Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የሰብዓዊ መብት ቀን በፍራንክፈርት ተከበረ!

$
0
0

በዮሐንስ ደሳለኝ (ጀርመን – ፍራንክፈርት)
በየዓመቱ ዲሰምበር 10 የሚከበረው የሰብዓዊ መብት ቀን ሐሙስ December 10,2015 በፍራንክፈርት የዋናው ባቡር ጣቢያ አካባቢ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አመሸ። ከተለያዩ አገሮች የመጡ ተገን ጠያቂዎች የተገኙበት ይህ አከባበር ለየት ያለና የወቅቱ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚገባው ብርድ ያልበገረው ነበር።

 

frankfort 


ሁኑ ሰዓት በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች በሚገኙ ተገን ጠያቂዎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት አለመከበርና የተወሰኑ አገሮች ብቻ እየተመረጡ ተገን መስጠት አግባብነት የሌለውና ከተባበሩት መንግስታት የ1948ቱ ህግ ጋር የሚጻረርና ዴሞክራት ነን፣ የሰው ልጅ መብትም ተከብሯል በሚሉት አገሮች ይህ መፈፅሙ የሚያሳፍርና መፍትሄ ሊበጅለት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን በዕለቱ የነበሩት ወደ ስምንት መቶ የሚጠጉ የተለያዩ አገር ዜጎች አሳስበዋል።

frankfort2በአሁኑ ሰዓት በተለይ ወደ ጀርመን እየጎረፈ ያለውን የስደተኛ ቁጥር ለመቀነስ የጀርመን መንግስት ባወጣው ህግ ላይ ቅሬታቸውን የሚያሰሙት ቁጥራቸው እየበረከተና የወጣውም ህግ የጥቂት አገሮችን ተገን ጠያቂዎችን ብቻ ያካተተ መሆኑ ከሰብዓዊ መብትና ከተባበሩት መንግስት የስደተኞች ኮሚሽን አንፃር ተቀባይነቱ እምብዛም ነው።

በዕለቱ አከባበር ላይ በርካታ ኢትዩጵያኖች ከተለያዩ ከተሞች በመምጣት ተሳትፈዋል፣ የተለያየ መፎክሮችን በመያዝ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በአምባገነኑ ወያኔ መንግስት በኦሮሞና በአማራ ገበሬዎች ላይ በግድ ከቀያቸው በልማት ሰበብ እያፈናቀለ መሆኑንና ይሄንንም የተቃወሙ የአንደኛና ሁለትኛ ደረጃ እንዲሁም የዩንቭርስቲ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በማውገዝ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢ ከአስራ አምስት ሰዎች በላይ ሲሞቱና በርካታ ቁስለኞች በየአካባቢው ያሉ ሆስፒታሎችንና ክሊኒኮችን ማጨናንቃቸው ይታወቃል።

ከነበሩትም መፍክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፣
ወያኔ ሁሉንም ያላሳተፈ ልማት ይቁም
Killing us never stop the struggle
Stop land grabbing
ለሁለት ሰዓት የቆየው አከባበር የሚገርም ድባብ የነበረውና የሁሉንም አገር ዜጎች በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ያግባባና ሁሉም በህግ ፊትና በሰውነቱ እኩል መሆኑን ያመላከተ ሆኖ በአገሩ አቆጣጠር 7pm ተጠናቋል።

The post የሰብዓዊ መብት ቀን በፍራንክፈርት ተከበረ! appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles