Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

ነገረኢትዮጵያ

ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ መጥራታቸውን አቶ ነገሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡Merera Gudina and Yilkal Getnet

ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ የጠሩት ሰልፍ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ፤ እንዲሁም መንግስት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ላይ በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ መንግስት እየወሰደው ያለውን እፈና እና እርጃዎቸ እንደሚያወግዙ ምክትል ሊቀመንበሩ ተገልፆአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ የሚያደርጉት ሰልፍ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አድርጎ፣ በቸርቺል አደባባይ የሚያልፍ ሲሆን መዳረሻው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ መሆኑን ታውቋል፡፡ መንግስት እየወሰዳቸው ባሉ የተሳሳቱ እርምጃዎች ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ መሆኗን የገለፁት አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ሀገራችን ካለችበት ችግር ለማውጣት ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙና በሰልፉም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሰልፉ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ላይ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles