። ውጊያው የተካሄደው ቅዳሜ ሰኔ 17 2009 ነው። በርካታ መትረጌስ፣ እስናይፐር፣ ክላሽ፣ በርካታ የእጅ ቦንቦች እና ጥይት የቋራ የጎበዝ አለቆች እጅ ገብቷል። ልዩ ቦታው እና የታጋዮች ስም ለደህንነት ስንል አይገለፅም።

ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ሰራዊቱ የተረፈረፈባት ወያኔ መልሳ ሌላ ሀይል ልትልክ እንደምትችል ጭምጭምታ ስላለ የጥንቄቃ እርምጃ እየተወሰደ ነው። እንደሚታወቀው የቋራ አካባቢ አርሶ አደር ከሰፋፊ መሬቱ በግፍ እየተፈናቀለ ድንበሩ ለሱዳኖች እየተሰጠበት ይገኛል። የተቀረውንም መሬት ወያኔ በኢንቨስተር ስም ለስርአቱ አገልጋዮችና ለባለ ጊዜ ባለሃብቶች እየቸበቸበው ነው። ይህ የተከፋ ህዝብ መሳሪያ አንስቶ በርሃ ገብቶ የተከፈቱበትን ተከታታይ ጥቃት አክሽፎ ድል እየተቀዳጀ ነው። ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተልነው ነው።
የነፃነት ጥያቄ በአፈና አይቀለበስም!
ድል የህዝብ ነው©!

 

ዜና ጥቃት

ሰኔ 20 2009

የዳሽን ቢራ ከፍተኛ አመራር የሆነ የፋይናንስ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ዘውዱ ማንነቱ ባልታወቀ ግለስብ ጎንደር ከተማ ከሚገኘየው የዳሽን ቢራ ቅጥር ግቢ ወሰጥ በጩቤ ተወግቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ወደ ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል እንደተወሰደ መረጃ ደርሶናል፡፡ ጥቃቱን የሰነዘረው ሰው ቢሮው ድረስ ገብቶ መሆኑ ተገልፁአል።

ዳሸን ቢራ ንብረትነቱ የብአዴን/ወያኔ ሃብት ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የደም መጠጥ አንጠጣም ብሎ አድሞበታል። ለጎንደር ህዝብ ምንም ፋብሪካ ሳይከፍቱ የቢራ ጠጭ እንዲሆን ይህን አምተው መደንቀራቸው በተደጋጋሚ ሲተች የቆየ ነው። አሁን በቅርብ እንኳን አጎራባቿ ባለጊዜዋ ትግራይ ግዙፍ የሆኑ የመገጣጠሚያና የማምረቻ ፋብሪካወች እየተመረቁላት ነው። ከአራት በላይም ኤርፖርት ለትግራይ ተከፍቷል።
የጥቃቱን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።
የጎንደሩን ቋሚ አምደኛ ሪፖርተራችንን እናመሰግናለን።
Asnakew Abebe

 

The post ታላቅ የድል ዜና ከቋራ – አስናቀው አበበ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles