Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ዘመነ እንኳን ለዚህ አበቃህ!!! – ወይንሸት ሞላ

$
0
0

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚድያዎች ጎልተው ከተሰራጩት መረጃዎች መካከል የታጋይ ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ምድር ወጥቶ ወደ ነፃ ምድር መሸጋገሩን የሚያበስሩ መረጃዎች ናቸው:: የመረጃዎችን እውነትነት ለማረጋገጥ በቪዲዬ ቀርፆ ያሰራጨውን መልክትም ከራሱ ከዘመነ ካሴ ንግግር ተመልክቻለሁ:: ከዘመነ ንግግር የተረዳሁት
1.ባለፉት 15 ወራት ለአላማው ከሄደበት የትግል ስራ ላይ እንዳልነበረ እና ሰው የተራበበትም ጊዜ እንደነበረ
2.በነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ የነበረዉን ነገር እንደማያውቅ እና ስለሱ መጥፋትና መሰወር ሲጨነቁ ስለነበሩ ሰዎች ያወቀው ዘግይቶ እንደሆነ
3.ከኤርትራ ወጥቶ አሁን ያለበት ቦታ ለመድረስ በገንዘብ የረዱትን ሰዎችና ስለሱ ሲጨነቁ ለነበሩ ወገኖቹ ምስጋና ማቅረቡን
4.ከነበረበት ድርጅት ሳይወድ በግድ መለየቱን
5.በእሱ እና በነበረበት ትግል ዙርያ ግልፅ መሆን ስላለባቸው ነገሮች ማለትም ላለፉት 15 ወራት የነበረበትን ሁኔታና ከትግሉ እንዴት እንደተለየ እንዲሁም ከኤርትራ ወጥቶ አሁን የሚገኝበት ቦታ እስከሚደርስ ማን አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ወደ ፊት በዝርዝር ሁኔታ እንደሚመለስበት ከንግግሩ ለመገንዘብ ችያለሁ::

ዘመነ እንዳለው የእግዚአብሄር እርዳታ እንዳለ ሆኖ ዛሬ ላለበት ሁኔታ እንዲበቃ በሀሳብ በገንዘብ በፀሎት እንዲሁም ስለሱ ያለ መታከት ስትጮሁና ነገሩ ተድበስብሶ እንዳይቀር ጫና ስትፈጥሩ ለነበራችሁ ወገኖች ምናልባት ለዚህ ውጤት እረድቶ ከሆነ ምስጋና ይድረሳችሁ::

Woyinshet Molla

The post ዘመነ እንኳን ለዚህ አበቃህ!!! – ወይንሸት ሞላ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Latest Images

Trending Articles



Latest Images