Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የአንበጣው መንጋ የወረራቸው አካባቢዎች የመንግሥት እገዛ ተነፍጓቸዋል፤ – ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0

በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች የገበሬውን ሀብት ንብረት የሚያወድም አደገኛ አንበጣ ተከስቷል፡፡ አንዱ የአንበጣ መንጋ በቀን 16 ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ የሚችል ሲሆን ባሕር ዛፍን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ሰብልና እጽዋት መድምዶ በመብላት ያወድማል፡፡ በምዕራብ ጎጃምና በአዊ ዞኖች ከአራት ወረዳዎችና ከ50 በላይ ቀበሌዎች በአንበጣው መንጋ ተወረዋል፡፡

አንበጣው የሚመርጠው የለም፤ ገበሬዎች ‹‹ሁሉን በይ አንበጣ›› ይሉታል፡፡ የግብርናና የልማት ባለሙያዎች ለክልሉ መንግሥት ግብርና ቢሮ አንበጣው መጥፋት የሚችልበትን መድኃኒት ወይም ማንኛውም ዓይነት እገዛ ቢጠይቁም በአገር ውስጥ ለዚህ ዓይነት አንበጣ መከላከያ የሚሆን መድኃኒት የለም የሚል መልስ እንደተሰጠ ሰምተናል፡፡ አስቸኳይ ርብርብ ተደርጎ መከላከል ካልተቻለ በስተቀር አጠቃላይ የምዕራብ ጎጃምንና የአዊ አካባቢዎች ያለውን ሰብልና እጽዋት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊያወድም ይችላል ተብሏል፡፡
እስካሁን ድረስ ባለው ከሃምሳ በላይ ቀበሌዎች በበልግ ዝናብ የበቀለ ሰብልና በአካባቢው ያለውን እጽዋት ሁሉ እንዳወደመ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሙሉቀን ተስፋው ።

The post የአንበጣው መንጋ የወረራቸው አካባቢዎች የመንግሥት እገዛ ተነፍጓቸዋል፤ – ሙሉቀን ተስፋው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles